FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, March 26, 2013

ESAT Tamagn with ESAT Europe journalists Ethiopia


”አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች ነበሩ”


ፍኖተ ነጻነት መጋቢት 15 ቀን 2005 ዓ.ም.

የዛሬው እንግዳችን አቶ ታዲዎስ ታንቱ ይባላሉ፡፡ አቶ ታዲዎስ የታሪክ ምሁርና በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ነፃ ፕሬስ ውስጥ ትልቅ ሚና ያላቸው ሲሆን በአሁን ወቅት “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ዋና ሰብሳቢ ናቸው ፡፡ በተለይ ለፋሺስቱ ግራዚያኒ ከተሰራው ሐውልት ጋር በተያያዘ አጭር ቆይታ አድርገናል ተከታተሉን፡፡
በጣሊያን የሩዶልፍ ግራዚያኒንን የሐውልት ለመቃወም የሐሳቡ ጠንሳሽ ማን ነው?
አቶ ታዲዎስ፡- የፋሽቱ ጣሊያን የኢትዮጵያውያን ዋና ጨፍጫፊ የነበረውን ሩዶልፍ ግራዚያኒ ሐውልት መሰራት ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞው የተጀመረው በውጭ ሀገር ባሉ 
Interview with Ato Tadiwos Tantu
አቶ ታዲዎስ ታንቱ
ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት
ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ
ኢትዮጵያውያን ነው፡፡ በሀገር ውስጥ ግን የሐሳቡ ጠንሳሽ “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ነው፡፡ ከዛ በኋላ የባለዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር ሰልፉን ለማስተባበር ፈቃደኛ መሆኑን ገለፀልን፤ በዚህም ላይ ሰማያዊ ፓርቲ እንደሚተባበረን ከገለፀ በኋላ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ሰልፉን ለማካሄድmወሰንን፡፡
ተቃወቅሞውን ለማቅረብ ያነሳሳችሁ ዋነኛ ምክንያት ምን ነበር?
አቶ ታዲዎስ፡- ብዙውን ጊዜ እኔ በጋዜጦች ስለ አርበኞች ታሪክ ያነበብኩትንና ያወቅሁትን እፅፋለሁ፣ እመረምራለሁ፡፡ የጣሊያኑ ፋሽስት ግራዚያኒ ሀገራችንን በመውረር በአባቶቻችንና እናቶቻችን አርበኞች ላይ የፈፀሙት የግፍ ግድያ አሰቃቂ እንደነበር ስለተረዳሁ፤ ያ ሲቆጨኝ ደግሞ አሁን በጣሊያን ሀገር ለእሱ ሙዚየምና ሐውልት የመሰራቱን ወሬ ከኢንተርኔት ምንጮች ስላየሁ በጣም ተናድጄ እንደውም ተቃውሞ ማሰማት አለብን ብዬ ተነሳሁ፡፡ በኋላ ደግሞ እኛም የአንተ ዓይነት ሐሳብ ነበረን ብለው የባለ ዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር አነጋገሩን፡፡ ከዛ በመቀጠል ሰማያዊ ፓርቲ በጋራ እንስራ የሚል ጥያቄ አቀረበ፡፡ በዚህ ምክንያት ሶስቱ አካላት በጋራ ሰልፉን ለማድረግ ዝግጅት ማድረግ ጀመርን፡፡ ስለዚህ ለኢትዮጵያ ጠላት አይደለም ጣሊያን ሀገር ጨረቃም ላይ ቢሆን ሀውልት እንዲሰራ አንፈቅደም፡፡
በጊዜው ሩዶልፍ ግራዚያኒ ወንጀለኛ በመሆኑ የነበረው ፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተገፎ ከወታደርነቱ ተባሮ በጦር ወንጀል ተከሶ 19 ዓመት ተፈርዶበት ቅጣቱን ሳይጨርስ ከእስር ቢለቀቅም እ.አ.አ. በ1955 ዓ.ም. ሞቷል፡፡ ታዲያ ይህ በጊዜው ወንጀለኛ ለተባለው ሰው ሐውልትም ሆነ የመታሰቢያ ሙዚየም ማሰራት ኢትዮጵየውያንን መናቅና የአባቶቻችንን ክብር የሚነካ በመሆኑ ሊሰራለት አይገባም፤ እንደውም ለፈፀመው እልቂት ጣሊያን በቂ ካሳ ስላልከፈለች ካሳ መክፈልና በይፋ ይቅርታ መጠየቅ ይገባታል የሚል አቋም ይዘን ነው የወጣነው፡፡ ስለዚህ ግራዚያኒ ከነ አዳፋ ታሪኩ ሌላው እንዳይደግም ሲወሳ መኖር አለበት እንጂ እንደ ጀግና ሐውልት ሊሰራለት፣ሊወደስና ሊመሰገን አይገባም እንላለን፡፡
በወቅቱ የደረስው ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ ይቻላል?
አቶ ታዲዎስ፡- በወቅቱ ግራዚያኒ በፊርማው በግፍ ኢትዮጵያውያንን ያስጨፈጨፋቸው ሰዎች ስም ዝርዝር ከነደብዳቤው አለ፤ የዚህ ቅጂ እኔም ጋር አለ ይታወቃል፡፡ በተለይ የካቲት 12-14 ቀን 1929 ዓ.ም. ከ30 ሺህ በላይ ዜጎቻችንን በግፍ አዲስ አበባ ላይ እራሱ ግራዚያኒ አስጨፍጨፏል፡፡ ከ250 በላይ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ጨምሮ መነኮሳትን አስጨፍጭፏል፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት በ1938 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው አለም አቀፍ ጉባኤ ያቀረበው ሰነድ እንደሚያስረዳው 760,300 ሺህ ዜጎች ወዲያው ሲገደሉ 525,000 ደግሞ ከነቤት ንብረታቸው እንዲቃጠሉ ተደርጎ ህይወታቸው አልፏል፡፡ ከሁለት ሺህ በላይ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለው መነኮሳት ተገድለዋል፣ በርካታ ቅርሶች ተዘርፈው ተወስደዋል፡፡ በርግጥ ከተዘረፉ ቅርሶቻችን መካከል እስካሁን የተመለሰው የአክሱም ሐውልት ብቻ ነው፤ ሌሎቹ ግን አሁንም እዛው ናቸው፤ ሊመለሱልንም ይገባል፡፡ ከዛ ውጭ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የቀንድ ከብቶች በወቅቱ ተዘርፈው ተወስደዋል፤ 7 ሺህ ግመሎችም ተገድለውብናል፡፡ ይህም በሰነድ በተደገፈ ማስረጃ ለዓለም አቀፉ የሰላም ጉባዔ የቀረበ ነው፡፡ በወቅቱ ሰነድ ያልቀረበባቸውና ሰፊ ጥናቶች ሊደረግባቸው የሚገቡ በርካታ ጥፋቶች ተፈፅመዋል፡፡
ይህንን ተቃውሞ በዋነኝነት ማቅረብ የነበረበት መንግስት ነበር የሚሉ ወገኖች አሉ፤ እርስዎስ ምን ይላሉ?
አቶ ታዲዎስ፡- እኔም እስማማለሁ፤ ነገር ግን መንግስት ማዘጋጀት ካልቻለ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ማዘጋጀት ይችላል፡፡ እኔ እንደሚገባኝ መንግስት ተቃውሞ ያላቀረበው ከጣሊያን የሚያገኘው ዕርዳታ ይቀርብኛል በሚል ይመስለኛል፡፡ እኔ እስከማውቀው ይሄ መንግስት ዕለታዊና የፖለቲካ ገበያ ጥቅምን መሰረት ያደረገ እንጂ ወደፊት ትውልድ የሚኮራበትን ስራ የመስራት ዓላማ የለውም፡፡ ከዚህ በፊት የቀደሙ አባቶቻችን የሰሩትን በጎ ታሪኮች ሲያንቋሽሽ የኖረ መንግስት ስለሆነ እንዲህ ዓይነት የአባቶቻችንና እናቶቻችን አርበኞች ታሪክና ክብር የሚያስጠብቅ ስራ ይሰራል ብዬ አላስብም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያዊ ስሜት ያለው፣ ብሔራዊ ስሜትን የጠበቀ ህዝባዊ መንግስት ቢሆን ኖሮ ህዝቡን አስተባብሮ ይሄንን ስራ በቀዳሚነት መስራት የነበረበት እሱ ነበር፡፡ ስለዚህ መንግስት ባያደርግም ዜጎች ይህንን ሰልፍ የማድረግ መብት ስላላቸው እኛም ሰልፉን አድርገናል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የሀውልት ግንባታውን አለመቃወሙ ምን ያስረዳናል?
አቶ ታዲዎስ፡- ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ በእጅ አዙር ለሀውልት ግንባታው እውቅና እንደሰጠ ይቆጠራል፤ ይህንን እኔም አምናለሁ፡፡ ከዚህም በላይ አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች የነበሩ ናቸው፡፡ እንደውም ነፃነታችንን ባወጅንበት ሁለት ዓመት ሳይሞላ በአርበኞች ላይ ጦርነት የከፈቱ ናቸው፡፡ ስለዚህ ለግራዚያኒ የጀግና ሐውልት መሰራቱን ባይቃወሙ አይገርመኝም፤ ምክንያቱም እነሱ የማን ልጆች ናቸው? እስኪ በስልጣን ላይ ካሉት (ከኢህአዴግ) መካከል ለሀገሩ እና ለወገኑ ብሔራዊ ስሜት፣ ነፃነትና ክብር የተዋጋ የአርበኛ ልጅ አንድ ሰው ካለ ንገረኝ? አንድም ሰው የለም፡፡ ስለዚህ የባንዳ ልጅ ለጨፍጫፊው ግራዚያኒ በእጅ አዙርም ሆነ በቀጥታ እውቅና በመስጠት ድጋፍ ቢያደርጉ አያስደንቀኝም፡፡
እናንተ ሰላማዊ ሰልፉን ከማድረጋችሁ አንድ ቀን በፊት መጋቢት 7 ቀን 2005 ዓ.ም ስምንት ሰዎች መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ ይህ ክስተት በሰልፉ ወቅት እስር እንደሚኖር አልጠቆማችሁም?
አቶ ታዲዎስ፡- እሱን አውቀንም ነው ሰልፍ የወጣነው፡፡ አንድ ቀን አስቀድሞ ሌሎች ቢታሰሩም መውጣት አለብን ብለን ነው የወጣነው፤ እኛም ብንታሰር ሌሎችም እንደሚወጡ እናውቃለን፡፡ ችግር ይፈጠራል ብለን አልተውንም ፤መተውም የለብንም፡፡ ምክንያቱም ይሄ የሀገርና የወገን ጉዳይ ነውና፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሰልፉ ላይ የተገኙትን ላመሰግን እወዳለሁ፡፡
የታሰራችሁት ምን ወንጀል ሰርታችኋል ተብላችሁ ነው?
አቶ ታዲዎስ፡- ፍቃድ አልጠየቃችሁም ፣ አላስፈቀዳችሁም በሚል ነው፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵያ በነበሩ የአጼ ኃይለስላሴ፣ በደርግ ዘመንም ሆነ አሁንም በወያኔ አገዛዝ ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት ፈቃድ ይጠየቃል የሚል የተፃፈ ህገመንግስትም ሆነ አዋጅ አልነበረም፤የለምም፡፡ ዋናው ከእኛ የሚጠበቀው ሰላማዊ ሰልፍ እንደምናደርግ ማሳወቅና አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግ ማድረግ እንጂ ፈቃድ መጠየቅ አይደለም፡፡ ይህንንም ለእኛ ጥቅም እንጂ እነሱን ለማስደሰት አይደልም፡፡ እኛ ደግሞ የሀገሪቱን የተፃፈ ህግ ተከትለን ሰልፉን ከማድረጋችን 10 ቀናት አስቀድመን አሳውቀናል፡፡
ኢትዮጵያውያንን በግፍ ለጨፈጨፈው ግራዚያኒ የተሰራለትን ሐውልት በመቃወማችሁ በኢትዮጵያ መንግስት መታሰራችሁ ምን ስሜት ፈጠረባችሁ? ለእኛ የበለጠ የተነሳሽነት ስሜት ሰጥቶናል፡፡ ጉዳዩንም አጠናክረን እንድንሄድ ትልቅ የሞራል ድጋፍ ሆኖናል፡፡
ከእስር ሲለቋችሁ ምን ብለው ነው?
አቶ ታዲዎስ፡- ምንም ሳይሉን ለሁለት ሰው አንዳንድ ዋስ በማስጠራት ለቀውናል፡፡ ምክንያቱን ግን አልነገሩንም፤አላወቅንም፡፡ ከዛ ስትፈለጉ ትመጣላችሁ ብለው በዋስ ለቀውናል፡፡
በታሰራችሁበት ወቅትስ የገጠማችሁ ችግር አለ?
አቶ ታዲዎስ፡- በርግጥ እኔ ላይ ድብደባ አልፈፀሙም እንጂ ተመትተው ፊታቸው በተለይም አፋቸው አካባቢ የደማ ወጣት አይቻለሁ፡፡ ፊታቸው ያባበጠ ወጣቶችንም አይቻለሁ፡፡ ሌሎችንም ወጣቶች እንደደበደቧቸውም ሰምቻለሁ፡፡ በተለይ ደህንነቶች ማታ መጥተው በግል እያስጠሩ በቢሮ ያናግሩ ነበር፡፡ ስራው ግን የፖሊሶች እንጂ የደህንነቶች አልነበረም፡፡ በታሰርንበት ዕለት ያለምግብና ውሃ ቀን ሙሉ እንድንውል ተደርገናል፡፡ በተለይ እስር ቤቱን ስቃይ አራዳ ፖሊስ መምሪያና ጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ያለውን ስታይ ዕቃ ለማስቀመጥ ሆነ ለሌሎች እንሰሳቶች ለአንዲት ደቂቃ እንኳን እንዲቆዩበት አይመችም፡፡ እስር ቤቱን ስታይ በጣም ያሳዝናል፤ እዛ የገቡ እኮ ጤነኛ ሆነው የመውጣታቸው ዕድል እራሱ አነስተኛ ነው፤ለበሽታ የሚያጋልጡ ብዙ ነገሮች አሉ፤ ብቻ በጣም ያሳዝናል፡፡ ይሄ ደግሞ የወንበዴ ስራ ነው፤ ይሄንን መንግስት ማረም አለበት፡፡ ሌላው መርማሪ ፖሊሶችና ደህንነቶች ያልተገቡና ከእስሩ ጋር የማይገናኙ የግል ህይወትን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ፣ የኢ-ሜይል የይለፍ ቃል ይጠይቃሉ፣… ብቻ ብዙ ነው፡፡ በግል እኔን ደግሞ ፊታቸውን በኮፊያ የሸፈኑና ጥቁር መነፅር ያደረጉ ደህንነቶች ዋስ ጠርቼ ከወጣሁ በኋላ አንተ የአርበኞችን ታሪክ እያነሳሳህ ወጣቶችን እያነሳሳህ ስለሆነ ብታርፍ ይሻልሃል፤ በግል ልናናግርህ እንፈልጋለን እያሉ ለማስፈራራት ሞክረዋል፡፡ እኔ ግን በህጋዊ ደብዳቤ ያውም ያመንኩበት ካልሆነ ብትጠሩኝ አልመጣም፤ አላናግርም ብያለሁ፡፡
ከዚህ በኋለስ ይህን ተቃውሞ ለመቀጠልስ እቅዱ አላችሁ?
አቶ ታዲዎስ፡- አዎ አለን፡፡ ይህ ተቃውሞ ምላሽ አግኝቶ ያሰብነው እስኪሳካ እንቀጥላለን፡፡ ነገር ግን ዝርዝር ሁኔታውን በተመለከተ እያጠናን ስለሆነ ወደፊት ሀገር ውስጥ ያለነው ውጭ ካሉ ወገኖቻችን ጋር በመመካከር ምን መልክ መያዝ እንዳለበት ስንወስን ይፋ እናደርጋለን፡፡
በመጨረሻም የሚሉት ነገር ካለ ዕድሉን ልስጥዎት
አቶ ታዲዎስ፡- ህዝቡ ዓላማችን ከግብ እንዲደርስ የተለመደ ድጋፉን ከመስጠት ወደ ኋላ እንዳይል አደራ እላለሁ፡፡
http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/6715

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና የመደራደር አቅማቸው (ክፍል 1)


ዳዊት ተ. ዓለሙ
ምንጭ፣ ዞን ዘጠኝ ጦማር
የፖለቲካ ፓርቲዎች የመደራደር አቅም (Bargaining power) ለዴሞክራሲያዊ ፖለቲካ ስርአት ግንባታም ሆነ በዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ ላይ ተመስርቶ ለሚደረጉ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ስኬታማነት ወሳኝ ነው:: ሁሉን የፖለቲካ ቡድኖች ያማከለ የዴሞክራሲያዊ ተቋማት ምስረታም ሆነ የተቋማቱ ዘላቂነት በዋናነት የሚወሰነው የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚኖራቸው የመደራደር አቅም ልክ ነው:: ሚዛናዊ ያልሆነ የመደራደር አቅም ባላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች መሀካል በሚደረግ ስምምነት የሚፈጠሩ ተቋማትና ስርዓቶች በአመዛኙ ሊያስጠብቁ የሚችሉት ይበልጥ ጠንካራ የመደራደር አቅም ያለውን የፖለቲካ ኃይል ፍላጎቶች ነው:: ይበልጥ የዴሞክራሲ ስርአት ሰፍኖባቸዋል በሚባሉ ሀገራት ውስጥ በትንሹ ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑና የተቀራረበ የመገዳደር አቅም ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚገኙባቸው ናቸው:: የተቀራረበ የመገዳደር አቅም ባላቸው ፓርቲዎች (መሪዎች) ድርድር የሚመሰረቱ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት በአብዛኛው የሁሉንም ፖለቲካ ኃይሎች ፍላጎቶች የማንጸባረቅ እዳላቸው የሰፋ ነው:: ለምሳሌ ያህልም ሮበርት ፑትናም Making Democracy Work ብሎ በሰየመው የምርምር ስራው ለ20 አመታት የኢጣሊያንን ፖለቲካ በቅርብ ከተከታተለ በኋላ ይህንን እውነታ በሰፊው አመልክቷል:: ስለዚህም የፖለቲካ ፓርቲዎች የተቀራረበ የመደራደር አቅም ለሰላማዊ ፖለቲካና ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ወሳኝ ነው::
በሀገራችን የፖለቲካ ቡድኖች (ፓርቲዎች) የመደራደር አቅማቸው የማይመጣጠን በመሆኑ የመገዳደር ፖለቲካ ባህላችን በአፈሙዝ የበላይነት የሚደመደምበት እንዲሆን አድረጎታል:: በዚህም የተነሳ በየወቅቱ ሲገነቡ የነበሩት ተቋማት በስልጣን ላይ ያለውን ቡድን ጥቅምና ህልውና የሚያስጠብቅ ባህሪና ቁመና የተላበሱ ሆነዋል:: የፖለቲካ ፓርቲ እሳቤና ተሞክሮ የሀገራችን የፖለቲካ ባህል ከተዋወቀበት ጊዜ አንስቶ የተመሰረቱ ፓለቲካ ፓርቲዎች ሁሉም ሊያስብል በሚችል መልኩ የመደራደር አቅማቸው በጉልበት ላይ ወይም በተወሰ ጉዳዮች ላይ ብቻ የተነጠለጠለ ነው:: ይህም በመሆኑ በሀገራችን ደካማ ወይም ኢ-ዴሞክራሲያዊ ስርዓትና ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የራቀው ፖለቲካዊ ባህል እንዲሰራፋ ሆኗል::
የመደራደር  አቅም ሲባል
የመደራደር አቅም (Bargaining power) በተለያዩ ጸሃፊዎች በተለያዩ የአረዳድና እውቀት ዘርፎች የተለያየ ትርጓሜ ተሰጥቶታል:: በግርድፉ የመደራደር አቅም ሲባል በአንድ በተወሰነ ሁኔታ ላይ አንድ ተቋም/ግለሰብ በሌሎች ተቋማት/ግለሰቦች ላይ ተጽእኖ ለማሳደር የሚያስችለው አንጻርዊ የተቋማት/ግለሰቦች አቅም ማለት ነው:: ጊዲዮን ዳሮንና እቲኢ ሰንድ በጋራ ባዘጋጁት መጸሃፍ (Political Bargaining: Theory, Practice and Process) ፖለቲካል የመደራደር (Political Bargaining) አቅምን ትርጓሜ ሲሰጡት:- “a tangible effort made by two or more agents with some conflict of interests to reach an agreement over an authoritative allocation of scarce resources” በማለት ነው:: በዚህ አረዳድ ውስጥ ፖለቲካ የታየበት አግባብ ወሳኝ ሃብቶችን ስርጭት መሰረት ያደረገ ነው:: ይህም ከክላሲካል „ፖለቲካ“ ትርጓሚ ማለትም „ፖለቲካ ማለት ከስልጣን ጋር የተያያዘ ጉዳይ ሲሆን ስልጣንም የሀብት ክፍፍልን የሚመለከት ነው“ ከሚለው ዕሳቤ የመነጨ ነው:: ስለዚህም የመደራደር ሂደት የተለያዩ ማህበረሰባዊ ወይም ቡድናዊ ፍላጎቶችን ለማስታረቅና ስምምነት ላይ የተደረሰበት የወሳኝ ሃብቶች ስርጭት ስርዓት መዘርጋት ማለት ነው:: በዚህም የተነሳ የመደራደር አቅም በፖለቲካ ሳይንስ ውስጥ የምንረዳበት አግባብ አንጻራዊነትን የሚላበስና ብዙ አላባውያንን (elements)የሚያቅፍ መሆኑን ነው:: የመደራደር አቅም ከሚታይበት አላባውያን መካከል ወሣኞቹ ድርጅታዊ ጥንካሬ፣ ፍላጎቶችን የማስታረቅና ተጽእኖ የመፍጠር አቅም፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለቸው የቅቡልነት ደረጃ፣ፖለቲካል ታክቲክ እንዲሁም ፖለቲካል ውሳኔያቸው ተተንባይነት ነው:: እያንዳንዱን ጉዳይ ብቻ በመያዝ ብዙ ሊያጽፍ ቢችልም፣ በዚህ ጽሁፍ ተከታታይ ጽሁፍ ለሁለት ከፍለን በተወሰነ መልኩ እንደሚከተለው እንዳስሳቸዋለን::
ድርጅታዊ ጥንካሬና የመደራደር አቅም ውስኑነት
ድርጅታዊ አቅም የተለያዩ ፍቺዎች ቢኖሩትም በሶስት ቁምነገሮች ላይ ያተኩራሉ:: እነርሱም የሰው ኃይል፣ አደረጃጀት እና አሰራር ናቸው:: ኢትዮጵያ በፖለቲካ ፓርቲ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ባህል ውስጥ የገባችው የ1960ዎቹንፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ ነው:: ይህም ሁናቴ በኢትዮጵያ ውስጥ የተመሰረቱት ፖለቲካ ፓርቲዎች በግራ ዘመም ባህል በተለይ ደግሞ ጆሴፍ ስታሊን “የሌኒን ፓርቲ” ብሎ በሰየመው አረዳድ ላይ የተመሰረቱ ናቸው:: ይህ ግራ ዘመም የፓርቲ ፖለቲካ ባህል በፓርቲዎች ርዕዮተ-ዓለማዊ አቋም ብቻ የሚንጸባረቅ ሳይሆን እንደብረት በጠነከረ የፓርቲ ስነ-ስርዓት፣ በዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት፣ ጥብቅ ከላይ ወደታች የዕዝ ሰንሰለት ጭምር የሚታይ ነው:: በዚህ ፓርቲ ፖለቲካ ባህል መሰረት ብሎ ያምናል:: ምንም እንኳን የሃገራችን ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያዩ ርዕዮተ አለምን የሚከተሉ ቢሆንም ይህ አስተሳሰብ በከፍተኛ ሁኔታ የተጫናቸው ናቸው:: በዚህ የአስተሳሰብ ማዕቀፍ ውስጥ ነው እንግዲህ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ድርጅታዊ ጥንካሬና የመደራደር አቅም የሚታየው::
እንደማንኛውም ታዳጊ ሀገር ፖለቲካ በአብዛኛው የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የተመሰረቱት ዘመናዊ ትምህርት በቀሰሙ የማህበረሰብ ክፍሎች ናቸው:: አብዛኛዎቹ ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ የተማሪዎች ንቅናቄ የተሳተፉና በተለያዩ የአመራር ደረጃ የነበሩ ናቸው:: ይህም የተቀዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ልምድና ዕውቅት እንዲኖሯቸው አስችሏቸዋል:: በሌላ መልኩ ደግሞ አብዛኞቹ አመራሮች በተለያዩ ቡድኖች ውስጥ ተሳታፊ ስለነበሩና እርስ በራሳቸው በአይነ ቁራኛ የሚጠባበቁና በከፍተኛ ጥላቻና ቂም በቀል  ስሜት የተዋጡ እንዲሆኑ ስላረጋቸው ከጊዜያዊ ትብብር የዘለለ በመርህ ላይ የተመሰረት አንድነትን መፍጠር እንዳይችሉ አድርጓቸዋል:: በዚህም የተነሳ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እግጅ በጣም ትናንሽ በሆኑ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሞላቱ የሚያመለክተው ቁምነገር የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮች በራሳቸው ዙሪያ የተገነቡ ፓርቲዎችን እንጂ በመርህ ላይ የተመሰረተና የጋራ ፖለቲካዊ አጀንዳ ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ፓርቲዎችን መመስረት አለመቻላቸውን ነው:: ይህም ወደአንድ ላይ መሰባሰብ ቢችሉ ሊያመጡ ከሚችሉት ውጤት አንጻር እጅግ ዝቅተኛ ውጤት እንዲያመጡ ሲያደርጋቸው፤ ልምድ ያላቸው ከፍተኛ አመራሮችም እንዲበታተኑ ሆነዋል::
መሃከለኛ አመራር ደረጃ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ያላቸው የሰው ኃይል አቅም በጣም ትንሽ ነው:: አንደኛ ተምሯል ከሚባለው አጠቃላይ ኢትዮጵያዊ አንጻር ሲታይ በተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ ያለው ሰው እጅግ በጣም አናሳ ነው:: ሁለተኛ ከፍተኛ አመራሮች መሀከል በሚፈጠሩ አለመግባባቶች ፓርቲዎች ሲሰነጠቁ ከፖለቲካ ትግሉ የሚርቀው ከሁለቱም ወገን ከቀረው የሰው ኃይል አንጻር በጣም ከፍተኛው ነው:: ይህም የሚታየው ፓርቲዎች ከተሰነጠቁ በኋላ እንደቀድሞአቸው ለመሆን አለመቻላቸው ላይ ነው:: ሶስተኛ ፖለቲካ ፓርቲዎቹ በአብዛኛው አቅምና እውቀት ላይ ሳይሆን በጥቅመኝነት (Patronage) ላይ የተመሰረቱ ስለሆነ መካከለኛ አመራሮቹ ደካማ አቅም ያላቸው ይሆናሉ:: በአባላት ደረጃም ቢሆን የሚታየው እውነታ የሰው ኃይል ልማት ላይ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ያላቸው አነስተኛ አቅም ነው::
በተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች አደረጃጀትና አሰራር በጣም ደካማ ነው:: አደረጃጀት በመሰረቱ የመጨረሻ ውጤትን ለማሳካት፣ ተጠያቂነትንና ግልጽነትን ለማስፈን እንደግብአት የሚታይ ነው:: በአብዛኛው የተቃማዊ ፖለቲካ ፓርቲዎች አደረጃጀት ግልጽነት የጉደለውና የፖለቲካ ፕሮግራሞቻቸውን ከማሳካት ይልቅ ቁጥጥርና የከፍተኛ አመራሮችን ተክለ-ስብዕና በሚያጎላ መልኩ የሚቀረጽ ነው:: እንደምሳሌ ሊታይ ከሚችሉ ጉዳዮች መካከል የተለያዩ ጥናቶች እንዳመለከቱት አብዛኛዎቹ ፖለቲካ ፓርቲዎች ስምና ፖለቲካዊ ፕሮግራም ሳይሆን የመሪዎች ስም ነው በስፋት የሚታወቀው:: አሰራር (internal working system) ፖለቲካ ፓርቲዎች እንዴት የፖለቲካ ስራዎቻቸውን እንቅስቃሴዎቻቸውን እንደሚያከናውኑ የሚመለከት ነው:: በአብዛኛው የዴሞክራሲ ማዕከላዊነት (democratic centralism) የሚለው የአደረጃጀትና አሰራር እሳቤ ጎልቶ የሚታይ ነው:: ይህም በመሆኑ አብዛኛዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጣም ምስጢረኛነት የበዛው አሰራር፣ የገነነ ማዕከላዊነትና ጥብቅ ከላይ ወደታች አደረጃጀት እንዲሁም ግልጽነት የሚጎላቸው የውስጥ አሰራር ድንጋጌዎች ያሏቸው በመሆናቸው ውስጣዊ ዴሞክራሲያዊ ባህል የጎደላቸው ናቸው:: በዚህም የተነሳ ተራ አባሎቻቸውንና ዜጎችን በተለምዷዊ የፖለቲካ ፓርቲ ስራዎች በሚባሉት ውስጥ የማያሳትፉና በማህበራዊ መሰረቶቻቸው ከሞላ ጎደል አየር ላይ የተንሳፈፉ ናቸው::
ይኸም በመሆኑ ፖለቲካ ፓርቲዎች ያላቸው የመደራደር አቅም እጅግ አናሳ ነው:: አንደኛ፣ እርስ በራሳቸው ያላቸው ድርጅታዊ ግንኙነት ሻካራና ጥርጣሬ ላይ የተተመሰረተ ስለሆነ በአብዛኛው “አንድ-ለብዙ” በሚደረጉ ከገዢው ፓርቲ ጋር የመገዳደር ሂደቶች እስካሁን ውጤታማ ሊሆን አልቻሉም:: ለምሳሌ “28ቱ ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች” ብለው እራሳቸውን የሰየሙት ከገዢው ፓርቲ ጋር በምርጫ ስነ-ስርአቱና በሌሎች አጀንዳዎች መወያየት ቢፈልጉም እስካሁን ያሰቡት ፖለቲካዊ አጀንዳዎች ማስፈጸም ይቅርና ከኢህአዴግ ጋር በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ መወያየት አልቻሉም:: ይህም የሚያመላክተው ተቃዋሚ ፓርቲዎች የጋራ አጀንዳ ቀርጸው ህዝቡና በማስተባበር ገዢውን ፓርቲ የማስገደድ አቅማቸውን መገንባት አለመቻላቸውን ነው::
“አንድ-ለአንድ” በሚደረጉ የመደራደርና የመገዳደር ሂደቶች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያላቸው አቅም እዚህ ግባ የሚባል አይደለም:: ከ1997 ምርጫ በፊትም ሆነ በኃላ ከገዢው ፓርቲ ጋር የተደረጉ የተለያይ ድርድሮች ውጤት አልባ ከመሆናቸውም በላይ ለገዢው ፓርቲ ፖለቲካዊ ጥቅም ለተቃዋሚዎች ደግሞ ፖለቲካዊ ክስረትን ያስከተሉ ናቸው:: ለምሳሌ መድረክ ከምስረታው ጀምሮ ከኢህአዴግ ጋር መደራደር እፈልጋለው እያለ በተለያዩ ወቅቶች ፍላጎቱን ቢገልጽም እስካሁን ከኢህዴግ ጋር መደራደር አልቻለም:: እዚጋ ሊነሳ የሚችለው ጉዳይ ገዢው ፓርቲ የመንግስትን፣ የመከላከያን፣ የደህንነትንና ኢኮኖሚያዊ ተቋማትን በበላይነት ስለተቆጣጠር በተቃዋሚ ፓርቲዎችና በአጀንዳዎቻቸው ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራል የሚል ይሆናል:: ነገር ግን ላለፉት ሁለት አስርተ-አመታት የተቃውሞ ጎራው የገዢውን ፓርቲ አካሄድ ተረድቶ ይህንኑ የሚመጥንና አሸናፊ ወይም ተገዳዳሪ የሚያደርጋቸውን አቅም አለመገንባታቸው ሙሉ በሙሉ በገዢው ፓርቲ ሁሉን-አቀፍ አቅም (overwhelming power) የሚገለጽ አይደለም:: ወሳኝ በሆነ መልኩ ውስጣዊ ድክመታቸውን የሚያሳይ እንጂ:: ፈረንጆቹ እንደሚሉት ወረራ በራሱ የድክመት ማሳያ ሲሆን በወረራ ተሸናፊነት ምንጩ ደግሞ ውስጣዊ ድክመት ነው:: የገዢው ፓርቲ ተጽእኖ ውጤታማነት ምንጩ የተቃማዊ ኃይሎች ውስጣዊ ድክመት ነውና::
በሌላ በኩል ደግሞ ተቃዋሚዎች እርስ በራሳቸው ያላቸው ድርጅታዊ ግንኙነት ሸካራና ጥርጣሬ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ በረጅም ጊዜ በሚደረጉ ግንኙነቶችና መስተጋብሮች (Isomorphic process) ሊፈጠሩ የሚችሉ የጋራ አጀንዳዎችና ሊደረስበት ይችል የነበረው በጋራ አብሮ የመስራት ተቋማዊ ዝግጅት አናሳና ዘገምተኛ እንዲሆን ሆኗል:: በተቃዋሚ ፖለቲካ ውስጥ የሚሳተፉ አመራሮች ምንም እንኳን በአካዳሚክ ዕውቀታቸው አንቱ የተባሉ ቢሆኑም የመሰረቷቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች በአብዛዎቹ ውስጣዊ መረጋጋትና አንድነት የጎደላቸው ናቸው:: ይህም በመሆኑ በሚደረጉ ድርድሮች አብዛኞቹ አንድም ያነሷቸውን ፖለቲካዊ ፍላጎችውን ከገዢው ፓርቲ ጋር በሚደረጉ ውይይቶች ለማሳካት በሙሉ አቅማቸው በመሳተፍ፤ ሁለትም የገዢውን ፓርቲ ሌሎችን ፓርቲዎች በማዳከም የሚያረገውን እንቅስቃሴ ከመግታት አንጻር “ታማኝ ተቃዋሚ” በመሆን መካከል አጣብቂኝ ውስጥ የገቡና የሚዋዥቁ ናቸው:: በዚህም የተነሳ የተቃዋሚዎች የመደራደር አቅም ባላቸው ውስጣዊ ድርጅታዊ አቅም እየተሸረሸረ የማስገደድ አቅማቸው እየተመናመነ ከገዢው ፓርቲና እርስ በራሳቸው በሚያደርጓቸው ድርድሮች ተቀባይ አሊያም ከድርድሩ የሚርቁ ሆነዋል::
ከላይ እንደጠቀስኩት የድርጅታዊ አቅም ውስንነት ከመደራደር አቅም አላባውያን አንዱና ዋነኛው ሲሆን በተከታዩ ክፍል ቀሪዎቹን ሁለቱን አላባውያን ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታና ማጠቃለያ ጋር እንመለስበታለን፡፡
ጸሐፊው አቶ ዳዊት ዓለሙ የUniversity of Passau Governance and Public Policy ድኅረ ምረቃ ተማሪ ናቸው፡፡ ጸሐፊውን ለማግኘት በኢሜይላቸው dhabesha@hotmail.com ይጻፉላቸው፡፡
http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/6711

ከእሁድ እስከ እሁድ


(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)
bottle


አንድ ላስቲክ ውሃ 10 ብር!!
በአፋር የቡሬ ነዋሪዎች ለከፍተኛ የውሃ ችግር መዳረጋቸውን ውሃ የሚሸጥበትን ላስቲክ በፎቶ በማያያዝ የጎልጉል የአይን ምስክር ከስፍራው አስታውቋል። በክልሉ የጎልጉል ተከታታይ የሆኑ እንደገለጹት በመጠጥ ውሃ ችግር እየደረሰ ያለው ችግር ከፍተኛና ህይወትን የሚፈታተን ነው። አካባቢው የጦር ቀጠና ከመሆኑ አንጻርና የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር አሳሳቢ እንደሆነ ያስታወቀው የአይን ምስክር “እባካችሁ የሚሰማ ካለ ንገሩልን” ሲል ጥሪ አስተላልፏል።
የውሃ ችግር ጊዜ የሚሰጥ ባለመሆኑ አንድ ላስቲክ ውሃ 10 ብር ለመግዛት መገዳዳቸውን፣ በዚህም ቢሆን እንደ ልብ ማግኘት እንደማይቻል አመልክቷል። በስፍራው ያለውን የውሃ ችግር አስመልክቶ ሎጊያ የሚገኝ ጎልጉል የአይን ሪፖርተር አስተያየቱን እንዲሰጠን ጠይቀነው የበኩሉን ማጣራት ካደረገ በኋላ ችግሩ መኖሩን አረጋግጦልናል። ቡሬ አካባቢ ያለው ውሃ ችግር በዋናነት የሚጠቀስ ቢሆንም በተመሳሳይ የሚቸገሩና በድርቅ የተመቱ ቦታዎች እንዳሉ አመልክቷል። አንዳንድ የወታደር ተሽከርካሪዎች ውሃ እንደሚሸጡ መረጃ ማግኘቱንም ገልጿል።
“የልማት ሰራዊት” ያልተገነባበት ምክንያት ይገምገም ተባለ
ባህር ዳር ከተማ የአራት ቀን ጉባኤ ለማካሄድ የከተመው ኢህአዴግ በበቂ ሁኔታ የልማት ሰራዊት አለመገንባቱን፣ ከፍተኛ የሚባል የገንዘብ ችግር እንዳጋጠመው፣ ኢንዱስትሪው ግብርናውን ተረክቦ ያገሪቱን ኢኮኖሚ እንዲመራው የተያዘው እቅድ የተፋዘዘ መሆኑንና የግሉ ዘርፍ በሚገባ አለመንቀሳቀሱን በመግለጸ ጉባኤው ችግሮችን መርምሮ መፍትሄ እንዲፈልግ ተጠየቀ፡፡
የ2004 የግብርና ምርት አድገት ከተያዘለት መሰረታዊ የእድገት መጠን አማራጭ “አንሶ ማደጉን”፣ ለዚህም ምክንያቱ የልማት ሰራዊት ባግባቡ መፈጠር ባለመቻሉ ነው። በተፈጥሮ ጥበቃ የተሻለ የልማት ሰራዊት መገንባት ቢቻልም በሰብል ልማት ዘርፍ ግን ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር ያለፈ ስራ እንዳልተከናወነ ተጠቆመ። “ጓድ” ሃይለማርያም ደሳለኝ ዘጠነኛው የኢህአዴግ ጉባኤ የልማት ሰራዊት መገንባት ያልተቻለበትን ምክንያት ፈትሾ፣ የድርጅቱንና የህዝቡን የማስፈፀም አቅም በመገንባት ዘርፉን ወደፊት ለማሸጋገር የሚያስችል አቅጣጫ የማስቀመጥ ሀላፊነት እንዳለበት አመልክተዋል።
የፋና ብሮድ ካስቲንግን ጨምሮ የተለያዩ የኢህአዴግ መገናኛዎች እንዳሉት “ጓድ” ሀይለማርያም በንግግራቸው በአገሪቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ “የአክራሪነት አስተሳሰቦች” ብቅ ማለታቸውን አንስተዋል። እነዚህ የአክራሪነት አስተሳሰቦች ከመሰረታዊ የአገሪቱ ህገ መንግስት መርህዎች ጋር የሚጋጩ ናቸው ብለዋል። የህዝቡን ዲሞክራሲያዊ አንድነትና እኩልነት፣ የመንግስትን ከሀይማኖት ነፃ ሆኖ ሁሉንም በእኩልነት የማገልገል ሀላፊነቱን የሚፃረሩ በመሆናቸው ሁሉም ሊታገላቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል። በሃይማኖት ቤቶችና ደጆች አስተዳደራቸው ውስጥ ሙሉ በሙሉ የሚዋኘውን መንግሥታቸውን አቶ ሃይለማርያም በንግግራቸው “አሁንም መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም” ሲሉ ገልጸውታል።
አንደበት
“……አቶ መለስ ህወሓትን ከፊት አድርገው አዲስ አበባ ሲገቡ እውነተኛ ብሔራዊ እርቅ አድርገው ቢሆን ኖሮ ዛሬ ተገፍተን በስደት ያለን ሁላችን በየሙያችን አገራችንና ወገኖቻችንን እናግዝ ነበር። የሆነው ግን የተለየ ነው። መለስ “እነሱ” ብሎ ሌሎችን በመወንጀል ጥላቻን ማወጅ ጀመረ። ትውልድን የሚያንጽ ብሄራዊ ሚዲያ ሳይቀር የጥላቻና የቂም ስብከት እንዲያስተጋባ ተደረገ። የዚህ መዘዝ ዛሬ ላይ ጣለን። የጋራ ንቅናቄያችን “እነሱ” የሚል ቋንቋ የለውም። ስንጀምር “እኛ” ብለን ነው። ይህ ልዩ ያደርገናል። የሰው ልጆች ጥላቻን ለመሸከም አይመጥኑም። ጥላቻ የሚዘራብን እንደሰው ስለማንታይ ነው። እንደ ሰው ስላልተከበርን ነው። ሰው መልካም ነገር እንዲያደርግ ከፈጣሪ የተሰጠው ልዩ ስጦታ አለው፡፡ መለስ ግን ይህንን ረስቷል። በብሄር ብሄረሰብ ስም ሲምል ሁላችንንም ሳያሳፍር ነው። ብቻውን ወይም ጥቂት ሰዎች ይዞ ወደ ጥፋት ሄደ፤….”
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር  አቶ ኦባንግ ሜቶNovember 16, 2012 ለጎልጉል ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ
“በአፋር የከብት መኖ ለምግብነት እየዋለ ነው”
በአፋር ክልል ካለፉት አራት ወራት ጀምሮ የተከሰተው ከፍተኛ ረሀብና የውሀ እጥረት የበርካታ ህጻናትን ህይወት መቅጠፉን ነዋሪዎች እንደገለጹለት ጠቅሶ ኢሳት ዘገበ። ምንም እንኳ 60 በመቶ በሚሆነው የአፋር አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የምግብና የውሀ እጥረት ቢከሰተም፣ ችግሩ ከሁሉም ወረዳዎች አስከፊ በሆነበት የእዳ ወረዳ 6 ህጻናት በአንድ ወር ውስጥ ሞተዋል። ይህ አሀዝ በአንድ ሰፈር ብቻ የተጠናከረ እንጂ በአጠቃላይ በወረዳው በተከሰተው ረሀብና የውሀ እጥረት የሟቾች ቁጥር በብዙ መቶዎች ሊደርስ እንደሚችል ኢሳት ነዋሪዎችን ጠቅሶ አመልክቷል።
አንድ ጀሪካን ውሀ በ60 ብር ለመግዛት መገደዳቸውን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የእዳ ወረዳ ነዋሪ መናገራቸውን የገለጸው ኢሳት፣ የአካባቢው ነዋሪ ፍየሎቹና ግመሎቹ አልቀውበት ወደ አሳይታ ስደት መጀመራቸውን፣ አሳይታ በሰላም የደረሱት በህይወት ሲትረፉ ሌሎች ደግሞ በመንገድ ላይ ማለቃቸውን አትቷል።
የመንግስት እርዳታ እንዳልመጣላቸው የተናገሩት ነዋሪዎቹ ፣ አስቸኳይ እርዳታ ካልደረሰ አስከፊ እልቂት እንደሚከሰት መናገራቸውን ኢሳት አውስቷል። በአካባቢው የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ የሚገኘው የአፋር ጋድሌ (የአፋር ተቃዋሚ ድርጅት) ሊ/መንበር ኮሎኔል ሙሀመድ አህመድ ከፍተኛ ረሀብ በአካባቢው መግባቱን ድርጅታቸው እንደሚያውቅ ለኢሳት ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ እሁድ ኢሣት ፍኖተ ነጻነትን ጠቅሶ ባሰራጨው ተመሳሳይ ዜና በአፋር ረሃብ ጠንቶ የሰዎችን ህይወት ማጥፋቱን አስታውቋል፡፡ የተረፉትም በዕርዳታ የመጣ የከብት መኖ እየጋገሩ ለመመገብ መገደዳቸውን አመልክቷል፡፡
ሚድሮክ ከ632 ሚሊዮን ብር የግብር ዕዳ አለበት
ሚድሮክ ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ከንግድ ትርፍ ግብርና ከተጨማሪ እሴት ታክስ ከ632 ሚሊዮን ብር በላይ ዕዳ በመንግሥት እንደሚፈለግበት ሪፖርተር ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል። በዜናው መሰረት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በቅርቡ ለሚድሮክ ኢትዮጵያ በላካቸው ሦስት የትርፍ ግብር ውሳኔ ማስታወቂያዎች የተጠቀሰው ገንዘብ እንዲከፈል ጠይቋል፡፡
ደብዳቤው አዋጅ ጠቅሶ ከማንኛውም ንግድ ትርፍ፣ ከተጨማሪ እሴት፣ ከተጨማሪ ግብር በመቶኛ በማስላት የተጠየቀውን ገንዘብ በ30 ቀናት ውስጥ ገቢ እንዲያደርግ መጠየቁን ያስረዳው የሪፖርተር ዘገባ ሚድሮክ ግዳጁን ካልተወጣ በህግ እንደሚጠየቅ እንደተገለጸለት ያስረዳል። በሌላም በኩል ቅሬታ ካለ አቤት ማለት እንደሚችሉ በደብዳቤው ላይ መጠቀሱን ለሪፖርተር የነገሩት የሚድሮክ ምንጮቹ ናቸው።

አልጀዚራ ከታነቀ በኋላ ጠንካራ ሪፖርት አቀረበ
የአልጀዚራ የቴሌቪዥን ስርጭት ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይተላለፍ መደረጉን አልጀዚራ ድርጊቱን በመቃወም ያስታወቀው በሳለፍነው ሳምንት ነበር። ጣቢያው ስርጭቱ የተቋረጠበትን ምክንያት እንዲገልጹለት ኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄ ቢያቀርብም መልስ እንዳልተሰጠው አስታውቋል። አልጀዚራ የቢቢሲ የስለላ ሪፖርት የኢትዮጵያን መንግስት ባጋለጠ ማግስት ማስተባበያ የሚመስል ስርጭት አስተላልፎ እንደነበር የሚያስታውሱ መንግስትን በመደገፍ መልኩ ሳይሆን አልጀዚራ ለበርካታ ጉዳዮች ሽፋን እንደማይሰጥ በመጥቀስ “የጁን አገኘ” ሲሉ ተጠምደዋል። አልጀዚራ በወቅቱ የምግብ እህል ርዳታ ለፖለቲካ አላማ ይውላል በተባለበት ቦታ አርሶ አደሮች ቤታቸው ድረስ በመግባት ነበር ሰፊ ከኢቲቪ የበለጠ ሪፖርት ያቀረበው።
የአልጃዚራ ድረገጾች እንዲታነቁ የተደረጉበት ዋናው ምክንያት የቴሌቪዥን ጣቢያው ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተቃውሞ በሰጠው ሽፋን እንደሆነ አመልክቷል። እንደ ጉግል የመረጃ ትንተና በኢትዮጵያ ውስጥ የእንግሊዝኛው ድረገጽ ባለፈው ዓመት ሀምሌ ወር 50ሺ ተጠቃሚ የነበረው ሲሆን፣ በመስከረም ወር የተጠቃሚው ቁጥር ወደ 114 ወርዷል። የአረቢኛው ድረገጽም ከ5,371 ተጠቃሚዎች ወደ 2 መውረዱን ያሳያል። ይህንን መረጃ የዘረዘረው አልጀዚራ ይህ መረጃ የሚያሳየው ጣቢያው በነሃሴ ወር የኢትዮጵያ መንግስት በእምነት ጣልቃ እንደሚገባ ካስተላለፈ በኋላ በተወሰደው የእግድ ርምጃ መሆኑንን አመልክቷል። አልጀዚራ ከታገደ በኋላ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ሁኔታና የጋዜጠኞችን እስር በስፋት በዶክመንታሪ መልክ አቀናብሮ አስተላልፏል።
የኤሌክትሪክ መቋረጥ ማሽን እያቃጠለ ነው
በአዲስ አበባ ሰሞኑን በተደጋጋሚ ኤሌክትሪክ እየተቆራረጠ በመሆኑ ስራችንን በአግባቡ መስራት አልቻልንም ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን እያቀረቡ ነው። ከነዋሪዎች በተጨማሪ አንዳንድ ፋብሪካዎችና የተለያዩ ተቋማትም የሃይል መቆራረጡ ችግር እየፈጠረባቸና ማሽኖቻቸውን እያቃጠለባቸው መሆኑን በመግለጽ  የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ከአገር ውስጥ ተዘገበ።
በኮርፖሬሽኑ የዲስትሪቢዩሽን ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ መስፍን ብርሀነ እንዳሉት፥ የግንባታ ስራዎች በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የወሰን ማስከበር ስራ ሲሰራ በቦታው የነበሩ የኤሌክትሪክ መስመሮችን የማዛወር ስራ ስለሚሰራ ፤ በአንዳንድ አካባቢዎች በኔትዎርኮቹ ላይ የሚካሄደው ዝርፊያ እና የሚደርሰው የመኪና ግጭት ለችግሩ መንስኤ መሆናቸውን፣ ሰሞኑን እያጋጠመ ያለው ንፋስም ለችግሩ ምክንያት ሲሆን ፥ በዚህም የኤሌትሪክ መስመሮች ላይ ጉዳት ስለሚደርስና የኤሌትሪክ መስመሩን መልሶ መጠገን እስኪቻል የኤሌትሪክ ማቋረጡ ያጋጥማል ብለዋል። በዚህ ምክንያት በተለይ በኤሌክትሪክ እቃዎች ላይ ለሚፈጠረው መቃጠልና መሰል ችግሮች ፣ ኮርፖሬሽኑ አስፈላጊውን ካሳ እንደሚከፍል ሃላፊውን ገልጾ ፋና ዘግቧል። ሃላፊው ይህንን ቢሉም የችግሩ ሰለባ የሆኑ በተባለው መሰረት ካሣ እንደማያገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡
http://www.goolgule.com/briefs-22/

ነጋሶ ሞገቱ ወይስ ተሞገቱ?


“ኢህአዴግ በህዝብ (ያልተመረጠ) ስለሆነ እውቅና አንሰጠውም”
N G


“ … አንተም ሆንክ ማንም ኢትዮጵያዊ ውጪ ያሉትን ጨምሮ ቢደግፉን ደስ ይለናል። በዚህ መንገድ ሂዱ ብለው እንዲጠመዝዙን ግን አንፈልግም። … ሰላማዊ ትግል የምትሉት ለውጥ አያመጣም ይሉናል። እንደዚህ የምትሉ ከሆነ ከፈለጋችሁ ገንዘብ አትርዱን እንላቸዋለን … ኢህአዴግን እንደ መንግስት እውቅና አንሰጠውም” ከዶ/ር ነጋሶ የተመረጡ መልሶች መካከል የተጠቀሱ ናቸው። በዚህና በሌሎች ምክንያቶች ዶ/ር ነጋሶ ሊሞገቱ ሄደው ሞገቱ የሚል ርዕስ ለጽሁፌ መረጥኩ።
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አንድነትን በመወከል ሬዲዮ ፋና በሚያዘጋጀው የ”ሞጋች” ቃለ ምልልስ ክፍለ ጊዜ ላይ ተገኝተው ነበር። ቃለ ምልልሱ ከመጀመሩ በፊት “ጋዜጠኛው” ፕሮግራሙ ፈረንጆቹ እንደሚሉት “ሃርድ ቶክ አይነት ነው” አለ። ይህን ጊዜ ቀልቤን ሳበኝ። የቢቢሲው የሃርድ ቶክ ክፍለጊዜና የጠያቂው ጠልቆ የመግባት ችሎታ ታየኝና ዶ/ር ነጋሶ ሲዝረከረኩ ለመስማት ተዘጋጀሁ።
ጥያቄ ተጀመረ። ዶ/ር ነጋሶ መመለስ ቀጠሉ። የመጀመሪያዎቹ ጥያቄዎች የተለመዱ፣ የተረገጡ፣ የተሰለቹና በየመድረኩ ብዙ የተባለላቸው ሆኑብኝ። ዶ/ር ነጋሶም ሳይቸገሩ ከፈገግታ ጋር መለሱ። በመነሻው የቀረቡትን የተለመዱ ጉዳዮች በመዝለል በሶስት ጉዳዮች ላይ በማተኮር ሪፖርት ለማዘጋጀት ወሰንኩ።
ስለ ጠያቂው
አቶ ሴኩ ቱሬ ጌታቸው
ጠያቂው ጋዜጠኛ ነጋሶን ሲጠይቅ ላዳመጠ ጋዜጠኛ ሳይሆን ትክክለኛ ስሙ “ካድሬ” ነውና በዚህ ይስተካከል። መጀመሪያ ላይ “ይባላል፣ ይነገራል፣ ይደመጣል፣ አስተያየት ይሰጣል …” በማለት አግባብ ያለው አካሄድ ተከተለና በኋላ ላይ ግምገማ ፍርሃቻ ነው መሰል ነጋሶን አላናገር ብሎ ጭልጥ ያለ ክርክር ውስጥ ሲገባ ከኋላው አቶ ሴኩ ቱሬ ጌታቸው ምናምን የሚያሳዩት ይመስል ነበር። ያም ቢሆን “ገራም”፣ ቀስ ብሎ የሚናገርና በድርጅት ፍቅር የደረቀ አይመስልም።
የግራ ዘመም ስለመሆናቸው
ነጋሶ አሁን የሚመሩት አንድነት ፓርቲ የሊብራል ፖለቲካ እሳቤ አቀንቃኝ ነው። እሳቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ “የግራ ዘመም” ፖለቲካ አፍቃሪ ነበሩ። ኢህአዴግ ውስጥም ዋናው የልዩነታቸው መሰረት የግራውን መንገድ በትክክል መከተል ያለመቻልና የመበረዝ ችግር ነው። ዛሬ ምን ተገኘና ነው አዲስ አቋም የተያዘው በሚል ጠያቂው ያነሳው ሃሳብ የስሙን ያህል ባይሆንም ሙግት አስነስቶ ነበር። ጥያቄው ግን ምላሽ ያገኘው ውይይቱ ሲያልቅ ነው።
“ግራ ዘመም ምንድነው” አይነት ጥያቄ አንስተው ከዓለም ወቅታዊ ሁኔታ ጋር መመሳሰል አግባብ እንደሆነ በማስገንዘብ አስተያየታቸውን የሰጡት ነጋሶ፣ “ትክክለኛ” የሚሉትን ሶሻሊዝም እንደሚናፍቁ አልሸሸጉም። ይህ አስተሳሰባቸውና እምነታቸው አንድነት ከሚከተለው መንገድ ጋር እንዴት ሊጣጣም እንደሚችል የገለጹት ግን ዓለምን መምሰል በሚለው እሳቤ ነው። ጠያቂው በውይይቱ ማሳረጊያ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት በድጋሚ ይህንኑ ጉዳይ አንስቶ ነበር። ነጋሶ ግን “አንድ ሰው ድንጋይ አይደለም። አቋሙን መቀየር ወንጀል አይደለም” በሚል ዘጉት። አዎ፣ አቋም ለያውም በፖለቲካው ጎዳና የሚቀያየር፣ ዓለምን እያዩ የሚበውዙት የካርታ አይነት ጨዋታ ነው። እናም “እሰይ አበጀሁ” አይነት መልስ መልሰው ተሰነባበቱ።
የጣመኝ ፈርሙ” ክርክር
የምርጫ የስነ ምግባር ኮድ ጉዳይ ለዚህ ሪፖርት አቅራቢ ምርጥ የተባለና የነጋሶ የህግ ግንዛቤ በቀላሉ ነገሮችን በማስረዳት ጎልቶ የወጣበት ነበር። እንዲህ ተባባሉ። ጠያቂው “የምርጫ ስነ ምግባር ኮዱን ብትፈርሙ ምን ትሆናላችሁ?” አለ። “አዋጅ በሆነ ጉዳይ ላይ ለምን እንፈርማለን። እንደዚህ ከሆነ ባገሪቱ በየጊዜው በሚወጡ ህጎች ላይ እንፈርማ?” የነጋሶ ውድ መልስ ነበር።
ጥያቄ፦ ብትፈርሙ ምን ይጎዳችሁዋል …?
ነጋሶ፦ ለምን እንፈርማለን? ለህዝብ ጥቅም ሁላችንም ስንሰራ ኢህአዴግ በሚለው ተንበርክከህ ኢህአዴግን በምርጫ በማጀብ አይደለም …
ጥያቄ፦ ጉዳት አለው ህዝቡ ይጎዳል? ህግ ሆኗል አይደለም?
ነጋሶ፦ የስነ ምግባር ኮዱ ብቻውን በቂ አይደለም፤…. የኢህአዴግ አዲሱ ሊቀመንበር በመጀመሪያው ንግግራቸው ያሉትን አልሰማህም?
(ፎቶ: Martin Edström)
ጥያቄ፦ … ምን ጉዳት ይደርስባችኋዋል?
ነጋሶ፦ እነሱ ቢወያዩና ችግራቸውን ቢያስወግዱ ምን ችግር አለው?
ጥያቄ፦ ፖለቲካ አብሮ የመኖር ጥበብ ነው። አብሮ መስራት ጥቅም አለው፤
ነጋሶ፦ ያ! ያ! አብሮ መስራት በእኩልነት ነው እኮ!! ኢህአዴግ አንድ የፖለቲካ ሃይል ነው ወይስ አይደለም? ለምን እንበረከካለን? ንግረኝ?
ጥያቄ፦ ለህጉ ትገዙ አይደል?
ነጋሶ፦ ያ!! እኮ፤ አዋጅ ሆኖ በወጣ በስንት ህግ ላይ እንፈርማለን? ይህ ከሆነ ፓርላማ ቢስማማም ባይስማማም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሁሉም ጉዳዮች ላይ መፈረም አለበት ማለት ነው፤
በቀጣይ ወደ ሌላ የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ አልፉ። ማጠቃያው ላይ አነሳዋለሁ፡፡
ለስደተኞችና ለስደተኛ አስተሳሰብ ትገዛላችሁ?
ጠያቂው ሊሞግት ያሰበበት ዋናው ጉዳይ መድረክም ሆነ አንድነት ከዲያስፖራው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በሚያውጣጣና በትጥቅ ትግል ከሚያምኑ ወገኖች ጋር ለመደመር ነበር። ከውጪ ሃይሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ እንደሚታሙና ለዚህም መረጃ እንዳለው አንስቶ ላቀረበው ጥያቄ ማሰሪያ ያደረገው “አገር ቤት ያለውን ህዝብ አክብሮት አትሰጡትም። ለስደተኛና ለስደተኛ አስተሳሰብ ልዩ አክብሮት አላችሁ” የሚል ነበር።
ነጋሶ ከወትሮው ለየት ብለው ፖለቲካኛ የሆኑበትን መልስ የሰጡት ዲያስፖራውም ሆነ ማንም፣ ጋዜጠኛውን ጨምሮ ቢደግፉዋቸው ደስተኛ መሆናቸውን በማመለካት መልስ ጀመሩ። አስከትለውም “በየኤምባሲው ደጅ አይታጡም” እንባላለን አሉ። ነጮቹ የሚሰጡት ድጋፍ ለተሰጠበት ዓላማ እንዳልሆነ ለምን አትናገሩ ይባላል? በማለት ጠየቁ።
ስለ ዲያስፖራውና “ስደተኛ አስተሳሰብ” ስለተባሉት ሲናገሩ የሰላማዊ ትግል መንገዱ አያዋጣም የሚሉዋቸው እንዳሉ አመለከቱ። ሲያጠቃልሉት ማንም ይሁን ማን “ሰላማዊ ትግል አያዋጣችሁም ለሚሉን ከፈለጋችሁ ገንዘባችሁን አትርዱን እንላቸዋለን” በማለት የራሳቸውን መንገድ እንደሚከተሉ ገልጸው ጥያቄውን ቆለፉት።
አገር ውስጥ ያለውን ህዝብ አታከብሩትም ለሚለው ግን “በርግጥ በሚፈለገው ደረጃ ህዝብ ውስጥ ላንቀሳቀስ እንችላለን” በማለት ራሳቸውን ጥፋተኛ አስመስለው ቢሮ ይታሸግብናል፣ እኛን የሚደግፉ ከስራ ይባረራሉ፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አይፈቀድልንም፣ ሰላማዊ ሰልፍ እንድናደርግ አይፈቀድም፣ መምህራን እኛን ስለደገፉ ይባረራሉ፣ … ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ኢህአዴግ እንደሆነ ተናገሩ።
ኢህአዴግን ተቀብለውና ደግፈው ከሚሰሩ ፓርቲዎች ጋር አብረው መስራት እንደማይችሉ ሲገልጹ “ኢህአዴግን ከሚደግፉት ጋር ተቀምጠን ምን አብረን ልንሰራ እንችላለን” ካሉ በኋላ “ኢህአዴግን እንደመንግስት እውቅና ሰጥተው ከሚንቀሳቀሱት መካከል ኢዴፓ በርካታ ልዩነቶች አሉት ግን ኢህአዴግን እንደ መንግስት እውቅና በመስጠት ይቀበላል። እናንተስ?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ “ኢህአዴግ በህዝብ፣ በምርጫ ገዢ ያልሆነ ፓርቲ ስለሆነ እውቅና አንሰጠውም” የሚል ግልጽ መልስ ሰንዝረዋል።
“ስለ አንቀጽ 39 ለምን አሁን ትጠይቀኛለህ?”
ነጋሶ ፓርቲያቸው አንቀጽ 39 እና የመሬት ጉዳይ ላይ ስላለው አቋም ግልጽ ያለ መልስ እንዲሰጡ በተደጋጋሚ ተጠይቀው ነበር። በግራም ሆነ በቀኝ፣ እሳቸው በጻፉት መጽሃፍ ላይ ካቀረቡት ሃሳብ ጋርና ቀደም ሲል ኢህአዴግ በነበሩበት ወቅት ሲያራምዱት ከነበረው ሃሳብ አንጻር የሃሳብ መንሸራተት እንዳጋጠማቸው በማስመሰል ጠያቂው ሊሞግታቸው ሞክሮ ነበር። በተደጋጋሚ ለማስረዳት ቢሞክሩም ሊቀበላቸው ባለመቻሉ “አንድ ሰው ድንጋይ አይደለም። የአቋም መቀያየር ወንጀል አይሆንም” በማለት አሳርገውታል።
በጥቅሉ ግን ካላይ የተነሱት ሁለት መሰረታዊ ሃሳቦች ህዝብ ውሳኔ ሊያሳልፋቸው እንደሚገባ አመልክተዋል። መገንጠል መብት ቢሆንም እርሳቸው እንደማይደግፉት በግልጽ አስቀምጠው ያለፉት ነጋሶ፣ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በመመስረት የሚመለሱ ጉዳዮች እንደሆኑ ግን አስምረውበታል። ምንም እንኳ ፓርቲያቸው የኒዎ ሊብራል ሃሳብ አራማጅ ቢሆንም በግላቸው በነጻ ኢኮኖሚ ስም መንግስት ከዋናና ህዝብን ከሚያገለግሉ ዋና ዋና የኢኮኖሚ አውታሮች መውጣት አለበት ብለው እንዳማያምኑ አስምረውበታል። በመድረክ ውስጥ ያሉት ፓርቲዎች ተመሳሳይ አቋም ባልያዙበት ሁኔታ ግንባር መመስረቱ ችግር እንዳለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነና ዋና የሚባሉት የልዩነት ቁልፍ ጉዳዮች ህዝብ ውሳኔ እንዲሰጥባቸው በመዘርዘር አልፈዋቸዋል።
ጠያቂው መሃል በመግባት አንቀጽ 39ን ትቀበላላችሁ? በሚል ላቀረበላቸው “አሁን ለምን ትጠይቀኛለህ” በማለት አስረግጠው መልስ ሰጥተዋል። በዚሁ የራዲዮ ፋናን ስቱዲዮ በስንብት ለቀው ወጥተዋል።
ነጋሶ እንደ ፖለቲከኛ ድርጅቱ ላይ ደረሱ የተባሉትን ችግሮች በየመካከሉ በማስገባት ጥያቄን በጥያቄ መመለስ ቢችሉ ኖሮ ይበልጥ አሸናፊ ሆነው መውጣት ይችሉ ነበር። ለምሳሌ ስለህጋዊነት ሲነሳ የራዲዮ ፋና አፈጣጠር ህጋዊ አለመሆኑንና ኤፈርት ስለተቆታጠረው የኢኮኖሚ የበላይነት፣ ስለ እስርና የሚዲአ አፈና … በየመልሶቻቸው መካከል በማስገባት ቢመልሱና ጥያቄ ቢሰነዝሩ ቢያንስ ሃሳባቸውን በአድማጭ ላይ አራግፈው መውጣት በቻሉ ነበር። እንዲህ ያለ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን ሲገኝ መሰረታዊ ብቻ ሳይሆን ራሳቸው የኢህአዴግ አባላት የሚያጉረመርሙትን ጉዳዮች በማንሳት የራሳቸውን ልምድና ተሞክሮ ማካፈል ይችሉ ነበር። ጠያቂው ከኢህአዴግ ስለተለዩበት ምክንያት በሰሚ ሰሚ ላነሳላቸው ጥያቄ “ቆቅ” ፖለቲከኛ ሆነው መረጃ ማስተላለፍ ሳይችሉ መቅረታቸው የዕለቱ ድክመታቸው ቢሆንም ሊሞገቱ ተጋብዘው ሞግተው ስለመውጣታቸው የዚህ ሪፖርት አቅራቢ ምስክራቸው ነው፡፡
http://www.goolgule.com/interview-negasso/

Monday, March 25, 2013

የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው



ከመጋቢት 2 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ማቆም አድማ ላይ የነበሩት የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ እንደሆነ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፁ፡፡

የትምህርት ጥራት መጓደል፣ የአስተዳደራዊ ችግሮችና በምግብ ጥራት መጓደል ምክንያት ጥያቄያቸውን ለኮሌጁ አስተዳደር ቢያቀርቡም ምላሽ በማጣታቸው የትምህርት ቆም አድማ ለማድረግ የተገደዱት ቅድስት ስላሴ መንፈሰሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት በርሀብ ተጎድተው ራሳቸውን በመሳት በመጀመራቸው በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል መወሰድ መጀመራቸውን ስቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ተማሪዎች ተናግረዋል፡፡   

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኛም በቅድስት ስላሴና በየሆስፒታሎቹ ተዘዋውሮ እንደተመለከተው አባ እያሱ ሰብስቤ የተባሉ ተማሪ በየካቲት 12 ሆስፒታል እንዲሁም ደቀመዝሙር በኃይሉ ሰፊ ምኒሊክ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ መሆኑን አረጋጧል፡፡ አመሻሹ ላይም ገ/እግዚያብሄር የተባሉ ተማሪ በአምቡላንስ ከኮሌጁ ተወስደዋል፡፡ ተማሪዎቹ በደል አድርሰውብናል ከሚሉዋቸው የኮሌጁ ሀላፊዎች ውስጥ መምህር ፍስሀፂዮን ደሞዝ አካዳሚክ ዲን እና መምህር ዘላለም ረድዔት የቀን ተማሪዎች አስተባባሪ በዋነኝነት ተጠቅሰዋል፡፡

ደረሰ ስለተባለው ችግር ለማጣራት ጥያቄ ያቀረብንላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሀፊ ብፁዕ አቡነ ህዝቅኤል በኮሌጁ ጉዳይ ስብሰባ ላይ እንደሆኑ ተናግረው የነበረ ቢሆንም ተሰብሳቢ ባለመሟላቱ ስባሰባው እንዳልተደረገ ለፍኖተ ነፃነት የደረሱ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

ከለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ የተሰጠ መግለጫ


london church


ቀን፤ 21/03/2013
ለርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና ወዳጆች፤ እንዲሁም በUK እና በመላው ዓለም ለሚገኙ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ሁሉ።
  የተቀበሉትን የክህነት ኃላፊነት ጠብቀው በንጽሕና በመቆም እግዚአብሔርንና ሰውን ከማገልገል ይልቅ ሥጋዊ ጥቅምን አስቀድመው የተነሱ ጥቂት የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ካህናት በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ በሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና በምእመኑ መካከል ጸብና ጥላቻ ቀስቅሰው ሁከት እንዲሰፍን በማድረግ ባለፈው ሳምንት ለንደን ወደ ሚገኘው የኢህአዲግ መንግሥት ኤምባሲ በመሄድ ቤተ ክርስቲያንን ያህል ነገር እንደ ግል ንብረት ለማስረከብ እንፈልጋለን በማለት  ከጠየቁ በኋላ ከዛ በማስከተል ቤተ ክርስቲያኗን የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በመባል በኢህአዲግ መንግሥት ጣልቃ ገብነት ለንደን ላይ ለተቋቋመው አካል አሳልፎ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኑን አስተዳደርና ንብረት ለማስረከብ በድርድር ላይ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል።
ይህ የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት (ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH DIOCESE OF NORTH WEST EUROPE) በሚል መጠሪያ የተቋቋመው ከ11 November 2011ጀምሮ ሲሆን በቻሪቲ ቁጥር 1144634 መሠረት በቻሪቲ ኮሚሽን ተመዝግቦ የሚገኝ ነው።
የዚህ ለሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ተብሎ የተቋቋመ ሀገር ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቢ አዕላፍ ተወልደ ገብሩ ሲሆኑ፤ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ደግሞ አቡነ እንጦስ የተባሉ አባ ጳውሎስ በህይወት ሳሉ በጎሳና በመንደር ልጅነት መርጠው ጵጵስና በመሾም ወደ ለንደን የላኳቸው ናቸው። በዚሁ ሃገረ ስብከት ውስጥ በትረስቲነት (Trustees) ሆነው የተዋቀሩት ደግሞ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2005 ዓ/ም ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያንን ጥለው በመሄድ ሌላ ቤተ ክርስቲያናትን የመሠረቱ ሰዎች ናቸው።
ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለንደን ላይ ከተመሠረተች 40 ዓመታትን ያስቆጠረች ሲሆን በዚህ ረጅም የስደት ታሪኳ ወቅት ካለፈው ከደርግ መንግሥትም ሆነ አሁን ካለው የኢህአዲግ መንግሥት ጋር ሳትወግን በልጆቿ ጥረትና ተጋድሎ ከማንኛቸውም የመንግሥትና የፓለቲካ ተጽዕኖ ራሷን ነጻ በማድረግ ሁሉም በእኩልነት የሚያመልክባት ቤተ ክርስቲያን ሆና ኖራለች።
በዚህ የፓለቲካ ወገንተኝነት በሌለው አቋሟም ቤተ ክርስቲያኗ በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም ዙሪያ ለሚከሰቱ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ሁሉ ነጻና ፍትሐዊ የሆነ መሥመርን በመከተል ከክርስትና ሃይማኖትና ከቤተ ክርስቲያን የሚጠበቅን የእውነት ተግባራት ስታከናውን ቆይታለች።
ዛሬ በሕይወት ያሉና በህይወት የማይገኙ አባላቶቿ ካህናትና ምእመናን ላለፉት 40 ዓመታት ባደረጉት ከፍተኛ ጥረትና ድካምም በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስቲያኗ በእግዚአብሔር ተራዳኢነት ለከፍተኛ የእድገት ደረጃ የበቃች ከመሆኗም በላይ ወደፊትም ከማንኛቸውም የመንግሥትና የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነጻ በመሆን የበለጠ በማደግና በመስፋት ለስደተኛው ሕዝብና በስደት ላይ ለሚፈጠረው ትውልድ የምትተላለፍ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፤ ሃብትና ቅርስ ሆና የምትኖር ነች።
ይህንን የመሰለውን የቤተ ክርስቲያኗን ያለፈ ታሪክና የወደፊት ራዕይ በማፍረስ በአሁኑ ወቅት አስተዳደሯንም ሆነ ሃብትና ንብረቷን ዛሬን ኖሮ ነገ በሚያልፍ የኢህአዲግ መንግሥት የእጅ አዙር ቁጥጥርና ተጽዕኖ ሥር ለማዋል የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪና ተከታዮቻቸው በመፈጸም ላይ ያሉት  የክህደት ሥራ ቤተ ክርስቲያኗን ለዚህ ያበቋት አባላቷም ሆኑ ደጋፊዎቿና መላው በስደት ዓላም የሚገኝ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚታገሱትና የሚቀበሉት አይሆንም።
በዚህ መሠረት ይህችን በሕዝብ ጥረትና ድካም ደርጅታ በእግዚአብሔር ተራዳኢነት ለከፍተኛ የእድገት ደረጃ የበቃች ቤተ ክርስቲያንን ያለ ሕዝብ ፍቃድ፤ እውቅናና ይሁንታ በስውር በመደራደር ለሌላ አካል አሳልፎ በመሸጥ መሾሚያና መሸለሚያ ለማድረግ መሞከር አጠቃላይ ስደተኛውን ኢትዮጵያዊ ከማዋረድ አልፎ በቁመናው እንደ መግደል ስለሚቆጠር የቤተ ክርስቲያኗ አባላት፤ የማርያም ወዳጆችና በአጠቃላይ በስደት ዓለም የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የተሰነዘረበትን ጥቃት በመረዳት የተንኮሉን ገመድ በመበጣጠስ ሴራውን አክሽፎ ከእግዚአብሔር በታች የቤተ ክርስቲያኗ ባለቤት፤ አዛዥና ወሳኝ ሕዝብ ብቻ መሆኑን በተግባር የማረጋገጥ ሃይማኖታዊና ኢትዮጵያዊ ግዴታ አለበት።
በዚህ መሠረት የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላት፤ ወዳጆችና በUKና በመላው ዓለም የምትገኙ ስደተኛ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ሕግን ተከትሎ በመሄድ ቤተ ክርስቲያኗን ለማዳን የሚደረገው ጥረት ገንዘብ፤ ጊዜና አቅምን የሚጠይቅ መሆኑን በመረዳት አስተባባሪ ኮሚቴው በሚያወጣው መርሃ ግብርና ጥሪ መሠረት አቅማችሁ የፈቀደውን ሁሉ እንድታደርጉ በቅድስት ማርያም ስም ጥሪአችንን እናስተላልፋለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
http://www.goolgule.com/london-debretsion-church-press-release/

የመለስ ዜናዊ ራዕይና መተካካት ያልተንጸባረቀበት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ስብሰባ ተጠናቀቀ


News, Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy.

የመለስን ራዕይ ከግቡ ሳናደርስ እንቅልፍ አይወስደንም ብለዉ ሲዝቱ የከረሙት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች “መተካካት” የሚለዉን ዋናዉን የመለስ ፖሊሲ ወደ ጎን ትተዉ ሰሞኑን በተከታታይ ባካሄዷቸው ስብሰባዎች በአብዛኛው ነባር አመራራቸዉን መርጠዉ ድህረ መለስ ጉዟቸዉን መጀመራቸዉን ዘጋቢዎቻችን ከአዲስ አበባ በላኩልን ዜና ገለጹ፡፡ በዚህ ባሳለፍዉ ሳምንት ዉስጥ አዋሳ፤ መቀሌ፤ አዳማና ባህርዳር ላይ በተካሄዱት የየፓርቲዉ ጉባኤዎች ላይ መለስ ዜናዊ መተካካት ብሎ የጀመረዉ ነባር የፓርቲ ሹማምንትን በአዲስ የመተካት ፖሊሰ እምብዛም በተግባር ባይዉልም አራቱም ድርጅቶች በተወሰነ ደረጃም ቢሆን አንዳንድ ነባር አባላቶቻቸዉን ከፓርቲዉ የስራ አስፈጻሚ ከሚቴ አስወግደዋቸዋል፤  በዚህም መሠረት ደአህዴን ተሾመ ቶጋን፤ ህወሀት ስዩም መስፍንን፤ብርሀኔ ገ/ክርስቶስንና አርከበ ዕቁባይን፤ኦህዴድ  አባዱላ ገመዳን፣ ግርማ ብሩንና ኩማ ደመቅሳን ብአዴን ደግሞ ብርሃን ኃይሉን ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት አሰናብተዋቸዋል።
ሟቹ መለስ ዜናዊ በቀየሰዉ ዕቅድ መሰረት መተካካት እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ቀጥሎ ከ2007ቱ ምርጫ በሁዋላ ነባር የአመራር አባላት ሙሉ በሙሉ ይለቃሉ ተብሎ የተገመተ ቢሆንም በሰሞኑ የፓርቲዎች ስብሰባ እንደታየዉ ግን ነባር ታጋዮች ስልጣናቸዉን እንደያዙ እንዲቀጥሉ ተደርጓል። በ2003 ዓ.ም በተደረገዉ የመተካካት ሹምሽር የኃላፊነት ቦታዉን አጥቶ የነበዉ የብአዴኑ አዲሱ ለገሰ ተመልሶ ወደ ስልጣን የመጣ ሲሆን በቅርቡ በወጣት መሪዎች ይተካሉ ተብሎ ሲጠበቅ የነበረዉ በረከት ስምኦን፤ ህላዊ ዮሴፍና፣አባይ ወልዱ ጭራሽ ስልጣናቸውን እያጠናከሩ መምጣታቸዉ ታዉቋል።
በ2003 ዓም በተደረገዉ መተካካት የመንግስትና የፓርቲ ኃላፊነታቸውን የለቀቁት ስዩም መስፍንና ሌሎች ዘጠኝ የህወሃት አባላት ከጤና ጋር በተያያዘ በራሳቸው ፈቃድ  ድርጅቱን ለመልቀቅ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የተሰናበቱ ሲሆን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ግን የእነዚህን ሰዎች መሰናበት ከመተካካት ጋር አያይዞ ዘግቧል። በአጠቃላይ ብዙ ዉጣዉረድና ድራማ የታየበት የዘንድሮዉ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ስብሰባ ሲጀመር የመለስ ዜናዉን ራዕይ ከግቡ እናደርሳለን በሚል መሪ ቃል የተጀመረ ሲሆን ሲፈጸም ግን በመርገጥ “መተካካት” የሚለዉን የድርጅቱን መስራች አላማና ራዕይ በሌላ ነገር በመተካት ተፈጽሟል።
ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በአንድ ጊዜ መልቀቂያ ማቅረባቸው አጋጣሚ ሳይሆን ከመለስ ህልፈት በሓላ በህወሃት ውስጥ ከተፈጠረው ልዩነት ጋር በተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ምንጫችን ቢጠቅስም ይህን በተመለከተ ለማረጋገጥ ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም፡፡ ብዙዎች እንደሚገምቱት ከአርከበ እቁባይ ጋር ጤነኛ ግንኙነት ያልነበራት  አዜብ መስፍን በዚህ ጉባኤ በድል አድራጊነት ወጥታለች።
ከፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን እስከ 17 ቀን 2005 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ የሚካሄደው የኢህአዴግ ጉባዔ ኃይለማርያም ደሳለኝን በሊቀመንበርነት፣ ደመቀ መኮንን በምክትል ሊቀመንበርነት በድጋሚ ይመርጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
የወያኔ ኢህአዴግ ድርጅቶች ያደረጉትን ሹም ሽር በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አንድ የቀድሞ የሀወሀት ነባር ታጋይ ፡ ምርጫውን “ውሀ ቢወቅጡት ነው” ብለውታል። “ከእነዚህ ሰዎች ምንም የሚጠበቅ ነገር የለም፣ ምን አዲስ ነገር እንደማይፈጥሩም ይታወቃል። የአፈና ስርአቱ እንደሚቀጥል ጥሩ ማሳያ ነው” ብለዋል ታጋዩ።
http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/6695

በቆብ ላይ ሚዶ ትምህርትና ተማሪ ቤት


(ክፍል አንድ)
ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም
ጥር 2005
በአለፉት አርባ ዓመታት ውስጥ አንድ ልብ ያላልነው መሠረታዊ ለውጥ አለ፤ እንዲያውም የመከራችን ሁሉ ምንጭ ነው ለማለት ይቻላል፤ የመሪዎቻችን አለመማር ብቻ ሳይሆን ትምህርትን መናቅ ወይምProfessor Mesfin Woldemariam is one of Ethiopia's well-known intellectuals ጭራሹኑ መጥላት ዋና ባሕርያቸው ሆነ፤ እስከደርግ ዘመን የነበሩት የአገር መሪዎች ቢያንስ የአንደኛ ደረጃውን (ዳዊት መድገም) የአገሩን ባህላዊ ትምህርት ያከናወኑ ነበሩ፤ ከዚያ በኋላ ለጨዋ ቤተሰብ ልጆች ትምህርት ማለት በቤተ መንግሥት በመዋል የሚገኝ ልምድ ነበር፤ ተፈሪ መኮንን በአሥራ ሦስት ዓመቱ ደጃዝማች የሆነውና ሥልጣን ላይ የወጣው በመወለድ ያገኘውን ዕድል በልምድ እንዲያዳብረው ነበር፤ ተክለ ሐዋርያት ከአሥር ዓመታት በላይ ሩስያ ተምሮ ሲመለስ ተፈሪ ያገኘውን አላገኘም።
በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ትውልድ ለሥልጣን መነሻ አይሆንም ነበር ባይባልም፣ ለእድገት ትምህርት አስፈላጊ መሆኑ በመታመኑ የዓየር ኃይል እጩ መኮንኖችም ሆኑ መኮንኖቹ ከደብረ ዘይት እየተመላለሱ ይማሩ ነበር፤ በማታው ትምህርት ብዙ የፖሊስና የጦር ሠራዊት መኮንኖች (ኮሎኔል ሚካኤል አንዶም ጭምር) ይማሩ ነበር፤ ማታ ከተማሩት የፖሊስ መኮንኖች ውስጥ ሁለቱ አምባሳደሮችም ሚኒስትሮችም ሆነው ነበር፤ ከሐረር አካደሚ የወጣ መኮንንም አምባሳደር ሆኖ ነበር፤ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ የደሀ ልጆች ወደሥልጣን ወንበሩ አልተጠጉም የሚሉ ካሉ የማያውቁ ናቸው፤ ትምህርታቸውን በታማኝነት ከፍነው ቀብረው ሚኒስትርና ሌላም ሹመት ያገኙ የደሀ ልጆች ብዙዎች ናቸው።
ከዚያ ወዲህ ከጨዋ በመወለድ ሥልጣንን ከማግኘት በባለጌ ጡንቻ ሥልጣን ወደማግኘት ተዘዋውረናል፤ ትውልድን ወደእኩልነት የሚገፋ አስተሳሰብ ስንቀበል ብልግናንንና ጡንቻን ወይም ሕገ አራዊትን፣ ተሳዳቢነትንና ዘራፊነትን፣ድንቁርናንና ሚዛነ-ቢስነትን የእኩልነትና የነጻነት አካል አድርገን የተቀበልን ይመስላል፤ በስድነትና በነጻነት መሀከል ያለውን ገደል ባለጌ አያየውም፤ የጨዋ ልጅ ዳዊት ከደገመ በኋላ እንደበቅሎ እየተገራ ያድጋል፤ ከጃፓን እስከእንግልጣር ተመሳሳይ ሁኔታ የነበረ ይመስላል፤ ነገር ግን ወደአውሮፓውያን ሥልጣኔ ስንንደረደር በጃፓናውያንና በእኛ መሀከል የታየው ልዩነት እነሱ ጨዋነታቸውን እንደያዙ እኛ ደግሞ ጨዋነታችንን ትተን መነሣታችን ነው።
አብዮት ወይም ወያኔ ማለት ትምህርትም ሆነ ጨዋነት ለሥልጣን አስፈላጊ እንዳልሆኑ በአደባባይ ማሳየት ሆነ፤ (አብዮትን ከማየቴ በፊት አብዮተኛ ነበርሁ ለማለት የምችል ይመስለኛል፤ አብዮትን ካየሁ በኋላ ግን ወዲያው ጠላሁት፤) አብዮተኛ ማለት አእምሮ የሌለው፣ ኅሊና የሌለው፣ እግዜአብሔር የሌለው፣ ሚዛን የሌለው ከጡንቻ በቀር ሌላ ኃይል የማያውቅ ማለት ሆነ፤ በጡንቻ የማይሠራ ነገር ከሌለ ትምህርት ለምን ያስልጋል? ከሁሉም ይበልጥ የሚያስደንቀውና የሚያስደነግጠው ትምህርትን በሥልጣን የመለወጡ ሙከራ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መጀመሩ ነው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ላዩን በግልቢያ የተደረጉ ጥናቶች ብዙ ቢሆኑም ጠለቅ ያለና የውስጡን መነሻ እየመዘዘ የሚያወጣ አንድም የለም።
ደርግ ሥልጣን እንደተሸከመ በየመሥሪያ ቤቱ አንዳንድ መኮንኖችን ‹‹የለውጥ ሐዋርያ›› በሚል ስያሜ ፈላጭ-ቆራጭ አድርጎ አስቀመጠ፤ ትእዛዙ በወታደራዊ ፍጥነት እንደውሀ ከላይ ወደታች እንዲፈስ ተፈልጎ ነበር፤ ነገር ግን ሥራ ሁሉ ወደመቆም ስለደረሰ ደርግ ቶሎ ብሎ ተለወጠና የለውጥ ሐዋርያት የሚባሉትን አነሣቸው፤ ከዚያ በኋላ ደርግ በሁለት ተቃራኒ ሁኔታዎች ተወጥሮ ተያዘ፤ በአንድ በኩል ከባሕር ኃይልና ከዓየር ኃይል፣ ከሐረር የጦር ትምህርት ቤትና ከአገር ውጭም የተማሩ መኮንኖች ነበሩ፤ በሌላ በኩል ከሆለታ ማሠልጠኛ የወጡ ነበሩ፤ በነዚህ በሁለቱ በተለያየ የትምህርት መሠረት ላይ በቆሙ መኮንኖች መሀከል አጉል ፉክክርና መናናቅ ነበረ፤ በተለይም ጄኔራል አማን በተማሩት መከበቡ የተማሩትን ዓይን እንዲገቡ አደረጋቸው፤ አብዛኛዎቹ የከፍተኛ ትምህርት ምሩቆች የሆኑ መኮንኖች በየሰበቡ የተጠረጉት በዚህ ምክንያት ይመስለኛል፤ በዚህም ምክንያት ደርግ ገለባ ያንሳፈፈበት ድርጅት ሆኖ ነበር ለማለት ቢቻልም ከደርግ ውጭ የተመለመሉት ሎሌዎች (ባለሥልጣኖች) የተማሩና በማናቸውም መመዘኛ የማያሳፍሩ ነበሩ።
የደርግ አባሎችም አለመማር ያስከተለባቸውን ጉድለት ለመሙላት በየሶሺያሊስት አገሩ የይድረስ-ይድረስ ለብ ለብ ትምህርት-ቢጤ በጉርሻ እየተሰጣቸው ተመለሱ፤ (የዛሬ ዘመን ትውልድ ያለጉርሻ ያደገ ነው፤ አሽከር ወይም ልጅ ገበታ ከመቅረቡ በፊት እጅ ያስታጥባል፤ ቆሞ፣ ኩራዝ ይዞ ካበላ በኋላ ጉርሻ ይቀበላል፤ ከዚያም እጅ አስታጥቦ ጉርሻውን ይበላል፤) በአቋራጭ ዲግሪም አገኘን ብለውም ተኩራርተው ነበር፤ በሶሺያሊስት አገሮች ሁሉ እየተሽከረከሩ ትምህርት የተባለውን ቢያርከፈክፉባቸውም ውሀ በስንጥቅ መሬት ውስጥ ሰተት ብሎ እንደሚገባ በእነሱ አንጎል ውስጥ አልገባም፤ ሆኖም በሶሺያሊስት መንግሥቶች ዓለም-አቀፋዊ ፍቅርና ብርቱ ሎሌዎችን የማፍራት ፍላጎት ለስድስት ወራት ያህል በድሎት አቆይተው የፈለጉትን ብራና አስታቅፈው ይልኳቸው ነበር፤ ብዙዎቹ ምንም ቢሆን ኢትዮጵያዊ ይሉኝታ እየያዛቸው ‹‹ዶክተር›› የሚለውን የትምህርት ማዕርግ አልደፈሩትም ነበር፤ ከመሀከላቸው አንዱ ግን እንደተመለሰ በያለበት እየዞረ ‹‹ዶክተር›› መሆኑን ሰዎች ሁሉ እንዳይረሱት እያደረገ አስታወቀ፤ ራሱን ለፌዝ አጋለጠ፤ መሳቂያ ሆነ፤ በመጨረሻም አውነቱና አጉል ፍላጎቱ እየተጋጩ በመቸገሩ ከፎቅ ላይ ተከስክሶ ሁለቱንም ራሱን (ማለት የእውነቱንም የውሸቱንም) አጠፋ፤ ያሳዝናል።
በቆብ ላይ ሚዶ ጥቅም አይሰጥም፤ በቆብ ላይ ሚዶ ለጌጥ አይሆንም፤ ትምህርትን መሣሪያ አድርገው ሊጠቀሙበት የማይችሉ ሰዎች፣ ከዚያም አልፈው ሥልጣንን በትምህርት ማስጌጥ የማይችሉ ሰዎች ሥልጣንን ያዋርዳሉ፤ በኋላ ሥልጣንም ያዋርዳቸዋል።
(ክፍል ሁለት)
የዛሬዎቹ ባለሥልጣኖች በደርግ ጊዜ አልነበሩም፤ የደርግን ስሕተት በማየት አልተማሩም፤ ትምህርታን አቋርጠው ወደጫካ የገቡት ከትምህርት የሚበልጥባቸው ምኞት አጋጥሟቸው ነው፤ የትምህርት ገዜያቸውን በጫካ ባለሥልጣን በመሆን፣ እነሱው ሕግ አውጪና ዳኛ፣ እነሱው የጫካ አስፈጻሚ ሆነው ቀዩ፤ ደርግ በጠራራ ጸሐይ የሚሠራውን እነሱ በጫካ ጭለማ ሲሠሩ ቆዩ፤ በሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላም በጣም ቆይተው ትምህርት አስፈላጊ መሆኑን በትንሹ ተገነዘቡ፤ በጣም የተማሩ ሰዎች ጋር ሲገናኙ ማፈር አስጨነቃቸው፤ ስለዚህም ቀላሉ ነገር የተማሩ ሰዎችን አለማቅረብ፣ ትምህርታቸውን በጠባያቸው ካላጠቡ የተማሩ ሰዎች ጋር በቀር አለመገናኘት፣ እንዲያውም የትምህርትን ዋጋና ጥራት በማዋረድ አዲስ የሚመረቁት ሁሉ ለባለሥልጣኖች አንገታቸውን የሚደፉ ዓይነት እንዲሆኑ ማድረግ ዓላማ ሆነ።
የተማሩና የሠለጠኑ የጦር መኮንኖችም ተሸናፊዎች በመሆናቸው ትምህርታቸው ዋጋ እንደሌለው ማረጋጋጫ እያደረጉ የወያኔ መሪዎች በአደባባይ ተናገሩ፤ ትንሽዋ ቢምቢ ሰውን መግደል እንደምትችል ያልተገነዘቡት ከጫካ የመጡ ሰዎች በመግደል ማሸነፍን የትምህርትን ዋጋ-ቢስነት ማረጋጋጫ አደረጉት፤ የተማሩ ሰላማዊም የጦር መኮንኖችም ዋጋ-ቢስነታቸው ኑሮአቸውን በማናጋቱ በችግር ወደሌላ ሥራ ተሰማሩ፤ ወይም አገር ጥለው ተሰደዱ፤ በሰላማዊውም ሆነ በፖሊስና በጦር ሠራዊቱ የተማረ ሰው እጥረት መፈጠሩ ለወያኔ መግቢያና መደላደያ ምቹ ሁኔታን ፈጠረ።
በየትኛውም የሥልጣን ወንበር ላይ ለመቀመጥ ማናቸውም ዓይነት የትምህርት መመዘኛ ተሽሮ ሚዛኑ ስለተሰበረ ማንንም ከሜዳ እያነሡ በተፈለገው ወንበር ላይ ማስቀመጥ እየተለመደ ሄደ፤ በየሚኒስቴሩ ከመከላከያ ጀምሮ እስከአገር አስተዳደርና የውጭ ጉዳይ ወንበሮች ላይ የተደለደሉት ሁሉ ችሎታም ሆነ ብቃት ሳይኖራቸው ነበር፤ አንዳንዶች ብልጥ የሆኑት ከዱሮው መንግሥት ባለሥልጣኖች ውስጥ አንገታቸውን ደፍተው ሊሠሩ የሚችሉትን በጓዳቸው አስቀምጠው እንዲሠሩላቸው ያደርጉ ነበር፤ ቀንደኛ የኢሠፓ አባሎች ሳይቀሩ በጓዳ በር ተቀጥረው ነበር፤ በመሠረቱ የተማረ ሰው ለአሽከርነት አይመችም፤ ሆኖም የአሽከርነት ባሕርይ ያለው ሰው ቢማርም ትምህርቱ የባሕርዩን ጉድፍ አያጥበውም፤ አንዳንዶቻችን እንደምናውቀው ለአጼ ኃይለ ሥላሴም፣ ለኮሎኔል መንግሥቱም፣ ለመለስም በተከታታይ ታማኝ እየሆኑ ያገለገሉ ሰዎች አሉ፤ የማይታመኑ መሆናቸውን ያስመሰከሩ ሰዎች የሚታመኑበት አገር ከኢትዮጵያ ሌላ መኖሩን አላውቅም፤ ከኢጣልያ ወረራ ጀምሮ ይህ የእንጀራ ሎሌነት እየተለመደ ብሔራዊ ባሕርይ ወደመሆን እየተጠጋ ነው።
በትምህርትና በተግባር መሀከል ድልድይ የማይገኝለት ገደል ተፈጠረ፤ ትምህርት በሎሌነት! ሎሌ ለመሆን መማር! መማር ሎሌ ለመሆን! ሎሌነት ለአንድ ሰው፣ ሎሌነት ለአንድ ቡድን፣ ሎሌነት ለአንድ እምነት፣ ሎሌነት ለሆድ! አስቡት እንዲህ ያለ ሰው ምን ይማራል? ማን ያስተምረዋል? እንዴትስ ይማራል? ተምሮስ ምን ይሠራል? የተወረሰውን አንጎል ማጣጠብ ይቻል ይሆናል፤ አእምሮን ለሚያንጽ ትምህርት ግን ነጻነት ያለው አስተማሪ፣ ነጻነት ያለው ተማሪ፣ ነጻነት ያለበት መድረክ ያስፈልጋሉ፡፡
የሆነላቸው ባለሥልጣኖች ወደውጭ እየሄዱ ልዩ የአቋራጭ ሥልጠና እየተሳተፉ፣ አለዚያ አስተማሪዎች ለጥቂት ጊዜ እዚሁ መጥተው የአቋራጩን ሥልጠና በአጭር ጊዜ ውስጥ እየሰጡ፤ ‹‹ተማርን›› ብለው ራሳቸውንና ተከታዮቻቸውን አሳመኑ፤ ለምን የውጭ አገር ሰዎች አስፈለጉ? እነሱን ለማስተማር የሚችሉ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች አልነበሩም ወይ? እነዚህንና ሌሎች ተመሳሳይ ጥያቄዎች አእምሮአቸው ማንሣት ባይችልም ወዳጅ ዘመዶች ሳይነግሯቸው የቀሩ አይመስልም፤ ግን እንዲህ ያለውን ምክር መቀበል አላዋቂነታቸውን ማጋለጥ ስለሚሆን ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም!
የትምህርት ጊዜያቸውን ሥልጣንን በማሳደድ ለውጠው ሳይማሩ የቀሩት ከፍተኛ የአገር ገንዘብ ወጪ እያደረጉ በስማቸው ላይ የሚጨምሩት ምልክት የትምህርትን እውነተኛ ፍቺ እንዳልተገነዘቡ የሚያሳይ ነው፤ የትምህርት ማዕርጎች ከቢ.ኤ. ጀምሮ እስከፒኤች.ዲ. የትምህርት ቤት በራፉን ሳይረግጡ በግዢ ሊገኙ ይችላሉ፤ በግዢ የሚገኘው የምስክር ወረቀት እንጂ ትምህርት አይደለም፤ ለመሆኑ ኢትዮጵያን ያህል አገር እያስተዳደሩ የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመከታተል ይቻላል ወይ? ከተቻለ ወይ አገር መግዛቱ ጨዋታ ነው፤ ወይ ትምህርት የተባለው ጨዋታ ነው፤ ወይም ሁለቱም ጨዋታ ነው፤ ያለትምህርት አገር መግዛት ጨዋታ ነው፤ ያለሥርዓት ትምህርት ጨዋታ ነው፤ ለአዋቂ ሰው በጥንት ነገሥታት ዘመንም ቢሆን ያው ነበረ የሚል ክርክር ማንሣቱ ራስን ያጋልጣልና የሚበጅ አይመስለኝም፤ በቆብ ላይ ሚዶ ጌጥ አይሆንም፤ ጥቅምም የለው፤ ከቆቡ ስር ያለው መላጣ ቢሆንስ!
በትዕቢት የተወጠሩት በአገር ላይ ባለሙሉ ሥልጣን የሆኑት ሰዎች የትምህርትን መሠረታዊ ባሕርይ ስተውታል፤ በመጀመሪያ መደበኛ ትምህርት በተወሰነ የእድሜ ክልል ውስጥ ወደተማሪ ቤት ለብዙ ዓመታት እየተመላለሱ የሚያገኙት እውቀት እንጂ በሥልጣን ወንበር ላይ ተቀምጠው እያዘዙ እንደዕቃ የሚያስመጡት አይደለም፤ መማር ደረጃ በደረጃ አስተማሪዎች የሚሰጡትን ትምህርት ተከታትሎ ፈተናዎችን እያለፉ የሚጓዙበት የእውቀት ጎዳና ነው፤ ትምህርት የአስተማሪና የተማሪ ግንኙነት ነው፤ አስተማሪና ተማሪ ማለት አዋቂና አላዋቂ ማለት ነው፤ በየኔታ(የኔ ጌታ)ና በልጅ መሀከል ነው፤ አስተማሪው የተማሪውን አእምሮ በሕገ ኀልዮት፣ ጠባዩን በሥነ ሥርዓት እየገራ፣ እየተቆጣ፣ እየኮተኮተ የሚያሳድግ ነው።
ትምህርት በተማሪዎች መሀከል ያለ ግንኙነት ነው፤ ተማሪዎችን የሚገራው አስተማሪው ብቻ አይደለም፤ ተማሪዎቹም እርስበርሳቸው አንዱ ከሌላው የሚማረውና የሚገራበት መንገድ ብዙ ነው፤ እርስበርሳቸው እየተቀላለዱ፣ እየተሰዳደቡ፣ እየተራረሙ፣ እየተፎካከሩና እየተገማመቱ የሚያድጉበት ሥርዓት ነው፤ ስለዚህም ተማሪዎች ትምህርት የሚያገኙት ከአስተማሪዎች ብቻ አይደለም፤ ይህ ሁሉ ሁኔታ በሌለበት በሥልጣን ወንበር ላይ ተኮፍሶ በሎሌነት በግል የተቀጠረውን አስተማሪ ወደታች እያዩ መማር የሚቻለው እንዴት ነው? መማር ማለት ወደላይ እያዩ ነው፤ ወደታች እያዩ መማር አይቻልም፤ አንድ ሰው ስለህክምና ምንም ሳይማር አውቃለሁ ብሎ ሥራ ከጀመረና አጉል መድኃኒት እየሰጠ የባሰ ሲያሳምምና አካልን እየቀደደ መልሶ መስፋት ሲያቅተው፣ በኋላ ሕመምተኞቹን አጋድሞ ህክምና ልማር ብሎ አስተማሪ ቢፈልግ ምን ይባላል?
ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ከኢትዮጵያ ተርፈው ብዙ ሌሎች አገሮችን አዳርሰዋል፤ የወያኔ ሹሞች ግን በከፍተኛ ወጪ ከአሜሪካና ከእንግልጣር የውጭ አገር ሰዎችን ሲያስመጡ የነበረው አንደኛ በኢትዮጵያዊ ተበልጠው ላለመታየት፣ሁለተኛ የአለማወቃቸውን መጠን እንዳይናገር ሹልክ ብሎ ገብቶ ሹልክ ብሎ ሳይታወቅ ቶሎ ወዳገሩ የሚመለስ የውጭ ሰው በማስፈለጉ፣ ሦስተኛ የገንዘብ ችግር ስለሌለ ነው።
ባለሥልጣን ሆኖ አላዋቂ መሆን ያሳፍራል፤ አዋቂ መስሎ አላዋቂ ሆኖ መገኘት የባሰ ያሳፍራል፤ ሳይማሩ በጉልበት ባለሥልጣን መሆን ሰውዬውን ራሱን የሚያሳፍርበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፤ ያፈረ ባለሥልጣን በጎ ነገርን አያስብም፤ በየሳምንቱ አንዳንድ ለጆሮ የሚቀፉና አገርንና ሕዝብን የሚጎዱ ነገሮችን እንሰማለን፤ አይታረሙም፤ የሚናገሩት ክፉ ነገር ነገ ክፉ ውጤትን ሊያስከትል እንደሚችል አያውቁም፤ ሥልጣን አፋቸው እንዳመጣ እንዲናገሩ ያስችላቸዋል፤ አለመማራቸው ከዚያች ቅጽበት አልፈው እንዳያዩ ይጋርዳቸዋል።
እድገት የሚመጣው ትምህርት በነጻነት ሲመራና፣ ሥልጣን በሕዝብ ቁጥጥር ሲያዝ ነው፤ ሥልጣን በነጻነት፣ ትምህርት በቁጥጥር የቁልቁለት መንገድ ነው።
www.ecadforum.com/Amharic/archives/6688

Saturday, March 23, 2013

ESAT Daliy News Amsterdam March 23 2013 Ethiopia


“የመለስ አስተምህሮት” ጉባኤ ታዳሚዎች

EPRDF CONGRESS


ኦህዴድ ዘግይቶ ምርጫውን ይፋ ያደረገበት ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኋላ ባህር ዳር ለሚካሄደው ዘጠነኛው የኢህአዴግ ጉባኤ የተሰየሙትን የየድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ስም ዝርዝር ኢህአዴግ ይፋ አድርጓል። ጉባኤው “በመለስ አስተምህሮዎች ጠንካራ ድርጅትና የልማት ሃይሎች ንቅናቄ ለህዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል ከቅዳሜ ጀምሮ በባህር ዳር ከተማ የሚካሄድ ሲሆን ጉባኤው አራት ቀናት እንደሚፈጅ ይፋ ተደርጓል። በጉባኤው ያለፉት ሁለት ዓመታት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸምና ቀጣይ እቅዶች ላይ ይወያያል፣ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። ምርጫን አስመልክቶ በከፍተኛ ደረጃ ለውጥ ይኖራል ተብሎ እንደማይጠበቅ ከወዲሁ ለማወቅ ተችሏል።
ፋና ያወጣው የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፡፡
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/ህወሓትማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው የተመረጡ
1. ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል
2. አቶ አባይ ወልዱ
3. ወ/ሮ አዜብ መስፍን
4. አቶ አባይ ፅሃየ
5. ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
6. ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር
7. አቶ በየነ መክሩ
8. አቶ ኪሮስ ቢተው
9. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ
10. አቶ ሚኬኤለ አብርሃ
11. ወ/ሮ ሮማን ገብረስላሴ
12. ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ
13. አቶ አለም ገብረዋህድ
14. አቶ ጎበዛይ ወልደአረጋይ
15. ወ/ሮ አረጋሽ በየነ
16. ዶ/ር አብርሃም ተከስተ
17. አቶ ጌታቸው አስፋ
18. አቶ ቴድሮስ ሀጎስ
19. አቶ ሀጎስ ጎደፋይ
20 አቶ ዳንኤል አሰፋ
21. አቶ ኢሳያስ ወልደጊወርጊስ
22. አቶ አባዲ ዘሙ
23. አቶ ገብረመስቀል ታረቀ
24. አቶ ተክለወይኒ አሰፋ
25. አቶ ነጋ በርሀ
26. ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማርያም
27. ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ
28. አቶ ሓዲሽ ዘነበ
29. አቶ ተስፋአለም ይህደጎ
30. አቶ ተወልደ ገብረፃዲቅ
31. አቶ ይትባረክ አምሃ
32. አቶ እያሱ ተስፋይ
33. አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም
34. አቶ ፀጋይ በርሃ
35. ወ/ሮ ያለም ፀጋይ
36. ዶ/ር ክንደያ ገብርሂወት
37. አቶ ጥላሁን ታረቀኝ
38. አቶ ተወልደ በርሀ
39. አቶ ብርሃነ ፅጋብ
40. አቶ ሃይለ አስፋሃ
41. ወ/ሮ ኪይሪያ ኢብርሃም
42. አቶ ጎይቶአም ይብርሃ
43. አቶ ሀፍቱ ሀዱሽ
44. አቶ ተወልደብርሃን ተስፋአለም
45. ዶ/ር ገብርሂወት ገብረእግዚአብሄር
የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴንማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ሆነው የተመረጡ ስም ዝርዝር
 1.አቶ አዲሱ ለገሰ
2.አቶ በረከት ስምኦን
3.አቶ አያሌው ጎበዜ
4.አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
5.አቶ ደመቀ መኮንን
6.አቶ አለምነው መኮንን
7.አቶ ካሳ ተክለብርሃን
8.አቶ ህላዊ ዮሴፍ
9.አቶ ተፈራ ደርበው
10.አቶ ታደሰ ካሳ
11.አቶ ብናልፍ አንዷለም
12.አቶ መላኩ ፈንታ
13.አቶ ከበደ ጫኔ
14.ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰ
15.ዶክተር አምባቸው መኮንን
16.አቶ ፈንታ ደጀን
17.አቶ ጌታቸው አምባየ
18.ዶክተር ምስራቅ መኮንን
19.ዶክተር ይናገር ደሴ
20.አቶ ለገሰ ቱሉ
21.ወይዘሮ ዝማም አሰፋ
22.ወይዘሮ ብስራት ጋሻው ጠና
23.ወይዘሮ ሽታየ ምናለ
24.ወይዘሮ ወለላ መብራቴ
25.አቶ ፀጋ አራጌ
26.ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል
27.አቶ ዮሴፍ ረታ
28.ዶክተር አምላኩ አስረስ
29.አቶ መለሰ ጥላሁን
30.አቶ መኮንን የለውምወሰን
31. አቶ ገለታ ስዩም
32. ወይዘሮ ፍሬህይወት አያሌው
33. ዶክተር ፋንታሁን መንግስቴ
34. አቶ እሸቴ አስፋው
35. ወይዘሮ ገነት ገብረእግዚአብሄር
36. አቶ ፍስሃ ወልደሰንበት
37. አቶ ግዛት አብዩ
38. አቶ ምግባሩ ከበደ
39. አቶ ጌታቸው ጀምበር
40. አቶ መሃመድ አብዱ
41. አቶ ባዘዘው ጫኔ
42. አቶ እዘዝ ዋሴ
43. አቶ አየነው በላይ
44. አቶ ብርሃን ሃይሉ
45. ወይዘሮ ምስራቅ ማሞ
46. ወይዘሮ አበራሽ ታደሰ
47. ወይዘሮ ወርቅሰው ማሞ
48. አቶ አህመድ አብተው
49. አቶ ደሳለኝ አምባው
50. አቶ አለባቸው የሱፍ
51. አቶ ተስፋየ ጌታቸው
52. ወይዘሮ ነጻነት አበራ
53. ወይዘሮ አበባ የሱፍ
54. አቶ ንጉሱ ጥላሁን
55. አቶ ይልማ ወርቁ
56. አቶ ዘለቀ ንጉሱ
57. አቶ ያለው አባተ
58. አቶ አባተ ስጦታው
59. አቶ ደሳለኝ ወዳጀ
60. አቶ ጌታቸው ሃይለማርያም
61. አቶ ከበደ ይማም
62. ወይዘሮ ውባለም እሰከዚያ
63. አቶ ደስታ ተስፋው
64. አቶ ስዩም መኮንን
65 አቶ ጌታቸው መንግስቴ
የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት
1/ አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ
2/ አቶ ሙክታር ከድር
3/ ሀብታሙ ሀይለሚካኤል
4/ አቶ በዙ ዋቅቤካ
5/ ወ/ሮ አስቴር ማሞ
6/ አቶ አብዱልቃድር ሁሴን
7/ አቶ ሲሳይ ሁሪሳ
8/ አቶ ኑሬ ቀመር
9/ አቶ ሰለሞን ቁጩ
10/ አቶ ተፈሪ ጢያሮ
11/ አቶ ጌታቸው ባልቻ
12/ አቶ ኩማ ደመቅሳ
13/ አቶ ለቺሳ አዩ
14/ አቶ ጆስፔ ሲማ
15/ አቶ አበራ አየለ
16/ አቶ አባዱላ ገመዳ
17/ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ
18/ አቶ አልዬ ዑመር
19 / አቶ ተስፋዬ ቱሉ
20/ አቶ ዑመር ሁሴን
21/ አቶ ሻፊ ዑመር
22/ አቶ አብይ አህመድ
23/ አቶ ፈይሳ አሰፋ
24/ አቶ ሙስጠፋ ከድር
25/ አቶ ነጋ ሞሮዳ
26/ አቶ ሞቱማ መቃሳ
27/ አቶ ሰለሞን አበበ
28/ አምባሳደር ግርማ ብሩ
29/ አቶ ኢብራሂም ሃጂ
30/ አቶ ዳባ ደበሌ
31/ አቶ ረጋሳ ከፍአለ
32/ አቶ ሱፊያን አህመድ
33/ አቶ ድሪባ ኩማ
34./ ወ/ሮ ደሚቱ ሃምቢሳ
35/ አቶ ዘላለም ጀማነህ
36/ አቶ ደዋኖ ከድር
37/ አቶ ዘውዴ ቀፀላ
38/ አቶ አብዱልአዚዝ መሀመድ
39/ አቶ ሰማን አባጎጃም
40/ አቶ ሞሾ ኦላና
41/ አቶ ዓለማየሁ ተገኑ
42/ ወ/ሮ ራብያ ኢሳ
43/ ወ/ሮ ፎዚያ አማን
44/ ወ/ሮ ሮዛ ዑመር
45/ ወ/ሮ ሎሚ በዶ
46/ አቶ ጌቱ ወየሳ
47/ አቶ እሸቱ ደሴ
48/ አቶ ፈቃዱ ተሰማ
49/ አቶ ገዳ ሮቤ
50/ አቶ ታምራት ጥበቡ
51/ አቶ ሞገስ ኤዴኤ
52/ አቶ ፈይሰል አልዬ
53/ አቶ ደምሴ ሽቶ
54/ አቶ ለማ  መገርሳ
55/ ወ/ሮ ሰዓዳ ከድር
56/ አቶ በከር ሻሌ
57/ አቶ አህመድ ቱሳ
58/ አቶ አበራ ሀይሉ
59/ አቶ አህመድ ሙሀመድ
60/ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው
61/ ዶ/ር ካባ ኦርጌሳ
62/ ዶ/ር ምትኩ ቴሶ
63/ አቶ ሻሎ ዳባ
64/ አቶ አብረሃም አዱላ
65/ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ
66/ አቶ ሽፈራው ጃርሶ
67/ አቶ አሊ ሲራጅ
68/ አምባሳደር ጊፍቲ አባሲያ
69/ አቶ ጫላ ሆርዶፋ
70/ አምባሳደር ደግፌ ቡላ
71/ አቶ ኤቢሳ ዲንቃ
72/ አቶ ኢተፋ ቶላ
73/ አቶ ጌታቸው በዳኔ
74/ አቶ ቶሎሳ ገደፋ
75/ ፕሮፌሰር ፈቃዱ በየነ
76/ አቶ ከፍያለው አያና
77/ ዶክተር ግርማ አመንቴ
78/ አቶ መሀመድ ጅሎ
79/ ወይዘሮ ብሌን አስራት
80/ ዶክተር መሀመድ ሀሰን
81/ አቶ ስለሺ ጌታሁን
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴንየማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት
1. ሃይለማርያም ደሳለኝ
2. አቶ ሙደር ሰማ
3. አቶ አለማየሁ አሰፋ
4. አቶ ሽፈራው ሽጉጤ
5. አቶ ሃይለብርሃን ዜና
6. አቶ ሬድዋን ሁሴን
7. አቶ መኩሪያ ሃይሌ
8. ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል
9. አቶ ሳኒ ረዲ
10. አቶ ታገሰ ጫፎ
11. አቶ ተስፋየ በልጅጌ
12. አቶ መለሰ አለሙ
13. አቶ ሲራጅ ፈጌሳ
14. ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ
15. አቶ አብርሃም ማርሻሎ
16. ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም
17. አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ
18. አቶ ምትኩ በድሩ
19. አቶ ካይዳኪ ገዛኸኝ
20. አቶ ደበበ አበራ
21. አቶ ደሴ ዳልኬ
22. አቶ ክፍሌ ገብረማርያም
23. አቶ አስፋው ዲንጋሞ
24. አቶ ተክለወልድ አጥናፉ
25. አቶ ኑረዲን ሃሰን
26. አቶ ማቲዎስ አኒዮ
27. አቶ ጥላሁን ከበደ
28. ወይዘሮ ብዙነሽ መሰረት
29. አቶ ኢዮብ ዋኬ
30. ወይዘሮ አልማዝ በየሮ
31. አቶ ሁሴን ኑረዲን
32. አቶ ያዕቆብ ያላ
33. ዶክተር መብራቱ ገብረማርያም
34. አቶ ይገለጡ አብዛ
35. አቶ አባስ መሃመድ
36. አቶ ሞሎካ ውብነህ
37. አቶ ዮናስ ዮሴፍ
38. አቶ ዴላሞ ኦቶሮ
39. ወይዘሮ አበባየሁ ታደሰ
40. አቶ ታገሰ ኤሮሞ
41. አቶ ተመስገን ጥላሁን
42. አምባሳደር ተሾመ ቶጋ
43. አቶ ቃሬ ጫዊቻ
44. ወይዘሮ አስቴር ዳዊት
45. ወይዘሮ መሰረት መስቀሌ
46. አቶ ሞገስ ባልቻ
47. አቶ መሃመድ አህመድ
48. አቶ ተስፋየ ይገዙ
49. ዶክተር ዘሪሁን ከበደ
50.አቶ ገሌቦ ጎልቶሞ
51. አቶ አማኑኤል አብርሃም
52. አቶ ሰማን ሽፋ
53. አቶ ሰለሞን ተስፋየ
54. አቶ ወዶ አዶ
55. አቶ ደረጀ ዳኬጉቾ
56. አቶ አሰፋ አብዮ
57. ወይዘሮ ህይዎት ሃይሉ
58. አቶ ወንድሙ ገዛኸኝ
59. አቶ ዘሪሁን ዘውዴ
60. አቶ አድማሱ አንጎ
61.ወይዘሮ ከፈለች ደንቦባ
62. አምባሳደር ለኢላ አለም
63. አቶ ገብረመስቀል ጫላ
64. አቶ ዳመነ ዳሮታ
65. ዶክተር ካሱ ኢላላ

http://www.goolgule.com/list-of-eprdf-top-cadres/