FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, April 30, 2013

የሠራተኛ ማህበሩ ሊቀመንበርና አመራሮቹ ለደህንነታቸው በመስጋት ተሰደዱ



  • digg
  • 0
     
    Share
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አርሲ ዞን በመንገድ ሥራ ላይ በተሠማራው የቻይና ድርጅት ማለትም የCGCOC/ ሲጂሲኦሲ/ዴራ ማኛ መቻራ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት የሠራተኞች መሰረታዊ ማህበር ሊቀመንበር አቶ ኩራባቸው ፍቅሩ ከሌሎች አመራሮች ጋር በመሆን ለደህንነታቸው በመስጋት ከሀገር መሰደዳቸውን የፍኖተ ነፃነት የዜና ምንጮች ገለጹ፡፡
የመረጃ ምንጮቻችን እደገለፁት የሠራተኛው ማህበር አመራሮች የሠራተኛውን መብትና ጥቅም ለማስከበር ባከናወኑት እንቅስቃሴ እንዲሁም ቻይናውያን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈፅሙትን በደል በማጋላጣቸው በተደጋጋሚ የተሞከረባቸውን ግድያ መቋቋም ባለመቻላቸው ከአገር ተሰደዋል፡፡
ለሰራተኛ ማህበሩ አመራሮች ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን እንደሚያስረዱት የሲጂሲኦሲ የቻይና መንገድ ሥራ ድርጅት ኃላፊዎች በሠራተኞች ላይ ከፍተኛ ግፍ ይፈፅማሉ ፡፡
“እኛ የምንተዳደረው በኢትዮጵያ ህግ ሳይሆን በቻይና ህግ ነው” በማለት ሠራተኛው በማህበር እንዲደራጅ አይፈቅዱም፡፡ 23 ጊዜ ማህበሩን ለማደራጀት ተሞክሮ በቻይናዊያኑ እንቢተኝነት ከሽፏል፡፡ በአቶ ኩራባቸው ጠንካራ ትግል በ24ኛው ሙከራ ተሳክቶ ማህበሩ ህጋዊ እውቅና አግኝቷል፡፡ ማህበሩ ህጋዊ እውቅና ካገኘ በኋላ ቻይናዊያን በኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ላይ እየፈጸሙ ያለውን ግፍ  በፍኖተ ነፃነት ጋዜጣና በተለያዩ ሚዲያዎች አጋልጧል፡፡
የሰራተኛ ማህበር አመራሩ በቻይናውያን የተፈፀመ ግድያ፣ የአካል ጉዳተኛ ሆኖ ለአልጋ ቁራኛ ስለሆኑ ሰራተኞች፣ የሰራተኞች ተገዶ መደፈር፣ ከሥራ መባረር ድብደባና ስድብ፣ ህገወጥ እስር እንዲሁም የመብት ጥሰት ደሞዝና ጥቅማጥቅምን መከልከል አጋልጧል፡፡
አቤቱታውን ከወረዳ እስከ ፌዴራል ብሎም ጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤትና ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አድርሰዋል፡፡ ለኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበር ኮንፌዴሬሽንም በቻይናውያኑ ስላደረሱት የመብት ጥሰት በቂ መረጃ አድርሰዋል፡፡ ሆኖም አንድም የተገኘ መፍትሔ የለም፡፡
እንዲያውም የመንግስት ባለሥልጣናት ለራሳቸውም መፍራት ጀምረዋል፡፡ ምንጮቹ አክለውም “በቅኝ ግዛት ህግ አንተዳደርም በማለት በመታገላቸው እነሱን ለማስገደል ተሞክሯል፡፡” ሲሉ በሰራተኛ ማህበሩ አመራሮች ላይ ስለደረሰው አደጋ ተናግረዋል፡፡
የመረጃ ምንጮቹ በመቀጠልም “የሠራተኛ ማህበራቱ በተለይም በማህበሩ ሊቀመንበር ላይ ከአራት ጊዜ በላይ የመግደል ሙከራ ተደርጎባቸዋል፡፡ በሠራተኛውና በህዝብ ትብብር ግድያው ከሽፏል፡፡” ካሉ በኋላ “አቶ ኩራባቸው እየተሠነዘረባቸው ያለውን ጥቃት መቋቋም ባለመቻላውና ህጋዊ የጥበቃ ከለላም በማጣታቸው አቶ እሸቱ አደም፣ ቄስ ብርሃኔ መኩሪያ፣ አቶ ጉልላት ከተማና እና አቶ ደምሴ ግርማ ከሚባሉ የማህበሩ አመራር ጋር ከአገር ተሰደዋል፡፡”ብለዋል፡፡
በተለይ አቶኩራባቸው በአገር ውስጥ እያሉ እየደረሰባቸው ያለውን  ጥቃትና ክትትል በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የገለጹ ሲሆን ቤተሰቦቻቸው ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት አቶ ኩራባቸው ከየካቲት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ከቤት እንደወጡ አልተመለሱም፡፡ ለተወሰነ ጊዜ ለህይወታቸው በመስጋታቸው ተሸሽገው ተቀምጠው ነበር እንደሚያውቁም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

አንድነት ፓርቲ በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ፔቲሽን ሊያስፈርም ነው



  • digg
  • 135
     
    Share
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በመላ ኢትዮጵያ የሚካሄደውን የዜጎች ማፈናቀል እንዲቆም፣ ተዘዋውሮ የመኖር ዋስትና እንዲረጋገጥ፣ የመስራትና ሀብት የማፍራት መብት እንዲከበር እንዲሁም በሀገሪቱ ያለውን ለከት ያጣ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰት በመቃወም የኢትዮጵያ ህዝብ የሚተባበርበትን  ዘመቻ ጀመረ፡፡
UDJይህንን አስመልክቶ የህዝብ ግንኙነት ክፍል እንደገለፀው ይህንን ሀገራዊ ዘመቻ በበላይነት የሚመራው የፓርቲው የፖለቲካ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሲሆን ዕቅድ በመንደፍ ተግባራዊ ለማድረግ የተግባር ኮሚቴ አቋቁሟል፡፡
በዕቅዱም መሰረት ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሀገራዊ ዋስትና እንዲኖራቸውና መብታቸውን ማስጠበቅ የሚችሉባቸውን ዕቅዶች አውጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት በቅድሚያ ሀገራዊ ይዘት ያለውን ማፈናቀል ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም፤ የተፈናቀሉትም ወደነበሩበት ስፍራ እንዲመለሱና ካሳ የሚገባቸውም ተገቢ ካሳ እንዲፈፀምላቸው፤ ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ ለማድረግ ፔቲሽን በማስፈረም ወደሚመለከተው አካል ማስገባት ቀዳሚው ነው፡፡ በተጨማሪም በሀገራቀፍ ደረጃ ምሁራን የተሳተፉበት የፓናል ውይይት በማካሄድ ከሙህራኑ የመፍትሄ አቅጣጫ የሚጠበቅ ሲሆን በሀገራቸው ጉዳይ ተሳታፊ ማድረግ ሌላው ዓላማ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር ህዝቡ መብቱን ለማስከበር እንዲችል ህዝባዊ ውይይቶችና ሰላማዊ ሰልፎች የሚደረጉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ከህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

"የተዘነጉት እስረኞች" እና የተዘነጋው የቤተሰቦቻቸው ስቃይ


Zone9
ላለፉት አራት ዓመታት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቅዳሜ እና እሁድ የሄደ ሰው ወጣቷን ናርዶስን ሳያገኝ አይመለስም፡፡ ናርዶስ ገና የ20 ዓመት ወጣትእና በኪያሜድ የመጀመሪያ ዓመት የነርሲንግ ተማሪ ናት፡፡ ናርዶስ ዘሪሁን በየሳምንቱ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትመላለሰው በ‹‹አሸባሪነት›› ‹በእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ› ከተከሰሱት 36 ሰዎች መካከል ዕድሜ ልክ የተፈረደባትን እናቷን ልትጎበኝ ነው፡፡ እነዚህ እስረኞች ሚያዝያ 16/2001 አመሻሹ 12 ሰዓት አካባቢ ነበር ሁሉም በያሉበት በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡ እኛም 4ኛ ዓመታቸውን ለማሰብ ተሰባስበን ወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት በተለይ እማዋይሽ ዓለሙን ለመጠየቅ ሄደን ነበር፡፡ እንደተለመደው ናርዶስንም አገኘናት እና ብዙ ነገሮችን አጫወተችን፡፡“የተዘነጉት እስረኞች” እና የተዘነጋው የቤተሰቦቻቸው ስቃይ
ናርዶስ ትረካዋን የጀመረችው እናቷን እና ሌሎችም በተመሳሳይ መዝገብ ተከሰው የተፈረደባቸውን ሰዎች አያያዝ ነበር፡፡ ‹‹ሳስበው የተረሱ ያህል እየተሰማኝ ነው፤ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ሚዲያዎች ስለነሱ አይደለም እያነሱ ያሉት፡፡በእናቴ ክስ የታሰሩት ከ30 ሰዎች በላይ ናቸው፡፡ አንድ ሰሞን ከይቅርታ ጋር በተያያዘ ስማቸው እየተነሳ ነበር አሁን ግን ሁሉነገር የተረሳ ይመስለኛል›› በማለት የእስሩ ሕመም ለታሳሪዎቹ እና ለቤተሰቦቻቸው ግን የሚረሳ ዓይነት አለመሆኑን ነገረችን፡፡
‹‹ሚያዝያ 16፣ አርብ ቀን ነበር ሁሉም የተያዙት›› በማለት ሲታሰሩ የነበረውን ጠቅላላ ሁኔታ በማስታወስ ትጀምራለች፡፡ ‹‹ለአንድ ሰው የመጡ የማይመስሉ ብዙ ሲቪል የለበሱ እና የፌዴራል ፖሊስ ልብስ የለበሱ ፖሊሶች መሳሪያቸውን አቀባብለው ነበር ወደቤት የገቡት፡፡ ስልካችሁን አጥፉ ወደማንም እንዳትደውሉ አሉን፡፡ የብርበራ ማዘዣ ይዘው ነበር፤ ‹ቤት ልንፈትሽ ነው የመጣነው እማዋይሽ ዓለሙ በቁጥጥር ስር ውለሻል› አሏት ቤት ፍተሻው እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ቀጥሏል፡፡ ቀኑ አርብ ነበር፤ እናቴ ደግሞ እስከ 12 ሰዓት ትጾም ስለነበር ከሥራ ወደቤት እንደገባች ‹ምግብ ስጡኝ› እያለች ነበር ፖሊሶች የገቡት ስለዚህ ምግብ ሳትበላ ውላ ነው ወደ እስርቤት የወሰዷት፡፡ ከዚያ በኋላ አራት ወራት ያክል ዓይኗን አላየነውም ነበር፤ ትሙት ትኑር የምናውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ደግነቱ በሌላ ጉዳይ ታስራ በተፈታች ሴት አማካይነት መልዕክት ደረሰኝ፡፡ ‹አንቺ ደህና ከሆንሽ ሽሮ እና ጎመን ሰርተሸ አስገቢልኝ፤ እኔ ደግሞ ደኅንነቴነን የባናና ማስቲካ ወረቀት እልክልሻለሁ፡፡ ደኅና ካልሆንኩኝ ግን ያ ነገር ይቀራል› ብላ ላከችብኝ፡፡ ከዚያ እኔም ሽሮ እና ጎመን ሠርቼ በመላክ፣ እሷም የባናና ወረቀት በመላክ ደኅንነታችንን የሚገልፅ መልዕክት እንለዋወጥ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ሰዓት እኛ በሌለንበት ጉዳያቸው ፍርድ ቤት ይታይ ነበር፡፡›› በማለት ጉዳያቸው በኢ ፍትሐዊ መንገድ በመንግሥት እንደተያዘ አጫውታናለች፡፡
‹‹እናቴ ስዕል መሳል ትወዳለች፡፡ እናም በየጊዜው የጀመረቻቸው ስዕሎች የተበላሹ ሲመስሏት ቅርጫት ውስጥ ትጥላቸዋለች፡፡ ይመስለኛል፤ የቤት ሠራተኛችን እጅ አለበት፡፡ ስትታሰር የቀረበባት መረጃ እነዚህ የተጣሉ ወረቀቶች ተሰብስበው ‹የድርጅቱን አርማ ስታዘጋጅ ነው› የሚል ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ፈቃድ የነበረው፣ ያውም የማይሠራ ሽጉጥም እንዲሁ በማስረጃነት የቀረበባት መሆኑ ነው፡፡›› በማለት ለእርሷ ፍርዱ ፍትሐዊ አለመሆኑን እና እናቷም ነጻ መሆኗን እንደምታምን ነግራናለች፡፡
‹‹የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ሲታሰሩ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተላለፈው ዜና ነው፤ እንኳን አገር ወዳዷ እናቴ ማንም ባገሩ ላይ የሚያደርገውን ነገር ነው አደረጉ ያለው፤›› የዜናውን ፖለቲካዊ ወገንተኝነት ወቅሳለች፡፡ እናቷ ሕዝብና አገር የማሸበር ፍላጎት ሊኖራት ለአገር ፍቅር ሕይወቷን የሰጠች መሆኗን ስታጫውተን ‹‹እናቴ ሁልጊዜ የምትነግረኝ ነገር አለ፤ ሕይወቴ ማለፍ ካለበት አገሬን በሚጠቅም ነገር መሆንአለበት ትለኝ ነበር፤›› ብላናለች፡፡ ነገር ግን መንግሥት በአንድ በኩል ‹‹ሕገ መንግሥቱን ለመናድ በመሞከር ነው ያሰርኳችሁ እያለ በሌላ በኩል ደግሞ የፖለቲካ እስረኞች የሉኝም ይላል፤›› ካለች በኋላ ‹‹ተቃዋሚ መባላቸው ካልቀረ የኢሕአዴግ መንግሥት የፖለቲካ እስረኞች እንደሆኑ ቢያምን እንኳ ጥሩ ነው፤›› ብላናለች፡፡ ‹‹እናቴ ለአገሯ ከማንም በላይ ሠርታለች ብዬ አምናለሁ፡፡ ነገር ግን አገራችን ለእናቴ ውለታዋን እየከፈለቻት ነው ብዬ አላምንም፡፡ ያለሃጢያታቸው ሃጢያት ተሰጥቷቸው ነው ያሉት›› በማለት ፍርዱ አገር ወዳድ እናቷን የሚያዋርድ እንደሆነ በሐዘን ተርካልናለች፡፡
የእናቷ በአሸባሪነት መፈረጅ ለናርዶስ ማኅበራዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ እያደረሰባት መሆኑንም አጫውታናለች፡፡ ‹‹ለትምህርቴ መስጠት የሚገባኝ ጊዜ ያህል መስጠት አልቻልኩም፤ እናቴ የታሰረችው እኔ ስምንተኛ ክፍል እያለሁ ነበር፡፡ ዩንቨርስቲ መግባት ሲኖርብኝ አሁን ግን ‹ነርሲንግ›እየተማርኩ ያለሁት በዚሁ ተፅዕኖ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ የእነርሱን የእስር ዜና ኢቲቪ ከአቀረበበት መንገድ አኳያ ትምህርት ቤት ውስጥ ራሱ እኔን መቅረብ የሚፈሩ ሰዎች አሉ፤› በማለት የእናቷ እስር በእርሷ ማኅበራዊ ሕይወቷ ላይ ያጠላበትን ጥላ አጫውታናለች፡፡
‹‹እስጢፋኖስ አካባቢ የሚገኘው እና በእናቴ ስም ተይዞ የነበረው የቀበሌ ቤታችን በልማት ስም ሲፈርስ እንኳን ለጎረቤቶቻችን በምትኩ ሲሰጣቸው ለእኛ ግን አልተሰጠንም፡፡ ሌላው ቀርቶ መታወቂያ እንኳን ለኛ ለመስጠት ፈቃደኞች አይደሉም›› ቤታቸውን ካፈረሱባቸው በኋላ አክስቷ ጋር እየኖረች እንደሆነ ስትነግረን በየመሐሉ እየገታችው ታወራልን የነበረው እምባዋ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሲወርድ ማድረግ የቻልነው ነገር ቢኖር በዝምታ ማጀብ ነበር፡፡
‹‹ያለአባት ያሳደገችኝን የእናቴን ፍቅሯን አልጠገብኩትም›› የምትለን ናርዶስ ‹‹በዚህ ዕድሜዬ ለኔ የሚገባኝ ቦታ ቃሊቲ አልነበረም፡፡›› በማለት ብዙ ነገር መሥራት በነበረባት ጊዜ ቃሊቲ በመመላለስ እንዲባክን መንግሥት እንደፈረደባት እንደሚሰማት ነግራናለች፡፡ ‹‹አራት ዓመቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ነው ያሳለፍኩት፤ ከ16 ዓመታት በኋላ ከእስር የተፈታው አባቴ የራሱን ሁሉ ነገር ትቶ ሕይወቱን ለኔ መስዋዕት ባያደርግ ኖሮ አልወጣውም ነበር›› በማለት እንደ ዕድል እናቷ ከመታሰሯ ሁለት ወርያክል ቀድሞ በተፈታው አባቷ ድጋፍ ከብዙ ቀውስ እንደተረፈች እየነገረችን ከናቷ ጋር የነበራትን ፍቅር ‹‹እናቴ ሁለ ነገሬ ነች!››ብላለች፡፡
‹‹እናቴን ሊጎዳ የሚያስብ ሰው እኔን አንድ ነገር ሊያደርግ ይችላል በሚል ተሳቅቄነው የምኖረው›› በማለት በዙሪያዋ ያለውን ወዳጅ እና ጠላት እንኳን ማመን እየቸገራት እሷ ራሷም ቢሆን ከማኅበረሰብ የመነጠል እና የመስጋት ስነልቦናዊ ችግር ውስጥ እንደሆነች አስረድታናለች፡፡
‹‹የርዕዮት ዓለሙ እህት እስከዳር ዓለሙ ‹የቤታችን ሰላም እና ፍቅር ከርዕዮት ዓለሙ ጋር ታስሯል› ያለችው በጣም ትክክል ነው›› በማለት በታሰሩት ሰዎች ቁጥር እኩል የሚሆኑ ቤተሰቦች በከፍተኛ ፈተናውስጥ እያለፉ መሆኑን አበክራ ነግራናለች፡፡
የናርዶስ ታሪክ የብቻዋ ታሪክ አይደለም፡፡ የሌሎች የብዙ ቤተሰቦቻቸው የታሰሩባቸው ቤተሰቦች ታሪክ ነው፡፡ ናርዶስም ‹‹እንደኔ ሁሉ ችግር ላይ ያሉ፣ አባቶቻቸው የታሰሩባቸው ብዙ ልጆች አሉ›› ብላናለች፡፡ በዚሁ መዝገብ ተከሰው የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው አቶ መላኩ ተፈራ ቤተሰቦችም ከሰኞ እስከ እሁድ ቃሊቲ ደጃፍ ላይ ከማይጠፉት ሰዎች ውስጥ ይመደባሉ፡፡ በሥራ ጉዳይ ከአገር ውጪ ያለችው ልጃቸው ፅዮንም አባቷን ለመጎብኘት ሲባል ቶሎ፣ ቶሎ እንድትመላለስ ተገድዳለች፡፡ እነጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ እነ አሳምነው ፅጌ እና ሌሎችም ደግሞ በእስረኞች መሐል ‹‹ተነስቷል በሚል ፀብ›› ሰበብ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ወደዝዋይ እንዲዛወሩ ተደርገዋል፡፡ ይህ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ሌላ ተጨማሪ ጫና አሳድሮባቸዋል ብላናለች፡፡ እዚህ የቀሩት ታሳሪዎችም አጋሮቻቸውን በማጣት ለብቸኝነት ስሜት ተዳርገዋል፡፡
ከነርሱ መዝገብ ውጪ ያሉ ሌሎችም እስረኞች እና ቤተሰቦቻቸው በተመሳሳይ ፈተና ውስጥ መሆናቸውን እስረኞችን ለመጎብኘት በሄድንባቸው ጊዜያት ተረድተናል፡፡መንግሥት ለፖለቲካ ግብአቱ የይቅርታ ደብዳቤ ካስፈረማቸው በኋላ እንኳን ለመፍታት ፍላጎት አያሳይም፡፡ ይልቁንም፤ ከቦታ ቦታ እያዘዋወረ ስቃያቸውን ያበዛል፡፡ ለዚህ እንደምሳሌ ባለፈው አርብ (ሚያዝያ 11/2005) ወደዝዋይ እንዲዘዋወር የተደረገው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ተጠቃሽ ነው፡፡ በእርሱ የጋዜጠኝነት ደሞዝ ላይ ጥገኛ የነበሩት ባለቤቱ እና ልጁ (ፍትሕ ውብሸት) በእናትዬው መፍጨርጨር ሕይወታቸውን እንዲመሩ ከመገደዳቸውም በላይ አሁን የቤቱን አባውራ ለመጠየቅ ዝዋይ ድረስ እንዲመላለሱ ተፈርዶባቸዋል፡፡ ለዚህም ነው መንግሥት የፖለቲካ አይደሉም የሚላቸውን የፖለቲካ እስረኞችን ከነቤተሰቦቻቸው ከሚቀጣበት መንገድ ይታረም ዘንድ ሊጠየቅ ይገባዋል በማለት የምንመክረው፡፡

Monday, April 29, 2013

ኢህአዴግ በኖርዌይ ገንዘብ ማሰባሰብ ተሳነው

oslo


በስደት አገራቸውን ለቀው የወጡ ሰዎች ያለመሰለል መብት አላቸው። በህግም የተደነገገ ነው። ከለላ የሰጣቸውም አገር ይህንን የመከላከልና የመቃወም ግዳጅም አለበት። ከለላ ያገኙ ስደተኞችም ሆኑ ከለላ እንዲሰጣቸው ያመለከቱ ወገኖች ስለመሰለላቸው ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ ከቻሉ ህጉን ጠቅሰው የመከራከር መብት አለቸው። ለመብታቸው ሲከራከሩ በመደራጀት ቢሆን ይበልጥ ውጤታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ አውሮፓ በስደት ያሉ ቀድሞ የውጪ ጉዳይ የዲያስፖራ ኢንጌጅመንት ዳይሬክቶሬት ዲፓርትመንት ኤክስፐርት ይናገራሉ።
እኚሁ ሰው እንደሚሉት ከ1997 ዓ.ም ምርጫ በኋላ በአቶ መለስ ቀጥተኛ ትዕዛዝ የተቋቋመው ይህ ዲፓርትመንት ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለወቅቱ የውጪጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍን ሪፖርት ያቀርብ ነበር። በጁላይ 2003 ስድስት አባላትን በመያዝ የተቋቋመው ዲፓርትመንት “ብዙሃን አድፋጭ” ዲያስፖራ ወይም “silent majority” የሚባሉትን ለመማረክና በስደት ውጪ አገር የሚኖሩትን የተቃዋሚ ድርጅት ዋና ደጋፊዎችንና አመራሮችን የሚከታተል ቻፕተሮች አሉት።
የአገዛዙ ደጋፊ ለሚባሉት ዲያስፖራዎች የቀረጥ ነጻ መብት በመስጠት፣ መሬት በማደል፣ በማህበራት በማደራጀት ቢቻል መታወቂያ በመስጠት፣ “ለአገር ግንባታ ደጋፊ ማድረግ” በሚል ሽፋን በያሉበት አገር ከኤምባሲ ጋር ግንኙነት እንዲፈጥሩ በማድረግ የተዘረጋው መዋቅር የአውሮፓውን የክትትል ስራ በግንባር ቀደምትነት እንዲመራ የመደበው የብራስልስ ኤምባሲን ነው። በቤልጂየም ኢትዮጵያ ኤምባሲ ካውንስለር በመሆን የሚያገለግሉት የቀድሞው የህወሃት ታጋይ ይህንኑ የአውሮፓ የክትትል ቻፕተር እንደሚመሩት የሚያስረዱት የቀድሞ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰራተኛ የቻፕተሩን ጠርናፊ “አቶ መለስ በታመሙበት ወቅት ብራስልስ ሆነው አስፈላጊውን ሁሉ ሲያደርጉ የነበሩ የስርዓቱ ታማኝ ሰው ናቸው” ሲሉ ይገልጹዋቸዋል።
በጥቅማ ጥቅም ዲያስፖራ ውስጥ ሆነው የክትትል ስራ በመስራት በያሉበት አገር ካለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር ግንኙነት በመፍጠር ስርዓቱን የሚያገለግሉ ስለመኖራቸው በውል የሚናገሩት እኚሁ ሰው “ስርዓቱን ሸሽተው ጥገኛነት የሚጠይቁ ኢትዮጵያውያን ስለ አገዛዙ የሚሰጡት መረጃ ስለሚያንገበግባቸው ዲያስፖራው ውስጥ ያለውን እንቅስቃሴ ለማኮላሸት ከፍተኛ በጀት ይመደባል። በዚሁ በጀት እጅግ ቀረቤታ ላላቸው ደጋፊዎቻቸው በሚኖሩበት አገር ተራ የጉልበት ሰራተኛ የሚያገኘው ክፍያ ተሰልቶ ይከፈላቸዋል” በማለት አገሩን፣ ቤተሰቡን፣ ንብረቱን፣ ቤተዘመዱን ጥሎ የሸሸውን ዜጋ እየተከታተሉ ሪፖርት ስለሚያቀርቡት ክፍሎች ይናገራሉ።
ሰፊ ማብራሪያ ያቀረቡት እማኝ የኢህአዴግ ደጋፊዎች የልማትና ድጋፍ ማሰባሰቢያ መድረኮችን በማመቻቸት ታማንነታቸውን እንደሚያሳዩ የሚገልጹት የቀድሞ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ባልደረባ “ይህ አሰራር የተኮረጀው ከቻይና ነው። የተለያዩ አገር አሰራሮችና የደህንነት መዋቅሮች የተጠኑ ቢሆንም የ  ቻይናው የተመረጠው ለስራውና ኢህአዴግ ለሚፈልገው አደረጃጀት አመቺ ሆኖ በመገኘቱ ነው” ሲሉ የመዋቅሩን ተፈጥሮ ያስረዳሉ።
ከሳምንት በፊት በኖርዌይ ስታቫንገር፣ ዛሬ ኤፕሪል 28/2013 ደግሞ በኦስሎ ስለተካሄደው የቁጣ ተቃውሞ አስተያየት የሰጡት እኚሁ ሰው “ኢህአዴግ ሊገለኝ ነው በማለት ሸሽተው ጥገኝነት የጠየቁ ወገኖች ከመንግስት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የላቸውም። ሊኖራቸውም አይችልም ማስረጃ በማሰባሰብ ጉዳዩን ወደ ህግ ማቅረብ ይቻላል” ባይ ናቸው።
“ተሰደን አገር ለቀን ወጣን። አገራችን እንዳንኖር ተደረግን። በስደት በምንኖርበት አገር ድረስ መጥተው ገንዘብ ሊጠይቁን ማሰባቸው ይገርማል። እንደዚህ ገንዘብ የተጠሙበት ምክንያት ምን ይሁን? ኢህአዴግ አገሬ እንዳልኖር አደረገኝ፣ ህይወቴ አደጋ ላይ ነው በሚል ከለላ የጠየቀ ሰው እንዴት መንግስት ደጅ ይቀርባል። ይህ እኮ ህገወጥ ነው። ወንጀል ነው። ከለላ የሰጠው አገርም ሆነ ዋናው የስደተኞች ህግ አይደግፈውም” በሚል አንድ ጥግ ይዘው የሚነጋገሩና የሚወያዩም አጋጥመውኛል።
መከላከያው አክራሪንና አልሸባብን ይደመስሳል በሚል የማይነጥፍ ገበያ አላቸው። መሬት ይሸጣሉ። ንግዱን ተቆጣጥረውታል። ኢንቨስትመንቱን በጃቸው አድርገውታል። አስመጪና ላኪነቱን የግላቸው አድርገውታል። ባዕድ ሃይል የማያደርገውን የከፋ ተግባር እንመራዋለን በሚሉት ህዝብ ላይ ይፈጽማሉ። አገሪቱን በዘርና በጎሰኝነት አስተሳሰብ መርዝ በክለው እርስ በርስ እያጫረሱ ምድሪቱን የበቀል ቡቃያ አድርገዋታል። ታዲያ እነዚህ ሰዎች በየትኛው ሞራላቸው ነው ስደት የሚለበልባቸውን ዜጎች ሰብስበው ገንዘብ የሚጠይቁት? የሁሉም ጥያቄ ነው።
በተጠቀሰው ቀን ለአባይ ግድብ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ለማካሄድ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ አጭር የስልክ መልዕክት (የኤስ ኤም ኤስ) ጥሪና በተለያዩ አደረጃጀቶች ጥሪ ተበትኖ ነበር። ኦስሎ የሚኖሩ የስርዓቱ ሰለባዎች ራሳቸውን አደራጅተውና ግብረኃይል አቋቁመው በስብሰባው ለመገኘት ዝግጅታቸውን አስቀድመው እንዳከናወኑ በስፍራው የነበሩ ለጎልጉል ዘጋቢ አመልክተዋል።
እንደተባለው ጠዋት ረፈድ ፈድ ሲል በስቶኮልም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰው ስብሰባውን ለመምራት ወዳጆቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ያዘጋጁት መድረክ ላይ ለመቀመጥ Radisson Blue Scandinavia Hotel ሲደርሱ የጠበቃቸው ሌላ ነበር። በስብሰባው ለመገኘት የሚያስችል “የዜግነት” መብት ያላቸው ወገኖች ስብሰባውን ለመካፈል ጠየቁ። “አትገቡም” ሲባሉ ተቃውሟቸውን ከቁጣ ጋር አሰሙ። ባለስልጣኑ ማሽላ እያረረ ይስቃል እንደሚባለው ፈገግታ በማሳየት በምሬት በሚወርደው የተቃውሞ ቃል መገረፋቸውን ለመደበቅ ሞከሩ። ንዴታቸውን ለመደበቅ ሲታገሉ ጭራሹኑ ስብሰባውን ማድረግ በማይችሉበት ደረጃ ተቃውሞው ስለጨመረ ለአባይ ግድብ ብር ለማሰባሰብ የተወጠነው የኦስሎው ውጥን ስታቫንገር እንደሆነው ተኮላሸ። ፖሊስ ስብሰባው ሊካሄድ እንደማይችል አረጋገጠ።
በኖርዌይ ከሚታተሙትና ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ ዜና ካሰራጩት መካከል፣ ቬጌ የሚባለው ጋዜጣ አስራ አንድ ሰዎች ህገወጥ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል በሚል መታሰራቸውን አስነበበ። በስፍራው ቁጣቸውን የገለጹ ወገኖች ሳያስፈቅዱ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል በሚል ጋዜጣው የእስሩን ምክንያት ፖሊስን ጠቅሶ አስፍሯል። በስፍራው የተገኙም ሆኑ የዚህ ሪፖርት አቅራቢ እንደታዘበው ዜጎች አስቀድመው የጠየቁት በስብሰባው ላይ እንሳተፍ የሚል የዜግነት ጥያቄ ነበር። በጥያቄያቸው መሰረት ወደ ስብሰባው ቦታ ለመግባት ሳይችሉ መከልከላቸው እንደ ዜጋ የሞራልና የማንነት ጥያቄ በመሆኑ ቁጣቸው ከስርዐቱ ተፈጥሮ ጋር ተዳምሮ የነደደ ነበር።
ከፍተኛ ቁጥር የነበረው የፖሊስ ሃይል አስራ ሁለት ተሽከርካሪዎችን አሰልፎ የቁጣውን ሰልፍ “ለመቆጣጠር” እንደቻለ፣ የሰለጠኑ ውሾችና ከሆቴሉ በቅርብ ርቀት ሄሊኮፕተርም ተዘጋጅቶ እንደነበር ቬጌ አስነብቧል። የጎልጉል ሪፖርተር ባሰባሰበው መረጃ አባይ ቢገደብ የሚጠሉ ወገኖች የሉም። ቅድሚያ ሊከናወኑ የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ግን ይስማማሉ። ቅድሚያ አፈናውና ያለ ህዝብ ውክልና በጠመንጃ ከህዝብ ጫንቃ ላይ መንሰራፋት ሊቆም ይገባዋል። የመብት ገደብም ሊቆም ግድ ነው። ይህ ሲሆን ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፣ ገንዘብ የሌለው በጉልበቱ አድርግ የተባለውን ያደርጋል። አገርም በዜጎቿ ፍላጎትና እኩል ተሳትፎ ያለ ስጋት ትለማለች።
የታሰሩት ሰዎችን በተመለከተ ይህ ሪፖርት እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ ስለመፈታታቸው የተሰማ ነገር የለም። በሳምንት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ጠንካራ ሊባል የሚችል ተቃውሞ ያጋጠመው ኢህአዴግ፣ በኖርዌይ ተመሳሳይ ፕሮግራም ለማካሄድ ባይሞክር እንደሚሻለው ገለልተኛ ነን የሚሉ ወገኖች ተናግረዋል። አቶ መለስ በህይወት በነበሩበት ወቅት በኖርዌይ የገጠማቸው ተቃውሞ የከፋ እንደነበርና የመጡበትን ጉዳይ በወጉ ሳይጨርሱ መመለሳቸውን ያስታወሱት እነዚሁ ክፍሎች “አሜሪካ በዲቪ የተጓዙ ደጋፊዎች ሊኖሩ ይችላሉ። አውሮፓ ግን በትምህርት መጥተው የቀሩ ካልሆኑ በስተቀር ኢህአዴግ በግልጽ ሊደግፉት የሚችሉትን አባላት ለመግኘት አይቻለውምና አባይን እንደጀመረው ከቻይና ተበድሮ ቢያጠናቅቀው ይመረጣል” ብለዋል። ኢህአዴግ በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች፣ በሳዑዲ አረቢያ፣ በዱባይ፣ በደቡብ አፍሪካ ተመሳሳይ ተቃውሞ እንደገጠመው በተለያዩ ሚዲያዎች መዘገቡ የሚታወስ ነው። (ፎቶ: VG)

ከእሁድ እስከ እሁድ


(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)
exim china bank


ኢትዮጵያ በቻይና ብድር እየተንበሸበሸች ነው
በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ታላላቅ ስምምነቶች ይጠበቃሉ
ከአፍሪካ ጋር መሳ ለመሳ የገባችው ቻይና በሳምንት ጊዜ ውስጥ ለኢትዮጵያ 4.5 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ለማበደር ወስናለች። ከአባይን ግድብ የሚመነጨውን ሃይል የማስተላለፍና የማከፋፈል ጣቢያ ለመገንባት ከሚፈለገው 1.2 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 85 በመቶውን ለመስጠት መዋሰኗን የመንግስት ሚዲያዎች ዘገበዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዘወትር እንደሚደረገው የቻይና የኤሌክትሪክ ፓወር ኢኪውፕመንት ቴክኖሎጂ ኩባንያ ግንባታውን በሰላሳ ቀን ውስጥ ለመጀመርና በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማስረከብ ተስማምቷል። ስለዚህ ብድሩ ከቻይና ኪስ ወጪ ተደርጎ ወደ ቻይና ኪስ ይዛወራል።
በሌላ ተመሳሳይ ወሬ ለአትዮጵያና ለጅቡቲ የባቡር መስመር ግንባታ የሚውል 3.3 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት የቻይና መንግስት መወሰኑን ሪፖርተር አስነብቧል። ስምምነቱ ከወር በኋላ ለሚደረገው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ከሚመጡ ከፍተኛ ቻይና ባለስልጣናት ጋር የቻይና ኤግዚም ባንክ ባለስልጣኖች አዲስ አበባ ተገኝተው የስምምነቱን ፊርማ እንደሚያኖሩ ጋዜጣው ገልጿል።
ከብድር ስምምነቱ በፊት በተጠናቀቀው የግንባታ ስራ ተቋራጭ ውል መሰረት ከሰበታ ተነስቶ ጅቡቲ የሚደርሰውን የባቡር መስመር ሁለት የቻይና ኩባንያዎች እንደሚያከናውኑት ሪፖርተር በስም ጠቅሶ አመልክቷል። አንደኛው ኩባንያ የአዲስ አበባን ቀላል የባቡር መስመር ዝርጋታ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል።”
የመከላለያ ጄኔራሎች በታንታለም ንግድ ዝርፊያ ተሰማርተዋል”
የመከላከያ ጀነራሎች በታንታለም ማዕድን ዝርፊያ ላይ መሰማራታቸውን ኢሳት አስታወቀ። ኢሳት ሰራተኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው የመከላከያ ሰራዊት ኩባንያ በአካባቢው የመንገድ ስራ ተቋራጭ በመሆን መንገድ እየሰራ ሲሆን፣ ለመንገድ ስራ ተብለው የተመደቡት ተሽከርካሪዎች ከመንገድ ስራ ይልቅ የታንታለም ማእድንን እየዘረፉ በሶማሊላንድ በኩል ያሻግራሉ። ማዕድኑንን  የማውጣቱን ስራ ከሚሰራው የቻይና ኩባንያ ጋር ሽርክና በመፍጠር ዝርፊያውን እንደሚያካሂዱም ኢሳት አመልከቷል።
ይህ ውድና ስትራቴጂክ ማእድን በርካሽ ዋጋ መሸጡ አገሪቱን እንደሚጎዳ የዘርፉ ባለሙያዎች ለሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ደጋግመው አቤቱታቸውን በማቅረብ፣ ጥሬ እቃውን ወደ ውጭ መላኩ እንዲቋረጥ ተደርጎ እንደነበር ያስታወሰው ኢሳት፣ በቅርቡ መንግስት ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ያጋጠመው መሆኑን ተከትሎ፣ የማእድን ማውጣቱን እና መላኩን እንደገና ለመጀመር በመወሰኑ እነዚህ የህወሀት ጄኔራሎች ከአንድ የቻይና ኩባንያ ጋር አክሲዎን በመመስረት ታንታለም በጅቡቲ በኩል መላክ መጀመራቸውን ሰራተኞቹ አስረድተዋል።tantalum
አገር ወዳድ የሆኑ ሰራተኞች “ይህ ማእድን እያለቀ ነው፣ ታንታለም ስትራቴጂክ ማእድን ነው፣ ማእድኑ አሁን ካለቀ አገሪቱ ለወደፊቱ ከፍተኛ የሆነ ገቢ ታጣለች” በማለት መናገራቸውን ኢሳት አመልክቷል። የህወሀት ጄኔራሎች ዝርፊያውን የሚፈጽሙት ከዞን ባለስልጣናት ጋር በመዛመድ መሆኑን ምንጮች እንደነገሩት ኢሳት ጠቁሟል።
ምንም እንኳ በአካባቢው ካሉ ተወካዮች ለማረጋገጥ ባይችልም፣ በህገወጥ መንገድ ከሚወጣው ማእድን ጨረር ጋር በተያያዘ በርካታ የአካባቢው ሰዎች መሞታቸውን ኢሳት ሰራተኞቹን በመጥቀስ ይፋ አደርጓል።
መንግስት እገዳው ከመጣሉ በፊት 80 በመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያን ታንታለም የሚሸጠው ቻይና ውስጥ እንደነበር ያመለከተው ኢሳት በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ወገንን ሪፖርት ለማካተት ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካ ተናግሯል።
ታንታለም ሊተካ የማይችል እጅግ ውድ የሆነ ማእድን ሲሆን፣ የሞባይል ስልኮችን፣ ኮምፒዩተሮችን እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ፣ ለተለያዩ የኬሚካልና የፋርማሲዩቲካል ውጤቶች መስሪያ፣ ለኤሮስፔስ፣ ለኢነርጂና ባልስቲክ ምርቶች በግባትነት ያገለግላል። ቀንጢቻ ቦረና የኢትዮጵያ ማእድን ልማት አክሲዮን ማህበር የተባለ መንግስታዊ ድርጅት ከአመታት በፊት በጉጂ ዞን በሻኪሶና አናሶራ ወረዳዎች 2ሺ 500 ቶን የሚጠጋ ንጹህ የታንታለም ማእድን ማግኘቱ የመገናኛ ብዙሀንን ትኩረት ስቦ እንደነበር ኢሳት በዘገባው አስታውሷል።
የሳዑዲ የመከላከያ ሚኒስትር በኢትዮጵያ አቤቱታ ተነሱ?
የሪፖርተር አስቂኝ ዜና የሳምንቱ መዝናኛ ተደርጎ ተወስዷል። ዜናው የሚጀምረው “የህዳሴውን ግድብ የተቃወሙት የሳውዲ ልዑል ከሃላፊነታቸው ተነሱ” የሚል ነው። የሳዑዲ አረቢያ  ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር በቅርቡ በግብጽ ተደርጎ በነበረ የዓረብ አገሮች የውሃ ምክር ቤት ኮንፍረንስ በመገንባት ላይ ያለውን “የህዳሴ ግድብ” መቃወማቸውን በማስረጃነት ያሳየው ሪፖርተር ከዜናው ግርጌ ሚኒስትሩ ስለተነሱበት ምክንያት የሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ ያለው ነገር እንደሌለ አመልክቷል።
Khaled_Bin_Sultanሚኒስትሩ  በአገራቸው ፖለቲካ ውስጥ አወዛጋቢ ጉዳይ ማንሳታቸውን ፣ በዚህም ምክንያት  ከሃላፊነታቸው  መነሳታቸውን  የሚገልጹ ጠንካራ አስተያየቶች ከሳዑዲ እየወጡ ነው። ጉዳዩን  የሚከታተሉ ወገኖች የሚኒስትሩ መነሳት አገራቸው ውስጥ እያራመዱ ካለው ያልተለመደ እንቅስቃሴ ጋር ከመያያዙ ውጪ አባይ ግድብን አስመልክቶ ከተናገሩት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ለጎልጉል ተናግረዋል።
የህዳሴው ግድብ በማንኛውም ምክንያት የመፍረስ አደጋ ቢገጥመው ሊያጠራቅም የሚችለው 70 ቢሊዮን ሜትሪክ ኪዩብ ውኃ ሱዳንን ሙሉ ለሙሉ ያጠፋል፡፡ ከዚህ አልፎም በግብፅ የአስዋን ግድብ ላይ ተጨማሪ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ነበር ምክትል የመከላከያ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡ በዚህ የኢትዮጵያ ግድብ በዋናነት ተጎጂ የምትሆነው ግብፅ መሆኗን፣ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ግብፅ ከዓባይ ውኃ ውጭ ሌላ አማራጭ የሌላት በመሆኑ ነው ብለው ነበር፡፡ በማከልም ኢትዮጵያ በዚህ ግድብ አማካይነት እያደረገችው ያለ እንቅስቃሴ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ይልቅ ፖለቲካዊ ትንኮሳው ያመዝናል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዓላማ ፍፁም ፖለቲካዊ ሴራ መሆኑን በመግለጽ መናገራቸውን ሪፖርተር በዜናው መጨረሻ አስታውሷል። ኢትዮጵያም ባለስልጣኑ ለተናገሩት የሳዑዲ መንግስት ማብራሪያ እንዲሰጥበት መጠየቋ አይዘነጋም።
ኬኒያና ኢትዮጵያ ለወደብ ግንባታ በጋራ ብር ሊያፈላልጉ ነው
በኬኒያ ተፈጽሞ በነበረ የጅምላ ግድያ ተከስሰው ጥፋተኛ የተባሉት አዲሱ የኬኒያ ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታና በጠ/ሚ/ር haile uhuruሃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራ ልዑክ ኬንያ ተገኝቶ በልማትና በግልጽ ባልተነገረ ጉዳይ መወያየታቸው ተሰምቷል።
የኢህአዴግ ልሳናትና የተለያዩ መገናኛዎች ሁለቱ መሪዎች ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ደቡብ ሱዳን በጋራ ለሚጠቀሙበት ግድብ ማስገንቢያ ገንዘብ በጋራ ለማፈላለግ መስማማታቸው ተመልክቷል። በሶማሊያና በቀጠናው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በሚቻልበት ሁኔታ ላይም መክረዋል።
አቶ ሃይለማርያም አወሮፓ ያደረጉትን “የቃል ማደስ” ጉዞ እንዳከናወኑ ወደ ኬኒያ ማምራታቸው ሶማሌ ውስጥ ከኬኒያ ጋር መስራት ስለሚገባቸው ጉዳይ የተቀበሉትን የቤት ስራ ለመተግበር ያስችላቸው ዘንድ እንደሆነ ግምት አለ።
አቶ ሃይለማርያም ናይሮቢ በነበራቸው የአንድ ቀን ቆይታ አብረዋቸው ከተጓዙት መካከል ወታደራዊ ባለሙያዎችም እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል።
በአዲስ አበባ አፍሪካ ፍልስጤምን ነጻ ስለመውጣት ልምድ ልታካፍል ነው
በፍልስጤም ጉዳይ በሚቀጥለው ሳምንት የሚዘጋጀው ዓለም አቀፍ ጉባዔ በአዲስ አበባ እንደሚስተናገድ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል አስታወቀ። የኢህአዴግ አንዱ የንግድ ተቋም የሆነውና ዜና ከመንግስት እየወሰደ ለመንግስት የሚሸጠው ዋልታ ጉባኤው አዲስ አበባ ስለሚካሄድበት ምክንያት አላስታወቀም።
Ethiopian President Meles Zenawi (R) and PLO chair
(Photo: Getty Images)
“ጉባዔው የፍልስጤማውያን የማይገሰሱ መብቶችና ለፍልስጤም ሉአላዊና ነጻ አገር የአፍሪካውያን አጋርነት” በሚል መሪ ቃል ሚያዝያ 21 እና 22 ቀን 2005 ዓ ም እንደሚካሄድ ዋልታ አመልክቷል። ጉባኤው አፍሪካ ከቅኝ አገዛዝ በመውጣት ሉአላዊነቷንና ነጻነቷን ለመጎናጸፍ ያደረገችውን ተጋድሎ እንደ ልምድ ተወስዶ ውይይት ይደረግበታል። ፍልስጤም ባለችበት አስተዳደር የገጠሟት ችግሮችና አስተዳደሩ በዓለም አቀፍ ሕጎች ያለበትን ኃላፊነትና ተጠያቂነትም ይገመግማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዋልታ በዘገባው አስፍሯል።
በጉባዔው ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሐፊና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ሚስተር ካርሎስ ሎፔዝ፣ የፍልስጤማውያን የማይገሰሱ መብቶች ኮሚቴ ሊቀመንበር አብዱ ሰላም ዲያሎ፣ የፍልስጤም ነጻ አውጪ ድርጅት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ጣሂር ካሊድ እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል።
ለእሥራኤልና ፍልስጤም ሰላም ሂደት ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ድርጅቶች እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰቡ እያበረከቱት ያለውን ድርሻም ጉባዔው እንደሚያጤን የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የላከው መግለጫ ጠቅሶ ዋልታ ዘግቧል። እስራኤልን በጉባኤው ላይ ስላላት ሚናና ስሜት በዘገባው ላይ የተባለ ነገር የለም።
አንደበት
. . . እነዚህ “ሕገ ወጦች” ከሰሜንም ይምጡ ከምስራቅ፣ ከምዕራብ ይፍለሱ ከመሀል አገር ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ጥርጥር የለውም፡፡ የሀገሪቱ ሕገ መንግስት ደግሞ ዜጎች በፈለጉት አካባቢ ሄደው ለመስራት፣ ሀብት ለማፍራትና ለመኖር እንደሚችሉ ደንግጓል፡፡ እናም እነዚህ “ሕገ ወጥ” የተባሉት ሰዎች ከተወለዱበት ክልል ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ ሌላ ክልል ሄደው ኑሮአቸውን መመስረታቸው ከቶም ወንጀል ሊሆንና ወደ መጣችሁበት ተመለሱ ሊባሉ አይችሉም፡፡ ደን መጨፍጨፍና ሕገ ወጥ ሰፈራ ማካሄድ ግን ወንጀል ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ፤ ዜጎች (ሰሜንም ይወለዱ ደቡብ) ሕግ ጥሰው፣ ስርዓት አፋልሰው፣ ጥርስ ሰብረው፣ ቋንጃ ቆርጠው፣ ንብረት ዘርፈው፣ ቤት አቃጥለው፣ እንስሳ ነድተው፣ ወይም ሌላ ወንጀል ሰርተው ቢገኙ በአገሪቱ ሕግ መሰረት ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲቀጡ ይደረጋል እንጂ “ወደተወለዳችሁበት ቀዬ ተመለሱ” ማለት ተገቢም ሕጋዊም አይመስለኝም … እኔ አቶ አያሌው ጎበዜን ብሆን ኖሮ ሁልጊዜ አማራ ተፈናቀለ፣ አማራ ተፈናቀለ የሚለውን መስማት ስለማልፈልግ ይህንን እርምጃ እወስድ ነበር፡፡ አማራ ክልል እንደ ሌሎቹ ክልሎች ሁሉ ለተወላጆቹ በቂ የሆነ መሬትም ሀብትም እንዳለው አምናለሁ፡፡ የክልሉን ተወላጆች ይሄ “የነፍጠኛነት” ውርዴ አለቅ ብሏቸው ካልሆነ በስተቀር ጉራ ፈርዳ ድረስ የሚያስወርድ ሁኔታ ያለ አይመስለኝም …” አቶ አብዱራህማን አህመዲን የቀድሞው የፓርላማ አባል ለሰንደቅ ጋዜጣ በዘር ላይ የተመረኮዘ መፈናቀልን አስመልክቶ ካቀረቡት ጽሁፍ የተወሰደ
ታዳጊዋን የደፈሩ አዛውንት 11 ዓመት እስር ተፈረደባቸው
አዛውንቱ የፈጸሙት ተግባር የአውሬ ነው። የልጅ ልጃቸው የምትሆን ታዳጊ አስገድደው በመድፈር ላልተፈለገ እርግዝና ዳርገዋታል።injustice1 አዲስ አድማስ የፍርድ ሂደቱን አስመልክቶ እንደሚከተለው ዘግቧል። በምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ ግራባ ፊላ ቀበሌ ገበሬ ማህበር፣ የ14 ዓመቷን ታዳጊ አስገድደው የደፈሩ የ60 ዓመት አዛውንት፣ የአስራ አንድ ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸው፡፡ የታዳጊዋ ወላጆች በእርሻ ሥራ ላይ የቀጠሯቸው እኚሁ አዛውንት፣ ወሲባዊ ጥቃቱን የፈፀሙት ቤተሰቧ‹‹ቤት ጠብቂ›› ብለው ወደ ገበያ መሄዳቸውን አረጋግጠው እንደሆነ ፖሊስ ገልጿል። ታዳጊዋ የደረሰባትን የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ወዲያው ለቤተሰቦቿ አልተናገረችም፡፡
ወራት እየተቆጠሩ ሲሄዱ ግን ሰውነትዋ እየወፋፈረ፤ ሆድዋ እየገፋ መሄዱን የተረዱ ቤተሰቦችዋ ጥርጣሬ አድሮባቸው ጠየቋት፡፡ ታዳጊዋ የደረሰባትን ተናገረች፡፡ ያኔ የአምስት ወር እርጉዝ ነበረች። ቤተሰቦችዋ ጉዳዩን ለፖሊስ አመለከቱና ክስ ተመሠረተ፡፡ ከትናንት በስቲያ በዱግዳ ወረዳ የዋለው ችሎት፤ ተከሳሹ ድርጊቱን መፈፀማቸውን በማረጋገጡ የ11 ዓመት ፅኑ እስራት እንደፈረደባቸው፤ የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኢንስፔክተር አስቻለው አለሙ ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡ ዘወትር እንደሚባለው ሁሉ ፍርዱ አነስተኛና ከበደሉ ጋር የሚጣጣም እንዳልሆነ ግን አልተዘገበም።
የሱዳን ታጣቂዎች በመተማ አርሶ አደሮችን ገደሉ
በሰሜን ጎንደር በመተማ ዞን ደለሎ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ለረዥም ዓመታት ግብር እየከፈሉ የሚኖሩበትን  ህጋዊ መሬት ለቀው እንዲወጡ በወረዳው እንደተወሰነባቸው ሪፖርተር ምንጮች ጠቅሶ ዘገበ። የሱዳን ታጣቂዎች ሶስት አርሶ አደሮችን መግደላቸውም ተገልጿል።
አርሶ አደሮቹ ለዓመታት ከኖሩበት ርስታቸው እንዲፈናቀሉ መታዘዙን የወረዳው አስተዳደርና የክልሉ የአካባቢ ጥበቃና የመሬት አስተዳደር ባለስልጣን ሃላፊ አስተባብለዋል። ይሁን እንጂ ሶስቱ አርሶ አደሮች መገደላቸውን ሳያስተባብሉ አምነዋል።
soldierየመተማ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ተስፋ መኮንን አርሶ አደሮቹ በሱዳን ታጣቂዎች ተገድለዋል መባሉ እውነት መሆኑን ቢያረጋግጡም፣ ምክንያቱ ግን ከድንበር ልኬትና ከእርሻ ጋር የተገናኘ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የመተማ አርሶ አደሮች ድንበር ተሻግረው የመስፈር ሁኔታ መኖሩንና ከሱዳኖቹም በኩል ተመሳሳይ ባህሪ እንደሚታይ የገለጹት አቶ ተስፋ፣ ከሱዳኖች በኩል አንድ ታጣቂ ተገድሎ እንደነበርና በዚያ ድርጊት ቂም ይዘው ግድያውን ሳይፈጽሙ እንዳልቀሩ ግምታቸውን ገልጸዋል፡፡ የድንበሩን ጉዳይ በፀባይ መያዛቸውን የገለጹት አስተዳዳሪው፣ ለኢንቨስትመንት የሚሆነውንና የማይሆነውን መሬት ለመለየት በጂፒኤስ ለክተው መጨረሳቸውንም አሳውቀዋል፡፡ ዝቅተኛ የመሬት መጠን ያላቸው አርሶ አደሮች በገመድ ተለክቶ እንደሚከፋፈሉም አክለዋል፡፡
አቶ ተስፋ የአርሶ አደሩን መፈናቀል በሚመለከት ለተነሳላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ ‹‹አርሶ አደሩ መሬቱን አልተነጠቀም፡፡ ቦታው ተለክቷል፡፡ መሬቱ ሲለካ አርሶ አደሩ መረጃ ስላልደረሰውና ወጥቶ ስላላየ የሚደረገውና የሚወራው አንድ ዓይነት አይደለም፡፡ አርሶ አደሩ አግባብ ባልሆነ መንገድ አግበስብሶ የያዘው መሬት አለ፡፡ የሚመለከተውን ያህል ይሰጠዋል፡፡ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እየተሠራ በመሆኑ ማንም አይፈናቀልም፡፡ ሲለካ ለምን ይለካል ብሎ የሚያኮርፍ አለ፡፡ ይኼ ደግሞ ሥርዓትና አሠራር በመሆኑ ሕጉን ጠብቆ ይሠራል፤›› ማለታቸውን ሪፖርተር አመልክቷል።
በአዲስ አበባ የትራፊክ መብራቶች ከጥቅም ውጪ ናቸው
በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ መብራቶች ቆመው ቢታዩም አገልግሎት እንደማይሰጡ አዲስ አድማስ ዘገበ። ጋዜጣው ተገልጋዮችንaddis-ababa-city-traffic በማናገርና ተዘዋውሮ በመመለክት እንደዘገበው በከተማዋ ካሉት 26 የትራፊክ ማስተናበሪያ መብራቶች ውስጥ አገልግሎት የሚሰጠው አንዱ ብቻ ነው። አዲስ አድማስ ባይገልጸውም የትራፊክ መብራቶቹ ምሶሶዎች ቀለማቸው የወየበ። የተገነጣጠሉና  የከተማውን ውበት እንዲያበላሹ ታስበው የተቀመጡ መስለዋል።
በየደረጃው ያሉ ሃላፊዎችንና የአዲስ አበባ የትራፊክ ጽ/ቤት ችግሩን እንዳመኑ ያመለከተው አዲስ አድማስ ዜናውን አስገራሚ አድርጎ ያቀረበው የማይሰሩትን የትራፊክ መብራቶች ለመጠገን የመለዋወጫ ችግር መከሰቱን በመግለጽ ነው። ጥገና ለማካሄድ ተፈልጎ የመለዋወጫ እቃ ሲጠየቅ “እንዲህ ያለ እቃ አለ እንዴ”  የሚል መልስ እንደሚሰጥ የጠቀሰው ጋዜጣው የአዲስ አበባ የትራፊክ መብራት ዘመን ያለፈበትና ሊጠገን አይችልም ብሏል። ከባቡር ግንባታው ጋር በተያያዘ አዲስ የመብራት ተከላ ለማካሄድ ጨረታ መውጣቱንም አመልክቷል።

ESAT Breaking news conflict in Awi Zone Ethiopia


Seattle Tamagne Beyene


ESAT WAZA ENA KUMENGER ETHIOPIA


Sunday, April 28, 2013

በአባይ ስም ዶላር ለመሰብሰብ በሲውዲን የወያኔ አምባሳደር ወደ ኖርዌይ ተጉዛ ለሁለተኛ ጊዜ በኦስሎ


ሰበር ዜና! ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ዛሬም በኦስሎው፣ ታሪክ ሰሩ!


ወያኔ በልማት ስም ገንዘብ ለመቃረምና ደጋፊ ለመመልመል አቅዶ ከሳምንት በፊት በስታቫንገር አንዲሁም በዛሬው እለት ደግሞ በኦስሎ ስብሰባ ለመጥራት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ሳይሳካላቸው የውርደት ካባቸውን ለብሰው መሄድ እጣፋንታቸው እንዲሆን የግድ ሆኗል፡፡ እንደሚታወቀው ባለፈው ሳምንት ማለትም እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ሚያዝያ 20፣ 2013 በነበረው ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያዊያን ከየተለያዩ ቦታዎች በመሰባሰብ የወያኔ አምባሳደር በስዊድን የሆኑትንና የዲያስፖራ ተወካዩን ከስብሰባ በማባረር ከፍለውበት የነበረውን አዳራሽ ተረክቦ ኢትዮጵያዊያን የራሳቸውን አጀንዳ እና ለተፈናቀሉት ወገኖቻችን እርዳታ የሚሆን ገቢ እንዲሰበሰብና ይህን አምባገነንና ዘረኛ ቡድን መታገል የሚቻለው በ አንድነት መሆኑን ሁሉም የሚስማሙበትና እጅ ለእጅ ተያይዘን መታገል እንዳለብን አስምረው፣ ከ አንድ ሳምንት በሗላ ለሚደረገው የወያኔ ገቢ ማሰባሰቢያ ይህንኑ ድል መደገም ያለበት መሆኑን በመስማማት ነበር የተለያዩት፡፡
ይህንንም ተከትሎ የስታቫንገሩን የወያኔ ፕሮግራም ለማክሸፍ ከፍተኛው ሚና የተጫዎተውን ግብረ-ሓይል በማጠናከር ሳምንቱን ሁሉ ውጤታማ ሥራ ለማድረግ የሙስሊም ወንድሞቻችንን፤ ኦሮሞና ሶማሌ ኢትዮጵያዊያንን በማስተባበር ሌት ከቀን  ሲሰራ ሰነንብቷል፡፡ የጀግኖች ኢትዮጵያዊያንን ከፍተኛ ዝግጅትና ቅስቀሳ ሲከታተሉ የነበሩ የወያኔ ቅጥረኞችና አገላጋዮች ስብሰባ ሊደረግ ታቅዶበት የነበረውን አዳራሽ የስብሰባው ሰዓት ሊደርስ አንድ ሰዓት ተኩል ሲቀረው የመሰብሰቢያው አዳራሽ በፀጥታው፣ በጥራቱና በደህንነቱ በታወቀው ራድሰን ብሉ ሆቴል እንደሚካሄድ አስታውቀው፣ ስብሰባውን ለመሳተፍ ግን ህጋዊ መታወቂያ እንደሚያስፈልግ ተገልፆ የሞባይል አጭር መልዕክት ተላለፈ፡፡ ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ስብሰባው ይካሄድበታል ተብሎ ከታሰበበት አዳራሽ አካባቢ ከአስር ሰዓት ጀምሮ ወደዚያ የሚያልፈውን የወያኔ ቅጥረኛ ለመቃኘት ወረውት የነበረ ቢሆንም ዘግይቶ የመጣውን አጭር የሞባይል መልዕክት ማለትም የስብሰባ ቦታ መቀየር በመረዳት፣ ወደዚያው ተመመ፡፡
ብዙዎቹ ኢትዮጵያዊያን ከመድረሳቸው በፊት በገቡት የወያኔ ተወካዮች በመበሳጨቱ ወደ ሆቴሉ ለመግባት በነበረው ግብግብ፣ ምንም ዓይነት ሰው እንዳይገባ ተከለከለ፡፡ ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያዊያንን ቁጣ ለማስቆም ከ15 መኪና በላይ የፖለስ ሃይል የተጨመረ ቢሆንም የጀግኖች ኢትዮጵያዊአንን ቁጣና እልህ መቋቋም አልቻሉም ነበር፡፡ አካባቢው የግልና ተቃውሞውም ህገወጥ እንደሆነ በማስረዳት  ከአካባቢው ገለል ለማድረግ ቢሞክሩም አልተቻለም፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ በሆቴሉ የታደሙት የወያኔ ቅጥረኞት ወጥተው ካልሄዱ አካባቢውን ለቀን አንሄድም፤ ይውጡ እንለቃለን፤ ይውጡ እንለቃለን፤ ይውጡ እንለቃለን፤ ይውጡ እንለቃለንበማለት አብዘተው ጮሁ፡፡ ይህንንም ተከትሎ ሁለት ሴቶች እህቶቻችንና ዘጠኝ ወንድሞቻችን ለሰዓታት ታስረው የተፈቱ ሲሆን፤ ፖሊስም የተቃውሞውን ሓይለኝነት በማየት የወያኔ ተወካዮችንና የስብሰባው አስተባባሪዎች በጓሮ በር ማለትም በመኪና ማቆሚያ በኩል ከህዝብ ሰውረው ከሆቴሉ ሸኝተዋቸዋል፡፡
ከዚያም ኢትዮጵያዊያን አያ ሆሆ ማታ ነው ድሌ፤ አያ ሆሆ ማታ ነው ድሌ፤ አያ ሆሆ ማታ ነው ድሌ እያሉ በመዝለል ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡ የሚከተሉትን የፎቶ ትዕይንት ይመልከቱ፡፡
DSC_0010DSC_0012DSC_0015DSC_0922DSC_0931DSC_0938Arrestationarrestation 2.

Wednesday, April 24, 2013

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ቤንሻንጉሉ መፈናቀል ተናገሩ


በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚገኙ አርሦ አደሮች ሕገወጥ በሆነ መንገድ መፈናቀላቸውን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አረጋገጡ፡፡Haile
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብዙ ሰው እንደተንገላታበት በተደጋጋሚ የተዘገበበትንና ብዙም ያነጋገረውን ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ የተናገሩት ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት የስምንት ወር አፈፅፀም ሪፖርታቸው ወቅት በሰጡት አስተያየት ለድርጊቱ ተጠያቂ በሆኑ የበታች ባለሥልጣናት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል።
በየትኛውም የሀገሪቱ ክልል የሚገኙ የአመራር አባላት የዜጐችን ሕገመንግሥታዊ የመዘዋወርና የመሥራት መብት እንዲያከብሩም አሳስበዋል።
ለተጨማሪና ዝርዝር ማብራሪያ የተያያዘውን እስክንድር ፍሬው ከአዲስ አበባ የላከውን  ዘገባ ያዳምጡ፡፡

የማረሚያ ቤቱ ድራማ በርዕዮት እምቢተኝነት ከሸፈ



ከፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ
ባሳለፍነው እሁድና ሰኞ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን ለመጠየቅ በዛ ያሉ የሞያ አጋሮቿና አድናቂዎቿ በስፍራው ተገኝተው ነበር፡፡ የጠያቂዎቹ በዛ ብሎ የመገኘት ዋነኛ ምክንያት ደግሞ ርዕዮት በቅርቡ የዩኔስኮን የ2013 አለም አቀፍ ሽልማት በማግኘቷ እንኳን ደስ አለሽ በማለት የደስታዋ ተካፋይ መሆናቸውን ለመግለጽ ነበር፡፡ የባልንጀሮቿን የደስታ ምኞት እየተቀበለች ለሁሉም ሽልማቱ የእርሷ ብቻ እንዳልሆነም ትገልጽ ነበር፡፡
ርዕዮት ጠያቂዎቿን በመቀበል እያነጋገረች በነበረችበት ሰዓት(ሰኞ ዕለት) የቪዲዩ ካሜራ በመደገን ለመቅረጽ ይሞክር የነበረ አንድ ሰው በጋዜጠኞች እይታ ስር ይወድቃል፡፡ ርዕዮት ላይ ያነጣጠረውUntitled ካሜራ የፈለገውን እንዳያገኝም በስፍራው የነበሩ ሰዎች ጋዜጠኛዋን በመክበብ ምስሏን እንዳይቀርጽ አድርገዋል፡፡ በጠያቂዎቿ እንደተከበበች ርዕዮትን መቅረጽ ያልሆነለት ስውሩ ጋዜጠኛ በመጨረሻ ርዕዮትን ነጥሎ ለማናገር ይሞክራል፡፡ በዚህ ወቅት ግን የጠያቂዎች ሰዓት በማለቁ የርዕዮት ጠያቂዎች ማረሚያ ቤቱን ለቅቀው እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡
የፍኖተ ነጻነት ምንጮች እንዳረጋገጡት ጋዜጠኛው ርዕዮትን በማግኘት ‹‹አንቺ ጋዜጠኛ አይደለሽ፣ በራስሽ የምትተማመኚ ከሆነስ ለምን ለመቀረጽ እምቢ ትያለሽ›› ይላታል፡፡ ርዕዮትም  ‹‹ከአንተ ጋር ከመነጋገሬ በፊት የማረሚያ ቤቱን ሃላፊዎች  ማነጋገር እፈልጋለሁ›› በማለቷ ሃላፊዎቹ ይመጣሉ፡፡ ርዕዮት ቀጠለች‹‹ይህ ጋዜጠኛ የሚፈልገውን ቃለ ምልልስ የመስጠት ችግር የለብኝም፣ ነገር ግን የተናገርኩትን ቆራርጦና ጨማምሮ ሊያቀርበው የሚችል በመሆኑ የነጻ ሚዲያ አባላት በቃለ ምልልሱ ወቅት እንዲገኙ ይደረግ፣ ከዚህ ውጪ ግን ለጥያቄው ምንም አይነት ትብብር እንደማላደርግ ይታወቅልኝ›› በማለት አቋሟን ግልጽ አድርጋለች፡፡
እንደሚታወቀው መንግስት በሽብርተኝነት ከስሶ በእስራት እንድትቀጣ እያደረጋት የምትገኘው ጋዜጠኛ የጤንነቷ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መገለጹን ተከትሎ በአገር ውስጥና በውጪ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና እየተደረገ ይገኛል፡፡ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄን ጨምሮ የአውሮፓ ፓርላማ አባል የሆኑት ሚስ አና ጎሜዝ፤ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንትና ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት ጋዜጠኛዋ ተገቢውን የህክምና ክትትል እንድታገኝ መጠየቃቸው አይዘነጋም፡፡
ከዚህ ቀደም ፖለቲከኛና ዳኛ የነበሩት ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በታሰሩበት ወህኒ ቤት ለህመም ተጋልጠዋል የሚሉ መረጃዎች በመውጣታቸው ጫና የተፈጠረበት መንግስት ብርቱካን በጤንነት ላይ ይገኛሉ ለማለት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አማካኝነት አንድ ዘገባ መስራቱ አይዘነጋም፡፡ርዕዮት ማረሚያ ቤቱ ያስገባው ስውሩ ጋዜጠኛ ከእውቅናዋ ውጪ  ሊሰራው የነበረውን ድራማ ቀድማ በመንቃቷ ሊሳካ አልቻለም፡፡

Ethiopia transfers editor Woubshet Taye to remote prison (CPJ)


New York, April 22, 2013–The Committee to Protect Journalists protests Ethiopian authorities’ transfer of independent newspaper editor Woubshet Taye to a remote prison several hours away from his family’s home. Woubshet has been imprisoned since June 2011 on vague terrorism charges that CPJ has determined to be unsubstantiated.
Ethiopia's Anti-Terror Task Force
Woubshet Taye
“Moving detainees to prisons far from their families is a tactic long used by governments that wish to not only further penalize the individuals but to punish their loved ones as well,” said CPJ Africa Advocacy Coordinator Mohamed Keita. “Woubshet Taye should not be in prison at all, never mind held in one so far from his family. We call on Ethiopian authorities to return him to a facility closer to his home, and to reconsider the unjust conviction that put him behind bars in the first place.”
Authorities on Friday transferred Woubshet from Kilinto Prison, outside Addis Ababa, to a detention facility in the town of Ziway, about 83 miles southeast of the capital, according to local journalists and the U.S.-based exile-run AwrambaTimes.com. The authorities did not provide a reason for the transfer. Local journalists told CPJ that Woubshet’s wife and four-year-old son would now have to travel more than four hours to reach the prison to visit the journalist.
Woubshet, former deputy editor of the now-defunct independent weekly Awramba Timesand a recipient of Human Rights Watch’s Hellman/Hammett Award, was sentenced in January 2012 to a 14-year prison sentence on charges lodged under Ethiopia’s broad anti-terrorism law. The journalist was arrested a couple of weeks after he published a column inAwramba Times that critically assessed the ruling party’s performance in its two decades of rule. The paper was known for its bold coverage of local issues.
The U.N. Special Rapporteur on torture and other forms of cruel, inhuman or degrading treatment or punishment, said last month that Ethiopia had violated Woubshet’s rights by failing to address his allegations of being tortured in custody, despite Ethiopia’s commitment to “uphold the highest standard of human rights.”
CPJ research shows that other states that have imprisoned journalists have used the tactic of moving journalists to prisons far from their homes as a means of punishing them and their families. Cuba, for example, placed journalists in prisons hundreds of miles from their families at the height of the Black Spring crackdown in 2003, according to CPJ research.

Tuesday, April 23, 2013

የመሠረታዊ ነፃነት ቀበኞች!


በሰሎሞን ተሰማ ጂ.
Email: solomontessemag@gmail.com
የነፃነት ቀበኞች (ፀሮች) የተደራጁትም ያልተደራጁትም ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶቹ ጡንቻቸውን አፈርጥመው፣ ክራንቻቸውን ስለው፣ ጥፍሮቻቸውን ወድረው ሊዘነጣጥሉ የሚችሉበት አቅምና ጉልበት አላቸው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ያ ጉልበት ስለሌላቸው፣ ቀበኛ ባሕሪያቸውን በጩኸትና በስም ማጥፋት ተግባር ላይ ተሰማርተው ያከናውኑታል፡፡ በልዩ ልዩ መልክና ቅርጽ የተደራጁት “የመሠረታዊ ነፃነት ጠሮች (ቀበኞች)” ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ገሚሶቹ በገዢነት (በፓርቲነት)፣ አንዳንዶቹ በሃይማኖታዊ ማኅበራት ሽፋን፣ ሌሎቹ ደግሞ በአነስተኛና ጥቃቅን ቡድንነት የተደራጁ አዳሚዎችና አሳዳሚዎች ናቸው፤ ቀሪዎቹ ደግሞ በአንድ-ለአምስት ሕዋስ ሥር (as a gangster) የተደራጁ “የጎበዝ አለቆች” ናቸው፡፡ በነዚህ አካላት ጭፍን አካኼድ የተነሳ፣ የዜጎች መሠረታዊ ነፃነትና መብት ይደፈጠጣል፡፡ የሥልጣናቸውና የመጉዳት አቅማቸው መጠን የተለያየ ይሁን እንጂ፣ ሁሉም የመሠረታዊ ነፃነት ቀበኞች (ፀሮች) ናቸው፡፡ ለምን እንደሆኑና እንዴትስ ከዚህ ደረጃ እንደደረሱ ለማሳየት ጥረት አደርጋለሁ፡፡Freedom: the quality or state of being free
የሥነ-መንግሥት ተመራማሪዎች፣ ልዩ ልዩ ዓይነት ነፃነት አለ-ይላሉ፡፡ ሁሉንም ለመዘርዘር አልቃጣም፡፡ ለምሳሌ ያህል፣ የሐሳብ መስጠት ነፃነት፣ አንድ ሰው አምላኩን ሃይማኖቱ በሚፈቅደው መንገድ የማምለክ ነፃነት፣ ተሰብስቦ የመወያየት ነፃነት፣ የመናገርና የመፃፍ ነፃነት፣ እና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትና ነፃነት፣ የመሳሰሉት እያሉ ይዘረዝራሉ፡፡ ሁሉም ታዲያ “ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ነው የሚከወኑት” ይላሉ፡፡ አልተተገበረም አንጂ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ-መንግሥት በአንቀጽ 27 መሠረት፤ የሃይማኖት፣ የእምነትና የአመለካከት ነፃነት የዜጎች መብት እንደሆነ ይደነግጋል፡፡ በተጨማሪም፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 30 መሠረት፣ የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታንም የማቅረብ መብትን በተመለከተ ነጩ ወረቀት ላይ ሰፍሯል፡፡ ግን አልተተገበረም፡፡ የከፋ በደል ነው፡፡ የበደልም በደል! (“የሰው ልጅ በሠለጠኑትም ሆነ ባልሰለጠኑት አገሮች መሠረታዊ ነፃነት እንጂ ፍፁም ነፃነት ሊያገኝ እንደማይችል የሚታወቅ ነው፤” ሲሉ ተመራማሪዎቹ ያክላሉ፡፡)
ስለ“መሠረታዊ ነፃነት” ምንን ከመጻፌ በፊት፣ ስለዚህ የነጻነት ዓይነት ለመፃፍ ያሳሰቡኝን ምክንያቶች ላነሣ እፈልጋለሁ፡፡ የመጀመሪያው የሩዶልፎ ግራዚያኒ ደጋፊዎች በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 30 መሠረት፤ “የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የመድረግ ነፃነትና አቤቱታንም የማቅረብ መብትን” እንዴት በካልቾ እንደመቱት በመመልከቴ ሲሆን፤ ሁለተኛው ምክንያቴ ደግሞ፣ አንዳንድ ሰዎች (በግልም በቡድንም ሆነው) እንዴት የሌሎችን መሠረታዊ ነፃነት እንደሚጣረሩ ለማሳየት ነው፡፡ ከሁሉ አስቀድሜ ግን፣ “ነፃነት ማለት ምንድነው?” የሚለውን ጥያቄ ለመመለስም እሞክራለሁ፡፡ በአቦ ሰጡኝ የመጣልኝ መልስ፣ “ነፃነት የሰው ልጅ ከአላህ ወይም ከእግዚአብሔር (አዳላህ እንዳትሉኝና ከእግዚአብሔር ወይም ከአላህ) በተፈጥሮ የተሰጠውን ክብር መጠበቂያው ሚዛን ነው፡፡” የሚል ሆነ፡፡ መሠረታዊ ነፃነት የሌለው ሰው፣ በሰው ፊት ሰው የበለጠው፣ ከሰው በታች የሆነም ነው፡፡ ነፃነት የሌለው ሰው፤ በሰው ፊት የተዋረደ፣ የተናቀ፣ ሕቁር (Inferior) ፍጥረት ነው፡፡ ነፃነት የሌው ሰው በአፀደ ሕይወት ቢኖር እንኳን፣ መኖሩ እንደሰው ሳይሆን እንደዕቃ፤ እንደ“እንትና” ሳይሆን እንደ“እንትን” የሚታይና የሚቆጠር ፍጡር ነው፡፡ “እንትን” የሚል ቅጽል የሚሰጠው፣ መሠረታዊ ነፃነት ለሌለው ሰው ነው፡፡ እንትንነት ክብራቸውን በፍርፋሪ ለሸጡና መሠረታዊ ነፃነታቸውን ለተገፈፉ የሚሠጥ ቅጽል ነው፡፡ ለሕቁር ፍጥረታት የሚሠጥ ቅጽል ነው፡፡ እንደዔሳው የብኩርና ክብራቸውን በምስር ንፍሮ ለሸጡና ለለወጡ ፍጥረታት የሚሠጥ ስያሜ ነው፡፡ እነዚህ አምላክ/ፈጣሪ በተፈጥሮ የሰጣቸውን ክብር የቸበቸቡ ፍጥረታት ደግሞ፣ ሰላማዊ ሰልፎችን የሚከለክሉ፣ የመናገርንና የመጻፍን መብት ለመገደብ የሚንጠራወዙ፤ ፖሊስ ወይም የፀጥታና ደኅንነት ኃይል ተቀጣሪዎች ሲሆኑም ሌሎችን በዱላ የሚደበድቡ፣ የሚሳደቡና በተራ ስም አጥፊነት ተግባር የሚጠመዱ ናቸው፡፡ ኅቁር ፍጥረታት ክብር ስለሌላቸው፣ ማንንም አያከብሩም፡፡
ኅቁር ፍጥረታት ሰላማዊ ሰልፍ ሲሏቸው፣ እፊታቸው ድቅን የሚልባው የአመጽ ሰልፍ ነው፡፡ ለኅቁር የፀጥታና የዘመኑ ሹሞች የሚታያቸው፣ በሕግ ፊት ሰዎች እኩል መሆናቸው ሳይሆን፣ ተደብዳቢነታቸው ነው፡፡ ኅቁራን ሹሞችና አሽቃባጮቻቸው፣ ሰብዓዊ መብትን መጣስና መሠረታዊ ነፃነትን ማሳጣት የእንጀራ ገመዳቸው እንዳይበጠስ ማረጋገጫ ነው፡፡ ኅቁራን ባለሥልጣኖች፣ የጉልበት ሥልጣን እንጂ የመንፈስ ሥልጣን የላቸውም፡፡ ለኅቁር ፍጥረታት፣ ካላግባብ በአሸባሪን ስለታሰሩ ወገኖቻችን ሲነገራቸው፣ እንደሰረሰር ሰርሳሪ የቄራ ለማጅ፣ ዋናውንና ሙዳውን ስጋ ትተው አገጭና ሌንጬጭ ይፈልጣሉ፡፡ ኅቁራን ፍጥረቶች፣ “ለአህያ ማር አይጥማትም” እንደሚባለው፣ ትልቁ ዓላማ አይጥማቸውም፡፡ ለኅቁር ፍጥረታት፣ መሳደብና ስም ማጥፋት ቋሚ ተግባራቸው ነው፡፡ ለኅቁራን፣ መቼም ቢሆን የቃላት ስንጠቃና “ከቁንጫ መላላጫ” ማውጣት የተለመደ ተግባር ነው፡፡
እንደአለመታደል ሆኖ ብዙዎቹ የኢትዮጵያ ገዢዎች የዔሳው የመንፈስ ልጆች ናቸው፡፡ የእነሱ አጫፋሪዎችና ሎሌዎቻቸው ደግሞ የባሰባቸው “ኅቁሮች” ናቸው፡፡ ኅቁርነት፣ “ከመምህሩ ደቀ-መዝሙሩ” እንደሚባለው እየከፋና እየሰፋ የሚሄድ ነቀርሳ (Cancer) ነው፡፡ በቅርቡ ፕሮፌሰር መስፍን እንዳሉት፣ ኅቁራን “በቆብ ላይ ሚዶ” የሚሽጡም ናቸው፡፡ በዚህ አላዋቂነትና ጠብደል መታወር ውስጥ እየኖሩ እንደምን የሌሎችን መሠረታዊ ነፃነት ሊያከብሩ ይችላሉ? ፈጽሞ ፈጣሪ ለሰው ልጆች ስለሠጠው መሠረታዊ ነፃነት ስለማያውቁ፣ ወይም በያውቁም ሆን ብለው ስለሚክዱት፣ የሌሎችን ነፃነትና ክብር የገፋሉ፡፡ (ኋላ እመለስበታለሁ፡፡) አባቶቻችን አገራችን በተወረረች ጊዜ ነፃነትን አጥቶ ሆድን በፓስታና በሹታ ጎስሮ፣ ገላን በአቡጀዲና በጨርቅ ሸፍኖ ከመንቀዋለል ይልቅ፣ መሠረታዊ ነፃነትን ማጣት ምን እንደሚደርስባቸው ስላወቁ፤ “ነፃነት ወይም ሞት!” ብለው በጀግንነት ተጋድለው አለፉ፡፡ በፍርሃትና በጥቅመኝነት ታውረው፣ “ከመሞት መሰንበት” ያሉትም ቢሆኑ፣ ያለመሠረታዊ ነፃነት መኖር ምን ምን እንደሚል አሳምረው ቀምሰውታል፡፡ በዱር በገደል የተጋደሉትና በእስር አዚናራ የተጋዙት ምንኛ እድለኞች ነበሩ?
በነሐሴ 1960 ዓ.ም በወጣው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ላይ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ፣ ስለመሠረታዊ ነፃነት ሲያወሱ፣ “የባሕል ነፃነት ነው” በማለት ሊገልፁት ሞክረዋል (ገጽ 5 ላይ ይመልከቱ)፡፡ “በሀገራችንና በሕዝባችን ዘንድ የባሕል ነፃነት ወይም የመሠረታዊ ነፃነት ከነትርጉሙም አይታወቅም፡፡ ነገሩ ግን የሀገርን ነፃነት የማጣትን ያህል ደም የሚያፋስስ ነው፤” (የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ ነሐሴ 9/1960)፡፡ ይሄው የመሠረታዊ ነፃነትን የማጣትና የማሳጣት ተንኮል፣ ከጥንት ጀምሮ በምዕራባውያን (በቄሳራውያን ሃይሎች) ዘንድ የተለመደ ተግባር ነው፡፡ መሠረታዊ ነፃነት ገፈፋው ዘዴ በጣም ረቂቅና ስልታዊም ነው፡፡ ከባሕልና ከመሠረታዊ ነፃነት ገፈፋ ስልቶች መካከል አንዳንዶቹን ለመጥቀስ እፈልጋለሁ፡፡ የመጀመሪያው ዘዴ፣ የገዢዎችን መብት ለአንዳንድ ተገዢዎች መስጠት ነው፡፡ ሁለተኛ፣ ተገዢዎች ማንነታቸውን ክደው፣ የሀገርና የብሔራዊ ስሜታቸውን ማስካድ ነው፡፡ ሦስተኛውና ዋናው ችግር ደግሞ፣ ተገዢው ባሕሉንና ወጉን እንዲንቅና በራሱ እንዳይተማመን የማድረግ የሥነ-ልቦና ክሽፈት ነው፡፡
ከመጀመሪያው ነጥብ ጀምሮ መተንተን ያለበት ነው፡፡ ገዢዎቹ ለአንዳንድ ተገዢዎች፤ “በብሔር፣ በዘር ወይም በሃይማኖት ተዋጽዖ ስም” የይስሙላ የገዢነት መብት ይሠጧቸዋል፡፡ የአገሩን ሰርዶም በአገሩ በሬ ማለት እንደዚህ ነው እያሉ ይደልሏቸዋል፡፡ ጣሊያን አንዴ ልጅ አያሱን ልጅ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ የአፄ ዮሐንስን ወይም የንጉሥ ተክለ ሃይማኖትን ልጆች ከተገዢነት አውጥታ ገዢ ልታደርጋቸው ያልፈነቀለችው ድንጋይ አልነበረም፡፡ ገዢዎች የሚከተሉት ስልትና ብልሃት ተመሳሳይ ነው፡፡ መሠረታዊ ነፃነቱን የተገፈፈው ሰው፣ የነፃነት ገፋፊውን ቋንቋና አነጋገር በቅጡ እንዲኮርጅ ከተደረገ በኋላ፣ የነፃነት ገፋፊውን አገር ዜጎች ያላቸውን ክብርና የይስሙላ ማዕረግ ይሰጡትና፣ የትውልድ አገሩንና የወገኖቹን መሠረታዊ ነፃነት የሚንድ “ምልምል አሽከር” ይሆናል፡፡ እንደዚያ ለመሆን የሚጠበቁበት ነገሮች ቀላል ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ቋንቋውን ማጥናት፣ ሁለተኛ፣ የወራሪውን ሀገር ዜጎች አክባሪ መሆኑን ለማሳየት መስገድ/እጅ መንሳት፣ ሦስተኛ፣ የወራሪውን አገር ከትውልድ አገሩ በላይ እንደሚያፈቅርና እንደሚወድ ማሳየት ነው፡፡ በተቻለ መጠን የሀገሩ ሕዝብና የሀገሩን ፍቅር ክዶ የብሔራዊ ስሜቱን አንጠፍጥፎ ደፍቶ ሞራለ-ቢስ መሆን በቂው ነው፡፡ ያን ጊዜ፣ ከተገዢነት ወጥቶ፣ የፈረስ ስም ተሰጥቶት፣ (ማጆር፣ ወይ ሰር፣ አልያም ደግሞ አፈ-ቄሳር፣ ማንትሴ እየተባለ) የይስሙላ ገዢ/ሹም ይሆናል፡፡ እንዴት ዓይነት አዘቅት ነው ጃል!
ሌላው ከተገዢነት ደረጃ ወጥቶ ወደ ይስሙላ ገዢነት መብት የሚደርስ ሰው፣ ከአፋፉ ጫፍ ላይ ለመድረስ ክህደትን የሙጥኝ ማለት አለበት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የይሁዳ ሰው ሆኖ ሳለ፣ የገዢዎቹን ሮማዊነት መብት ያገኘውና ከእስር ቤት የተለቀቀው በዚሁ መንገድ ነው፡፡ እንደጳውሎስ ያለውን መብት ያገኘ ሰው፣ ከእስር ቤት ወጥቶ ስለፎለለ ነፃነትን ያለገደብ ያገኘ ይመስለዋል፡፡ ለሌሎች ተገዢዎችም ትልቅ ሰው መስሎ ስለሚታያቸውና በየአደባባዩም ስለሚወጣጠርና ስለሚበጣጠስም ጭምር፣ እርሱን መስሎ ለመገኘትና እርሱ የደረሰበት የክህደት አፋፍ ላይም ለመቆም ብዙ ወገኖቹ በማመጽ ፈንታ ጀርባቸውን ለሸክም፣ ኅሊናቸውንም ለሎሌነት ይሰጡታል፡፡ ተገዢዎች መሠረታዊ ነፃነታቸውን ለማግኘት ከመታገል ይልቅ፣ የገዢነትን መብት ለማግኘት ይንጠራወዛሉ፡፡ ብዙዎችም ነፃነት የሚባለውን አኃዝ ከነመኖሩም ይረሱታል፡፡ ትግሉ ሮማዊ፣ እንግሊዛዊ፣ አሜሪካዊ፣ ፈረንሳዊ፣ ጣሊያናዊ፣ ሳዑዲአረባዊ ወይም ሊባኖሳዊና ኳታራዊ ምንትስ ለመሆን መንጠራራት ይሆናል፡፡ ገዢዎች ከሚሠሩት ሃጢያት ሁሉ እንዲዚህኛው ዓይነት በክፋት የተሞላና የረጅም ጊዜ ቀውስ የሚያስከትል መርዝ የለም፡፡
ነፃነት ገፋፊዎች ይሄንን ሳያደርጉ ሁለት ዓላማዎችን ይዘው ነው፡፡ 1ኛ) የገዢዎቹን (የራሳቸውን) ትልቅነትና የሌላውን ትንሽነት አሳምኖ የበላይም ሆኖ ለመኖር የተዘየደ ደባ ነው፡፡ 2ኛ) አገሩና ሕዝቡም የኋላ ኋላ የይስሙላ ነፃነት ሲሰጠው፣ የባሕል ተገዢ ሆኖ እንዲቀርና የመሠረታዊ ነፃነት ጣዕም ሳይቀምስ እንዲቀር ለማድረግ የተሸረበ ታክቲክ ነው፡፡ በመሆኑም ነፃነት ገፋፊዎች በእቅድና በብልሃት ወደ ዓላማቸው ይደርሳሉ፡፡ አንዱ ዘዴ ከላይ የጠቀስነው የገዢነት መብት መስጠት ሲሆን፣ ሁለተኛው ዘዴ ደግሞ የነሱንና የባሕላቸውን ትልቅነት እንዲሁም ከፍተኝነት የተገዢዎቹንና የባህላቸውን ትንሽነትና ዝቅተኝነት ከልጅነታቸው ጀምሮ በማስተማር ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ትምህርት በአንድ ሕዝብ አእምሮ ውስጥ ሲቀረጽ ባሕል ለዘላለሙ ይጠፋል፡፡ አብሮትም መሠረታዊ ነፃነት ድራሹ ይጠፋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በየአውደ ምህረቱ፣ በየመስጂዱ፣ በየማኅበር ቤቱና በየመንዙማ ዝየራው፣ በየጽዋውና በየወዳጃ ቤቱ ሳይቀር የባሕል ወራሪዎቹ ትልቅነት ስለሚሰበክና ስለሚደሰኮ ዜጎች ከማይወጡት የመሠረታዊ ነፃነት እጦት ውስጥ ገብተው እንዲዘፈቁ ይዳርጋሉ፡፡ የፖሊስና የወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ስለገዢዎች የበላይነትና ስለሠልጣኞቹ የበታችነት በዘዴ እንዲማሩ ይደረጋል፡፡ ከዚያ ፀጥ-ለጥ ብለው ተገዢ ከመሆን ውጭ ምርጫ አይኖራቸውም፡፡ ጃስ ሲሉት የሚናከስ፣ ጭላጭ ሲያቀርቡለት የሚልስ ውሻና ድመት ይሆናል፡፡
የተገዢዎቹን ሥነ-ልቦናም የበለጠ ለማኮስመንም ሲባል፣ ገዢው በተገዢው ዓይን ከታምራት የማያንሱ ነገሮችን ሲሰራ እንደነበረና እየሠራም እንዳለ ተደርጎ በየመድረኩና በየአደባባዩ ይደሰኮራል፡፡ ተገዢው ሕዝብ የፈለገውን ያህል ቢማርና ጥበበኛ ቢሆን እንኳን፣ ገዢዎቹ የሚሠሩትን ምትሃት ከቶም የማይደርስበት “ራዕይ” መሆኑን እንዲገነዘብ ተደርጎ ይሰበካል፡፡ የገዢዎቹ ራዕይና አርቆ-አሳቢነት ከሞቱም በኋላ በመገናኛ ብዙሃን እየተደሰኮረለት፣ ለሙት መንፈስ ሳይቀር ታማኝ ሆኖ እንዲገዛ ይደረጋል፡፡ ዱሮ-ዱሮ “ሰማይ አይታረስ፣ ንጉሥ አይከሰስ” ነበር የሚባለው፡፡ አሁን ደግሞ “ከጓድ አብዮታዊ መሪያችን ጋር ወደፊት!” ወይም “ከባለራዕዩ መሪ ጋር ወደፊት!” በሚል ሽፋን፣ ሕዝቡ መሠረታዊ ነፃነቱን እንዳይጠይቅ፣ አልፎ-ተርፎ ነፃነቱን ሲገፈፍም ዝም ብሎ እንዲያይ፣ “አሜን” ብሎ እንዲገዛም ያመቻቹታል፡፡ (ብቻቸውን አይደለም፣ ጭፍራና ጀሌ አስከትለው ነው፤ ካድሬዎቻቸውን አስደግድገው ነው፡፡)
ፕ/ር ጌታቸው እንደጠቀሱት፣ ገዢዎች የሚፈጽሙት ሦስተኛው መቅሰፍት ከሁሉ የባሰ ነው፡፡ ተገዢዎች ነፃ ቢወጡ እንኳን ራሳቸውን ችለው የሚያድሩም እንዳይመስላቸው አድርገው በባዶ ፕሮፓጋንዳ ያሸብሯቸዋል፡፡ ገዢዎቹ (ከሃሊዎቹ) የሌሉበት ነገር እንደሚዘባረቅ፤ “እነርሱ ያልገዙት አገር እንደሚበታተን፤ ዜጎች እንደ ሩዋንዳና ቡሩንዲ እንደሚተላለቁ፣” ሟርትና ጥላቻን ይደሰኮራሉ፡፡ ባዶ ሟርትና ፕሮፖጋንዳ መሆኑን ለመረዳት ተገዢዎች ለማመን እስኪቸገሩ ድረስ ፕሮፓጋንዳ ይሠራባቸዋል፡፡ ያንንም ለማወቅ፣ “በእርግጥ ባህላችንና እምነታችን የተመቸ ነውን?” ብሎ የሚጠየቅ ሰው ያስፈልጋል፡፡ ያን ጊዜም፣ የገዢዎቹ ሟርትና ማስፈራሪያ በሥልጣን ከመቆየት የዘለለ ቁብ እንደሌለው ይረዳል፡፡ “ጠመንጃ ነካሾች፣ በሥልጣን ኮርቻው ለመፈናጠጥና ለመቆየት ብለው የሚነዙትን ሽብር ፋይዳ-ቢስነት ለመረዳት፣ በመጀመሪያ ባህልን ጠንቅቆ ማወቅ” እንደሚያስፈልግ ኤድዋርድ ሳይድ Orientalism በተባለው መጽሐፉ ይመክራል፡፡
ስለባህል ምንነት ለመረዳት የሚፈልግ ሰው ካለም፣ “ባሕል ማለት ቋንቋ፣ ዜማ፣ ዘፈን፣ የአለባበስ ዓይነትና ዘዴ፣ የጸሎት ወይም የአምልኮ ሥነ-ሥርዓት፣ ከቤተሰብና ከጎረቤት ጋር ያለው ተራክቦ፣ በአረጋውያንና በልጆች ብሎም በወራዙት መካከል ያለውን ግንኙነትና ሥርዓት እንዴት ነው?” ብሎ መጠየቅና መመርመር አለበት (ፕ/ር ጌታቸው፣ 1960)፡፡ እስከምናውቀውና እከተረዳነው ድረስ፣ የኢትዮጵያውያን ባሕል በፈሪሃ እግዚአብሔር ላይ የተመሠረተ ነው በመሆኑ፣ ዕልቂትን አያስከትልም፡፡ እልቂት ቢከሰት እንኳን የእልቂቱና የግድያዎቹ ፈፃሚዎች ራሳቸውንና ሀገራቸውን ክደው፣ የገዢዎቹ ደረጃ ላይ ደርሰናል በሚሉት የነፃነት ገፋፊዎች ጭካኔ የሚፈፀም ነው፡፡ የእውነተኛ ኢትዮጵያውያን መዋግደ ኅሊና የተገራና ፈሪሃ-እግዚአብሔር ያለው በመሆኑ፣ ለጭካኔ ብርታት የለውም፡፡ ትክክለኛ ኢትዮጵያውያን ኅቁር ፍጥረታት አይደሉም፡፡ ከነፃነታቸውና ከሰብዐዊነታቸው ያለፈ፣ የሚያስቀድሙት ሃብትም ሆነ ሥልጣን የላቸውም፡፡ ኅቁር ፍጥረታት ከፈረሱ በፊት ጋሪውን ያስቀድማሉ፡፡ “ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ይቅደም!” ሲሏቸው፣ “መልካም አስተዳደር እናሰፍናለን!” ይላሉ፡፡
ምዕራባዊያኑም ሆኑ አንዳንድ የምስራቅ አገሮች በአገራችን ላይ የባሕልና የመሠረታዊ ነፃነት ገፈፋን ስፖንሰር ያደርጋሉ፡፡ በከተሞቻችን አካባቢ እንደምናየው፣ ኦርቶዶክስሰ ክርስቲያኖቹ እንደሶሪያና ሊባኖስ ካህናት፣ ሙስሊሞቹም እንደ ሳዑዲና የመን ሼኪዎች፣ ካቶሊኮቹም እንደቫቲካን ቀሳውስት፣ ፕሮቴስታንቶቹም እንደጀርመንና አሜሪካን ፓስተሮች ለመሆን ይቸጋገራሉ፡፡ የሃይማኖትና የፖለቲካ መሪዎቹ፣ ራሳቸውን ክደው በሌሎች ባሕል ኮራጅነት ተጠምደው እሽቅድምድም ይዘዋል፡፡ ከራሳችን አለባበስ የእነርሱ አለባበስ፤ ከራሳችን ዜማና ዘፈን የነርሱ ጋጠወጥ ስልት፣ ከራሳችን የቤተሰብ ኑሮ የነርሱ ቤተሰባዊ ኑሮ፣ ከራሳችን ወግና ሥርዓት የነርሱ ወግና ሥርዓት፣ ከራሳችን አገር የነርሱ አገር የሚሻል መሆኑን ሊያሳምኑን ጥረዋል፡፡ የዚህ የዚህ ታዲያ፣ በዓድዋና በማይጨው ለምን የብዙ ኢትዮጵያውያን ንፁህ ደም ፈሰሰ? በሽንብራ ኩሬና በመተማ፣ በዶጋሊና በኦጋዴን ለምን ጀግኖች ተሰው? አገራችን እንዳትገዛና በእነርሱ እንዳትተዳደር አልነበረምን?!” እንጂ፤ “አገሪቱማ ሳትገዛና ሳትተዳደር መቼ አድራ ታውቃለች! ዋናው ምክንያት እነሱ በምንም መልኩ እንዳይገዙን መሰረታዊ ነፃነታችንን እንዳናጣ አልነበረም እንዴ? የራሳችን ባህል እንድንጠብቅና የነሱን ባህል እንዳንይዝ አልነበረምን?” አሁን ታዲያ ምን ነካን? ምን ዓይነትስ ጥንጣን በላን? ምን አነቀዘን? (ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ፣ 1960፡፡)
ከላይ በጠቀስነው መጣጥፋቸው ላይ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ እንደገለጹት ከሆነ፣ “በማናቸውም ረገድና በየትኛውም ሥርዓት ውስጥ መሠረታዊ ነፃነት እንጂ ነፃ ነፃነት የለም፡፡” ነፃ ነፃነት (Absolute Freedom) የሌለው፣ በነፃ ነፃነት ውስጥ መኖርም ስለማይቻል ነው፡፡ ነፃ ነፃነት አለ ካልን፤ የሕዝቡ የርስ በርስ ግንኙነት ባዶ (ዜሮ) ነው ማለታችን ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ኃላፊነትና ግዴታ እስካለ ድረስ “ነፃ ነፃነት” የለም፡፡ ያለው መሠረታዊ ነፃነት ነው፡፡ አንዱ ከሌላው የሚቀበለውና ለሌላውም የሚሠጠው እስካለው ድረስ ነፃ ባህልም የለም፡፡ አንዱ ከሌላው ይዋሳል፤ ያውሳልም፡፡ ነፃ ባህል የለም፤ ነፃ ነጻነትም የለም፡፡ ያለው መሠረታዊ ባህልና መሰረታዊ ነፃነት ነው፡፡ ግራዚያኒን ለመቃወም ሰልፍ መሰለፍ አትችሉትም የሚሉትና የሚያስሩት ወገኖች፣ የመሠረታዊ ነፃነት አፈና እያካሄዱ ነው፡፡ አንድ ሃሳብ ወይም አጀንዳ ሲነደፍ የሚጮኹና የሚፎክሩትም ወገኖች፤ መሠረታዊ ነፃነትን ለመግፈፍ በአነስተኛና ጥቃቅን ገዢነት ተግባር ላይ የተሰማሩ ናቸው፡፡ ሃሳቡን ሳይሆን አሳቢውን የሚዘልፉና የሚሳደቡም ኅቁራን ካሉም፤ አንድ ለአምስት የተደራጁ የገዢዎቹ አባሪዎችና ተባባሪዎች ናቸው፡፡ ከዚህ ሌላ አይደሉም፡፡
መሠረታዊ ነፃነትን የሚገድበው መንግሥት የሚባለው አካል ብቻ አይደለም፡፡ የመንደር ጎረምሳ፣ የቀዬ ጠብደልና የአጥቢያም ጎበዝ አለቃ ጭምር ናቸው፡፡ በግሌ መሠረታዊ ነጻነትን የሚገፍን አገዛዝ፣ ሥርዓትና መንግሥታዊ መዋቅር ለማጋለጥና አላህ ወይም እግዚአብሔር የሰጠኝንም ነፃነት ለማስከበር እጥራለሁ እንጂ፤ በአንድ ለአምስት ወይም በአነስተኛና ጥቃቅን ከተደራጁ የመሠረታዊ ነፃነት ገፋፊዎች ጋር ቅንጣት ሴኮንድም አላጠፋም፡፡ በአንድ ለአምስት ወይም በአነስተኛና ጥቃቅን የጎበዝ-አድማ ላይ ለተሰማሩት ወገኖቼም ሆነ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን የምናገረው ሃይለ-ቃልም የሚከተለተው ነው፡፡ “እርስ በርስ መፎካከታችንን ትተን፤ መሠረታዊ ነፃነታችንን የሚገፉትንና እያወናበዱ እንግዛችሁ የሚሉንን፤ ካድሬ ሆናችሁ፣ ሎሌ ሆናችሁ ቋንቋችንን ተናገሩ፤ የእኛን ባሕል ተከተሉ፣ የእኛን ሃይማኖት እመኑ፣ እናንተ ምንም ስለማታውቁ፣ እኛ ሁሉንም እናውቅላችኋለን፤ በአጠቃላይ “እኛን ምሰሉ” ባዮችን የአገዛዝ ዘመን እናሳጥር፡፡ እርስ በርስ ስንቦቃቀስ፣ የገዢዎቻችን እድሜ አራዝመን የእኛንም ሆነ የሕዝባችን ስቃይ ከማራዘም፣ የመሠረታዊ ነፃነት ገፋፊዎችን ጎራ ከማጠናከር በስተቀር የምናተርፈው ቅንጣት ታክል ፍርፋሪም ሆነ ሰደቃ እንደሌለ ማወቅ አለብን፡፡ አይመስላችሁም ጎበዝ?!
(የሳምንት ሰዎች ይበለን!)