FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Monday, September 30, 2013

አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ (ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)


ኢህአዴግ ከቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በተከሰተበት ውስጣዊ ልዩነት በተለዋዋጭ የኃይል ሚዛን ሥር ለማደር በመገደዱ የስልጣኑን መዘውር የሚያሽከረክረውን አካል ለመለየት አዳጋች ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ ሽኩቻ መፍትሄ ማግኘቱን የሚያመላክቱ ሁናቴዎች መፈጠራቸውን የውስጥ አወቅ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡Journalist Temasegan Dasaleg
እንደ መግቢያ
ድንገቴው የመለስ ህልፈት ህወሓትን ቢከፍለውም፣ ብአዴን ራሱን እንዲያጠናክር መደላድል ፈጥሮለታል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት መለስ ዘመኑን ሙሉ በብአዴን ታማኝነት ላይ ጥርጣሬ ስላልነበረው ቀድሞውንም እንዲዳከም ባለማድረጉ ይመስለኛል፡፡ እርሱ በአይነ ቁራኛ ይጠብቀው የነበረው ህወሓትን ነበር፤ በተለይም በሠራዊቱ እና በደህንነቱ ውስጥ ‹‹ተፅእኖ መፍጠር ይችላሉ›› የሚባሉት አቦይ ስብሃት ነጋ እና የትግራይን መዋቅር በእጁ ያደረገው የቀድሞ የክልሉ አስተዳዳሪ ፀጋዬ በርሄ በጥርጣሬ ዓይን የሚታዩ ሆነው ቆይተዋል፡፡ በምርጫ 2002ቱ ማግስትም ድርጅቱ አቦይን ‹‹በክብር›› እንዲሸኝ ሲደረግ፣ ፀጋዬ በርሄን ደግሞ ‹‹አማካሪ›› በሚል ሽፋን ከመቀሌ ወደ ቤተ-መንግስት (ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ) አዛውሮ በቅርብ እይታ ስር በማዋሉ ሁለቱንም ከጨዋታ ውጪ አድርጓቸዋል፡፡
በግልባጩ አዜብ መስፍንና ‹የመለስ ታማኞች› የሚባሉት እነአባይ ወልዱና ቴዎድሮስ ሀጎስ የፖሊት ቢሮውን ተቀላቅለዋል፡፡ ሁነቱም ከእነአቦይ ጋር በስጋ ዝምድናና በጋብቻ የተሳሰሩ ባለስልጣናትን በማስከፋቱ በድርጅቱ ውስጥ ብቻ የሚታወቅ (አደባባይ ያልወጣ) ልዩነት ፈጥሮ እንደነበረ ይታወሳል (በነገራችን ላይ ኦህዴድ የማዳከሙ ሴራ ሰለባ ነው፡፡ ይህ ሁናቴ ከመለስ ህልፈትም በኋላ ቀጥሏል፤ ለምሳሌ ባለፈው ዓመት የግንባሩ አባል ድርጅቶች፣ የየራሳቸውን ጠቅላላ ጉባኤ ባካሄዱበት ወቅት ብአዴን በ‹ክብር› ካሰናበተው ሁለት ዓመት ያለፈውን መሪውን አዲሱ ለገሰን ወደ ቦታው መልሶ ራሱን ሲያጠናክር፣ በተቃራኒው ኦህዴድ አንጋፋ አመራሮቹን፡- አባዱላ ገመዳ፣ ኩማ ደመቅሳና ግርማ ብሩን ከስራ አስፈፃሚነታቸው እንዲያነሳ ተገድዷል፡፡ ይህንን ነው መተካካት የሚሉትም፡፡
ህወሓት
የመለስን ህልፈት ተከትሎ በውስጡ ያደፈጠው ቅራኔ ፈንቅሎ በመውጣቱ ህወሓትን የ‹መቀሌው› እና የ‹አዲስ አበባው› በሚል ለሁለት ከፍሎት ነበር፤ ይህ ግን የመቀሌው-በአዲስ አበባ፤ የአዲስ አበባው-በመቀሌ ደጋፊ አልነበረውም እንደማለት አይደለም (የመቀሌውን አዜብ መስፍን፣ አባይ ወልዱ፣ ቴዎድሮስ ሀጎስ… መርተውታል፤ የአዲስ አበባውን ደግሞ አቦይ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃዬ፣ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እና ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ በርካታ አንጋፋ ታጋዮች ዘውረውታል)፡፡ ይህ አጋጣሚም ከእነ አዜብ ቡድን ጋር ትብብር የፈጠረውን ብአዴንን ለጊዜያዊ ድል አብቅቶት ነበር (በ93ቱ ክፍፍልም የብአዴን ድጋፍ መለስ በአሸናፊነት እንዲወጣ ጉልህ ድርሻ ማበርከቱ ይታወሳል)፡፡ አቦይ ስብሃት ነጋ በትግርኛ ቋንቋ በሚታተመው ‹‹ውራይና›› መፅሄት ላይ ‹‹ህዝቢ ትግራይ ዘቃልሶ ኣቃሊሱ ዝጠቕሞ ወያናይ ውድብ ይግብኦ›› (የትግራይ ህዝብ የሚያታግለው፣ ታግሎም የሚጠቅመው ወያኔያዊ ድርጅት ይገባዋል) በሚል ርዕስ በፃፉት ፅሁፍ ችግሩን እንዲህ ሲሉ ገልፀውታል፡-
‹‹አባይ ወልዱም ባለፈው የህወሓት ጉባኤ ላይ በተደጋጋሚ ‹ህወሓት ውስጥ ማጠለሻሸትና (የሥልጣን) ሽኩቻ በስፋት እየተስተዋለ ነው› በማለት ሁኔታውን ገልፆታል፡፡ ከዚህ በላይ ማረጋገጫ ደግሞ የለም፡፡ እንዲህ ያለ በኃይል አሰላለፍ ደረጃ ሊታይ የሚችል የአንድን የፖለቲካ ድርጅት አቅም ከማዳከምና መርሀ-ግብሩን ከማሰናከል አልፎ ተርፎም ድርጅቱን ለአስከፊ ውድቀት ሊጥል ከሚችል አደገኛ ሁኔታ የበለጠ አደጋ ያለ አይመስለኝም፡፡›› (‹ውራይና› ቁጥር 4 ነሐሴ 2005 ዓ.ም)
ከኃይለማርያም ጀርባ
ኃይለማርያም ደሳለኝ የግንባሩ ሊቀ-መንበር በመሆኑ ጉዳይ ላይ ብአዴንም ሆነ ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ቅሬታ አልነበራቸውም፤ ምክንያቱም እርሱም ሆነ ‹ደቡብን እወክላለሁ› የሚለው ድርጅቱ ለአሸናፊ ኃይል ከማገልገል አልፈው የፖለቲካ አመፅ ሊያስነሱ እንደማይችሉ ይታወቃልና፡፡ ይሁንና በወቅቱ ኃይለማርያም ሰልፉን በ‹መለስ ባርኔጣ› ከሚንቀሳቀሰው ከመቀሌው ህወሓትና ብአዴን ጋር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝበማስተካከሉ የኃይል ሚዛኑ በአንፃራዊነት ወደእነርሱ እንዲያጋድል አድርጓል፡፡ በግልባጩ ለእነ አቦይ እና ደጋፊዎቻቸው የመሸነፍ መገለጫ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ እንግዲህ እስከ ዘጠነኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ድረስ ‹መልከ-ኢህአዴግ› በዚህ መልኩ ነበር የቀጠለው፡፡
‹መፈንቅለ-ህወሓት›
ብአዴኖች፣ ከመቀሌው ህወሓት ጋር የፈጠሩትን ግንባር፣ ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር መንበር ካገኙት ድጋፍ ጋር በማዋሀድ፡- የአዲስ አበባውን ህወሓት የአመራር አባላት ሙሉ በሙሉ፣ የደህንነት ሀላፊው ጌታቸው አሰፋን እና አንጋፋ የህወሓት ታማኝ ጄነራሎችን ከመንግስታዊውም ሆነ ከፓርቲው ኃላፊነታቸው በማንሳት በአሸናፊነት ለመወጣት ስልታዊ እንቅስቃሴ አድርገው እንደነበር ለድርጅቱ ቅርብ ከሆነ ሰው አረጋግጫለሁ፡፡ በባህርዳሩ ጉባኤ ላይም መላኩ ፈንቴ ‹አላሰራ አሉኝ› ብሎ በአደባባይ እንዲያጋልጣቸው ከተደረጉት የንግድ ደርጅቶችና ሀብታም ነጋዴዎች አብዛኞቹ ከአዲስ አበባው ህወሓት ጋር የተሳሰሩ እንደነበረ ይታወቃል፡፡
እነዚህን ኩነቶችም ነው ‹መፈንቅለ-ህወሓት› ለማለት የተገደድኩት፡፡ ሴራው የከሸፈው በሁለት ምክንያቶች ይመስለኛል፤ የመጀመሪያው በሰውየው ህልፈት ማግስት (ተተኪው ጠቅላይ ሚንስትር ገና ባልተመረጠበት) እነአባይ ፀሀዬ ሶስት ሜጀር ጄነራል እና ሰላሳ አራት ብርጋዴር ጄነራሎች (አብዛኞቹ የህወሓት ሰዎች ናቸው) መሾማቸው ኃይላቸውን ሲያጠናክርላቸው፣ በአንፃሩ የመቀሌውን ህወሓትና ብአዴንን በሠራዊቱ ውስጥ የነበራቸውን ተፅእኖ ከማዳከሙም በላይ ኃይል የማሰባሰብ ሩጫቸውንም ገትቶታል፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በደህንነት መስሪያ ቤቱ አቀናባሪነት በ‹ፀረ ሙስና› ሽፋን የተከፈተው ዘመቻ ነው፤ እነበረከትንም ስልታቸውን መልሰው እንዲያጤኑ ያስገደዳቸው ይህ አይነቱ አስደንጋጭ እርምጃ ይመስለኛል፡፡
መላኩ ፈንታ።
የህወሓት ‹ቆሌ›
የኢትዮጵያን ልማዳዊ ፖለቲካ ከነሴራው ጠንቅቀው ከተረዱት ጥቂት ሰዎች መሀል አቦይ ስብሃት ነጋ አንዱ መሆናቸው ተደጋግሞ ተነግሯል፡፡ አቦይ ህወሓትን ጠፍጥፎ በመስራቱም ሆነ በስልጣን ለማቆየት የመለስን ያህል (ሊበልጥም ይችላል) ለፍተዋል፡፡ ዛሬም ተፈጥሮ ላመጣባቸው እርጅና እጅ ሳይሰጡ በህወሓት ላይ የሚሴረውን-ለመበጣጠስና ለተቀናቃኞቻቸው-ጉድጓድ ለመቆፈር እንደማይሳናቸው አሳይተዋል፡፡ ይህ ሁኔታም ነው ‹የህወሓት ቆሌ› የሚል ቅጥያ ያሰጣቸው፡፡
ከመለስ ዜናዊ ጋር የነበራቸው ጥብቅ የመተባበር መንፈስም ከጓዳዊነትም በላይ እንደነበር የቅርብ ሰዎቻቸው ይመሰክራሉ፡፡ ግና ይህ የጦፈ ፍቅራቸው ከ2000 ዓ.ም ወዲህ መደብዘዝ ጀምሮ ነበር፤ ልዩነታቸውም ቅስ በቀስ እየሰፋ ለመምጣቱ ብዙ ማሳያዎች አሉ፡፡ አንዱ መለስ፣ ለአዜብ መስፍን እየሰጠ የነበረውን የፖለቲካ ጉልበት፣ አቦይ ‹ህወሓትን በሴት ቀሚስ እንደማሳደር› አድርገው መውሰዳቸው ነበር፡፡ ሌላው የሴቲቱ ኃይለኝነት የአቦይን የተሰሚነት ክልል ከመፈታተን አልፎ በአደባባይ ክብራቸውን እስከ መዳፈር መድረሱ ይመስለኛል፡፡ ችግሩን ለመፍታትም ከመለስ ጋር ተገናኝተው መነጋገር አልቻሉም፤ ለህወሓት ቅርብ የሆኑ ወዳጄ እንደነገሩኝ መለስ ህይወቱ ሲያልፍ አቦይን ካገኛቸው ከሁለት ዓመት በላይ ሆኖታል፤ ምክንያቱ ደግሞ እርሱ ማግኘት ባለመፈለጉ ነበር፤ ይህም ሆኖ አቦይ ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም በልዩ ረዳቱ አማካኝነት ‹አስቸኳይ ጉዳይ ላይ ነው› እያስባለ መልሷቸዋል፤ በስራ አጋጣሚ ከቢሮ ውጪ ሲገናኙም ‹አጣዳፊ ስራ ስለተደራረበብኝ ነው፤ እኔ ራሴ አስጠራሀለሁ› እያለ ለሁለት ዓመት ያህል ሲርቃቸው ከቆየ በኋላ ነበር ድንገት ህይወቱ ያለፈው፡፡
አቦይ ወደ ህወሓት ተመልሰው በንቃት መሳተፍ የጀመሩት የመለስን ጤንነት ሲከታተሉ የነበሩ ሐኪሞች ‹ተስፋ የለውም› ባሉበት ማግስት ነበር፤ እንደምክንያት ያስቀመጡት ህወሓት ከድህረ-መለስ በኋላ፣ የብአዴንን የትከሻ ግፊያ መቋቋም አይችልም የሚል ስጋትን ነው፡፡ የሰውየው መጨረሻ ከታወቀ በኋላም የተፈጠረውን ክፍፍል ተከትሎ የታየው የኃይል ሚዛን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነበር፡፡ በወቅቱም አቦይ ‹መፍትሄ› ብለው ያቀረቡት ‹ብአዴንና ከጎኑ የተሰለፉትን የህወሓት የአመራር አባላትን ማሸነፍ ስለማንችል፣ አንጃው (የእነ ስዬ ተወልደ ቡድን) ተመልሶ ያጠናክረን› የሚል ነበር፤ በስማቸውም ‹‹ውራይና›› መፅሄት ላይ በፃፉት (ርዕሱ ከላይ በተጠቀሰው) ፅሁፍ ጉዳዩን እንዲህ በማለት ገልፀውት ነበር፡-
‹‹…ሁላችንም ህወሓት ውስጥ እያለን እኮ አንጃው ድርጅቱን ተቆጣጥሮት በትረ-መንግስቱንም ሊጨብጥ ተቃርቦ ነበር፡፡ በአንጃው የመዋጥ አደጋ ጊዜ ሁላችንም ተኝተን ነበር፡፡ እነዚያ የተሰናበቱት ሰዎች በማዕከላዊ ኮሚቴው ውስጥ ቢቆዩ ኖሮ ይተኙ ነበር ማለት ግን አይደለም፡፡ አሁን ላለው አመራር ይደግፉት ነበር ይሆን ማለቴ ነው እንጂ፡፡ …ከዚህ ቀደምም ሆነ አሁን ከህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ የወጣ ሁሉ እንደአዲስ ተደራጅቶ አሁን ላለው ማ/ኮሚቴ እገዛ የሚያደርግበትን መንገድ ማፈላለግ አለበት፡፡…›› (‹ውራይና› ቁጥር 4 ነሀሴ 2005 ዓ.ም)
አቶ አባይ ጸሐዬ
ሆኖም አባይ ፀሀዬ፣ አርከበ እቁባይ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ ጌታቸው አሰፋን የመሳሰሉት ‹በጭራሽ አይሆንም! የእነርሱ መመለስ ያውከናል› የሚል አቋም በመያዛቸው ሃሳቡ ተፈፃሚ ሳይሆን ቀርቷል፡፡
ከዚህ በኋላ የእነ አቦይና አባይ ቡድን ‹ህወሓትን ማዳኛ› ያለውን ሁለት ወሳኝ እርምጃ ወስዷል፤ ከህግ ውጪ ሶስት ሜጀር እና ሰላሳ አራት ብርጋዴር ጄነራሎችን ሲሾም፣ በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ ቁልፍ ሰው የነበረውን ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤልን ከየትኛውም አይነት ‹ኦፕሬሽን› እንዲገለል አደረገው፤ ቀጥሎ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ከሀላፊነቱ አነስቶታል፡፡ በዚህ በኩል ያገኙትን የፖለቲካ ጉልበት በመመንዘር ከህገ-መንግስቱም ሆነ ከተለምዶአዊው አሰራር በማፈንገጥ ተጨማሪ ሁለት ም/ጠቅላይ ሚንስትሮች እንዲሾሙ ጫና ፈጥረው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፣ ኃ/ማርያም ደሳለኝን በቅርብ ርቀት እንዲከተል አድርገዋል (በነገራችን ላይ ባለፈው ዓመት አጋማሽ ህወሓት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን በመረጠበት ወቅት ወልደስላሴ ሲጠቆም፣ ጠንካራ ተቃውሞ አቅርቦ እንዳይመርጡት ያነሳሳበት የደህንነቱ ሀላፊ ጌታቸው አሰፋ ሲሆን፣ በአንፃሩ ጌታቸው የተጠቆመ ጊዜ ወልደስላሴ እና ገብረሃዋድ ተቃውሞውን ቢያስተባብሩም ታናሽ ወንድሙ በላይ አሰፋን ጨምሮ ከመመረጥ ማደናቀፍ አልቻሉም፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ወልደስለሴና ገብረሃውድ በሙስና ተጠርጥረው በእስር ላይ ይገኛሉ)፡፡
ሌላኛው የህወሓት ‹ጠባቂ መልአክ› አባይ ፀሀዬ ነው (በ2005 ዓ.ም ወርሃ ጥቅምት በታተመችው ‹አዲስ ታይምስ› መፅሄት ላይ አባይ፣ መለስ ያደረገውን ማድረግ የሚችል /ከንግግር ችሎታ በቀር/ አደገኛ ሰው መሆኑን መግለፄ ይታወሳል) ዘግይቶም ቢሆን ቡድኑን የበላይ ባደረገው የ‹ፖለቲካ ጨዋታ› እርሱም የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስድ ታይቷል፡፡ ደብረፅዮንም ቢሆን ከህወሓት ጋር ባሳለፈው ዘመን ‹ትጉህ ደቀ-መዝሙር› ስለነበር ያካበተው ልምድ ህወሓትን በታደገው ንቅናቄ ላይ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ የሆነው ሆኖ እነ አባይ ከባህርዳሩ ጉባኤ በኋላ ነው ‹ከመከላከል ወደ ማጥቃት› ተሸጋግረው ብአዴንንና የመቀሌውን ህወሓት በ‹ሙስና› ስም ሰለባ ያደረጉት፡፡ ይህንን እውነታም የሚያጠናክርልን አቦይ ስብሃት ‹‹ውራይና›› መፅሄት ስለ ጉዳዩ ጠይቋቸው የሰጡት ምላሽ ነው፡-
‹‹አሁን በእስር የሚገኙት [እነመላኩ ፈንቴን ማለታቸው ነው] ሙሰኞች ብቻ አልነበሩም፡፡ የፖለቲካዊ ኃይል አሰላለፍንም ሲለውጡ የነበሩ ናቸው፤ ያስፈራሩም ነበር፤ ‹የስልጣን ሹዋሚም ሻሪም እኛ ነን› አስከማለትም ደርሰው ነበር፡፡›› (‹ውራይና› ቁጥር 2 ሠኔ 2005 ዓ.ም)
የብአዴን የአመራር አባል የሆነ አንድ ሚንስትር ለእስር ሲዳረግ፣ ሌላ ሚንስትር ደግሞ ከኃላፊነቱ መነሳቱ ይታወቃል፡፡
አዲሱ ግንባር
ብአዴን የአዲስ አበባው ህወሓት ክንደ-ብርቱ እየሆነ በመምጣቱ፣ የእነ አዜብን ቡድን አውላላ ሜዳ ላይ ትቶ አብሮ ለመስራት ተደራድሯል፡፡ እነ አባይም ‹ከብአዴን ተሻርኮ ሊያስበላን ነበር› ያሉትን የመቀሌውን የህወሓት ኃይል ከሞላ ጎደል ሲያስገብሩት፣ የቡድኑ መሪን አዜብ መስፍንን ደግሞ ከኤፈርት ከማሰናበታቸውም በላይ የፓርላማ ወንበሯን የሰዋችለትን የአዲስ አበባ የከንቲባነት ምኞቷን አጨልመው፣ በመለስ ፋውንዴሽን ገድበዋታል (የመለስ ሙት ዓመት በተከበረበት ወቅት የትግሉን ዘመንና የመለስን ገድል በኢቲቪ ሲተርኩልን የነበሩት የታሪኩ ዋና ተዋንያን አቦይ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሀዬ፣ ሳሞራ የኑስ…ሲሆኑ፣ በህልፈቱ ሰሞን ግን መድረኩን ተቆጣጥረውት የነበሩት ብአዴኖች፣ እነኩማ ደመቅሳ እና ትግሉን በመፅሀፍትና በቴሌቪዥን የሚያውቁት እነ ሬድዋን ሁሴን መሆናቸውን ስናስታውስ የእነ አባይ ፀሀዬ ህወሓት ምን ያህል ተገፍቶ እንደነበረ እንረዳለን፡፡)
በአናቱም ብአዴን የበላይነቱን በጨበጠበት ወቅት እንደ ስጋት ቆጥሮት ‹ሊፐውዘው› አስቦ የነበረውን መከላከያም፣ ከድርድሩ በኋላ በሁለቱ ኃይሎች ስምምነት ለአምስት ቀናት ኪራይ ሰብሳቢነትን እና ሙሰናን በተመለከተ ብቻ ተገማግሞ እንዲታለፍ ተደርጓል፡፡ ከኃላፊነታቸው ለማንሳት የታሰቡት ጄነራሎች ጉዳይም ‹ያልታሰበ አደጋ ሊያመጣ ይችላል› በሚል ለጊዜው ተዘሏል፡፡ ይሁንና ኤታማዦር ሹሙን ጄነራል ሳሞራ የኑስን በዚሁ ዓመት መጨረሻ በ‹ክብር› ሸኝቶ፣ ጄነራል አበባው ታደሰን የመተካት ዕቅድ መኖሩን ምንጮች ጠቁመዋል (ከዚህ በኋላ በጡረታ የሚሰናበቱ ጄነራሎች ‹መከላከያ ቴክኖሎጂ› /መቴክ/ በሚመራውና ወደፊት በሚያቋቁማቸው ኢንዱስትሪዎች ውስጥ በስራ-አስኪያጅነት ወይም በቦርድ አባልነት እንደሚመደቡ ቃል ተገብቶላቸዋል)
ከኃ/ማርያም ጀርባ ያደፈጠ-ስውር እጅ
በሁለቱም ቡድን ካሉ ምንጮቼ ‹‹ኃ/ማርያም ስራው ከብዶታል›› የሚል ቅሬታ እንደነበራቸው ሰምቻለሁ፤ ይሁንና መፍትሄ ተደርጎ የተወሰደው በረከት ስምዖንን የጠቅላይ ሚንስትሩ ‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር› አማካሪ በሚል ሹመት በጽ/ቤቱ ማስቀመጥን ነው፤ እርሱሁሉንም ነገር ከጀርባ ሆኖ እንዲያከናውን ወስነዋል፡፡ በረከት የተመረጠው ‹ከመለስ ጋር በቅርብ ስርቷል፣ መለስ ያነበበውን አንባቧል፣ የመለስን የዕለት ተዕለት ሥራ በቅርብ ተከታትሏልና መንገድ ይመራል› በሚል እንደሆነ ምንጮቼ ነግረውኛል (በነገራችን ላይ መለስ ሞት ባይቀድመው ኖሮ የወደፊት ዕቅዱ ቤተ-መንግስቱ ውስጥ ጀምሮት የነበረውን ግንባታ አጠናቅቆ፣ ከ2007ቱ ምርጫ በኋላ ስልጣኑን፣ ከአሻንጉሊቶቹ ለአንዱ አስረክቦ፣ መኖሪያውንም ወደ አዲሱ ህንፃ አዛውሮ፣ በለቀቀው ቤት ውስጥ የሚያስገባውን ጠቅላይ ሚንስትር ከጀርባ ሆኖ መዘወር ነበር፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ህልፈቱን ተከትሎ ግንባታውም የተቋረጠው፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ግንባታው ሊቀጥል እንደሆነ ሰምቻለሁ፡፡ በረከት ስምዖን እንዲገባበት ታስቦ ይሆን? …አባይ ፀሀዬም ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ የጠቅላይ ሚንስትሩ ‹አማክሪ› ሆኖ እንደሚሾም ‹ፎርቹን› ጋዜጣ በ‹ጎሲፕ› አምዱ አትቷል፡፡ መቼም ኃ/ማርያም ‹‹ሰርክ ‹እኔም አንደ ዳዊት ጨርቄን ልጣልለት› እያልኩ እዘምርለታለሁ›› ያለን አምላኩ ካልታደገው በቀር፣ ከእነዚህ ጉልበታም ሰዎች በጤና መውጣቱን እንጃ!)
ህወሓትና ብአዴን ልዩነታቸው መፈታቱን ለማሳየት፣ በረከት ስምዖን ከአዲሱ ሹመት በኋላ በሃያ ሁለት ዓመታት የስልጣን ዘመኑ አድርጎት የማያውቀውን መንግስትን ወክሎ (በግሉ ሄዶ ሊሆን ይችላል) በትግራይ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች የስራ ጉብኝት አካሄዷል፡፡ ‹ድምፀ ወያኔ› የተባለው የክልሉ ሬዲዮ ጣቢያም ጉብኝቱን ሳምንት ሙሉ ሳይታክት ደጋግሞ አስተላልፎታል፡፡
ስብሃት ነጋ
ሽራፊ-መረጃ
የአቦይ ስብሃት ነጋ ቡድን በኢህአዴግ ውስጥ ተከስቶ ከነበረው ክፍፍል በአሸናፊነት መውጣቱ ከተረጋገጠ በኋላ አዲስ ወሬ እየተሰማ ነው፡፡ ይኸውም ‹ህወሓት የጠቅላይ ሚንስትርነት ቦታውን በመልቀቁ፣ ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የሚያስረክቡትን ወንበር አቦይ ስብሃት መያዝ አለባቸው› የሚል ነው፤ ምንም እንኳ ሃሳቡ ተፈፃሚነት ባይኖረውም፣ ምንጮቼ አቦይ ራሳቸው በዘወርዋራ መንገድ ያሰራጩት ወሬ ሊሆን ይችላል ብለው ያምናሉ፡፡ አዜብ መስፍንም ቦታውን የመያዝ ፍላጎት ያላት ይመስለኛል፡፡
ብዙ ሲባልለት የቆየው የድህረ-መለስ ኢህአዴግ ከላይ ለማቅረብ በሞከርኩት መንገድ ግራና ቀኝ ሲዋልል፣ የመከፋፈል ተግዳሮትን ሲሻገርና እንደገና እየተመለሰ ሲሰባሰብ እዚህ ደርሷል፡፡ በዚህ ኮሮንኮቻማ ሂደት ውስጥ የጠቅላይ ሚንስትሩ ሚና ‹እዚህ ግባ› የምንለው እንዳይመስለን ሆኗል፡፡ ኃይለማርያም መንግስታዊ ብቻ ሳይሆን የፓርቲው ሊቀ-መንበርነትን የመሰለ ጠንካራ ፖለቲካዊ ስልጣን መያዙ ይህ ሰው የሚባለውን ያህል የዳር ተመልካች ሆኖስ ይቆያልን? ለሚለው ጥያቄ ቀጣይ ጊዜያቶች ብቻ መልስ ይኖራቸዋል፡፡ የጠቀስኳቸው የስርዓቱ ጉምቱ ሰዎች በዚህ መልኩ እየተንቀሳቀሱም ቢሆን፣ ይህን የኃይል መገዳደር እያደረጉ ያሉት በስልጣን ሞኖፖሊ ላይ ተቀምጠው መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ እናም ባቀረብኳቸው ሂደቶች እያለፉም ይሁን አይሁን ለስልጣናቸው የሚያሰጋ ጠንካራ የታቃውሞ ስብስብ አለመኖሩን ማመናቸው ይመስለኛል፣ የኃይል ትንቅንቁን ‹ግዜው አይደለም› ብለው ለማራዘም ሳይጠነቀቁ በግላጭ እርስ በእርስ የተፋለሙት፡፡
የሆነው ሆኖ የፓርቲው የታሪክ ድርሳን እንደሚነግረን ‹ይሆናሉ› የተባሉት ተቀልብሰው፣ ባልተጠበቁ ሁነቶች (የኃይል መገለባበጥ ተከስቶ) ፖለቲካው የሚመራበት አጋጣሚ ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል ሊኖር እንደሚችልም መዘንጋት አያስፈለግም፡፡

Sunday, September 29, 2013

ዓመፅ በሱዳን፥ስጋት በኬንያ፤ ትኩረት በአፍሪቃ

በሱዳን የተቀጣጠለው ሕዝባዊ ዓመፅ ካርቱምን አልፎ መላ ሱዳንን አዳርሷል፤ ቢያንስ 30 ሰዎች ተገድለዋል። በኬንያ መዲና አሸባሪዎች ካደረሱት ጥቃት ወዲህ በነዋሪዎቹ በተለይም «ትንሿ ሞቃዲሾ» በሚባለው የናይሮቢ ሰፈር የሚኖሩ ሶማሌያውያን በስጋት ተውተውጠዋል። ከጥቃቱ ጀርባ በርካታ አወዛጋቢ ነገሮች መነሳት ጀምረዋል። ትኩረት በአፍሪቃ ይቃኛቸዋል።
ዓመፅ በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱምና በመላ ሀገሪቱ
የሚትጎለጎል ጥቁር ዳመና የሱዳን መዲና ካርቱምን ውጧታል። የቤንዚን ማደያዎች በእሣት ተያይዘው እየተንቀለቀሉ ነው። እዚህም እዚያም በየጎዳናዎቹ የመኪና ጎማዎች ይነዳሉ፤ የፀጥታ ኃይላት እንዳይጠጓቸው ለማድረግ በተቃውሞ ሰልፈኞቹ የተለኮሱ ናቸው። ፕሬዚዳንት ዖመር ኧል በሽር ባሳለፍነው እሁድ የወሰዱትን የቁጠባ ርምጃ በመቃወም ድንገተኛው ዓመፅ ዳግም መላ ሱዳንን አዳርሷል።
«ምጣኔ ሀብታችን ላይ የተጋረጠው ችግር ሶሥት ምክንያቶች አሉት። ወደ ሃገር የምናስገባው ወደ ውጭ ከምንልከው ይልቃል። ለፍጆታ የምናውለው ከምናመርተው በላይ ነው። የገንዘብ ሚንሥትር ከሚያስገባው የሚያወጣው በዝቶበታል። በርካቶች ለነዳጅ ፍጆታ ይሰጥ የነበረው ድጎማ መሰረዙ ድሆችን እንደሚጫን ይገልፃሉ። መርሳት የሌለባቸው ጉዳይ ግን በእርግጥም ጫናውን በድሆች ላይ እንዲጠነክር ያደረገው የምጣኔ ሀብቱ ቀውስ ነው። »
የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ዖመር ኧል በሽር የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ዖመር ኧል በሽር
የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ዖመር ኧል በሽር ነበሩ በአንድ የውይይት መድረክ ላይ የተናገሩት። ይህ ንግግራቸው ግን ሕዝቡን ከማረጋጋት ይልቅ አስቆጥቶ መዘዝ ነው የጠራባቸው። በሺህዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን የቤንዚን ዋጋ በእጥፍ ማሻቀቡን፣ የመጓጓዣ ክፍያ መናሩን እንዲሁም ያንን ተከትሎ የዕለታዊ የፍጆታ እቃዎች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ መጨመርን በመቃወም አደባባይ መዋል ከጀመሩ ቀናት ተቆጥረዋል።
በርካቶች የሱዳን መንግሥት ኅብረተሰቡ ላይ የኑሮ ጫና እየፈጠረ በሚያጋብሰው ገንዘብ ተቀናቃኞቹን ለሚወጋበት የጦር ሰራዊት ማደራጃ ያውላል ሲሉ ይነቅፋሉ። የዲሞክራሲ ተሟጋች አምጋድ ፋሪድ።
«የሱዳን ህዝብ በመላ፤ የዚህን ፈላጭ ቆራጭ መንግሥት ውሳኔዎችና የኅይል እርምጃውን ይቃወማል። መንግሥት የተቃውሞውን ወገን ለመጨቆንና ጦርነት ለማካሄድ ብዙ ገንዘብ ያወጣል። ይህን ትቶ ለምን ለህዝቡ ቤንዚንና መባልእት አያቀርብም?»
በሱዳን የዲሞክራሲ ታጋዮች፤ ከሁለት ዓመት ከመንፈቅ በፊት በዓረቡ ዓለም መቀጣጠል የጀመረው የፀደይ አብዮት ሱዳንም ደርሶ የረዥም ዘመን ገዢው የዖመር ኧል በሽር መንግሥትንም ማጋሉ አይቀርም የሚል ምኞት ሰንቀው ነበር። ሆኖም የኧል በሽር የፀጥታ ኃይላት በተቃውሞ ሠልፈኞች ላይ በወሰዷቸው ጠንካራ ርምጃዎች የተነሳ የዲሞክራሲ አቀንቃኞቹ ምኞት ሳይሳካ ቀርቷል። የሕዝባዊ ምክር ቤት ፓርቲ አባል ባሽር አደም ራሕማ የሚያክሉት ነገር አላቸው።
«መንግሥት ችግር ተጋርጦበታል፤ በጀቱ ክፉኛ ተናግቷል፤ የሚፈልገው ገንዘብ እየቦጠቦጠ የመንግሥት እና የባሽር ፓርቲ ወጪዎችን ብቻ መሸፈን ነው። ከእዚያ ባሻገር መንግሥት በዳርፉር፣ ደቡብ ኮርዶፋን እና በነጭ አባይ ግዛቶች ለሚመራው ጦርነት በርካታ ገንዘብ ያስፈልገዋል።»
በሣምንቱ መጀመሪያ ላይ በሱዳን ተቃውሞው ከተቀሰቀሰበት ቅፅበት አንስቶ በበርካታ የዓረቡ ሃገራት የተለመደ መፈክር በማስተጋባት ላይ ነው። «ሕዝቡ የመንግሥቱን መወገድ ይሻል» ሲሉ ሱዳናውያን በየአደባባዩ ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ናቸው። «ነፃነት፣ ሠላም እና ፍትኅ፤ ሕዝቡ ዓብዮት ይሻል!» የሚሉ መፍክሮች በጎረቤት ሀገር የሱዳን መዲና ካርቱም ውስጥ በተደጋጋሚ እያስተጋባ ነው። በሱዳን ኦምዱርማን ትናንትናም ከአርቡ ፀሎት በኋላ ወደ 3,000 የሚጠጉ ሰዎች አደባባይ ወጥተው «ነፃነት፣ ነፃነት» ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል። ፖሊስ በወቅቱ ሰልፈኞቹን በአስለቃሽ ጢስ ለመበተን መሞከሩም ተዘግቧል።
ስጋት የዋጣት የኬንያ መዲና፤ ናይሮቢ
ባሳለፍነው ሳምንት በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በሚገኝ አንድ ሰፊ የገበያ አዳራሽ አሸባሪዎች ጥቃት ካደረሱ በኋላ በርካቶች አሁንም ድረስ በስጋት ተውጠዋል። ከሶማሌ በተነሱ አሸባሪዎቹ በደረሰው ጥቃት ቢያንስ 70 ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል። የሶማሌው ኧል ሸባብ በኬንያውያን ላይ ሽብር የመንዛቱን ያህል ከደሙ ንፁህ የሆኑ ሠላማዊ ሶማሌያውያን ናይሮቢ ውስጥ በፍርሀት ተሸብበው ይገኛሉ።
ወደ ዌስት ጌት የገበያ ማዕከል የሚያቀናው ጎዳና አሁን ለተሽከርካሪዎች ክፍት ሆኗል። ላለፉት ቀናት ይህ መንገድ ተዘግቶ ነበር። አሁን ተዘግቶ የቆየው ዋናው መገንጠያ ብቻ ነው። ጥይት መከላከያ ልዩ ሠደሪያ አድርገው ወደ ገበያ አዳራሹ የሚገቡትን እና የሚወጡትን አንዳንድ ወንዶች እና ሴቶች እንቅስቃሴ ለመቃኘት የጓጉ አላፊ አግዳሚዎች ከርቀት ቆመዋል።
የጀርመን የወንጀል ምርመራ ጽ/ቤት በናይሮቢ የተከሰተውን ፍንዳታ ለሚያጠናው የኬንያው ቡድን ርዳታ ለማድረግ የፈንጂ አምካኝ ባለሙያዎቹን ልኳል። ከፍንዳታው በኋላ በርካታ ጥያቄዎች ማብቂያ የለሽ ጥያቄዎችን አጭረዋል።
«ከረዥም ጊዜ አንስቶ የታቀደበት ሳይሆን አይቀርም። መንግስት ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል ቀደም ያለ መረጃ ሳይደርሰው እንዳልቀረ ጭምችምታዎች እየተሰሙ ነው። ሆኖም ያ ትክክል እንደሆነ ምንም ማረጋገጫ የለኝም።»
የሀገር ውስጥና የውጭ ሃገራት የአሻራ ባለሙያዎች ፍንጭ ፍለጋሲል አንድ የጎዳና ሸቃጭ በከተማው የሚሰማውን ጭምጭምታ ተናግሯል። መላው የከተማው ነዋሪዎች አሸባሪዎቹ ጥቃቱን ለመፈፀም ምንያህል ሊዘጋጁበት እንደቻሉ እየተነጋገረበት ነው። ፈንጂዎች ቀደም ብሎ በገበያ አዳራሹ ውስጥ ሳይከማቹ አልቀረም ተብሏል። አንዳንድ ጋዜጦች የደኅንነት ሰዎች ጉቦ ሳይቀበሉ አይቀሩም ሲሉ ጥርጣሬያቸውን አሰምተዋል። በበርካታ የጥቃቱ ሠለባ ቤተሰቦች ዘንድ ሀዘን የመግባቱን ያህል አሁን ቀስ እያለ በኬንያውያን ዘንድ ቁጣ አለያም ጥላቻ እየተቀሰቀሰ ነው። ብዙዎች ምናልባትም ለዳግመኛ ጥቃት ናይሮቢ ከተማ ውስጥ ከሚገኘው የሶማሌያውያን ሰፈር ሴራ እየተጎነጎነባቸው እንደሆነ ይሰማቸዋል።
የሀገር ውስጥና የውጭ ሃገራት የአሻራ ባለሙያዎች ፍንጭ ፍለጋ
በመዲናዋ አንደኛው ክፍል የሚገኘው ኢስሊ የተሰኘው ሰፈር ውስጥ በርካታ ሶማሌያውያን ስለሚኖሩ ሰፈሩ «ትንሿ ሞቃዲሾ» እየተባለም ይጠራል። በሶማሌ የሚገኙ እስልምና አክራሪ ቡድኖችን በመፍራት ሸሽተው የመጡ ሶማሌያውያን እርስ በእርስ በተያያዙ ቤቶችና በተቀጣጠሉ ታዛዎች ስር ተጠልለው ይገኛሉ። ይሁንና የኧል ሸባብ ታጣቂዎች በገበያ አዳራሹ ውስጥ ጥቃት ለመፈፀም ተዘጋጅተው እንደነበር አስቀድመው የሚያውቁ እና ቡድኑን የሚደግፉ ሶማሌያውያንም እዚሁ ሰፈር ውስጥ መሽገው እንደሚኖሩ ይነገራል።
ከጥቂት ወራት አስቀድሞ ኬንያ ውስጥ በተደረገው የምርጫ ዘመቻ ይህን «ትንሿ ሞቃዲሾ» የተሰኘውን ሰፈር የማስወገድ ዕቅድ የምርጫ ቅስቀሳ ሆኖ ቀርቦ ነበር። እናም አሁን የሰፈሩ ነዋሪዎች የቁጣ ሰለባ እንዳይሆኑ ሰግተዋል።
«ሁኔታው አስጨናቂ ነው። ጥቃት ፈፃሚዎቹ ሙስሊሞች እንደሆኑ ተናግረዋል። ስለእዚህ ፖሊስ ወደ ኢስሊ መጥቶ በርካቶችን ማሰሩ አይቀርም። ፈርቻለሁ።»
«ጥቃቱ ዘግንኖኛል። ፖሊሶች ኧል ሸባብን ይደግፋሉ ሲሉ እኛን ነው ጥፋተኞች የሚያደርጉን። ግን እነሱ ይሄን ሁሉ ጭካኔ እየፈጠሩ ሙስሊሞች አይባሉም ። ያ ከእስልምና ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።»
አንዳንድ ተንታኞች ከናይሮቢው ጥቃት ጀርባ የሚገኙ አክራሪዎች በመዲናዋ ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ከእንግዲህ በጥርጣሬ እየተያዩ እንዲኖሩ ለረዥም ጊዜ ሳያቅዱበት አልቀሩም ይላሉ። ወጣት ሶማሊያውያን ሙስሊሞች ከሚደርስባቸው ጫና አኳያ በቀላሉ ወደ ኧል ሸባብ ሊገቡ ይችላሉ ሲሉም ስጋታቸውን ይገልፃሉ። የኬንያው ጥቃት እስልምና አክራሪዎቹ ምን ያህል በዓለም አቀፍ ደረጃ መረባቸው የዘረጉ እንደሆነ ጠቋሚ ነው ተብሏል።
እንደ ኬንያ የደኅንነት ሰዎች ከሆነ ከሽብር ጥቃት ፈፃሚዎቹ መካከል የአሜሪካን ዜግነት ያለው ግለሰብ እና አንዲት እንግሊዛዊት ሴትም እንደሚገኙበት አስታውቀዋል። በኢስሊ የሚኖሩ በርካታ ሶማሌያውያን ለጥቃቱ ሰለቦች የተሰማቸውን ሀዘን ለመግለፅና ከተጎጂ ቤተሰቦች ጎን መቆማቸውን ለማሳየት ባለፉት ቀናት ጥረት ሲያደርጉ ተስተውለዋል። እናም ልክ እንደ ተቀሩት ኬንያውያን እና መላው ዓለም ሁሉ እነሱም በጥቃቱ እጅግ መደንገጣቸውንና ማዘናቸውን ለማሳየት ይፈልጋሉ። ከእዚያም ባሻገር ከሶማሌያ የመጡ ሙስሊሞች በአጠቃላይ አሸባሪዎች አለመሆናቸውን ግልፅ በማድረግም እራሳቸውን ለመጠበቅ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ

በአንድነት ፓርቲ መሰከረም 19 የተጠራው ሰልፍ አጀማመር ፎቶና መፈክሮች በከፊል


አንድነት ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በጥሩ ሁኔታ የተጀመረ ሲሆን ከጅምሩ የአዲስ አበባ አሰተዳደር ፕሊስ እጅ ለእጅ በመያያዝ ሕዝቡን እንዳይንቀሳቀስ እየሞከረ ቢሆንም ሕዝቡ ግን ወደፊት ለመሄድ ዝግጁ እንደሆነና ወደፊት የመገስገሱ ሰሜቱ እየጨመረ ነው:: ዶ/ር ነጋሶና የ33 አመራሮች ወደፊት በመሄድ ሕዝቡን ለመምራት እየሞከሩ ይገኛሉ:: በዚህ አጋጣሚ ሕዝቡ በፕሊሶችና በአድማ በታኝ ወደፊት እንዳይሄድ እየተሞከረ ነው !!
ሙሰና የስርዓቱ መገለጫ ነው!!
ፍትህ ናፈቃን !!!
ፍትህ እያሉ ቃሊቲ ገቡ !!
መብትን መጣየቅ አሽባሪነት አይደለም !!!
ወኔ የሌለው ያገር ሽክም ነው !!
ርዮት አለሙ !! እሰክንድር ነጋ !!አንዷለም አራጌ!! እነ አቡበከር አሽባሪ አይደሉም !!
አምባገነኖች ያሉበት የሁሉም ቤት እሰር ቤት ነው !!
ሕገመንግስታዊ መብት መጠየቅ አሽባሪነት አይደለም !!
በመሳሪያ ሕዝብ ማንበርከክ አይቻልም !!
አንበረከክም !!
Andenat party
Andenat party
Andenat Party
Andenat Party
Andenat party
Andenat Party
Andenat party
Andenat Party
Andenat party
Andent Party

ሰበር ዜና፣ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል የገቢ ማሰባሰቢያ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ!


ዛሬ ሴፕቴምበር 28 በኦስሎ ኖርዌይ ለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል የታሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ ተደረገ። በገቢ ማሰባሰቢያው ላይ በስጦታ እና ጨረታ ብቻ 408 ,633.85 የኖርዌጅያን ክሮነር የተገኘ ሲሆን ። ይህ ገቢ ከምግብ ሺያጭ ፣ ከመግቢያ ትኬት፣ ከቲሸርት ሺያጭ እንዲሁም ከተለያዩ ባህላዊ ቁሳቁሶች ሺያጭ ሳይጭምር መሆኑ ወዳጆችን ሲያስፈነድቅ ጠላቶችንን አንገት አስደፍቷል ። በፕሮግራሙ ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ኮማንደር አሰፋ ማሩ በመገኘት ከሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያኖች ጋር ምክክር አድርገዋል። ሙሉ ዘገባውን በቅርብ ይዘን እንቀርባለን ።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !
ከኖርዌይ
Norway G7 fundrise

Saturday, September 28, 2013

በእስር ላይ የነበሩት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ተፈቱ (አንድነት ፓርቲ UDJ)


Andenat Party UDJዛሬ መስከረም 17 ቀን 2006 ዓ.ም. የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት እና የአሁኑ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እንዲሁም በፓርላማ ብቸኛው የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካይና የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ግርማ ሰይፉን ጨምሮ በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የታሰሩት 26 የአንድነት አባላት ከሰዓታት ቆይታ በኋላ ተፈተዋል፡፡ በፖሊስ ተይዘው ወደጣቢያ የተወሰዱት የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ አስራት ጣሴ፣ የፓርቲው ሊቀመንበር ለመሆን በእጩነት የቀረቡትና የፋይናንስ ኃላፊ አቶ ተክሌ በቀለ፣ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስዩም መንገሻ፣ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራና ሌሎች አመራሮችም ነበሩበት፡፡
አመራሮቹ የፊታችን እሁድ መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ ቀበና መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፊትለፊት ከሚገኘው የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት አንድነት ፓርቲ ከ33 ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በመሆን ለጠሩት የተቃውሞ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በተለይ በአራዳ ክፍለ ከተማ በቅስቀሳ ላይ እያሉ መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ ነገር ግን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ለእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ቢሰጥም የከተማው ፖሊስ ለቅስቀሳ የሚሰማሩ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎችን በተደጋጋሚ ያለምንም በቂ ምክንያትና ክስ እያሰረ መፍታቱ አዲስ አይደለም፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አመራሮቹንና አባላቱን ለምን እና በምን የህግ አግባብ ለሰዓታት እንዳሰረ ብንጠይቅም ታዘንነው ከማለት ውጭ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡

Friday, September 27, 2013

የደብሪቱ ወተት

(ወለላዬ)

cow milk


ሰፈራችንን መሀል ለመሀል ሰንጥቆ ከሚያልፈው መንገድ በስተቀኝ ሃያ አንድ መኖሪያ ቤቶች ይገኛሉ። ከነዚህ ቤቶች ነዋሪዎች ውስጥ ከአብዛኛዎቹ ጋር የስጋ ዝምድና አለን። በተለይ በአንድ ግቢ ውስጥ የምንኖረው ስምንት ቤተሰቦች ደግሞ የቅርብ – በጣም የቅርብ ዘመዳሞች ነን።
በነዚህ ቤቶች ውስጥ አያቶች፣ እናቶች፣ አባቶች፣ አክስቶች፣ አጎቶች፣ አማትና አማቾች ሲኖሩ ከሁሉም የተውጣጣን የልጅ ልጆችም እንገኛለን። ከአጎቶቻችንና ከአክስቶታችን መካከል ሁለቱ ከኛ ዕድሜ ብዙ ስለማይርቁ ቀረቤታችን የጎላ ነው።
አሰግድ ገ/እግዚአብሔርና …
አሰግድ ቀልደኛ ነው። በማንኛውም ጊዜ በትንሹም በትልቁም ነገር እራሱን አዝናንቶ ሌላንም ለማስደሰት ይጥራል። የወጣለት ፀሐፊም ነው። እንደዛሬው የትያትር ጥበብ ሳይስፋፋ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ከሚሉ ጥቂት ተዋናዮች መካከልም አንዱ ነበር። አሰግድ አጎቴ ብቻ ሳይሆን ከጉርምስናዬ ማግስት ጀምሮ ምርጥ ጓደኛዬም ሆኖ ቆይቷል። ስለ አሰግድ ይቺን ካልኩ ይበቃኛል ወደቤታችን ድራማ ላምራ።
በቤታችን ውስጥ ቀንና ሰዓታቸው ያልተወሰነ፤ አጫጭር ድራማዎች በየጊዜው ይቀርባሉ። እነዚህ ድራማዎች አይጠኑም፤ ተዋናይ ተመርጦ አይመደብባቸውም፤ ፀሐፊና አዘጋጅ የላቸውም። አንዱ ባሻው መንገድ ይጀምረዋል፤ ሌላው አውቆም ሆነ ሳያውቅም ያግዘዋል፤ በቅብብሎሽ ወይም በግል ድራማው ተሠርቶ ይፈጸማል። ድራማው አስቂኝ ቢሆንም የማያቄሙ ተበዳዮችም ይኖሩታል። ብዙ ግዜ ድራማው በልጅ ልጆች የሚቀርብ ሲሆን፤ አሰግድ ድምቀት ሰጭ ሆኖ ያገለግላል።
አንድ ቀን እንዲህ ተሠራ። አንዷ አክስታችን ከመንደሩ ጠዋት ጠዋት የሚመጣላት ወተት በኪራይ ይዛለች። አከራይዋ ወ/ሮ ደብሪቱ ይባላሉ። ደብሪቱ ዝቅአድርጌ። ኃይለኛነታቸው በሰፊው ስለሚወራ ሰው ሁሉ በጥንቃቄ ነው የሚይዛቸው። የወተት ሂሳብ በወቅቱ ያልከፈለ የጭቃ ጅራፋቸውን ስለሚያወርዱበት ከቀኗ ውልፍች አይልም።
አክስቴ ዘንግታው ይሁን በሌላ አጋጣሚ የዛን ወር የወተት ሂሳብ ሳትከፍል ሦስት ቀን አልፏታል። በአራተኛው ቀን ጠዋት ወፍ ሳይንጫጫ የወ/ሮ ደብሪቱ ድምፅ በግቢያችን ውስጥ ተሰማ።
“ወ/ሮ አሰገደች እንደምን አደሩ? ምነው ምነው ትልቅ ሰው አይደሉም እንዴ!? ከልጆቼ ጉሮሮ ነጥቄ ያከራየኽዎትን የወተት ሂሳብ ሊበሉኝ ነው? ወይስ ምን ሆነው ነው ሦስት ቀን ሙሉ ያላኩልኝ? ከኔ ከደሃይቱ ይሄን በልተው ምን ሊጠቀሙ ነው? ምነው ጡር አይሆንብዎትም ወይ? ነግሬዎታለሁ! ማንንም የምፈራ እንዳይመስልዎት፤ እንቢ ካሉ ሕግ ፊት ነው የምገትርዎት እከነሽና ደብሪቱ! ‘ግዛኝ ግዣኝ ብለው፣ ሊሸጠኝ አሰበኝ’ አለ ያገሬ ሰው! ዛሬ ባይልኩልኝ ውርድ ከራሴ …” የደብሪቱ ንግግር ማለቂያም የለው …
አክስቴ መግቢያ ቀዳዳ ጠፍቷታል፤ በሹክሹክታ ታወራ ጀመር “ይቺ ሴትዮ ጤናም የላት እንዴ?”
“ምን ጤናም የላት ትያለሽ? ለምንድነው! በወቅቱ ያልከፈልሽው?” ባለቤቷ ደነፋ።
“አንተ ደግሞ ዝም በል። ቢረሳ እንኳን ላኩልኝ ይባላል እንጂ፤ በጠዋት መጥቶ ምን ያስለፈልፋል።” አክስቴ ይበልጥ ጮኸች። የግቢው ቤተሰብ በሙሉ የሴትየዋን እሮሮ እየሰማ ነው። ማንም መልስ ሊመልስ አልፈለገም። ሁሉም አድፍጦ ዝም!
ደብሪቱ ብለው ብለው ድምጻቸው ሲጠፋ መሄዳቸው ስለታወቀ ከየቤቱ ብቅ ብቅ ማለት ተጀመረ። አክስቴ ከሁሉም ቀድማ ነበር ውጪውን የረገጠችው። የወንድሟ ልጅ በራፏ ላይ ቆሟል። “ውይ ሽመልስዬ እዚህ ምን ትሠራለህ? ይቺ እብድ በጠዋት ቀሰቀሰችህ አይደል?” አክስቴ ጥፋተኛነት ተሰምቷታል።
“ምን እኔን ብቻ የሰፈሩ ህዝብ በሙሉ እኮ ነው የተረበሸው! አዋጅ የሚናገሩ ነበር የሚመስሉት። ማን ያልሰማ አለ ብለሽ ነው” ሽመልስ ነገሩን ይበልጥ አደመቀው።
“ጉድ! ጉድ! ጉድ! አዋረደችን እኮ! እስቲ በለሊት መጥቶ አፍ መክፈት ምን አመጣው የሷን ብር ይዤ እንዳልጠፋ ነው? ወይስ ገንዘብ ሆነና እንዳልክድ …?”
“ኧረ! ሕግ ፊት እገትርሻለሁም ብለዋል!”
“ሂድ! አንተ ደግሞ ነገር አታንፏቅ፤ ለሃያ ብር ነው ሕግ ፊት የምትገትረኝ!?”
“እኔ ምን አውቃለሁ፤ ሲሉ የሰማሁትን ነው”
“እሷማ ምን ያላለችው አለ! ቆይ! ግድ የለም! እማደርገውን፤ እኔ ነኝ የማውቅ።” አክስቴ ወደ በሩ አመራች።
“እንዴ አሁን ልትሄጂ ነው እንዴ?” ሸመልስ ነገሩ አላማረውም።
“አሁንማ ምን ይሁን ብዬ እሄዳለሁ። እንደሷ አላበድኩ። እንደው እንዴት እንደገባች በሩን ለማየት እንጂ ቡናዬን ጠጥቼ ቀስ ብዬ እደርሳለሁ። የማደርገውን እኔ ነኝ የማውቅ። ሁለተኛ ግን የሷን ወተት … መርዝ ያስጠጣኝ።”
* * * * * * * * * * *
የአክስቴ ቡና ደርሶ ዘመድ ተሰብስቧል፤ ሁለት ሌሎች አክስቶቼና አንድ አጎቴ እስከሚስቱ ቦታቸውን ይዘዋል። አሰግድ አለ፤ ዙሪያውን በልጅ ልጆች ተከቧል። አያታችን በምርኩዛቸው መሬቱን እያንኳኩ ቀኝ እግራቸውን እየጎተቱ ገቡ። ሁሉም ብድግ ብሎ ተቀበላቸው። ማዕከላዊውን ቦታ ይዘው ከተቀመጡ በኋላ፤ “ጠዋት እንደዛ ትለፈልፍ የነበረችው ማናት?” ጥያቄ አቀረቡ።
“ወ/ሮ ደብሪቱ ናታ” አክስቴ ወ/ሮን ጠበቅ አደረገቻት።
“ምን ይሁን ብላ?” አባባ ነገሩ ገርሟቸዋል።
“አልሰሙም እንዴ ወተት አከራይዋ …
“እኮ ምን ይሁን ብላ መጣች?” አላስጨረሷትም።
“የወተት ኪራይ ሳትከፍይ ዘገየሽ ብላ፤ ልትሳደብ ነዋ! ጨፈረችብኝ እኮ! …”
“ለመሆኑ! በሩን ማን ከፈተላት?”
“እንጃላት! እጇን አስገብታ ከፍታ ወይም አንዱ ወጥቶ ይሆናላ”
“ገብቶ ማለትሽ ነው?” አባባ ወደ አሰግድ ተመለከቱ።
አሰግድ ሽሙጡ ቢገባውም መልስ ሊሰጥ አልፈለገም። “ደግሞ እኮ ስትናገር አንገቷን የታነቀች ነው የምትመስል” አለ አሰግድ፤ የሴትዬዋ ነገር እንዲሰፋ ፈልጓል፤ ሁሉም በጅምላ ሳቀ።
“ኧረ! የሚያንቅ ይነቃትና፤ ስትታይም የታነቀች ነው የምትመስል” የእህቷ መሰደብ ያንገበገባት ትንሿ አክስታችን ነበረች። የአሰግድ ሳቅ ጎልቶ ወጣ።
“አዎን ሳቅ አንተ! ጅብም ሲጎትተኝ ብታይ ሳትስቅ አትቀር። አይ! የኛ ወንድም!” አክስቴ ተናደደችበት።
“አንችስ ለምን ሳትከፍይ ቆየሽ?” አያታችን ሌላ ጥያቄ ወረወሩ።
“እርስት አደረኩት አባብዬ”
“እርስት አደረኩት! አንቺ የረሳሽ እንደሆን እሷም መርሳት አለባት?” ሁሉም ሳቁን ለቀቀው። አባባም በራሳቸው ንግግር ይስቁ ጀመር። ወርቅ ጥርሳቸው ከግራና ከቀኝ እንደ አንፖል ያበራል።
“እናስ! የሆነ እንደሆን ሀገር ጥዬ አልኮበልል፤ በጠዋት መጥቶ መለፍለፍን ምን አመጣው? ቆይ! ግድየለም! የማደርገውን እኔ ነኝ የማውቅ …”
“አክስቴ ገንዘባቸውን ወደዚያ ወርውሪላቸው እንጂ ምንም እንዳትናገሪ” ሽመልስ ጣልቃ ገባ።
“ለምንድነው የማልናገር? አንተን ደግሞ የሷ ጠበቃ ያደረገህ ማነው? ፎቃቃ”
“አይ! ወንድማቸው የአብዮት ጥበቃ ሊቀመንበር ናቸው ሲባል ስለሰማሁ …”
“ታድያ! የሆነስ እንደሆን በጠዋት እየተነሳሽ ሰው ስደቢ ብሎ ፈቅዶላታል ማለት ነው? ማነው ከዘሯ የነገሠ?” ትንሿ አክስት ተንጣጣች። አክስቴ እየተናገረች ሥራዋን አላቋረጠችም። ቁርስ አቅርባ ተበላ። አቦል ቡና ተዳረሰ፤ አሁን ሁሉም ጎኑ ካለው ሰው ጋር ጨዋታ ጀምሯል። አሰግድ ከኛ ጋር እየቀለደ ነው፤ አባባ ጣቶቻቸውን አቆላልፈው ሁለት አውራ ጣቶቻቸውን ማገለባበጥ ይዘዋል።
ሽመልስ ገባ ወጣ ይላል። አክስቴ አልወደደችለትም። “መቀመጫህ ላይ መርፌ የተሰካ ይመስል፤ ምን ያንቆራጥጥሃል? ቡና እያፈላሁ የሚክለፈለፍብኝ አልወድም … ትቀመጥ እንደሆን ተቀመጥ!” ሸመልስ ውጭውን መርጦ ወጣ።
ሁለተኛውና ሦስተኛው ቡና ተፈልቶ ተጠጣ። አክስቴ ስኒውን አነሳስታ፣ እቃውን አጣጥባ ልብሷን ለባብሳ ተነሳች። መሃረቧ ላይ ብር ቋጥራ ያዘች። ወ/ሮ ደብሬ ዛሬ ጉዷ ፈልቷል። ሁለቱ ሌሎቹ አክስቶቼ በዛው የምንደርስበት አለ ብለው ከአክስቴ ጋር ለመሄድ እየጠበቋት ነው። አሰግድ ሥራው ሊሄድ ተዘጋጅቷል። እግረ መንገዱን ግን የደብሬን ጉዳይ ለማየት ፈልጓል። አብዛኛው የልጅ ልጅ በር ላይ እንደዘብ ቆሞ ይሳሳቃል።
በዚህ መሀል ያልታሰበ ነገር ተፈጠረ። የደብሬ ልጅ እንደወትሮዋ ወተቱን በነጭ ጨርቅ ሸፍና በራፋችን ላይ ቆማ ታየች። አክስቴ እንደዛ ተናግረው ካሁን ወዲያ ወ/ሮ ደብሬ ወተት ይልካሉ የሚል ግምት አልነበራትም፤ አብዛኛውም የሚያስበው ይሄንኑ ነው።
አክስቴ ልጅቷን እንደጉድ እያየቻት “አንቺ! …” ብላ ልትናገር ስትጀምር ሸመልስ አንዳች የሚያህል ድንጋይ ይዞ እግሯ ላይ ተከመረ።
“ምንድንነው ነገሩ?” አክስቴ አንባረቀች። ሁሉም ገርሞት ሽመልስ ላይ ዓይኑን ተክሏል።
“አክስቴ ይቅር በይኝ፤ ይቅር በይኝ” ድንጋዩን አስቀምጦ እግሯን አንቆ ያዘ።
“ምንድነው ነገሩ? ጤናም አልያዘኽ? ምኑን ነው ይቅር የምልህ? ኧረ! ይሄ ልጅ አንድ በሉልኝ …” አክስቴ ቆጣ ማለት ጀመረች።
ሁሉም በጥያቄ ያጣድፈው ጀመር፤ ምንድነው? ምን አድርገሃል? አባባ ተነስተው ጎኑን በምርኩዛቸው ጎንተል አደረጉት። ተናደዋል። “ምንድንነው ያደረግኸው? አትናገርም?”
ሽመልስ ይሄን ጊዜ ተነስቶ ቆመ። ፊቱ ፀሐይ ወጥቶ የሚዘንብ ቀን መስሏል። ሳቅም ድንጋጤም ይዞታል።
“ምንድነው ምን አድርገኻል?” የአክስቴ የግንባር ቆዳ ተሰበሰበ።
“ጠዋት …”
“እ … ጠዋት”
“እማማ ደብሬ”
“እ … እማማ ደብሬ ትናገር እንደሆን ተናገር” አክስቴ ይበልጥ ተናደደች።
“እማማ ደብሬ አልመጡም።”
“ታድያ! ማነው እንደዛ ይለፈልፍ የነበረው? እኔ ነኝ እንዳትለኝ ብቻ” አክስቴ አፏን ይዛ ዓይኗን አፈጠጠች።
“አዎን! እኔ ነኝ አክስትዬ ይቅርታ አድርጊልኝ” እንደገና እግሯን አንቆ ያዘ። ሁሉም ሳቁን ለቀቀው አክስቴ እንደመሳቅ እያለች ከእግሯ ላይ ካነሳችው በኋላ እጁን ቀጨም አድርጋ ይዛ “እስቲ እንደጠዋቱ ተናገር” አለችው።
ሽመልስ በአንድ እጁ ጉሮሮውን ይዞ ድምፁን አስተካክሎ መናገር ጀመረ፤ “ወ/ሮ እጅጋየሁ እንደምን አደሩ? ወር ሙሉ ወተቴን ጠጥተው ገንዘቤን ያላኩልኝ ምን ሆነው ነው? ምነው ነውር እማይደል …?”
ጠዋት የተሰማው የደብሪቱ ድምፅ በድጋሚ ግቢውን ሞላው።
(Photo: ILRI – ወ/ሮ ደብሪቱ አይደሉም)

በኬንያ አልሸባብ አሸባሪዎችና ሳምንታ የተባለች እንግሊዛዊት

ኬንያ፤ በመዲናዋ በናይሮቢ ዌስትጌት በተባለው ግዙፍ የገበያ ህንጻ ውስጥ ፣ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ በሶማልያው አልሸባብ የአሸባሪዎች ቡድን፤ ቢያንስ 72 ሰዎች ከተገደሉ ወዲህ ፣የ 67ቱ ሰለባዎች የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጽሟል ። የ3 ቀን የኀዘን ጊዜም ታውጆ ተግባራዊ በመሆን ላይ ሳለ፣ የዩናይትድ እስቴትስ፤ የብሪታንያ፤ የእስራኤልና የሌሎችም ጠበብት ከኬንያ የምርመራ ጠበብትጋር በመተባበር፤ አደጋው እንዴት ሊሠነዘር እንደቻለ በማጣራት ላይ መሆናቸው ታውቋል። 40 ሚሊዮን ኑዋሪዎች ባሏት ኬንያ የሙስሊሞች ቁጥር 10 ከመቶ ገደማ ሲሆን፣ ተገቢ ቁጥጥር በማይደረግበት ድንበር፤ ሠርገው የሚገቡ የአልሸባብ ታጣቂዎች ከአንዳንድ ኬንያውያን የእምነት ተጋሪዎቻቸው ድጋፍ እንዳልተለያቸው ተነግሯል። አልሸባብ ፤ ሶማሌዎችን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ሃገራት ተወላጆችንም ማሰለፉ ይነገርለታል። ከእነዚህም አንዷ ሳምንታ የተባለችው እንግሊዛዊት መሆኗ ታውቋል። ይህች ሴትዮ እንዴት በሽብር ተግባር ለመሰማራት ተነሳሳች? የለንደኑን ዘጋቢያችንን ድል ነሣ ጌታነህን በስልክ ጠይቄው ነበር።

የአንድነት አመራር አባላት ጊዜያዊ እገታ(DW)

ንድነት ለዲሞክራሲ እና ፍትህ ዓመራር አባላት የፊታችን እሁድ አዲስ ኣበባ ላይ ለጠሩት ሰልፍ ቅስቀሳ ለማድረግ እንዳልቻሉ ስታወቁ በኢትዮጵያ ፓርላማ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑትን አቶ ግርማ ሰይፉን ጨምሮ የፓርቲው ዓመራሮች ዛሬ ለተወሰኑ ሰዓታት በፓሊሶች ታግተው መለቀቃቸውን ፓርቲው አስታውቋል 

የፓርቲው ሊቀመንበር  ነጋሶ ጊዳዳም ከትናንት በስቲያ በተመሳሳይ ሁኔታ ታግተው መለቀቃቸው ይታወሳል በኢትዮጵያፓርላማ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ እና አኣንድነት ለዲሞክራሲ እና ፍትህ ፓርቲ ከፍተና ዓመራር አቶ ግርማ ሰይፉዛሬ ከታገቱበት የአራዳ ከተማፓሊሲ መምርያ ሆነው በእልክ ለዶቸቤሌ እንደገለጹት እሳቸውን ጨምሮ ኣጠቃላይ የፓርቲውዓመራሮች እና ለቅስቀሳየተሰማሩ አባላቱ ባይታሰሩም በእሳቸው ኣባባል ታግተዋል አቶ ግርማእንደሚሉት በኣሰራር ሰላማዊሰልፉ ተከልክለዋል በሰበብ ኣስባቡ ሌላ ጊዜ ሌላ ቦታ እየተባለ ግን ይነገራቸዋል ምክኒያታቸው ደግሞ የቅስቀሳ ፈቃድ የላችሁም የሚል ነው የቅስቀሳ ፈቃድ በራሱ ህገወጥ ነው ያሉት አቶ ግርማ ሰይፉ ፈቃዱንም ለማምጣት ፈቃድ ሰጪውም ሆነ የሚሰጥበት ቦታምኣይታወቅምብለዋል።
ይሁን እንጂ ፖሊስ የቅስቀሳ ቡድኑንም ሆነ የፓርቲውን ዓመራሮች ከማዋከብ ኣልታቀበም ያለመያዝ መብት ያላቸው አቶ ግርማ ሰይፉም ጭምር ከእገታውአላመለጡም አቶ ግርማ እንደሚሉት ኣሁን የተያዘው ነገር እገታ ነው እሰሩን ብንልም ፈቃደና ኣይደሉም የሚሉት አቶ ግርማ ለጊዜው ቡድኑን በማገት እንቅስቃሴውን ማስተጎጎል ነው የተፈለገው ብለዋል  በኣጠቃላይ ይላሉ አቶ ግርማ ሰይፉ የዚህ ዓይነቱ ኣሰራር በሰላማዊ መንገድ ለሚንቀሳቀሱት ኃይሎች በር እየዘጋ በህገ ወጥ መንገድለመታገል ለመረጡ ቡድኖች ጥርጊያ መንገድ ማመቻቸት ነውድምጽ አምስት አቶ ግርማ ሰይፉ በአቶግርማ ሰይፉ መግለጫ መሰረት ዛሬከቀትር በኃላ በሶስት ተሽከርካሪዎች አማካይነት የተሰማራውየቅስቀሳ ቡድን ታግቶ ቅስቀሳውም ተጨናግፈዋል ዓላማውም ሰላማዊ ሰልፉን ማሰናከል ነው ያሉትአቶ ግርማ ሰልፉን በተመለከተ ኣመራሩ ተሰብስቦ ፖለቲካዊ ውሳኔ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል ይህንኑ ኣስመልክተው የበኩላቸውን ምላሽ እንዲሰጡን የኣራዳ ከተማ ፖሊስ መምሪያን በስልክ ለማነጋገር ያደረግነውተደጋጋሚ ሙከራ ኣልተሳካም::

ጃፈር አሊ
ሂሩት መለሰ