FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, November 27, 2014

“የደም ከፈን!”

ኦባንግ ለስዊድኑ ባለሃብት ማስጠንቀቂያ ላኩ

redclothing


የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ ለታዋቂው የስዊድን ጨርቃጨርቅ ዓለምአቀፍ ቸርቻሪ H&M Hennes & Mauritz AB (H&M) ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራአስኪያጅ ካርል ዮሐን ፔርሶን ከህወሃት/ኢህአዴግ ጋር ስለሚያደርገው የንግድ ውል ኩባንያቸው ሊገጥመው ስለሚችል አደጋ ማስጠንቀቂያ ልከዋል፡፡
ሰኞ በዋሽንግተን ዲሲ በተደረገ ሥነ ስርዓት ሚ/ር ፔርሶን የ2014 በንግድ የማያዳላ ተሸላሚ መሆናቸውን አስመልክተው በላኩት ደብዳቤ ላይ ኩባንያቸው በኢትዮጵያ ሊጀምር ያለው የንግድ ስምምነት ፍጹም አድሏዊነት የተሞላበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች እንደተመለከተው H&M ኩባንያ ከኢህአዴግ ጋር ለሚያደርገው ውል ለሸሪክነት የተመረጡት አምስት የአገር ውስጥ ኩባንያዎች ሶስቱ የህወሃት የግል ሃብት የሆነው የኤፈርት አባል ኩባንያዎች መሆናቸውን ኦባንግ በደብዳቤያቸው አሳውቀዋል፡፡ ሌላው ኩባንያ ደግሞ የህወሃት/ኢህአዴግ ቀኝ እጅ የሆኑትና በኢትዮጵያ ውስጥ የፈለጉትን ዓይነት ንግድ ያላንዳች የህግ ገደብ እንዲሁም ተገቢውን ግብር ሳይከፍሉ ንጹህ ትርፍ የሚያጋብሱት የሼኽ መሓመድ ሁሴን አላሙዲ ኩባንያ መሆኑን “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ሜቶ አመልክተዋል፡፡ የአምስተኛው ሸሪክ ኩባንያ ማንነት እስካሁን አልታወቀም፡፡
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) በመርህ ደረጃ ልማት፣ ዕድገት፣ የንግድ ሽርክና፣ ወዘተ የሚደግፍ መሆኑን በደብዳቤው ላይ የተመለከተ ሲሆን ችግር የሚሆነው ግን እንዲህ ያለው ሽርክና በሰብዓዊ መብትና ሌሎች የዜጎችን መብት በመርገጥ በአምባገነንነት ለተቀመጠው የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ዕድሜ ማራዘሚያ የመሆኑ ጉዳይ እንደሆነ ኦባንግ አመልክተዋል፡፡
ለአንድ ወገን (ለአንድ ዘር/ጎሣ) ፍጹም አድሏዊ በሆነ መልኩ “የራሴ” የሚላቸውን እየጠቀመ በሥልጣን ከቆየው ህወሃት ጋር በንግድ ውል መተሳሰር በመልካም አሠራሩ ለታወቀው እንደ H&M ላለው ኩባንያ ስም ወደፊት ትልቅ ችግር እንደሚፈጥር በደብዳቤው በዝርዝር ተመልክቷል፡፡ ከዚያም ባሻገር በአፍሪካ በሴራሊዮን “የደም አልማዝ” በመውሰድ ራሳቸውን እያበለጸጉ እንዳሉት ሁሉ ከህወሃት ጋር በጨርቃጨርቅ ንግድ ሽርክና መጀመር “የደም ከፈን” እያመረቱ ማትረፍ እንደሆነ በማስጠንቀቅ ኩባንያቸው ሊደርስበት የሚችለውን አስቸጋሪ መዘዝ ኦባንግ በደብዳቤያቸው ላይ ጠቅሰው የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ለባለሃብቱ ሰጥተዋል፡፡
ለሚገዛው ሕዝብ ቅንጣት ታህል ሐዘኔታ የማይሰማው ህወሃት/ኢህአዴግ በፖለቲካው መስክ ፓርላማ ብሎ ባስቀመጠው መሰብሰቢያ 99.6በመቶ መቀመጫውን መቆጣጠሩን፣ አፋኝ የመያድ፣ የጸረ ሽብርተኝነት ወዘተ ሕግጋትን በማውጣት ተቃዋሚዎቼ ናቸው የሚላቸውንን ሁሉ በአሸባሪነት እየከሰሰ ለእስር፣ ለግድያ እና ለስደት እንደሚዳርግ፤ በሰብዓዊ መብት ረገጣ በተደጋጋሚ የተወነጀለ መሆኑን፣ ወዘተ ማስረጃዎችን በመጥቀስ አቶ ኦባንግ አስረድተዋል፡፡ ለማስታወስም ያህልም በኦጋዴን ክልል በጋዜጠኛነት ተሰማርተው የነበሩት ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞች 438 ቀናት ታስረው ቢፈቱም በጸረ አሸባሪነት ሕጉ 11ዓመት ተፈርዶባቸው እንደነበር በመግለጽ የጋራ ንቅናቄው ዋና ዳይሬክተር የኢህአዴግን የጭከና አገዛዝ ሊዘነጋ የማይገባ መሆኑን ለስዊድኑ ባለሃብት አስገንዝበዋል፡፡
ኩባንያቸው ሽርክና የሚያደርግባቸው ኤፈርትና የአላሙዲን ድርጅቶች የሰራተኛ መብቶችን በመርገጥ፣ የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቦታ በግዳጅ በመንጠቅ፣ የዜጎችን ጉልበት ያለ አግባብ በመበዝበዝ፣ በሙስና የተጨማለቀና አድሏዊ አሰራር በመከተል፣ ወዘተ ተነግሮ የማያልቅ ግፍ የፈጸሙና እስካሁንም እየፈጸሙ ያሉ በመሆናቸው በተለይ ለሴቶች “የሥራ ዕድል” ይከፍታል የተባለው የኩባንያቸው ኢንቨስትመንት በምስኪን እና ደጋፊ አልባ ኢትዮጵያውያን ደም የዓለምን ሕዝብ የዲዛይነር ጨርቃጨርቅ ሳይሆን “የደም ከፈን” ለማልበስ መዘጋጀቱ ሊያስቡበትና ሊጠነቀቁበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን በጥብቅ በማሳሰብ የጋራ ንቅናቄው ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ ደብዳቤያቸውን አጠናቀዋል፡፡
የደብዳቤው ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ይነበባል፡፡

 Open Letter to Mr. Karl Johan Persson, Winner of 2014 Fairness Award Faces Significant Challenges in Partnering with Autocratic and Corrupt Ethiopian Government-Controlled Businesses
Head Office
H & M Hennes & Mauritz AB
Mäster Samuelsgatan 46A
SE-106 38 Stockholm
SWEDEN
Dear Mr. Karl Johan Persson,
On behalf of the Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE) and the Ethiopian people we represent, I extend my warmest congratulations regarding the upcoming event at the Historic Howard Theatre in Washington D.C. on November 24, 2014 when you will receive the 2014 Fairness Award given by the Global Fairness Initiative (GFI) along with Mr. Robert B. Zoellick, former president of the World Bank Group (2007-2012) and Ms. Nani Zulminarni, Founder of Perempuan Kepala Keluarga (PEKKA), Indonesia.
This is no small accomplishment. According to the Fairness Award website, this award honors “exceptional leaders whose work and life have opened opportunity and access for poor and marginalized communities. By honoring these outstanding individuals, GFI hopes to inspire a new generation of leaders to dedicate themselves to economic justice, fairness, and equality.”[i] As a Swedish businessman, and President and CEO of one of the largest global fashion retailers, H&M Hennes & Mauritz AB, we can see how you have combined value-based business practices with great success.
The reason for this letter is to express our deep concerns regarding a recently announced business venture H&M is planning in Ethiopia. H&M, with venture capital provided through a Swedish State-run group, Swedfund[ii], has announced a decision to invest in cotton projects within Ethiopia. Reportedly, it will involve partnering with five different companies in Ethiopia, three of which are members of the business conglomerate, EFFORT, which is essentially owned by the Tigrayan Peoples’ Liberation Front (TPLF), the controlling party of the Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front (EPRDF). Although the EPRDF is said to be a coalition government representing four of the nine ethnic-based regions of Ethiopia, the TPLF is recognized to be in charge. In other words, Ethiopia, with 86 different ethnic groups, is ruled by an ethnic-based minority party making up only 6% of the population. This has been the case since 1991.
The fourth company is owned by Saudi Arabian-Ethiopian businessman and billionaire, Sheik Mohammed al Amoudi, who is known as the right hand of the TPLF/EPRDF government. He has profited immensely from that association and in doing so, has been complicit in violating the rights of other Ethiopians. The identity of the fifth company is not yet known.
For your information, I am the Executive Director of the SMNE, a non-violent, non-political, grassroots social justice movement of diverse Ethiopians; committed to bringing truth, justice, freedom, equality, reconciliation, accountability and respect for human and civil rights to the people of Ethiopia and beyond. The SMNE was founded to build a better future for the people and is based on the belief that the future well being of our global society rests in the hands of those among us who can put “humanity before ethnicity,” or any other distinctions that divide and dehumanize other human beings from ourselves; inspiring us to care about these “others;” not only because of the intrinsic God-given value of each life, but also because “none of us will be free until all are free.”
In regards to H&M’s business interests in Ethiopia, we want to make it clear that the SMNE strongly supports business development, partnerships, and private and foreign investment in the country, believing that if Ethiopians are going to more widely prosper and increase food security to its growing population, a strong, market-driven economy is essential; however, what exists today is crony capitalism, the exploitation of the land, national assets, and resources of Ethiopians, and a brutal crackdown on the human and civil rights of the majority.
After reviewing the stated values and goals of H&M and Swedfund, which strongly affirm economic justice, fairness, respect, ethical behavior, inclusion, embracing diversity, a commitment to the protection of human rights, a zero tolerance policy on corruption—including bribery, gifts, and favors, integrity, transparency, honesty, equality, avoidance of conflicts of interest, following the law at all times, and striving for sustainability, we are in full agreement with them.
We believe H&M and Swedfund can provide an excellent model for doing mutually beneficial business in Ethiopia. However, we want to strongly caution H&M and Swedfund that the business climate is inseparable from the complete domination of the current corrupt regime and their friends and cronies. As the winner of the Fairness Award and as a business with high ethical standards, you will face significant challenges in partnering with Ethiopian government-controlled businesses. We believe it is critically important to your long-term success to know this in advance. Companies of high repute can unwittingly damage their reputations by acts of their partners. 
For example, in December 2003, Ethiopian National Defense Forces, along with militia’s they equipped, targeted my own indigenous ethnic group, the Anuak, massacring 424 of the most educated leaders within three days. Over the next several years, nearly two thousand others were killed, many others were beaten, arrested and tortured, thousands more fled to other countries. Much of the limited infrastructure in this marginalized Gambella region of southwestern Ethiopia was destroyed. The goal was to eliminate resistance to the extraction of possible oil reserves in the region. None was found, but companies involved in that effort were complicit in turning a blind eye to what was going on.
In Sierra Leone, the same thing happened in the extraction of diamonds, creating the name, blood diamondsWe seek to warn you of the risk of association with the TPLF/EPRDF regime, known for its ruthless treatment of its people so the legacy of H&M will not be associated with the blood and suffering of the Ethiopian people as these examples point out. This is a ethnic apartheid regime that does not care about the well being of all its own people. As a result, your goal of creating a business that benefits both the people of Ethiopia and H&M; that reduces poverty, enfranchises informal communities and advances human rights and livelihoods, as stated as GFI’s mission goal, will be challenged at every juncture for those doing business in Ethiopia under the egocentric control of this regime. This will be keenly felt by those, like yourself, who has a proven track-record of high standards in regards to business practice.
The only access into the economic structures of Ethiopia comes through close association and loyalty to the TPLF/EPRDF. All others are excluded, including the majority of people of Ethiopia. The impressive double-digit economic growth figures claimed by the Ethiopian government are not only questionable, but to the degree there is growth, that growth has gone into the pockets of the TPLF/EPRDF elite. Additionally, massive amounts of illicit capital leakage have ensured little improvement in the quality of life for the people.
Working in Ethiopia will present enormous challenges to H&M. I am not simply talking about the lack of infrastructure—roads, transportation, electricity, communication technology and even running water; neither are we talking about the challenges of undeveloped land, the abundance or lack of water, navigating through a maze of unfamiliar bureaucracy, or adjusting to working in a country of many different cultures, languages and geographical differences. Instead, I am talking about a conflict of values when H&M attempts to work with a regime whose goals, objectives and practices are in complete contradiction to most every ideal espoused by H&M—despite any deceptive rhetoric you might hear to the contrary.
The Public Image of Ethiopia versus the Ethiopia known by Ethiopians:
As a social justice organization that cares for the well being of the Ethiopian people, our concern is that the partners H&M has chosen are part of an autocratic regime representing the interests of a small minority at the top, most all coming from one ethnicity which does not even represent many of their own people. In the last flawed election, the highly unpopular TPLF/EPRDF party claimed to capture 99.6% of the total vote. Only one of the 547 seats in Parliament was taken by an opposition member. That member is allowed only 3 minutes of debate on any issue. As the next national election in May of 2015 looms ahead, the ruling regime has eliminated any political space. People are denied freedom of expression, freedom of association, and freedom of assembly.
Civil society has been decimated by using a law, the Charities and Societies Proclamation[iii] (CSO) which has closed over 2,600 civic organizations within Ethiopia. Those that currently exist are arms of the regime. The CSO law includes serious criminal consequences for any who advance human rights or rights for children, for women, or for the disabled if the organization has received over 10% of its funding from foreign sources. Similarly, it outlaws conflict resolution between ethnicities or religious groups or democratic advancement under the same criteria.
All sectors of society are controlled by the ruling party. (Please see link for examples.)This includes the media, public and private institutions, the military, federal and local security and police, the justice system, the educational system, the financial system—including access to loans, access to business opportunities, customs, taxes, and government jobs. Entry into any opportunity is blocked unless the doors are opened based on ethnicity (TPLF-Tigre), party membership (EPRDF) and loyalty to the ruling party. Human rights organizations have documented the politicization of humanitarian aid and services. This all has caused significant resentment and increasing tensions between the majority and the TPLF/EPRDF. Access to the Internet is controlled and websites are blocked. Landline phones and mobile phone usage is among the lowest in all of Africa due to a fear of what communication and technology might incite within its disenfranchised and repressed population.
Ethiopian laws are used to repress resistance rather than to protect the people. For example an anti-terrorism law, enacted in 2009, has been used to criminalize dissent, leading to Ethiopia being the second highest jailer of journalists in Africa, only topped by its neighbor, Eritrea. Numbers of Ethiopia’s most courageous voices of freedom languish behind bars, many victims of torture. Think of the arrest and long detention (438 days) oftwo Swedish journalists, Martin Schibbye and Johan Persson who were sentenced under the anti-terrorism law to 11 years in prison for documenting human rights abuses.
We realize you understand the repression of information and criminalization of journalists who report the truth due to H&M’s substantial donations to Civil Rights Defenders, a non-profit to uphold the human rights of people across the world. This organization wrote a letter to Prime Minister Hailemariam Desalegn regarding the recent jailing of Zone9 bloggers. One of those bloggers, Soleyana Shimeles, who was charged in absentia, was recently a guest of the SMNE at a forum we held in Washington D.C., Breaking the Cycle of Dysfunction in Ethiopian Institutions.
The ethnic apartheid regime of TPLF/EPRDF is also well known for its widespread, serial human rights abuses, its displacement of indigenous people from their land without consultation or compensation, and their absolute impunity from the courts they control for crimes committed. For example, Ethiopia has become a destination for those wanting to lease cheap agricultural land with access to water under long-term contracts. The people who live on the land are described in some of those contracts as impedimentsto be removedLarge scale land grabs have forced hundreds of thousands of small-scale farmers, pastoralists and villagers from land occupied by their families for centuries.
Similar evictions have been forced on city-dwellers throughout the country. When they resist, people have been intimidated, harassed, beaten, raped, arrested, disappeared or killed. Many have fled to refugee camps outside the country.
The TPLF/EPRDF government promised to resettle the displaced people in a villagization project where improved services would be available, but in reality this usually meant the people would have to build their own shelters, find new sources of water—often further away, clear land and replant crops on less fertile land and not find any new or improved services. Poverty and insecurity has increased and many of these people, who used to be self-sufficient, now must depend on food aid.
Our concerns:
  1. Doing business with members of the oppressive TPLF/EPRDF party will further empower and legitimize them, undermining the struggle of the people for freedom, justice and equality.
  2. No safeguards exist, other than empty rhetoric, which will protect the people, many of the most vulnerable; neither are there safeguards in place to protect the environment, already seriously affected, from the TPLF/EPRDF’s abuses, especially in regions where the people have no voice.
  3. This is a country where there is no transparency or accountability. The justice system is controlled from the federal level to the local level by the TPLF/EPRDF. It is used to reward friends of the regime and to fine, charge or impose difficult regulations or corruption charges on individuals and businesses that do not comply or who speak unfavorably towards the regime.
  4. EFFORT businesses account for some 90% of all businesses in Ethiopia.
  5. Sheik Mohammed al Amoudi, owner of Saudi Star Farm in Gambella, is leasing indigenous land to grow rice, most of it for export to Saudi Arabia.  Heavy use of water for irrigation is having an impact down river. Human rights abuses were inflicted in order to force the local people from the land.  Much of the land was forested, leading to clearing it of valuable Shea trees and much more. An incident of violence did erupt on the farm in 2013 between workers and the local people.
  6. A new anti-corruption law is being proposed that may act similarly to the anti-terrorism law in criminalizing any behavior by officials and companies, Ethiopian or foreign, who do not conform to TPLF/EPRDF expectations. This is a regime prone to changing the rules according to their self-serving needs. There is little recourse for outside companies and investors who are in conflict with the TPLF/EPRDF. It is to the regime’s advantage to engage a major company like H&M so they may lay out the red carpet; however, you may also be expected to conform to business practices that are unacceptable to you. Doing business with members of EFFORT is comparable to doing business with an unpredictable authoritarian regime where non-compliance may bring unfair charges or decisions. You are a company with strong values and an excellent reputation. Even though H&M may be willing to risk your capital, you may need to think twice before working with the TPLF/EPRDF, which may put your good reputation at risk.
We in the SMNE, with the help of the people, hope to correct these unfavorable business conditions through meaningful reforms, the restoration of justice and through reconciliation in order to build a more inclusive society for the people of Ethiopia.
If you want to invest in Ethiopia, we would welcome you, but urge you to look for long-term, sustainable partnerships where the rights and livelihoods of the people are upheld and where H&M can bring an outstanding model of how to do ethical, inclusive and profitable business in Ethiopia. This would be a real win-win solution for all of us!
If you do choose to go forward with your present plans, we genuinely hope that honorable companies like H&M will be a force for change for the common good of the people in countries of repression like Ethiopia—for our humanity has no boundaries. That means refusing to overlook the injustice; standing strong and firm in upholding all your values to the great benefit of the voiceless.
Please feel free to contact me should you have further questions, suggestions or comments.
Sincerely yours,
Obang Metho,
Executive Director SMNE
910- 17th St. NW, Suite 419.
Washington, DC 20006 USA
Phone 202 725-1616
Email: obang@solidaritymovement.org
Website: www.solidaritymovement.org

[ii] Swedfund, owned by the Swedish state, provides risk capital, expertise and financial support for investments in the emerging markets of Africa, Asia, Latin America and Eastern Europe. Our mission is poverty reduction through sustainable business, contributing to economic and environmental development as well as a positive impact to society. Since 1979 Swedfund has been engaged as an active, responsible and long-term investor in more than 230 companies in our countries of operation.
[iii] A repressive 2009 law against civil society, the Charities and Societies Proclamation now prohibits any organization that receives more than 10% of its budget from foreign sources from (a) advancing human and democratic rights, (b) promoting equality of nations, nationalities, peoples, gender and religion, (c) promoting the rights of the disabled and children, (d) promoting conflict resolution or reconciliation and, (e) promoting the efficiency of justice and law enforcement services. This has meant the closure of most every independent civic organization. In their place, the regime has created pseudo-organizations controlled by the regime, oftentimes appearing legitimate to outsiders. The law carries harsh criminal penalties for violators. It is used for political purposes and has paralyzed civil society. In its place, look-alike pseudo-institutions have sprung up, all created and controlled by the government.
Other articles:
http://www.goolgule.com/blood-cotton-open-letter-to-karl-johan-persson-of-hm/

Wednesday, November 12, 2014

ኢትዮጵያ የመብት ጥሰት እንድታቆም መጠየቁ

ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ላይ የምትፈጽመውን ጥሰት ካላቆመች የአፍሪካ ህብረት መቀመጫውን ከአዲስ አበባ መቀየር አለበት ተባለ። በደቡብ አፍሪካ ዊትስ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባኤ ላይ አንጎላዊው ጋዜጠኛ ራፋኤል ማርኩዌዝ ደ ሞራይዝ የኢትዮጵያ መንግስት ያሰራቸውን ጋዜጠኞች መፍታት አለበት ብሏል።

Rafael Marques
ራፋኤል ማርኩዌዝ ደ ሞራይዝ አንጎላዊ ጋዜጠኛ ነው። በሙያው በሃገሩ አንጎላ በርካታ ክስ እና እስር እንደገጠመው ይነገራል። ባለፈው ወር በደቡብ አፍሪካ ዊትስ በተካሄደው የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽን ጨምሮ በሰብዓዊ መብቶች ላይ ጥሰት በመፈጸም ከአፍሪካ ህብረት ህልም በተቃራኒ ቆማለች በማለት ተችቷል። ''የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በቀዳሚነት የመላ አፍሪካውያንን ህልም ይወክላል። የሰው ልጅ ክብር እና የሰብዓዊ መብት ክብር ደግሞ የሁሉም አፍሪካውያን የጋራ ህልም ነው። ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ የሰዎችን ሰብዓዊ መብት በመጣስ በተቃራኒው መንገድ እየተጓዘች ነው። ይህ ደግሞ የአፍሪካውያንን ህልም አይወክልም። የኢትዮጵያ መንግስት ያሰራቸውን ጋዜጠኞች በመፍታት ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ነጻነትን እንዲያከብር እና ዜጎች እና ጋዜጠኞች ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን በተግባር እንዲያውሉ እንዲፈቅድ የአፍሪካ ህብረት ጫና ማድረግ ይኖርበታል። ''

Neuer Hauptsitz der Afrikanischen Union in Addis Abbeba

ራፋኤል በጉባኤው የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችን እስር እና ክስ እንዲሁም የቀድሞው ፍትህ ጋዜጣ አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝን የሶስት አመት ብያኔ በማሳያነት አንስቷል። አፍሪካውያን ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በቸልታ አልፈዋል ሲልም ተችቷል። ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብትን ማክበር ካልቻለች የአፍሪካ ህብረት ከአዲስ አበባ መነሳት ይኖርበታል ብሎ ያምናል።
''የተወሰኑ ጋዜጠኞችን አውቃለሁ። በ2005 ተኩስ ሲጀመር እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ሲታሰሩ በአዲስ አበባ ነበርኩ። አሁን በሃገሪቱ ስላለው ሁኔታ በቂ ግንዛቤ አለኝ። ከኢትዮጵያውያን ምሁራን እና አሁን ባለው መንግስት የተለያየ ጫና የደረሰባቸውን ሰዎች አገኛለሁ። የአፍሪካ ህብረትን ለመወከል በመጀመሪያ ሰብዓዊ መብትን የሚያከብር ሃገር እንፈልጋለን። ኢትዮጵያ ይህንን ማድረግ ካልቻለች እንደ አፍሪካዊነታችን የአፍሪካ ህብረት መቀመጫውን ዜጎች ራሳቸውን የመግለጽ እና ሰብዓዊ መብት ወደ ተከበረበት ሃገር እንዲዛወር መጠየቅ ይኖርብናል። ምክንያቱም ግለሰቦች የሚከበሩባት መንግስታት የህዝብ አገልጋይ እንጂ ከህግ በላይ ያልሆኑባት አጋርነት የጠነከረባት አፍሪካን እንሻለን። ኢትዮጵያ ደግሞ በአሁኑ ወቅት ይህን እያደረገች አይደለም። ''''

Symbolbild Zeitungen in Ketten

ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ባለፈው ሳምንት ባወጣው ዘገባ ባለፈው አመት ብቻ በኢትዮጵያ ስድስት የህትመት ውጤቶች ሲዘጉ ከ ሰላሳ በላይ ጋዜጠኞች መሰደዳቸውን ይፋ አድርጓል። በምህጻሩ ሲፒጄ ተብሎ በሚጠራው የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ተቋም መሰረት ደግሞ ቢያንስ 17 ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ በእስር ላይ ይገኛሉ። ራፋኤል ማርኩዌዝ በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ አፍሪካውያን ሊተባበሩ ይገባል ሲል ይናገራል።
''አፍሪካውያን በሙሉ በተለይም ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በትብብር ከሰራን የኢትዮጵያ መንግስት ቆም ብሎ ራሱን እንዲፈትሽ ማድረግ እንችላለን። አላማችን ኢትዮጵያን ማግለል አይደለም። አላማችን ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እንድታከብር ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን በመጠቀማቸው የታሰሩትንም እንድትፈታ ነው።''
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሀመድ
http://www.dw.de/%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%89%A5%E1%89%B5-%E1%8C%A5%E1%88%B0%E1%89%B5-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B5%E1%89%B3%E1%89%86%E1%88%9D-%E1%88%98%E1%8C%A0%E1%8B%A8%E1%89%81/a-18051929

Saturday, November 8, 2014

“እኛ”!! እናንተ እነማን ናችሁ? ደረጃ ምደባ!!

(ርዕሰ አንቀጽ)

one 1



ደረጃ ምደባ ለሸቀጥ ወይም ለአንድ ምርት የሚወጣ ማነጻጸሪያ፣ መለያ፣ መተመኛ፣ የጥራት መጠን መለኪያ … ነው። የደረጃ ምደባ ሲከናወን እንደ አቅሚቲም ቢሆን አስፈላጊ የሚባሉ የመመርመሪያ መሳሪያዎች፣ ቤተ መመርመሪያ፣ መርማሪ ባለሙያና ተመርማሪው ሸቀጥ አስፈላጊ ናቸው። የወጉ አሰራር ካለ ማለት ነው።
“እኛ” ሲባል ባጭሩ ከአንድ በላይ ማለት ነው። በሌላ አነጋገር አንድ ብቻውን “እኛ” ሊባልም ሆነ እኛ ብሎ ራሱን ሊጠራ አይቻለውም። ስለዚህ “እኛ” የወል፣ የስብስብ ወይም የጋራነት መለያ ከሆነ፣ አንድ ሆኖ “እኛ” የሚል ተቀባይነት የለውም። አሁንም ባጭሩ የከሸፈ አስተሳሰብ ነው። የከሸፈ ብቻ ሳይሆን የሚያከሽፍም ነው። በነጠላነት ውስጥ ያለው “እኛ” ነት በርካቶችን አክሽፏል፤ አሸማቋል። አሁን ባለው አያያዝ ጉዳቱ ወደ “ውድቀት ህዳሴ” እያንደረደረ ነው። ግን ፍሬን ሊያዝበትና እንድርድሩ ሊገታ ይችላል።
ኢህአዴግ የሚባለው አገዛዝ፣ አብዛኞች ተቃዋሚዎች “መንግሥት” እያሉ የሚጠሩት፣ እኔ ያላቀድኩት፣ እኔ ያልተለምኩት፣ እኔ ያላወጅኩት ሁሉ “ቀሳፊ ተስቦ ነው” በሚል መስማት ከተሳነው 23 ዓመት ሆኖታል። ጆሮው ስለተዘጋና ልቡናው “ያለ እኔ” በሚል የእብሪት ስብ ስለተደፈነ “ወደብ ያስፈልግሃል” እንኳን ሲባል ላለመስማት ደንቁሮ ነበር። ዛሬ ወደብ ላላቸው አገር ጥሪት እያባከነና ሰግዶ እያሰገደን ያለው ኢህአዴግ እሱ ያላለማው ልማት ውድመት ነው። እሱ ያልተዋጋው ጦርነት ሁሉ ጭፍጨፋ ነው። እሱ ያላቦካው ዳቦና እንጀራ አይሆንም። እሱ እውቅና ያልሰጠው ህዝብ ህዝብ አይደለም። እሱ ያልባረከው ሚዲያ ጸረ ህዝብ ነው። እሱ ያላካለለው ወሰን የአድሃሪያን ትምክህት ነው። ይህ ለእርሱና ለሚያሳድራቸው ቢሆን አይገርምም። የሚያስገርመውና የሚያሳዝነው እሱ የሁሉም ነገር አባት፣ መሪና ፈጣሪ መሆኑንን የመቃወም የልዩነት ተፈጥሮ መብት እንኳን አይፈቅድም። የሚቃወሙት ሁሉ አሸባሪ እንዲባሉ በዲዳው ሸንጎ ማስወሰኑ ሌላው ቅሌት ነው። ግብዓት በሌለበት ደረጃ ምደባ!! ክሽፈት ማለት ይህ ነው።
በተቃዋሚ ሰፈርም ተመሳሳይነት አለ። ያገር ቤቱን እንኳ ብንተወው ነጻነት አለበት በሚባልበት አገር ያለው ሚዲያ መረጃ ለማሰራጨት የሚደረገው ጥረት የሚበረታታና ድጋፍ የሚያሻው ቢሆንም የሚጠበቅበትን እየሰራ ነው ለማለት አይቻልም። እኛን ጨምሮ። ተሸብበናል፤ ፈርተናል። በርካታ የሚያነጋግሩና ህዝብ በነጻነት የሚወያይባቸው ጉዳዮች እያሉ ቀድቶ በመለጠፍ (ኮፒ/ፔስት) ሥራ ተወጥረናል፤ ይህ ለሰው ሥራ ዕውቅና ሳይሰጡ የሚፈጸም ተግባር ሙያዊ ጋዜጠኝነት ሳይሆን “የዘረፋ ጋዜጠኛነት” ነው። ከመርህ አንጻር መደገፍና፣ ለሚደግፉት ሃሳብ ልዩ ትኩረት መስጠት አግባብ ቢሆንም ብዙም የተኬደበት ግን አይደለም። በግል የጎልጉል ድረገጽ ጋዜጣ በመርህ ደረጃ ከሚያራምደው ዓላማ አንጻር በተደጋጋሚ ወቀሳ ደርሶብናል። ይህ የተደረገው በግልጽ ዓላማችንን በማስቀደማችን ለማስጠንቅቅም ጭምር ነው።
ወቀሳዎቹ ከላይ እንዳልነው “እኛ” ሲሉ የዲያስፖራውን ማህበረሰብ የመወከል ስልጣን ለራሳቸው የሰጡ የሚሰነዝሩት ነው። እንደ ኢህአዴግ “ዲዳው ሸንጎ” በስብሰባ ያስወስኑት መቼና የት እንደሆነ በግልጽ ባይታወቅም “እኛ የዲያስፖራው ማኅበረሰብ” በሚል የማግለል አሠራር ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ቅልጥ ያለ ወያኔ ተደርጎ ተወስዷል። ፍትህን ለሚያጎናጽፍ የእርቅ ሃሳብና እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉና በይፋ ድጋፍ መስጠታችን “የወያኔን እድሜ አራዛሚዎች” በሚል እንድንዘለፍ አድርጎናል
ከመርሃችን አፋፍ ላይ ቆመን ለምናወጣቸው ዘገባዎችም ሆነ በስማቸው ባደባባይ አስተያየት የሚልኩልንን ስናስተናግድ ሃሳቡ ላይ “እኛ” ሳይባል “እኔ እንደሚመስለኝ” በማለት መሟገት ሲቻል፣ ባልተሰጠ ማንነት “እኛ … ዘራፍ” ማለት ዋጋው አይገባንም። ሰዎች ሃሳባቸውን “እኔ” እያሉ ሲገልጹ፣ “እኛ” በማለት መመለስ ለማስፈራራት የሚደረግ ከንቱ ሙከራ ሆኖ ይሰማናል። “እኛ የዲያስፖራው ማህበረሰብ” በማለት በህግም ይሁን ባገር ሽማግሌዎች ባልተሰጠ ሹመት አንድ ሰው ራሱን በራሱ ሹመኛ አድርጎ የአዋጅ ይዘት ያለው አስተያየት ሲሰጥ ያመናል፤ ይዘገንነናል። “እኛ” ሲባል በ“እኛ” ውስጥ ያልተቆጠሩትስ? ለምሳሌ እኛ ራሳችንስ? በዚሁ በፍርሃቻ ተሸብበው እንደ ከሸፈ ባሩድ ያደፈጡት አብዛኞችስ? ብዙ ብዙ … ዎችስ?!!!
ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ማንም ለማንም የሚለግሰው “ቦነስ” ወይም ገድቦ የሚሰጠው አይደለም። ሃሳባችንን አራግፈውና አብጠርጥረው ለሚተቹን፣ ለሚወቅሱን፣ ለሚያስተምሩን … ወዘተ ሁልጊዜም በራችን ክፍት ነው። የሳይበር ሚዲያውን የተቀላቀልነውም ለዚሁ ነው። በጨዋነት ሃሳብ ላይ መከሳከስ ይቻላል ስንል ባልተሰጠ ውክልና “እኛ” በማለት ደረጃ የመመደብ ሃላፊነትን ተላብሰው “ሊሰፍሩን” የሚፈልጉትን ግን “ኦ! ኦ! ወራጅ አለ እንላለን”። ምክንያቱም አካሄዱ የመናገር፣ ሃሳብን የመግለጽ፣ … ብቻ ሳይሆን የማሰብን ነጻነት ይጋፋል፡፡ ሰውን በራሱ ሃሳብ እንዲፈራና እንዲሸማቀቅ የሚያደርግ እርኩስ ነገር ስለሆነ እንጸየፈዋለን፡፡
አሁንም ደግመን ደጋግመን ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የእኛ ሳይሆን የናንተ መሆኑንን እንገልጻለን። ፍትህን ሊያመጣ የሚችል እርቅ አሁንም በመርህ ደረጃ የምንደገፈው፣ ማንም የማይሸልመን፣ ማንም የማይወሰድብን ፈርጥ ሃሳባችን መሆኑንን አበክረን እናስታውቃለን። ማንም በ“እኛ አልደገፍነውም” የማግለያ ማስፈራሪያ ሊነጥቀን የማይችል ዕንቋችን ነው፡፡ ሃሳብን በሃሳብ የመጣላትና የመማማር ልምድ እንዲመጣ እንመኛለን። በሃሳብ መከራከር ጠላትነት እንዳልሆነ ከሚያምኑ ጋር በህብረት እንሰራለን። በሃሳብ ተለያይቶ በመከባበር አብሮ መስራት የሚችል ትውልድ እንዲነሳ የበኩላችንን እናበረክታለን። ከጎናችን ሁኑ። ጻፉ፣ ተናገሩ፣ አስተያየት ስጡ፣ “እኛ” ግን አትበሉ። እኛ ለመሆን ተደራጁና በድርጅት ስም ተንፍሱ!! አለበለዚያ “እናንተ እነማን ናችሁ” ይመጣልና!!
http://www.goolgule.com/who-is-us-and-who-sets-the-standards/

የሰላም ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ ታሰረ

የሰላምና የዕርቅ ሃሳብ መስበኩ "ወንጀል" ሆኖበታል

fantahun berhanu



ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማስተባበርና በማቀራረብ እርቅ ለማስፈን እንደሚንቀሳቀስ የሚነገርለት የመግባባት፣ አንድነትና ሰላም (ሰላም) ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ መታሰሩን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አቶ ፋንታሁን የታሰረው ‹‹የሰላም ጥሪ›› በሚል ነጭ ሰንደቅ አላማ በማውለብለብና የማህበሩን አላማ የሚገልጹ፣ እንዲሁም ማህበሩ በአሁኑ ወቅት ለአገሪቱ ችግር የሚላቸውን ጉዳዮች በዝርዝር የያዘ በራሪ ወረቀት ለህዝብ በመበተን ማህበሩን በማስተዋወቅ ላይ በነበረበት ጊዜ እንደሆነ ታውቋል፡፡
በራሪ ወረቀቱ የህሊና እስረኞች መፈታት እንዳለባቸው፣ መንግስት በሀይማኖቶች ላይ ጣልቃ መግባት እንደሌለበት፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ዜጎችን ማፈናቀሉ እንዲቆምና መንግስት በተቋማት ላይ ከሚያደርገው ጣልቃ ገብነት እንዲቆጠብ የሚመክሩ ሀሳቦች እንዳሉበት ለማወቅ ተችሏል፡፡
ነጭ ሰንደቅ አላማ ሲያውረበልብ፣ የማህበሩን አላማና በህዝብ ላይ አሉ ያላቸውን ችግሮች ለህዝብ ሲያስተዋወቅ የተያዘው አቶ ፋንታሁን ህዝብን ለማነሳሳትና አመጽ ለመቀስቀስ ሙከራ በማድረግ በሚል እንደተከሰሰም ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
አቶ ፋንታሁን እሁድ ጥቅምት 23 ሽሮ ሜዳ አካባቢ በራሪ ወረቀት ሲበትን ተይዞ ላዛሪስት በሚባለው ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ (ምንጭ እና ፎቶ: ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia)
http://www.goolgule.com/selam-association-leader-fantahun-berhanu-arrested/

Tuesday, November 4, 2014

“ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ” የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፕሮግራሙን ይፋ አደረገ

የ24 ሰዓት (የአዳር) የተቃውሞ ሰልፍ ተጠርቷል

9 parties



ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም 9 ተቃዋሚ ፓርቲዎች የመሰረቱት ትብብር “ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ” በሚል ለአንድ ወር የሚቆይ የመጀመሪያ ዙር የህዝባዊ ትግል ፕሮግራሙን ዛሬ ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ይፋ አደረገ፡፡
“ነጻነት በሌለበት ፍትሃዊ ምርጫ የማይታሰብ በመሆኑ የተዘጋውን በር ለመክፈት የ‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ› በሚል የፕሮግራም መርሃ ግብር ለመክፈት ወስኖ የመጀመሪያው ዙር እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ” እንዳዘጋጀ ያሳወቀው ትብብሩ የትግሉ ዓላማ ፍትሃዊ ምርጫ እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን ገልጾአል፡፡
“ምርጫ ቦርድ ለገዥው ፓርቲ ያለውን ወገናዊነትና ጉዳይ አስፈጻሚነት ፍንትው አድርጎ አሳይቷል” ያለው መግለጫው በመጀመሪያ ዙር የአንድ ወር ፕሮግራሙ 6 ዋና ዋና ተግባራትን ለመፈጸም ዝርዝር እቅዶችን አውጥቶ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡ በህዳር ወር የሚያከናውናቸው ተግባራትም፡-
1. በቤተ እምነት ጸሎት እንዲደረግና ጥሪ ማቅረብና አማኞች እንደየ እምነታቸው ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማድረግ
2. የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማድረግ
3. የተቃውሞ ድምጽ ማሰማት (ሰላማዊ ሰልፍ)
4. ለመንግስት ተቋማት ደብዳቤ ማስገባት
5. በምርጫ ዙሪያ የፓናል ውይይቶችን ማድረግና
6. የህዝብን ተሳትፎ ማበረታታትና ድጋፍ ማሰባሰብ እንደሆኑ በመግለጫው አሳውቋል፡፡
ከእቅዶቹ መካከልም በሶስት ተከታታይ እሁዶች በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች 3 የአደባባይ ስብሰባዎች እንደሚኖሩ፣ በመጨረሻው መርሃ ግብርም ህዳር 27ና 28 በፕሮግራሙ ማጠቃለያነት የ24 ሰዓት (የውሎና የአዳር) የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚደረግ የትብብሩ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል፡፡
በገዥው ፓርቲና በምርጫ ቦርድ ጥምረት ይፈጸማል ያለውን ህገ ወጥ ተግባር በመታገል ለሰላማዊ ትግሉ አወንታዊ አስተዋጽኦ ለማበርከት እስከመጨረሻው በፅናት ለመቆም መዘጋጀቱን የገለጸው ትብብሩ በአገር ቤትና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ በትብብሩ ሂደት ቆይተው እስካሁን ያልፈረሙና ሌሎች ፓርቲዎች እና የዓለም አቀፉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡ (በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር)
http://www.goolgule.com/the-9-parties-coalition-made-its-program-official/

መንግስት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ገጥሞታል

1 ዶላር እስከ 22 ብር እየተሸጠ ነው፤"የብርን ዋጋ በቅርቡ ሊወርድ ይችላል"

etb-100-ethiopian-birr


የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደገጠመው የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የብሄራዊ ባንክ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አጥኚ እጥረቱ መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡
ከ20 ቀናት በፊት እያንዳንዱ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የውጭ ምንዛሬ ይሸጥ እንደነበር የተናገሩት ምንጮች፣ ከ20 ቀን ወዲህ ግን በሁሉም የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ማንኛውም አይነት የውጭ ምንዛሬ እንዳይሸጥ በደብዳቤ (circular ዞሯል) ተከልክሏል፡፡
በመሆኑም አሁን ላይ ዜጎች በውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደተቸገሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ “በተለየ ሁኔታ የሚሸጥላቸው ሰዎች ከጉዞ ወኪላቸውና ከበላይ አካል ይዘውት በሚመጡት ደብዳቤ መሰረት ብቻ ነው ምንዛሬ ሊያገኙ የሚችሉት፡፡ ከዚህ ውጭ ግን እንደበፊቱ ማንም የውጭ ምንዛሬ ማግኘት አይችልም” ሲል አንድ የንግድ ባንክ ሰራተኛ ገልጾዋል፡፡
የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ የተከሰተው በዶላር ምንዛሬ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የውጭ ምንዛሬዎች ላይ መሆኑንም ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ አሁን ላይ አንድ የአሜሪካ ዶላር በጥቁር ገበያ እስከ 22 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሌላ በኩል ከብሄራዊ ባንክ አካባቢ የደረሱት የነገረ ኢትዮጵያ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት መንግስት ቀደም ሲል በIMF የቀረበለትን የብር ዋጋን የመቀነስ “devalue” የማድረግ ጥያቄ መቀበሉ እንደማይቀር ታውቋል፡፡ “አሁን ያለው ሁኔታ እንደሚያሳየን መንግስት የብርን ዋጋ በቅርቡ መቀነሱ አይቀሬ መሆኑን ነው፡፡ አንዳንድ ‘አርቲፊሻል’ የውጭ ምንዛሬ እጥረቶች ቢኖሩም ዋናው የችግሩ መነሻ ግን የብር ዋጋ መቀነሱ ጉዳይ ነው” ሲሉ የብሄራዊ ባንክ የኢኮኖሚ አጥኚው ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድተዋል፡፡
ሰሞኑን መንግስት ለወራት ተከልክሎ የነበረው የአረብ ሀገራት የስራ ጉዞ እንደገና እንዲጀመር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ ይህም ወደ አረብ ሀገራት የሚሄዱ ዜጎች ተጨማሪ ምንዛሬ እንዲያስገኙ ከማሰብ ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል፡፡(ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ)
http://www.goolgule.com/ethiopia-shortage-of-foreign-currency/