FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, December 5, 2014

በአዳር ሰልፉ ኢህአዴግ “ተሸብሯል”

በስውርና በግልጽ አፈናው ተጧጡፏል

police 11


* የከምባታ ጠንባሮ ዞን ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጉ ተገለጸ
* የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ በፖሊስ ተከብቦ አደረ
የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በፖሊስ ተከብቦ ማደሩንና አባላት ከውጭ እንዳይገቡ መደረጋቸውን ለአዳር ሰልፉ ቅስቀሳ ዝግጅት ቢሮ ያደሩ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አመራሮችና አባላቱ እራት በልተው ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት ሲመለሱ ቢሮው በፖሊስ ተከብቦ እንዳገኙትና ወደ ውስጥ እንዳይገቡ እንደተከለከሉ በቦታው የነበሩት የፓርቲው አመራሮችና አባላት ገልጸዋል፡፡
police 14አመራሮችና አባላቱ ፖሊስ ከ200 ሜትር ርቀት ውጭ ወደ ፖለቲካ ፓርቲ ጽ/ቤት መጠጋት እንደማይችል ቢከራከሩም ፖሊሶቹ “መመሪያ ተሰጥቶናል፤ አንሄድም!” ማለታቸው ገልጸዋል፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ከፖሊስ ጋር ሲከራከሩ የአካባቢው ህዝብ በመውጣቱ ፖሊሶቹ ፓርቲው ጽ/ቤት እንደራቁ ታውቋል፡፡
በሌላ በኩል ከውጭ ወደ ቢሮ ከሚመጡበት ወቅት የፓርቲው ቢሮ አካባቢ ምንነቱ ያልታወቀ ወረቀት ተበትኖ እንዳገኙና እነሱ ሲደርሱ ፖሊሶቹ እንዳነሱት የፓርቲው የምክር ቤት አባል ወጣት እየሩስ ተስፋው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡
*********************
በነገረ ኢትዮጵያ የፌስቡክ ገጽ ላይ የታተመው መረጃ እንደሚያመለክተው ፖሊስና ደህንነቶች ወደ ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የሚገቡና የሚወጡ አባላትንና አመራሮችን እያዋከቡ ይገኛሉ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችንና አባላትን “እንፈልጋችኋለን!” በሚል እየያዙ ሲሆን በተለይ ደህንነቶቹ መታወቂያ አሳዩ ሲባሉ ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡
ሰማያዊ ቢሮ ጽ/ቤት የሚገኙ ደህንነቶች የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን እያፈኑ እየወሰዱ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ የሆነውን ፍቅረ ማሪያም አስማማውን አፍነው ወስደውታል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የገዥው ፓርቲ ደህንነቶች ተጨማሪ ሰዎችን አፍነዋል፡፡ የነገረ ኢትዮጵያ ምክትል ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ እና የሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ምክትል ኃላፊ እንዲሁም የብሄራዊ ምክር ቤት ፀኃፊ ወጣት ሳሙኤል አበበ በደህንነቶች ታፍነው መወሰዳቸውን ነገረ ኢትዮጵያ በዚሁ የፌስቡክ ገጹ ዘግቧል፡፡volunteers of 9 parties
ከጥቂት ሰዓታት በፊት የተሰራጨው መረጃ እንደሚያመለክተው የአዳር ሰልፉን የጠሩት የ9ኙ ፓርቲዎች ቢሮ በፌደራል ፖሊስ ተከብቧል፡፡ እንዲሁም የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አባል የሆነው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ቸርቺል የሚገኘው ጽ/ቤት በፌደራል ፖሊስ ተከቧል፡፡ ከሰማያዊ ጽ/ቤት መውጣትም ሆነ መግባት የማይቻል ሲሆን በርካታ አመራርና አባላት ታፍነው ታስረዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የትብብሩ አመራሮች ስልክ እንዳይሰራ እየተደረገ ሲሆን የሰማያዊ ፓርቲና የትብብሩ ሊቀመንበር የኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ስልክ እንዳይሰራ ተደርጓል፡፡
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በተሰራጨ መረጃ መሠረት የሰማያዊ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚ ፀኃፊ የሆነው ወጣት አወቀ ተዘራ ወደ ቤቱ በሚገባበት ወቅት በስርዓቱ የደህንነት ኃይሎች ተይዞ ታስሯል፡፡ ፍቅረማሪያም አስማማው፣ አወቀ ተዘራና ተስፋሁን አለምነህን ጨምሮ በደህንነቶች የታፈኑት ወጣቶች የካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
በተያያዘ ዜና የከምባታ ጠንባሮ ዞን ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጉ ተገለጸ፡፡ በገዥው ፓርቲ አድሏዊ አሰራር ምክንያት ልማትና መልካም አስተዳደር ባለመኖሩ የከንባታ ጠንባሮ ነዋሪዎች ዛሬ ህዳር 26/2007 ዓ.ም ዱራሜ ከተማ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን የከምባታ ህዝብ ኮንግረንስ ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርዲሎ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ህዝብ ያለ ማንም ቀስቃሽና አስተባባሪ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣቱን የገለጹት አቶ ኤርጫፎ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት አከብራለሁ በሚል ለፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያ ከማድረጉ ውጭ በተግባር ግን በህዝብ ላይ ከፍተኛ በደል እየፈጸመ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የከንባታና ጠንባሮ ህዝብ ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ተቃዋሚዎችን በተለይም የከምባታ ህዝብ ኮንግረንስን ትደግፋላችሁ በሚል በደል እንደሚደርስበት የገለጹት አቶ ኤርጫፎ “ህዝቡ በፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት በደል እየደረሰበት ነው፡፡ ምርጫ ሲደርስ መንገድ፣ ዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ ይሰራልሃል ይባላል፡፡ ምርጫው ሲያልፍ ለማታለያነት ይሰራሉ የተባሉ ነገሮች ተግባራዊ አይሆኑም፡፡ እስካሁን ከ1993 ዓ.ም አንስቶ ይሰራል የተባለ መንገድ አልተሰራም፡፡ በምርጫ ወቅት አርሶ አደሮችን እያፈናቀሉ ኮሌጅና ዩኒቨርሲቲ እንሰራለን ይላሉ፡፡ ከምርጫ በኋላ ግን ይህ መሬት የሚሰጠው ለሹመኞች ነው፡፡ ሁለቱም ጠቅላይ ሚኒስትሮች የምርጫ ሰሞን በየቦታው የመሰረት ድንጋይ ተክለዋል፡፡ ከምርጫ በኋላ ግን ለሹመኞች ይሰጣል፡፡ ዛሬ ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣውም ከዚህ አንጻር ነው” ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
የከንባታ ጠንባሮ ህዝብ ባለፉት ምርጫዎች ተቃዋሚዎችን በመምረጥ ከገዥው ፓርቲ ጋር ያለውን ልዩነት በግልጽ እንዳሳየ የገለጹት አቶ ኤርጫፎ “ወጣቶች ልማትና የትምህርት እድል ስለማያገኙ ወደ ደቡብ አፍሪካና አረብ አገራት እየተሰደዱ መንገድ ላይ እየሞቱ ነው፡፡ በቀን 11 አስከሬን የመጣበት ጊዜ አለ፡፡ በስርዓቱ አድሏዊ አሰራር ምክንያት ከንባታ ጠንባሮ ወጣቱ ከቀየው እየተፈናቀለ የሚሰደድበት ትልቁ ዞን ነው ማለት ይቻላል” በማለት አስረድተዋል፡፡
በዛሬው እለት አርሶ አደሩ፣ ተማሪውና ነጋዴው የዞኑ ጽፈት ቤት ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ከማድረጉም ባሻገር በቀጣይነት በየወረዳዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚየደርግ ገልጾአል ሲሉ ሊቀመንበሩ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ (ለመረጃ ጥንቅሩና ለፎቶዎቹ፡ ነገረ ኢትዮጵያ)
http://www.goolgule.com/eprdf-is-terrorized/

የጣሊያን ፖሊስ ሰዉ አስተላላፊዎችን ያዘ

አስሩ የኤርትራ ተወላጆች ከነመሪያቸው ለበርካታ ስደተኞች ሞት ተጠያቂዎች ናቸው

Migrants arriving in Sicily where the people trafficking investigation was launched in May Photo Giovanni Isolino AFP


የጣሊያን ፖሊስ በሕገ-ወጥ መንግድ ወደ አዉሮጳ ያሸጋግራሉ በማለት የተጠረጠሩ 10 የኤርትራ ተወላጆችን በቁጥጥር ሥር አዋለ። የካታኒያ-ሲሲሊ ፖሊስ እንዳስታወቀዉ ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት ስደተኞችን ወደ አዉሮጳ የሚያሸጋግር ሕብረ-ሐገራት መረብ መኖሩን የሚጠቁም መረጃ ከደረሰዉ በኋላ ባደረገዉ አሰሳ ነዉ። በፖሊስ መግለጫ መሠረት ስደተኞቹን የሚያሻግረዉ መረብ ኤርትራ፤ ሊቢያ፤ ሌሎች ሰሜን አፍሪቃ ሐገራት እና ኢጣሊያ ድረስ የተዘረጋ ነዉ። ለአሸገጋሪዎቹ ገንዘብ እየከፈሉ ወደ አዉሮጳ ለመግባት  ሲሞክሩ በርካታ ስደተኞች ሜድትራንያን ባሕር ዉስጥ እየሰመጡ ሞተዋል።
ፖሊስ ሰሞኑን የያዛቸዉን ተጠርጣሪ አሸጋጋሪዎች ካለፈዉ ግንቦት እስከ መስከረም ድረስ  23 የባሕር ላይ ጉዞዎችን አቀነባብረዋል በማለት ከሷቸዋል። ከተጓዦቹ ቢያንስ 240 ስደተኞች ሞተዋል። ከአስሩ ተጠርጣሪዎች ዘጠኙ ኅዳር 16 ቀን ኢጣሊያ ውስጥ የተያዙ ሲሆን አስረኛውና የቡድኑ መሪ ነው ተብሎ የሚጠረጠረው መዓሾ ተስፋማርያም ማክሰኞ ዕለት ጀርመን ውስጥ በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡ በተለይ ባለፈው ሰኔ ወር ከሊቢያ የሰሜን አፍሪካ ወደብ በበርካታ ተጓዦች ተጨናንቆ የተነሳውንና በኋላ በመስጠሙ ለ224 ስደተኞች ሞት ምክንያት የሆነውን ጀልባ የባህር ላይ ጉዞውን ሲጀምር መዓሾ ተስፋማርያም በአካል በመገኘት ሲቆጣጠር እንደነበር ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የካንታኒያ ሲሲሊ ፖሊስ ዘጠኝ ሶማሌዎችን በሕገወጥ መንገድ በማስተላለፍ ሥራ ላይ የነበረ 11ኛ የኤርትራ ተወላጅ ከዚሁ ጋር በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡ ሶማሌዎቹ በአንድ ቤት ውስጥ በአንድ የተቆለፈ ቤት የነበሩ ሲሆን ስምንቱ ለአቅመአዳም/ሔዋን ያልደረሱ መሆናቸውን የዜናው ዘገባ ጨምሮ ገልጾዋል፡፡ (ዜናው የተገኘው ከዶቸቨለ እና በእንግሊዝኛ ከሚታተም The Local የተሰኘ የጣሊያን የዜና መረብ ነው – Photo-Giovanni-Isolino-AFP)
http://www.goolgule.com/italiy-police-arrested-10-eritreans-suspected-of-human-trafficking/

ለለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን በሙሉ

የ9ኙ ፓርቲዎች የ24 ሰዓት ትዕይንተ ሕዝብ

9 parties 1


9 parties
መልዕክቱን አባዝቶ ለሌሎች በማዳረስ ለ24 ሰዓቱ ሰልፍ ቅስቀሳ የበኩላችሁን እገዛ እንድታደርጉ ጥሪ እናስተላልፋለን!
ያለመስዋዕትነት ድል የለም!
http://www.goolgule.com/9-parties-24-hours-demonstration/

በጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ ተሻሽሎ ቀርቧል የተባለው ክስ ተሰማ

zon e 9


በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው እየታየ ያሉት ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ላይ የተመሰረተው ክስ ተሻሽሎ ቀርቧል የተባለው የክስ ዝርዝር ከትላንት በስቲያ በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተሰምቷል፡፡
ዛሬ ህዳር 24/2007 ጠዋት በዋለው ችሎት፣ በጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ላይ ተሻሽሎ የቀረበው የክስ ዝርዝር በንባብ የተሰማ ሲሆን በክስ ወረቀቱ ላይ ከተመለከቱት ነጥቦች መካከል ግልጽ ያልሆኑ ነጥቦችን አካትቶ እንዲሰጥ ለአቃቤ ህግ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል፡፡ ስለሆነም ሙሉ የክስ ወረቀቱ አርብ ለጠበቆቹ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡
በጠበቆቹ በኩል ክሱ ቀደም ብሎ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት መሻሻሉን ለማረጋገጥ ያለፈው የፍርድ ቤቱ ብይን ግልባጭ እስካሁን እንዳልደረሳቸው በመግለጽ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲደርሳቸው ጠይቀዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የብይኑ ግልባጭ ሳይደርሰን ተሻሻለ የተባለው ክስ መሰማት የለበትም ብለው የነበር ቢሆንም፣ ክሱን አይታችሁ መቃወሚያ ካላችሁ አስተያየት እንድትሰጡበት እድል እንሰጣለን ያለው ፍርድ ቤቱ ክሱ እንዲሰማ አድርጓል፡፡
ፍርድ ቤቱ ጠበቆቹ ያላቸውን አስተያየት ይዘው እንዲቀርቡ ለታህሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል፡፡ (በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር)
http://www.goolgule.com/the-improved-charges-on-the-bloggers-and-journalists-was-heard/

የብሄር ነጻነት እስከ መጨፈር

(ክንፉ አሰፋ)

Nation and Nationality9
ማስታወሻ፡ ይህች ጽሁፍ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከተከሰሰባቸው ሁለት መጣጥፎች አንደኛዋ ናት። በመጭው ወር በአሶሳየሚደረገውን የብሄር ቀን ድራማ እሳቤ በማድረግ – በርካታ አንባብያን በጠየቁት መሰረት እነሆ በድጋሚ ለንባብ አቅርበናል።
“እኛ ጭቁን ብሄረሰቦች ከዚህ ቀደም በየሰው ቤት ተቀጥረን የምንሰራ፣ አሽከሮች እየተባልን ነበር የኖርነው። አሁን ግን ይኸውና ህገ-መንግስታችን መብታችንን ሰጥቶናል… ኑሯችንም ተሻሽሎ ዛሬ ዘመናዊ ኑሮ እየኖርን ነው።” እያለ የሚናገርን አንድ ጎልማሳ የቴሌቪዥኑ መስኮት ያሳያል። የደቡብ ቅላጼና ዘዬ ባለው አማርኛ ከደቡብ የመጣ ጎልማሳ ነው በቴሌቪዥን ቀርቦ መግለጫ እየሰጠ ያለው። ከአነጋገሩ በቀን ሶስቴ የሚበላ፣ የባቡር ሃዲድ እና የኤሌክትሪክ መስመር ገብቶለት፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚም… ይመስላል።
የዚህ ምስኪን ሰው ገጽታ እና አለባበሱ የሚነግረን ግን  ሌላ ነው። በኢህአዴግ ዘመን መብቱ እንደተከበረና ኑሮው እንደተሻሻለ የሚነግረን ይህ ሰው፣ መሰረታዊ የሆነውን  የሰው ልጆችን የኑሮ ፍላጎት እንኳን አላሟላም። ለእግሩ ጫማ የለውም። በባዶ እግሩ ነው የቆመው። ሃፍረተ ስጋውን ከሸፈነለት ብጣቂ ጨርቅ በስተቀር ሰውነቱም እርቃኑን ነበር።
ለመገናኛ ብዙሃን ፍጆታ አነጋገሩ እንዲያሳምር ተነግሮት ሊሆን ይችላል – ንግግሩ ልክ መካከለኛ ገቢ ካላቸው የምዕራብ አውሮፓ  ሃገሮች ተርታ የተሰለፈ ይመስላል። ይህ ደግሞ ገና የ’ትራንስፎርሜሽኑ’ ተስፋ እንጂ፤ ለውጡ በብሄር ብሄረሰቦቹ ላይ እንደማይታይ የቪድዮ ምስሎቹ ፍንትው አድርገው ነው የሚያሳዩት። ኢትዮጵያ በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች ተርታ ላይ እንደምትደርስ ኢህአዴግ ቃል ገብቷል። በአሁኑ ግዜ ሰባት በመቶ ብቻ የሆነው የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ብሄር ብሄረሰብ እና ሕዝብ በአምስት አመቱ እቅድ 80 በመቶ ይደርሳል ብለውናል። በእስር ያለው ጠንቋይ ታምራት ገለቴ ነግሯቸው ካልሆነ በስተቀር መቼም ይህንን ተረት ተረት በማህበራዊውም ሆነ በተፈጥሮ ሳይንስ ሊያረጋግጡልን እንደማይችሉ እርግጥ ነው። ከፈረሱ ጋሪው… እንዲሉ ከተግባሩ ወሬው፣ ከ’ህዳሴው ግድብ’ ስራም ሽልማቱ ቀድሞ መያዣ – መጨበጫው የጠፋ ነው የሚመስለው።
ከገጠር እየታፈሱ ለሚመጡት ለነዚህ ምስኪን ወገኖች የ ‘ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች’ መብት ማለት በአመት አንዴ በጎዳና ላይ  እየወጡ መጨፈር እና ያለፈውን ስርዓት ማውገዝ ብቻ ነው የሚመስለው። ጭፈራውና ውግዘቱ እንደ ጥምቀት በዓል ስለተለመደ የግድ መደረግ እንዳለበት ያመኑበትም ይመስላል።
የደርግ ስርዓት ሰዎች በባህላቸውና በቋንቋቸው እንዳይዘፍኑ ከልክሎ እንደነበር የሚጠቁም መረጃ የለም።  ደርግ አስራ ሰባት አመት ገዛ፣ 20 አመት ሙሉ በብሄር ጭቆናው ሲወገዝ ኖረ። በባንዲራ ቀን ውግዘት፣ በከተሞች ቀን ውግዘት፣ በብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ውግዘት፣ በግንቦት ሃያ ቀን ውግዘት…. በየሽልማቱ ስነ ስርዓት እና በየበዓላቱ ቀን ውግዘት…። የደርግ ሃጢያት መብዛት የነሱን ግፍ ይሸፍን ይመስል የኢህአዴግ በዓላት እና ውግዘቱ ከለት-ተለት ሲጨምር ብቻ ነው የምናየው – እንደ 11 በመቶው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያ እድገት።
የዚህ ሳምንት ወሬ ደግሞ በመቀሌ ስለተካሄደው ስድስተኛው የ ‘ብሄር – ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን’ ነው። የመከር ወቅት ስራቸውን እንዲያቆሙት ተደርገው፣ ከየክልሉ እየተጫኑ ለጭፈራ መቀሌ የገቡ አርሶአደሮች ቁጥር ቀላል አይደለም።  በዲያጎን እየተፈለጉ የተለቀሙ ልማታዊ አርቲስቶች እና የመድረክ አስተዋዋቂዎችም በስፍራው ተገኝተዋል።
የእውቁ ኪነጥበብ ሰው – የኪሮስ አለማየሁ ልጅ ዛፉ ኪሮስ ‘አንበሳ ገዳይ’ በሚለው የትግርኛ ዘፈንዋ መድረኩን ይዛዋለች። በርከት ያለ ሰው መድረኩን ከቦት ይጨፍራል። አዳራሹም በ ‘ብሄር – ብሄረሰቦች እና ህዝቦች’ ተሞልቷል። መቀሌ፣ ኅዳር 27 ቀን 2004 ዓ.ም.።
የእለቱ የመድረክ አስተዋዋቂ ‘አንበሳ ገዳይ’ የሚለው የዛፉ ኪሮስ ዘፈን የተስማማው አይመስልም፤ አልተዋጠለትም። አልያም ዘፈኑን እዚያው መድረክ ላይ እንዲያስተባብል ተነግሮታል። ተራውን ጠብቆ ማይክራፎኑን ያዘ።
“ህገ መንግስታችን ለብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ብቻ ሳይሆን ለዱር እንስሶችም…” ብሎ እየተናገረ እያለ እንደተለመደው መብራት ተቋረጠ።
በዚህ ‘ታላቅ’ ቀን መብራት መቆራረጡ ቢያበሳጭም፣ በእንግድነት ወደ መቀሌ የተጓዙት ‘ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች’ ኤሌክትሪክ ምን እንደሆነ ስለማያውቁ አልደነቃቸውም – የሚያውቁት ደግሞ የለመዱት ስለሆነ – ለእነሱ እንግዳ ነገር አይደለም። ከቆይታ በኋላ ግን መብራት መጣ። ልማታዊው አርቲስትም ንግግሩን ቀጠለ።
“…ህገ መንግስታችን ለብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ብቻ ሳይሆን የዱር አራዊቶችንም መብት ስላስከበረ አንበሶች አሁን አይገደሉም።…”
በማለት የዘፈኑን መልእክት ለማስተባበል እና ጭብጡን ለብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ለማስረዳት ሞከረ። እዚህ ላይ የመድረክ አስተዋዋቂው እና ዘፋኝዋ እንዳልተግባቡ መገመት ይቻላል። ዛፉ ኪሮስ ዘፈንዋን በዚህ መድረክ ታቅርበው እንጂ መልእክቱ ላሁኑ ትውልድ ሳይሆን ምናልባት ‘ተራራ ላንቀጠቀጠው’ ለዚያኛው ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ የተሳነው ይመስላል። ያ ቡድን የትኛውን ተራራ እንዳንቀጠቀጠ ባይገለጽልንም አሁን ያጠለለበት የለውጥ ደመና ግን በተራው እያንቀጠቀጠው ለመሆኑ ከሚያደርጋቸው ግራ ገብ ድርጊቶቹ  መረዳት ይቻላል።
የሆነው ሆኖ በአሉ ለመቀሌ ህዝብ ልዩ ስሜት እንደሰጠው ይታያል።  ይህ ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ተለይቶ፣ በእነ መለስ እና በረከት ካድሬዎች ታጥሮና ታፍኖ የሚገኝ ህዝብ ስለመሆኑ በርካታ መረጃዎች ይመሰክራሉ።  ከስፍራው የሚደርሱን መረጃዎች እንደሚተቁሙት ከመንግስት ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ውጭ ያሉ የመገናኛ ብዙሃንን በዚያ ክልል መጠቀም ራሱ እስከ ስድስት ወር የሚያሳስር ወንጀል ነው። ለ20 አመታት የታፈነ  ህዝብ ከሌላው ወገኑ ጋር ተቀላቅሎ፣  አብሮ ሲጨፍር የሚፈጥርበትን ስሜት መገመት አያደግትም። የደርግ ስርዓት የአሜሪካ እና የጀርመን ድምጽ ራዲዮን የትግራይ ህዝብ እንዳይሰማ አልከለከለም ነበር። ወያኔ ግን የትግራይ ህዝብን የመናገር ብቻ ሳይሆን የመስማት መብቱንም ጭምር ነው የነፈገው።
የሳተላይት ዲሽ ቴሌቪዥን ክልክል በሆነበት በዚያ ክልል የኢቲቪ አኬልዳማ ድራማ ይደገምልን ብሎ የትግራይ ህዝብ ቢጠይቅ ሊደንቀን አይገባም። ጆሮ ካሰለቸው የ’ህዳሴው ግድብ’ ወሬ እና እጅ እጅ ካሉት ከነ ሰራዊት ፍቅሬ አኬልዳማ ትንሽም ቢሆን ዘና ሳያደርጋቸው አልቀረም።  የቴሌቪዥኑ መግቢያ ላይ ታዲያ “እንደምን አመሻችሁ ዲሽ የሌላችሁ” ብሎ ነው የሚጀምረው እየተባለም ይቀለዳል።  ይህ ህዝብ በስሙ ሲነገድበት እና ከሌላው ወገኑ ጋር እንዲቃቃር ሲደረግ የትግራይ ኢሊቶች ዝም ማለታቸው እጅግ የሚያሳዝን ጉዳይ ነው።
ስለ ዱር አራዊት መብት እና ስለ አንበሳ መግደል ሲነሳ ትዝ ያለኝ የ1983ቱ የአምባሳደር ተስፋዬ ሃቢሶ ንግግር ነበር። ቻርተሩ ሲጸድቅ በነበረበት ጊዜ የከምባታና ሃድያን ጎሳ እወክላለሁ ብለው ወንበር ይዘው የነበሩት አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ በወቅቱ ሲናገሩ። “እኛ አናሳ ብሄር ብሄረሰቦች ዲሞክራሲ ብቻ ሳይሆን የሚያስፈልገን፣  እንደብርቅዬ እንስሣ እንክብካቤም ይገባናል።” ብለው ነበር።
ኢህዴግም በወቅቱ ለእነኚህ ‘አናሳ ጎሳዎች’ ልዩ እንክብካቤ እንደሚያደርግ ነበር ቃል የገባው።
አቶ ተስፋዬ ይህንን በተናገሩ ከአመታት በኋላ ታዲያ በሃዲያ እና ወላይታ ወገኖቻችን ላይ ጥይት እና ቦምብ እንደዝናብ ወረደባቸው። የ1993ቱ ብሄራዊ ምርጫ ተጭበርብሯል፣ ‘ድምጻችን ይከበር’ ብሎ የጮኸው የደቡብ ወገናችን በመለስ ወታደሮች ያለ ርህራሄ ነበር የተጨፈጨፈው። ልዩ እንክብካቤው እና ዴሞክራሲው ቀርቶ ይልቁንም የቆሙለት፣  በስሙም ስልጣን ያገኙበት፣ የራሳቸው ጎሳ በጥይት ሲቆላ አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ ሹመታቸውን ላለማጣት ሲሉ ትንፍሽ አላሉም። እንዲያውም ዛሬም ስለ ‘ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች’ መብት መከበር ከሚነግሩን እና የሌሎችን ጽሁፎች እየሰረቁ ከሚጽፉት ሰዎች አንዱ ናቸው።nationa nationalities8
ማሌሊቶቹ የሃገሪቱ የዘመናት ችግር የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መብት መነፈግ ነው ሲሉ ሰበኩ። የዚህ ችግር መፍቻ ቁልፍም በእጃቸው እንዳለ ነገሩን። በለስ ቀንቷቸው ምኒሊክ ቤተ መንግስት ሲገቡም ጫካ ውስጥ የጻፉትን ያንን የስታሊን ፍልስፍና ወደ ህገ-መንግስትነት ቀየሩት።  መፍትሄ ያሉት የጎሳ ፖለቲካም በጥላቻና በበቀል ተተካ።
የማሌሊት ፍልስፍና ሲተገበር ታዲያ የመጀመርያ ሰለባ የሆነው አማራው ወገናችን ነበር። ለፖለቲካ ትርፍ ሲሉ እነ አቶ መለስ ዜናዊ ይዘውት የመጡት የጥላቻና የብቀላ ፖለቲካ እንደስካር ቶሎ በረደ እንጂ አካሄዱ እጅግ ዘግናኝ ነበር።  በምስራቅ እና በምእራብ ኢትዮጵያ የአማራ ዘር ጨርሶ እንዲጠፋ ተዘምቶበት ነበር። የአማራን ዘር ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ከተበቀሉት በኋላም ጽዋው ወደ አኙዋክ – ጋምቤላ ሄደ ፣ ከአኙዋክ ጭፍጨፋ በኋላ ደግሞ ዘመቻው በኦሮሞ ወገናችን ላይ ቀጠለ። በወላይታ ተከተለ፣  በኦጋዴን… ተዛመተ። የብሄር መብት እስከመገንጠልን ያስከበረው ህገ-መንግስት ጸድቆ በወረቀት ላይ ተቀምጧል። ይህንን መብት እየጠየቁ ያሉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችንን ግን በዘራቸው ብቻ እየተመረጡ ማጥፋቱ ዛሬም በሚያሳዝን ሁኔታ እንደቀጠለ ነው።
እነ መለስ እነ በረከት ለዘመናት ተዋልዶና አብሮ ሲኖር የነበረን ህዝብ እንደ እንግሊዝ ከፋፍለህ ግዛው ቅኝ ስርዓት ለአገዛዝ እንዲያመቻቸው ህዝቡን እርስበርስ እያጋጩት ላለፉት 20 አመታት ለመቆየት ችለዋል። የዘር ፖለቲካው ምስጢር ይኸው ነው። ይህንን ባያደርጉ ኖሮ እስካሁን እንደ ጉም ተበትነው በጠፉ ነበር።
ወደመቀሌው በዓል እንመለስ።
ብሄር ብሄረሰቦቹ በመቀሌ ከተማ በቡድን በቡድን እየዘፈኑና እየጨፈሩ ይጓዛሉ። በተለይ ከደቡብ የመጡት ብሄር ብሄረሰቦች መብታቸው ተከብሮላቸው ወደ እድገት ጎዳና ከተጓዙ ከሃያ አመት በኋላም – ጥንታዊው የጋርዮሽ ስርዓት ከሚመስለው አለባበሳቸው እንኳን አልተቀየሩም።
ሐመር ከሃያ አመት በፊት ቅጠል ለብሶ ይጨፍራል፣ ዛሬም ቅጠሉን አልቀየረም። ዳውሮ ድሮ ለእግሩ ጫማ አያደርግም ነበር አሁንም ጫማ የለውም። ከፊቾ ከ20 አመታት በፊት ከቀንድ የተሰራ የሙዚቃ መሳርያ ነበር የሚጠቀመው፣ አሁንም እሱኑ ይዞ ነው መቀሌ የመጣው…። ሁሉም አንዳች ለውጥ አይታይባቸውም። ታድያ የዚህ ሕዝብ ነጻነቱ፣ ለውጡ እና እድገቱ የቱ ላይ እንደሆነ ማን ይሆን የሚያስረዳን?
ህገ መንግስታዊ መብቴ ይከበርልኝ ባለ ብቻ ምላሹ የጥይት እና ቦንብ የሆነ ሕዝብ ቅጠል ለብሶ መጨፈሩ ምን ትርጉም ይሰጠናል? ይህ  ነጻነቱን ያሳየናል እንዴ? ወይንስ ዛሬም የእግር ጫማ እንኳን አለማድረጉ እንደ ባህል ተቆጠረለት?
ጎንደሬው ሁመራ ላይ ለማረስ ፈቃድ ከመቀሌ መጠየቁ ነው የመብቱ መከበር? ወይንስ መቀሌ ላይ ሄዶ እስክስታ መምታት? አፋርና ኢሳ  – ጉርጉራ ላይ ካላረሰ -   አማራው ኦሮሞ ምድር ላይ እንዳይሰራ ከታገደ መብቱ ምኑ ላይ ነው?
ተረስቶ ይሆን ይሆናል እንጂ “የአክሱም ሃውልት ለወላይታው ምኑ ነው?…” ብለው ነበር አቶ መለስ። ታዲያ ዛሬ ምን አዲስ ነገር ተገኘ?  በመቀሌ እየተደረገ ያለው የወላይታ ጭፈራስ ለአድዋው ምኑ ሊሆን ነው?
‘የኢትዮጵያ ጥንታዊ ስልጣኔ አንተን አይመለከትህም’ ተብሎ የነበረ የወላይታ ህዝብ ዛሬ የመለስን ፎቶ እና ‘ለልማት የተጋ ብቸኛው መሪ’ የሚል መፈክር ይዞ በመቀሌ እንዲሰለፍ ተደርጓል።
ደቡቡ የየራሱን የአፍ መፍቻ ቋንቋ እርግፍ አድርጎ ትቶ ኢህአዴግ በፈጠረለት ‘ወጋ ጎዳ’ እንዲናገር አቶ መለስ፡ ሲያስገድዱት እነሱ ግን ልጆቻቸውን በአለም አቀፍ ቋንቋ ብቻ እንዲማሩ ነው ያደረጉዋቸው። ዛሬ አቶ መለስ የነዚህን ጎሳዎች መብት መከበር ነው በመቀሌ እያበሰሩ ያሉት።
ይህ ህዝብ እንዲሁ ‘ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች  እየተባለ ሲቀለድበት እንደዋዛ ሃያ አመታት አለፉ።
በኢህአዴግ ዘመን ተወልዳ፣  ተምራ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀች ወጣት አንድ አፍሪካ ሃገር አግኝቼ አወራኋት።  ሜሮን ትባላለች። ስለ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መብት እና ነጻነት ልትነግረኝ ሞከረች። ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ ውጤት ሳይኖራት ይልቁንም ኢህአዴግ በሰጣት እድል ዩኒቨርሲቲ ገብታ እንደተማረች ስለተነገራት የመለስ ዜናዊ አድናቂ ናት።
በወሬያችን መሃል በድንገት ‘ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ማለት ምን ማለት ነው?’ ብዬ ጠየቅኳት። ጥያቄዬ ዱብዳ ነገር ሆነባት። ለሚለኒየም ግብ ሲባል ከተከፈቱት ዩኒቨርሲቲዎች ለስታስቲክስ ማሟያ የተመረቀች ስለመሆንዋ አመለካከትዋ፣  አስተሳሰብዋ እና ንግግርዋ ይገልጸዋል።
ጥያቄዬን ለመመለስ እንደከበዳት ተረዳሁ። ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የሚለውን ቃል የሜሮን ትውልድ ለሃያ አመታት ያለማቋረጥ ሲሰማው የነበረው ጉዳይ ነው። ለዚህ ትውልድ የብሄር መብት ማለት ግን በየአመቱ በጎዳና ላይ ከሚደረግ ጭፈራ ውጭ የሚሰጠው ሌላ ትርጉም ያለ አይመስለኝም።
ማን ነው ብሄር? ብሄረሰሰቦችስ የትኞቹ ናቸው? ህዝቦች የሚባሉትስ? ለዚህ ጥያቄ እንኳንና ሜሮን – ወያኔም መልሱ እንደሚቸግረው ይገባኛል።
ሜሮን ግን ኮስተር ብላ “ህገ መንግስቱ ነዋ!” አለችኝ።
ከዩኒቨርሲቲ ከተመረቀች ወጣት ቀርቶ ከአንደኛ ደረጃ ተማሪ እንኳን የማልጠብቀውን መልስ በማግኘቴ ባዝንም – በመልስዋ ግን ትንሽ ፈገግ ማለቴ አልቀረም።
ከአፍታ ቆይታ በኋላ – ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ማለት ራሱ መለስ ዜናዊ ይመስለኛል ስትል ቀለደች ሜሮን።
እዚህ ላይ ልብ በሉ! ‘የህዳሴው ግድብ’ ሽልማት ስነ ስርዓት እየተደረገ በነበረበት ግዜ የግድቡ “ወደር የሌለው ተሸላሚ”ን ሰራዊት ፍቅሬ በቴሌቭዥን ሲያስተዋውቅ የሆነው ነገር ታወስውኝ።  ነገሩ ጤነኛ አእምሮ ላለው ሰው እንግዳ ነበር።
ሰራዊት እና ሙሉአለም እየተቀባበሉ – እየደጋገሙም ‘የህዳሴው ግድብ ወደር የሌለው ተሸላሚ’ ይላሉ። ከብዙ ደቀቃ በኋላም የህዳሴው ግድብ ወደር የሌለው ተሸላሚ ይፋ ሆነ።
“ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች!” ሲል ሰራዊት ፍቅሬ በሚለኒየም አዳራሽ ለተሰበሰበው ህዝብ አበሰረ።
ሸልማቱን የሚሰጠው አቶ መለስ ዜናዊ፣ ሽልማቱን የሚቀበለው የኢህዴግ ተወካይ ሲሆን ፣ ይህም በተዘዋዋሪ አቶ መለስ ዜናዊ መሆኑ ነው።
ሜሮን ይህንን ማለትዋ ከሆነ – ጥያቄዬን በትክክል እንደመለሰችልኝ ተረዳሁ።
ሽልማቱ መጣም አልመጣ ለብሄር ብሄረሰቦቹ የሚፈይደው ነገር አይኖርም።  በየአመቱ የሚደረገው የጎዳና ላይ ጭፈራ ግን የብሄረሰቦች መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታቸውም ሆኗል ብለን እንደምድም።
የብሄር ነጻነት እስከ መጨፈር! ከዛ ካለፈ ግን የህይወት ዋጋም ያስከፍላል። ኦጋዴንን ያስተውሏል?
http://www.goolgule.com/the-rights-of-nation-and-nationalities-without-freedom/

የሃና ላላንጎ ጉዳይ በዝግ ችሎት ታየ

ቤተሰቦቿ ሐኪሞችንና ፖሊሶችን ወቀሱ

Hana-lalango


* “አሸባሪዎችን” ለይቶ የመያዝ ልዩ ችሎታና ብቃት ያለው ፖሊስ ያልያዘው ተጠርጣሪ አለ
ሃና ላላንጎ የተባለችውን ተማሪ በሚኒባስ ታክሲ አፍነው በመውሰድ፣ በቡድን በመድፈርና ሕይወቷ እንዲያልፍ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙትን አምስት ተጠርጣሪዎች የፍርድ ቤት ጉዳይ በዝግ ችሎት መታየት ጀመረ፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ለሦስተኛ ጊዜ ኅዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት፣ ቂርቆስ ምድብ ችሎት የቀረቡ ሲሆን፣ ፖሊስ ቀደም ባለው ቀጠሮ እንደሚሠራቸው ያስመዘገበውን ቀሪ የምርመራ ሒደት፣ ለችሎቱ ያስረዳበትና ተጠርጣሪዎቹን ያቀረበበት ሰዓት፣ ከሌሎች ቀናት የተለየ ነበር፡፡
ሟች ሃና ላላንጎ በቡድን ተደፍራ ሕይወቷ ማለፉ በመገናኛ ብዙኃን ከተሰራጨበት ጊዜ አንስቶ እያነጋገረ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ በየቀጠሮው ፍርድ ቤት የሚገኘው ታዳሚ ቁጥር ጨምሯል፡፡ ኅዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም. እንደተለመደው ፖሊስ ዘግየት ብሎ ከ4፡30 ሰዓት በኋላ እንደሚመጣ በማሰብ፣ ሕዝቡ ወደ ፍርድ ቤት መድረስ የጀመረው በአብዛኛው ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ጀምሮ ነበር፡፡
የጠዋቱ ጊዜ ወደ እኩለ ቀን እየተቃረበ በመሄዱ፣ ሕዝቡ እርስ በራሱ “አራዳ አቅርበዋቸዋል አሉ፤ አይ አይደለም ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ክስ መሥርተዋልና ፖሊስ እንጂ ተጠርጣሪዎቹ አይቀርቡም፤” የሚሉና ሌሎች መላምቶችን በመነጋገር ላይ እያለ፣ ፖሊስ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ላይ ተጠርጣሪዎቹን ይዞ ቀርቦ፣ ማንም ወደ ችሎት ሳይገባ በዝግ ችሎት፣ የሠራውን የምርመራ ሒደት ለፍርድ ቤቱ ካስረዳ በኋላ፣ ለሚቀረው ተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናትን ጠይቆ እንደተፈቀደለት ተሰማ፡፡ ለታኅሣሥ 6 ቀን 2007 ዓ.ም. መቀጠሩም ታወቀ፡፡
የተነገረውን ለማረጋገጥና ተጨማሪ መረጃ ለመስማት ቀጠሮውን ወደሰጡት ዳኛ የሟች ዘመዶችና የመገናኛ ብዙኃን በመሄድ ሲጠይቁ፣ ጠዋት በሥራ ሰዓት ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ይዞ በመቅረብ፣ ችሎቱ በዝግ እንዲታይለት ባመለከተው መሠረት ፍርድ ቤቱም ስላመነበት በዝግ ችሎት መታየቱ ተረጋገጠ፡፡
በሕገ መንግሥቱም ሆነ በፍርድ ቤቶች አሠራር በዝግ መታየት ያለባቸው የወንጀል ድርጊቶች መኖራቸው እንዳለ ሆኖ፣ ተማሪ ሃና ላላንጎን ሕይወቷ እንዲያልፍ አድርገዋል የተባሉት ተጠርጣሪዎች ጉዳይ፣ ለሁለት ጊዜያት በግልጽ ችሎት ከታየ በኋላ፣ በየትኛው የሕግ መሠረት ሦስተኛው ቀጠሮ በዝግ ሊታይ እንደቻለ ማብራሪያ እንዲሰጡ ዳኛው ተጠይቀው ነበር፡፡
የሃና ጉዳይ በዝግ ችሎት እንዲታይ የተወሰነው፣ ፖሊስ ምርመራውን ሳይጨርስ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃንና ድረ ገጾች፣ የሆነውንና ያልሆነውን ዘገባ በማሰራጨት ለምርመራው እንቅፋት እየፈጠሩበት መሆኑን አስረድቶ፣ ምርመራውን እስከሚያጠናቅቅ ድረስ በዝግ ችሎት እንዲታይለት መጠየቁ አሳማኝ ሆኖ በመገኘቱ በዝግ ችሎት እንዲታይ መፈቀዱን አስረድተዋል፡፡
hana 2ፖሊስ ኅዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ተጠርጣሪዎቹን በችሎት አቅርቦ ቀደም ባለው ችሎት ያስመዘገበውን ቀሪ የምርመራ ሒደት ምን ያህሉን እንደሠራና ምን ያህሉ እንደቀረው ማወቅ ባይቻልም፣ ቀደም ባለው ቀጠሮ ተጨማሪ 14 ቀናትን ጠይቆ፣ ፍርድ ቤቱ ‹‹10 ቀናት ይበቃሃል›› በማለት ከጠየቀው ቀናት ላይ አራት ቀናትን የቀነሰ ከመሆኑ አንፃር፣ ኅዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም. የጠየቀውን 14 ቀናት ሙሉውን መፍቀዱ፣ ሌላ ተጨማሪ ተጠርጣሪ የመያዝና በርካታ ቀሪ ምርመራ ሳይኖረው እንዳልቀረ ጥርጣሬ አሳድሯል፡፡
የሟች ተማሪ ሃና ወላጅ አባት አቶ ላላንጎ አይሶ ኅዳር 21 ቀን 2007 ዓ.ም. በየሳምንቱ እሑድ ምሽት ላይ በኢቢኤስ በሚቀርበው “ሰይፉ ፋንታሁን ሾው” ላይ ቀርበው ፖሊስ አንድ ተጠርጣሪን መያዝ እንደሚቀረው በመናገራቸው፣ ኅዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ጉዳዩ በዝግ መታየቱንና 14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መፍቀዱን ተከትሎ ጥርጣሬውን አጠናክሮታል፡፡
አቶ ላላንጎ ሟች ልጃቸው መስከረም 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ታፍና መወሰዷንና ለ20 ቀናት አስታመዋት፣ በደረሰባት ከባድ ጉዳት ልትተርፍ አለመቻሏን ገልጸዋል፡፡ እንደ አቶ ላላንጎ ገለጻ፣ ልጃቸው ጦር ኃይሎች ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ተጥላ ከተገኘች በኋላ፣ ወዲያውኑ ወደ አለርት ሆስፒታል ወስደዋታል፡፡ የአለርት ሆስፒታል ዶክተሮች ተመልክተዋት በስለት በመወጋቷና በደረሰባት የመደፈር አደጋ ሕይወቷን ልታጣ እንደምትችል በመናገር፣ ሕይወቷ ከማለፉ በፊት ቃሏን ለፖሊስ እንድትሰጥ በመናገራቸው ቃሏን እንድትሰጥ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
የሃና ላላንጎ ወላጅ አባት ስለልጃቸው ስቃይ እንዳብራሩት፣ አለርት ሆስፒታል ከአቅሙ በላይ መሆኑን ገልጾ ወደ ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ሪፈር ተብለው ሲወስዷት፣ ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ደግሞ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በሪፈር እንዲወስዷት እንደነገራቸው አስረድተዋል፡፡ ያለምንም ሕክምና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ መልሶ ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ሲልካቸው ተስፋ የቆረጡት አቶ ላላንጎ፣ ልጃቸውን በቀጥታ ወደ ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል መውሰዳቸውን ትተው፣ ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመውሰድ አንድ ቀን አድራና ቤተሰቦቿን ተሰናብታ፣ በማግስቱ ወደ ጋንዲ ሆስፒታል እንደወሰዷት ገልጸዋል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ጋንዲ ሆስፒታል በሪፈር የሄደችው ሟች ሃና፣ ይኸ ሁሉ ውጣ ውረድ ሲደረግ ደም እየፈሰሳትና ቁስሏም ወደ ሌላ ሕመም እየተቀየረ መሆኑን የገለጹት አባቷ፣ ሙሉቀን በጋንዲ ሆስፒታል ከቆየች በኋላ፣ ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል አልጋ ተገኝቶላት መተኛት መቻሏን ተናግረዋል፡፡
የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ሐኪሞች የሃናን ጉዳትና ሕመም ሲመለከቱ፣ በከፍተኛ ሐዘንና እንባ ታጅበው ለማትረፍ የተረባረቡ ቢሆንም፣ ችግሩ ወደ ሌላ ነገር ተቀይሮ የነበረ በመሆኑ ሕይወቷ ሊተርፍ አለመቻሉን ገልጸዋል፡፡
አቶ ላላንጎ የልጃቸውን ስቃይ በሐዘን ሲገልጹ፣ ሐኪሞችንና ፖሊሶችን ወቅሰዋል፡፡ “ሁሉንም ሐኪምና ሁሉንም ፖሊስ በጅምላ መውቀስ አልፈልግም፤” ብለው፣ መልካምና ሥራቸውን የሚወዱ፣ ኃላፊነታቸውን የሚወጡ ሐኪሞችና ፖሊሶች ስላሉ እነሱን ማመስገን እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡ ልጃቸው ደም እየፈሰሳት በሄዱበት ሆስፒታሎች “አልጋ የለም፣ ውጭ አስመርምሯት” ማለትና ችላ ማለት ተገቢና የገቡለትም ቃል ኪዳን ባለመሆኑ፣ ተገቢ አለመሆኑን በመናገር፣ መንግሥትም ሊከታተለው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ፖሊሶችም ቢሆኑ፣ ጉዳዩን በትጋት ተከታትለውና ራሳቸው የሚሆነውን እንደማድረግ “እዚያ ውሰድ እኛ ጋ አይደለም” በማለት እንዲንገላቱ ማድረጋቸው ተገቢ ባለመሆኑ መንግሥትም ሊያየው የሚገባ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ (ምንጭ ሪፖርተር)
http://www.goolgule.com/closed-court-proceeds-with-hanas-cased/

“ሙሽራን ያላችሁ እስቲ እንያችሁ…”፤ [“የቲፎዞነት” ዘመን]

(ኤፍሬም እንዳለ)

Birds


እንዴት ሰነበታችሁሳ!
ሀሳብ አለን … ስብስባዎች ሁሉ … አለ አይደል… “እንዴት ሰነበታችሁ…” በሚል ብቻ ይከፈትና ወደ ጉዳዩ ይገባ! አሀ … “ክቡር እከሌ እከሌ፣” “ክብርት እከሊት እከሌ፣” “የተከበሩ እከሌ እከሌ” … ምናምን ሲባል የስብሰባው ሲሦ እያለቀ ነዋ! ለነገሩ … (“ለምን ይዋሻል!” የሚሉት ነገር ነበረ አይደል!) ብዙ ስብሰባዎች ላይ “እንትንህን እንደ ዳናኪል እንፋሎት እንዳላቦንልህ!” አይነት “የጉልበት ግማሹ ምላስ ነው…” ነገር በዝቷላ! (እኔ የምለው … አንዳንዱ መድረክ ላይ ወጥቶ እንዴት ነው እንዲህ ‘ልክ ልክ ማጠጣት’ የሚዋጣለት!)
አንድ ወዳጃችን ሲነግረን አለቅየው ‘መጠመቁን’ ለበላዮቹ ለማስመስከር የማይሞክረው ነገር የለም፡፡ በተለይ ስብሰባዎች ላይ የሚናገረው ‘ቦተሊካ’ ነክ ንግግር ካርል ማርክስን ጢሙንና ጸጉሩን አርግፎለት ‘አይ ሮቦት’ ነገር ያስመስለው ነበር፡፡ እናላችሁ…በቅርብ ጊዜ ሚጢጢና የሰማይ ስባሪ አለቆችና አለቆች ነገሮችን ይሰበስብና … “እዚህ ክፍል ውስጥ የግንዛቤ ችግር ያለባችሁ ሰዎች እንዳላችሁ ይታወቃል፡፡ የኒኦ ሊበራሊዝም አስተሳሰብ መሥሪያ ቤታችን ውስጥ እንዲገባ መፍቀድ የለብንም…” ምናምን እያለ እሱ ራሱ ባልገባው ነገር ግራ እንዳጋባቸው ሲነግረን ነበር፡፡ ወዳጃችን በሆዳችን ግን ሁላችንም ቂ…ቂ… ብለናል…” ብሎናል፡፡
እንግዲህ ጨዋታን ጨዋታ ያነሳው የለ…ለነገሩ በሆዳችን ቂ…ቂ… የሚያሰኙ ነገሮች መአት ናቸው፡፡ ጮክ ብለን ቂ…ቂ…ብንል አበሳ ነው፣ ዝም እንዳንል  እንዴት አስችሎን — በሆድ እንኳን እንሳቅ እንጂ!
እኔ የምለው…እንግዲህ ጨዋታም አይደል…ይቺን ስሙኝማ፡፡ ሰውየው ንግግር እያደረገ ነው አሉ… እናላችሁ …ሦስት አራቱ አንድ ላይ በመናገር በየመሀሉ ያቋርጡታል፡፡ ብሽቅ ይላል፡፡ ተራ በተራ እንዲናገሩ ለማድረግም ምን ይላል… “ዛሬ እዚህ አዳራሽ ውስጥ ብዙ ደደቦች አሉ፡፡ በአንድ ጊዜ አንድ ደደብ ብቻ ቢናገር አይሻልም…” ይላል፡፡
ተሰብሳቢዎቹ ምን ቢሉት ጥሩ ነው  “…እኮ ቀጥላ!” አሪፍ አይደል! ዘንድሮ በየቦታው “…እኮ ቀጥላ!” መባል የሚገባንን ቤቱ ይቁጠረን፡፡
ስሙኝማ…“ክቡራንና ክቡራት፣ ደህና  ሁኑ፣ አትሁኑ የእኔ ጉዳይ አይደለም… ምን አግብቶኝ ነው እንደምን አደራችሁ የምለው? አሁን ወደ ስበሰባችን እንገባ፣” የሚል የክብር እንግዳ የመጣ ቀን… ያኔ የምር ዘመኑ እየገባን ነው ማለት ነው፡፡ እንደምን ብንውል ብናድር ማንም ግዴለውማ! አይደለም የእኛ ቤጤ የዓለም ሰዎችን ቀርቶ አባቶች እና ምዕመናን እንደምን አደራችሁ!… እንደምን ዋላችሁ!… እንደምን አመሻችሁ…” ሲለን እንኳን አንዳንዴ እንደው ግድ ሆኖባቸው ነው እንላለን፡፡
እኔ የምለው…አርቲስቶች (እና ‘ሴሌብሪቲዎች’…) ምናምን … አለ አይደል…በሬድዮ፣ በቲቪ ምናምን ሲቀርቡ… “እወዳችኋለሁ…” የሚሏት ነገር አሁን፣ አሁን ቂ…ቂ…ቂ… ታሰኘን ጀምራለች፡፡ ልክ ነዋ… ከዘመድ፣ አዝማድ ጋር ሁሉ ተጠማምዶ “ሸንኮራ ጠበል ቢጠመቅ ይሻላል ወይስ አርሴማ ገዳም ቢገባ…” እየተባለ ምክክር እየተደረገበት… እኛን “እወዳችኋለሁ…” ሲለን አሪፍ አይደለም፡፡ እኔ የምለው…እግረ መንገዴን የሆነ ነገር ትዝ አለኝማ…አሁን አንድ አንድ ‘ቶክ ሾው’ ምናምን የሚባሉ ዝግጅቶች ላይ እየተለመደች የመጣች አባባል አለች፡፡ “እንዲህ ያሳመረኝ እንትን እንትን ቡቲክ ነው…” አይነት ነገር ይባላል፡፡ ደስ የሚል ዘመን ነው፡፡ ድሮ አፍ አውጥቶ “አምራለሁ…” ቢል የሰፈር ዕድር ሁሉ ባያድምበት ነው! ሀሳብ አለን…አንዳንድ ጊዜ… አለ አይደል… “ይህን የሚያምር ልብስ ያለበሰኝ…” ይባልልንማ! አሀ…እንደዛ ስናስብስ!  ቂ…ቂ…ቂ…
ስሙኝማ…ጨዋታን ጨዋታ ያነሳው የለ…ዘንድሮ የ‘ቲፎዞ ነገር’ አልበዛባችሁም! የምር አስቸጋሪ ነው…ጥሩ ነገር መሥራት ብቻውን በቂ ያልሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ “ስማ እንትን ኤፍ ኤም የምታውቀው ሰው የለህም!” መባባል ለመደብን፡፡ ምን ይደረግ!…‘ቲፎዞ’ ከሌለን ነገርዬው…አለ አይደል…“ከሌለህ የለህም…” አይነት ይሆናል፡፡
እናላችሁ…አሪፍ መጽሐፍ መጻፍ ብቻ፣ አሪፍ ዘፈን መዝፈን ብቻ፣ ብዙ የግጥም መድበል ማውጣት ብቻ፣ ጥሩ መተወን ብቻ ወዘተ. በቂ አይሆንም፡፡ በምላሳቸው “ወንድምና እህትን ማጋባት ይቻላል…” የሚባሉ አይነት ‘ሎቢይስቶች’ ያስፈልጋሉ፡፡
የምር ግን…አንዳንድ ሥራዎች ቆይተርው እናንተ ዘንድ ይደርሱና… አለ አይደል… “ይሄን ነገር እንዴት እስከ ዛሬ ድረስ አላየሁትም…” አይነት ነገር ትላላችሁ፡፡ መልሱ አጭር ነው… ‘ኖንቼ ቲፎዞ!’
ስሙኝማ… ብዙ ሠርግ ምናምን ላይ አይታችሁልኛል…ጠጁ ምናምኑ በ‘መሬት በታች መተላለፊያዎች’ (ቂ…ቂ…ቂ….) የሚሄደው ወደሚታወቁ ሰዎች፣ ወደ ሰፈር ሰዎች፣ ወደ መሥሪያ ቤት ባልደረቦች፡ ምናምን ነው፡፡ ዘመኑ የ‘ቲፎዞ’ ነዋ!
ደግሞላችሁ…አንዳንድ ቦታ የደረጃም ሆነ የደሞዝ እድገት የሚገኘውም በ‘ቲፎዞ’ ነው ይባላል፡፡ ዘንድሮ ደግሞ ለ‘ቲፎዞነት’ የሚያመቹ መመዘኛዎች በዝተዋል፡፡ ከሁሉ በላይ ግን ‘የአገር ልጅነት’ ዋናው ነው፡፡ እኔ እኮ አንዳንዶቹማ ከሰፊው ‘የአገር ልጅነት’ ወደ ሰፈርነት ሲወርዱ ስታዩ ነገ ደግሞ ‘በግቢ’ እንዳይሆን ትላላችሁ፡፡
ስሙኝማ…ዘንድሮ መንደሮች ‘መደብ’ የሚለይባቸው እየሆኑ አይደል… እዛም ለየት ያሉ ‘ቲፎዞነቶች’ ይኖራሉ ማለት ነው፡፡ ለመደብና! “ዘመድ ከዘመዱ…” ምናምን የሚባል ነገረ አለ አይደል፡፡ ይቺን ስሙኝማ… ሰውየው አንዱን ጎብኚ እያዟዟረ ኒው ዮርክን ያስጎበኘው ነበር፡፡ እናላችሁ… አንድ ቤተ መንግሥት የሚያክል መኖሪያ ቤት ይደርሳሉ፡፡
አስጎብኚውም እንዲህ ይላል… “ይህ በኒው ዮርክ እጅግ ሀብታም የሆነው ሰው መኖሪያ ቤት ነው፡፡ አብሳዩ ጀርመናዊት ነች፣ የቤት ሠራተኛዋ ፈረንሳዊት ነች፣ ዕቃ አመላላሹ ጃፓናዊ ነው፣ ሜካኒኩ ስኮትላንዳዊ ነው፣ የቤት ጽዳት ሠራተኛዋ ስዊድናዊት ነች፣  ፀሀፊው ደግሞ አሜሪካዊት ነች፡፡”ጎብኚው ሲመልስ ምን አለ መሰላችሁ… “ይሀ መኖሪያ ቤት ሳይሆን የዓለም ፍርድ ቤት ነው፡፡” ኧረ እዚህ በመጣ፣ ቤተ መንግሥት ሊያስንቁ ምንም የማይቀራቸው ቤቶች ባይኖሩ ነው! እንደውም አንዳንዶቹ እንዲህ አይነት ቤቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ሲያልፉ የመኪና ጥሩምባ ማሰማት ክልክል እንደሆነ በቀደም ወዳጄ እየነገረኝ ነበር፡፡ “ገና ምን አይተሽ!” አለ ባል ሚስት ላይ ሲፎክር!
እኔ የምለው…እግረ መንገዴን…ደግሞ የት አካባቢ ነው…“ከጥራት በታች የተሠራ መንገድ እየፈረሰ ነው…” ምናምን ሲባል ሰማን ልበል! …‘ማፍረስ’ ቀላል የሆነባት አገር! ሀሳብ አለን… ለማፍረስ ጥቅም ላይ የሚውሉ ዲጂኖ ምናምን አይነት መሣሪያዎች ከውጪ ይገቡ እንደሆነም፣ እዚሁ ይመረቱ እንደሆነም ብዛታቸው ይቀነስልንማ! አሀ…ችግር የሚፈጥርው እኮ ‘እንደ ልብ’ የሚገኝ ነገር ነው፡፡ ለነገሩ ዲጂኖውም ቢጠፋ… አለ አይደል… “በጥፍሬ እየቧጠጥሁ ካላፈረስኵ ሞቼ እገኛለሁ…” የምንል አንጠፋም፡፡ ዘመኑ እንዲህ ነዋ!
እናላችሁ… ‘የቲፎዞነት’ ዘመን ነው፡፡ እኛ “የለም…” የተባልነው የለስላሳ መጠጥ አይነት እዛው በዛው ለ‘ቲፎዞ’ ሲሰጥ ያየንበት ሬስቶራንት ነገር አለ፡፡
ታዲያላችሁ…በየስብሰባውም የሚገጥማችሁ ነገር ‘የቲፎዞ’ ነገር ነው፡፡ ያው ያቺ ከድሮ ጀምሮ የተለመደች ‘በተንተን ብሎ የመቀመጥ’ ስትራቴጂ አለች አይደል… ሰበሳቢውም “አንድ ከዚህ ጫፍ፣ አንድ ከመሀል፣ አንድ ከወዲያኛው ጫፍ…” ምናምን ይልና ስትራቴጂያዊ ቦታቸውን የያዙ ‘የቲፎዞ ስብስቦች’ ….ይቆጣጠሩታል፡፡
እናላችሁ… ሰዉ ከሁሉ አስቀድሞ “እንትን መሥሪያ ቤት ሰው ታውቃለህ…” ምናምን የሚባለው ዘመኑ ‘የቲፎዞ’ ስለሆነ ነው፡፡
አሁን፣ አሁን የሆነ ነገር፣ በተለይ የጥበብ ሥራ፣ ሲያደንቁልን ከሥራው ይልቅ “ሰውዬዋ ፕሮፓጋንዳ እየነሰነሰች ነው እንዴ!” እንላለን፡፡
እናማ… “ሙሽራን ያላችሁ እስቲ እንያችሁ…” አይነት የመጠቃቀስ፣ በምስጢር የመጠራራት ‘ቲፎዞነት’… አለ አይደል… ‘በጨው ደንደስ በርበሬውን እያስወደሰ’ ስለሆነ ጦሳችንን ይዞ ይሂድልንማ!
ደህና ሰንብቱልኝማ!
http://www.goolgule.com/age-of-favoritism/