FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Monday, April 14, 2014

የሽብርተኝነት እንቆቅልሽ

የኢትዮጵያው አዋጅ ትርጓሜና ክፍተቶቹ

terror


መንግስታት በተለያየ መልኩ ትርጉመው ያቀረቡትን ሽብርተኝነት ለመዋጋት በሚል ህግ ያወጣሉ፡፡ በእርግጥ በአዲስ መልክ በሽብር ላይ የታወጀው ዘመቻ በአሜሪካ ግፊት የመጣ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2001 አሜሪካ ከደረሰባት የሽብር ጥቃት በኋላ “war on terror” እንዲሁም “counter ter­rorism” የተሰኙ ዘመቻዎችን ነድፋ ተንቀሳቅሳለች፡፡ አሜሪካ ወዳጅም ሆነ የቀዩ ባላንጣዎቿን ሳይቀር ደልላም ሆነ ተማጽና የጀመረችው ይህ “ጸረ ሽብር ዘመቻ” መንግስታት በየ አገራቸው የራሳቸውን ጥቅም የሚያስጠብቁ አፋኝ “የጸረ ሽብር” ዘመቻ እንዲያወጡ እድል ሰጣቸው፡፡ አሜሪካ የሰብአዊ መብት ይጥሳሉ እያለች ስትወቅሳቸው የነበሩ ስርዓቶች ሳይቀሩ የተደላደለ የዴሞክራሲያዊ መሰረት ባልተጣለበት ሁኔታ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶችን የሚደፈጥጡ አዋጆች አጽድቀው ሲተገብሩ ከሀያሏ አገር የገጠማቸው ወቀሳና ግፊት ከዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በተቃራኒው አልቃይዳንና ቅርንጫፎቹ አሊያም ተያያዥ አሸባሪና አክራሪ የምትላቸውን ሁሉ እንዲያድኑ ወታደራዊ ድጋፍን አጋብሰዋል፡፡ ኢህአዴግ መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ከኒዮርኩ ጥቃት በኋላ አጋጣሚውን ከተጠቀሙት መንግስታት መካከል አንዱ ነው፡፡
አሜሪካ መራሹ ከሆነው በተጨማሪ በተለይም የምዕራባዊያን አገራት የደረሰባቸውን አደጋም አስከትለው ህጎችን አውጥተው ተግብረዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ጸረ ሽብር ህጎች መንግስታት ራሳቸው ያጸደቋቸውን ህጎች ሳይቀር ጥሰው ሽብርተኝነት ያሉንት ወንጀል እንከላከላለን የሚልባቸው ህግጋቶች ናቸው፡፡ በተለይ ዴሞክራሲ ባልተጠናከረባቸው አገራት እነዚህ ህጎች አምባገነኖች በአገራቸው ህዝብ ላይ ያሹትን እንዲፈጽሙ እና ህጉን ተገን አድርገው ለረዥም ጊዜ ስልጣን ላይ እንዲቆዩ ምክንያት እየሆነላቸው ይገኛል፡፡
የአዋጁ አውድ
በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ የሚገኙት የተለያዩ የሽብር ትርጉሞች የሚተረጎሙት በዝርዝር ተግባራት (ግድያ፣ ጠለፍ፣ እገታ፣ በመሳሰሉት ድርጊቶችና) እና ከተፈጸሙት ድርጊቶች በስተጀርባ አሉ የሚባሉት (አብዛኛዎቹ መንግስታት ራሳቸው ከጥቅማቸው አንጻር የሚተረጉሟቸው ናቸው) በዓላማና ፍላጎትን በማጣመር ነው፡ ፡ የኢትዮጵያ የጸረ ሽብር አዋጅ ትርጓሜም ይህንኑ መንገድ የተከተለ ነው፡፡ አዋጅ 652/2001 በድርጊት በኩል ሽብርተኝነትን ሲተረጉም፡-
  1. ሰውን የገደለ ወይንም በአካሉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ
  2. የህብረተሰቡን ወይንም የህብረተሰቡን ክፍል ደህንነት ወይንም ጤና ለከፍተኛ አደጋ ያጋለጠ እንደሆነ
  3. እገታ ወይንም ጠለፋ የፈጸመ እንደሆነ
  4. በንብረት ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ
  5. በተፈጥሮ ሀብት፣ በአካባቢ፣ በታሪካዊ ወይንም የባህል ቅርስ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ
  6. ማንኛውንም የህዝብ አገልግሎት ለከፍተኛ አደጋ ያጋለጠ፣ የያዘ፣ በቁጥጥር ስር ያደረገ፣ ያቋረጠ ወይንም ያበላሸ እንደሆነ ወይንም
  7. ከላይ የተጠቀሱትን ለመፈጸም የዛተ እንደሆነ በሽብርተኝነት እንደሚወነጀል ይገልጻል፡፡ ለጥፋቱም ከ15 አመት ጀምሮ የእድሜ ልክ ብሎም የሞት ቅጣት እንደሚያስወስንበት አስቀምጧል፡፡
ከላይ ከተጠቀሱት መካከል አብዛኛዎቹ ዝርዝሮች ህጉ ተወሰደባቸው ከሚባሉት የዴሞክራሲያዊ አገራት ጸረ ሽብር ህግ ያልተካተቱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል “ማንኛውንም የህዝብ አገልግሎት ለከፍተኛ አደጋ ያጋለጠ፣ የያዘ፣ በቁጥጥር ስር ያደረገ፣ ያቋረጠ ወይንም ያበላሸ” የሚለው በሰላማዊ እምብይተኝነት ጊዜ የሚፈጸምና በሌሎች አገራት ሽብርተኝነት ቀርቶ ተራ ወንጀል ስምም አያስከስስም፡፡
ዝርዝሮቹ በቂ ባለመሆናቸው ትርጉሙን ለማጠናከር ዓላማና ፍላጎት የግድ መጨመር ነበረበት፡፡ በመሆኑም አዋጁ ከላይ የተጠቀሱት ተግባራት ሽብርተኝነት ሊፈርጅ የሚችለው “ማንኛውም ሰው ወይንም ቡድን የፖለቲካ፣ የሀይማኖት ወይንም የአይዲዮሎጃዊ አላማን ለማራመድ በማሰብ በመንግስት ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር፣ ህብረተሰብን ወይንም የህብረተሰብን ክፍል ለማስፈራራት ወይንም የአገሪቱን የፖለቲካዊ፣ ህገ-መንግስታዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ወይንም ማህበራዊ ተቋማትን ለማናጋት ወይንም ለማፍረስ” የሚል አላማና ፍላጎት ይጨምርበታል፡፡ ይህ የሽብር ትርጉሙን ከተራ ወንጀልነት ወደ ሽብርተኝነት የሚቀይረው አብይ ክፍል ሲሆን መንግስታትም በዋነኛ ካርድነት ይጠቀሙበታል፡፡ በተለይ በአገራችን የተደላደለ ፖለቲካዊ ስርዓት ባለመፈጠሩ ምክንያት አብዛኛዎቹ ጥያቄዎች ፖለቲካዊ መሆናቸው አልቀረም፡፡ ከዚህም ባሻገር መንግስትን የተቆጣጠረው ፓርቲ ጥቃቅን ጉዳዮቹን ወደ “ሽብርተኝነት” ለመቀየር የሚያስፈልጉ ዓላማዎች ጋር በማገናኘት የሰላማዊ ትግሉን እያንዳንዱ እንቅስቃሴዎች “በሽብር” ስም እየፈረጃቸው ይገኛል፡፡
ኢቲቪ ታህሳስ 19 ባስተላለፈው ዶክመንተሪ አቶ መለስ ዜናዊ ስለ አዋጁ ዴሞክራሲያውነት ሲናገሩ አሳይቷል፡፡ አቶ መለስ አዋጁን በቀጥታ ከአውሮፓ ህብረት፣ ከእንግሊዝና ከአሜሪካ ቃል በቃል የወሰዱት ቃል ቢቀይሩ ይተቹናል በማለት እንደሆነ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ አቶ መለስ አዋጁ ከእነዚህ አገራት ቃል በቃል ስለተቃዳ ብቻ ምንም እንከን የማይወጣለት ብለውታል፡፡ ይህን የአቶ መለስ ንግግር የተጠቀሙበት አሁንም የኢህአዴግ አቋም (ማሳመኛ) ቢሆን ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ፣ ከአውሮፓ ህብረትና ከእንግሊዝ የተለየ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሰረት ያላት አገር እንደመሆኗ ለራሷ ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ህግ እንደሚያስፈልጋት ጥርጥር የለውም፡፡ ኢህአዴግ በውል የማይተረጉማቸው “አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ ልማታዊ መንግስት” ከአውሮፓ ህብረት፣አሜሪካና እንግሊዝ ኒዮ ሌብራሊዝም ይልቅ ከአገራችን (ከአፍሪካ) ነባራዊ ሁኔታ ተጣጥሞ የተቀረጸ መሆኑን ሲናገሩ ኖረዋል፡፡ የአውሮፓውያን ፖሊሲ ለአውሮፓውያን እንጅ ከአውሮፓ የተለየ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መሰረት ላላቸው አፍሪካውያን እንደማይጠቅም “AFRICAN DEVELOP­MENT: DEAD ENDS AND NEW BEGINNINGS” በሚለው ጽሁፋቸው ሊያስረዱ ሞክረዋል፡፡ ገና በመግቢያውም “የእኔ መከራከሪያ ኒዮ ሌብራሊዝም ያለቀለትና በአፍሪካ ህዳሴ ሊያመጣ የማይችል በመሆኑ የአፍሪካን ህዳሴ ለማምጣት ሌላ ስርዓት ያስፈልጋል የሚል ነው” ይላሉ፡፡ ታዲያ ኢትዮጵያም ሆነች አፍሪካ ከምዕራባዊያን የተለዩ በመሆናቸው ከአውሮፓውያኑ የተለየ ስርዓት ካስፈለጋቸው የጸረ ሽብር ህጉንስ ለምን በቀጥታ መገልበጥ አስፈለገ? ዴሞክራሲ፣ ሰብአዊ መብት፣ የግለሰብ ነጻነት፣ የመሬት ህግ፣ ኢኮኖሚውን ለግል ባለሃብት የማስተላለፍ ለምን እንደ ጸረ ሽብር ህጉ አቶ መለስ ሰለጠኑ ከሚሏቸው ምዕራባዊያን በቀጥታ አልተገለበጡም? የሚሉት ጥያቄዎች ሊያስረዱ የሚችሉት የጸረ ሽብር ህጉ በመልካም ተሞክሮነት ተገልብጦ መጠቀሚያ መሆኑን ብቻ ነው፡፡
ኢህአዴግ ያመነው ስህተት
ይህ ጸረ ሽብር አዋጅ የተለያዩ ክፍተቶች እንዳሉበት እየተተቸ ነው፡፡ ከእነዚህ መካከል ቀዳሚው ከህጋዊ ይልቅ ፖለቲካዊ ትርጉሙ ማመዘኑ ነው፡፡ አንድነት የጸረ ሽብር አዋጁን ለማሰረዝ ለሶስት ወር ባደረገው የድምጽ ማሰባሰብ ሂደት የተደናገጠው ኢህአዴግ ከወራት በፊት በአዋጁ ላይ ከተቃዋሚዎች ጋር ክርክር ማድረጉ ይታወሳል፡ ፡ በክርክሩ ወቅት ተቃዋሚዎችና ገዥው ፓርቲ የተስማሙበት ብቸኛው ነጥብ ቢኖር አዋጁ ከህጋዊ ይልቅ የፖለቲካ ትርጓሜ የተሰጠው መሆኑን ነው፡፡ ተቃዋሚዎች በህገ- መንግስቱ መሰረት ህግ ሊተረጎም የሚገባው በህግ አካላት እንጅ ፖለቲካዊ ሚናን በሚጫዎተው እንዲያውም የአንድ ፓርቲ አባላት በሞሉት ፓርላማ አይደለም በሚል ተከራክረዋል፡፡ በአንጻሩ ኢህአዴግ ሽብርተኝነት ከሌሎች ወንጀሎች ጋር ሊነጻጸር የማይችልና አንገብጋቢ በመሆኑ ፓርላማ ሊያጸድቀው የግድ መሆኑን በመጥቀስ ፖለቲካ ትርጓሜ እንደተሰጠው አምኗል፡፡ በጸረ ሽብር ህጉ መግቢያ ላይም ‹‹በስራ ላይ ያሉት (ህገ መንግስቱን ጨምሮ) የሀገሪቱ ህጎች በበቂ ሁኔታ ሽብርተኝነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ባለመሆናቸው ጠንካራ የህግ አቅም መፍጠር በማስፈለጉ ነው በሚል አዋጁ ከህገ መንግስቱ የተለየ (የጣሰ) መሆኑን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በአንደበቱ ተናግሯቶታል፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 25(1) “የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመንግስት አቅራቢነት አንድን ድርጅት በሽብርተኝነት የመሰየም እና የሽብርተኝነቱን ስያሜን የመሻር ስልጣን ይኖረዋል፡፡” ሲልም “ሽብርተኝነት” ከትርጉሙ ጀምሮ እስከ አፈጻጸሙ ፖለቲካዊ እንጅ ህጋዊ ማዕቀፍን የተከተለ እንዳልሆነ ያስረግጣል፡፡
ከኢትዮጵያውያን በተቃራኒ በሌሎች አገራት መንግስታት ከተቀናቃኞቻቸው ጋር የሚከራከሩት ህጉ ፖለቲካዊ ትርጉም ተሰጥቶታል አልተሰጠውም በሚለው ጉዳይ ላይ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ፖለቲካዊ ትርጓሜ የተሰጠው “ህግ” ከህግነት ይልቅ መጠቀሚያ በመሆኑ ሲሆን ኢህአዴግ ግን የጸረ ሽብር አዋጁ ፖለቲካዊ ትርጉም እንደተሰጠው አምኗል፡፡ በዚህ ረገድ ኢህአዴግ የጸረ ሽብር ህጉን ለራሱ ጥቅም የተጠቀመ መሆኑን ያመነ ብቸኛው ፓርቲ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የፖለቲካ ትርጉሙና አተገባበሩም ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ህጎችና ህገ-መንግስቱ ህዝብንም ሆነ የአገር ድህንነትን ለመጠበቅ የሚደረግ የትኛውም የመንግስት እርምጃዎች የዜጎችን የመደራጀት፣ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽና ሚስጥራቸውን የመጠበቅ ግዴታ እንዳለባቸው ቢያስቀምጡም የጸረ ሽብር አዋጁ እነዚህን ጨምሮ አብዛኛዎቹን ዴሞክራሲያዊ መብቶች በፖለቲካዊ አውዱ ጨፍልቋቸዋል፡፡ በሌላ ጊዜ ደግሞ አዋጁ ህገ መንግስቱን የማይጥስ፣ ህጋዊ ትርጓሜ እንጅ ፖለቲካዊ ትርጓሜ ያልተሰጠው (ለፖለቲካ ጥቀም የማይውል ነው) ሲል ይደመጣል፡፡terror
የጸረ ሽብር አዋጁ በፖለቲካዊ ትርጉምና አተገባበሩ ሁሉንም ነገር ከብሄራዊ ደህንነት ጋር ማገናኘቱ የተለመደ ተግባር ነው፡፡ ሽብርተኝነት ዋነኛው የደህንነት ትኩረታቸው በሆኑት አገራት ሳይቀር ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትና ብሄራዊ ደህንነት አብረው እርስ በእርሳቸው በማይጋጩበት አሊያም መጠቀሚያ በማይሆኑበት መንገድ ተግባር ላይ ይውላሉ፡፡ ‹‹ሽብርን›› መዋጋት ለዜጎች ደህንነት ነውና የዜጎችን ነጻነት የሚነፍግ ተግባር ራሱ ሽብር ከመሆን አያልፍም፡፡ አንዳንዴ ለዜጎች ለራሳቸው እንዲሁም ለአገሪቱ ሲባልም ነጻነታቸው ለደህንነት በሚያመች መልኩ ይቃኛል፡ ፡ በመንግስታት ቅቡልነትና ባህሪ መካከል ያለው ትርጉምና አተገባበር የተለያየ ቢሆንም ሁለቱን በተገቢውመንገድ የማጣጣም ሀላፊነት የሚወስደው ደግሞት መንግስት ነው፡፡
በህዝብ ይሁንታ ስልጣን ላይ ወጥተው ህዝብን የሚያስተዳድሩ መንግስታት አዋጁን የዜጎችንና ብሄራዊ ደህንነትን በማጣጣምና ለማስጠበቅ ይጠቀሙበታል፡፡ በተቃራኒው አምባገነን መንግስታት የጸረ ሽብር ህግ የተፈቀዱና ሰላማዊ የፖለቲካና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን በመቀፍደድ ለራሳቸው ስልጣን ማራዘሚያ በመሳሪያነት ይጠቀሙበታል፡፡ “ARTICLE 19″ የተሰኘ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለ ነጻ ሀሳብና የመረጃ ነጻነት የሚከራከር ተቋም “COMMENT on Anti-Terrorism Proc­lamation, 2009, of Ethiopia” በሚል ጥናቱ የኢትዮጵያው ጸረ ሽብር አዋጅ የህዝብንም ሆነ የብሄራዊ ደህንነትን የማያስጠብቅ የኢህአዴግ መሳሪያ መሆኑን ይደመድማል፡፡ በተቃራኒው አዋጁ ተጠቅሞ ከብሄራዊ ደህንነት ጋር በማይጋጭ መልኩ ለዜጎች ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት መቆም የነበረበት መንግስት ፖለቲካዊ ትርጉም የሰጠውን አዋጅ ተጠቅሞ መሰረታዊ መብቶቻቸውን እየጨፈለቀ እንደሚገኝ ይከሳል፡፡
የትርጉም ግልጽነት
አካላት ህግን ከራሳቸው ጥቅም አንጻር እንደፈለጉ እንዲጠመዝዙ ከሚያችላቸው አጋጣሚ አንዱና ዋነኛው ህጉ የሚኖረው የግልጽነት ችግር ነው፡፡ የግልጽነት ችግር በተለይም ጉዳዩን ለራሱ ጥቅም ለመጠምዘዝ ለሚችለው የበላይነት ያለው አካል መጠቀሚያ ሲሆን አቅም (ወቅታዊ ስልጣን) የሌላቸው ግልጽነት በጎደለው ህግ ተጎጅዎች ይሆናሉ፡ ፡ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያውያ መቼም ቢሆን የህይወት ስምምነት ውልን አይረሱትም፡፡ ጣሊያንኛውና አማርኛው በተምታታና ግልጽነት በጎደለው መልኩ የተጻፈው ውል በብዙ መልኩ ሀይሉ የነበራቸው ጣሊያኖች በፈለጉት መልኩ እንዲጠመዝዙት ሲያስችላቸው ኢትዮጵያውያኑ ደግሞ ተጎጅዎች ሆነዋል፡፡
የኢትዮጵያ “የጸረ ሽብር” አዋጅ ከህይወት ስምምነት የሚለየው ውሉ በኢትዮጵያ መንግስትና በአገሪቱ ህዝቦች መካከል፤ እንዲሁም የትርጉሙ ችግር ከቋንቋ ይልቅ አድበስብሶ የማለፍና ወደሚፈልጉት ለማስጠጋት አመች መሆኑ ብቻ ነው፡፡ አዋጁ ከመጠን በላይ ሰፊና ግልጽነት የሚጎድለው ነው፡፡ ከላይ በዝርዝሩ እንዳየነው በርካታ ተራ ወንጀል እንኳን የማይሆኑ የሰላማዊ ትግል አካላትን ጭምር በትርጉሙ አካቷል፡፡ ተራ ወንጀልነት በሌላ ህግ ሊታዩ የሚችሉትን ተግባራትም ከበስተጀርባቸው የራሱን ዓላማና ትርጓሜ በመጨመር ወደሚፈልፈው “የሽብር” አይነት ይቀይራቸዋል፡፡ አዋጁ “ንብረት”፣ “በሽብርተኝነት የተገኘ ንብረት”፣ “እገታ ወይንም ጠለፋ”፣ “ማነሳሳት”፣ “የህዝብ አገልግሎት”፣ “መንግስት”፣ “ፍርድ ቤት”፣ “ፖሊስ”፣ “ሰው” የሚሉትን ተራ ቃላት በግልጽ ደግሞ ደጋግሞ በተረጎመበት “ሽብርተኝነት” የሚለውን ተግባር ግን ግልጽነት እንደጎደለው በአከራካሪነት እንደተሞላ አልፎታል፡፡ ይህም የሆነው አሸባሪነት በግልጽነት ከሚተረጎም ይልቅ በድፍኑ ለመግዢያ መሳሪያነት ስለሚያገለግለው ነው፡፡
ከምንም በላይ አዋጁ በሰላማዊ ትግል፣ ሽብር፣ የትጥቅ ትግልና ተራ ወንጀል መካከል ያሉትን ልዩነቶች ለይቶ ለማወቅ አለማስቀመጡ አዋጁንም ስልጣን ላይ ያሉት ለጥቅማቸው የሚጠመዝዙት የዘመኑ የህይወት ውል ያደርገዋል፡፡ በአንቀጽ 3(6) ማንኛውንም የህዝብ አገልግሎት ለከፍተኛ አደጋ ያጋለጠ፣ የያዘ፣ በቁጥጥር ስር ያደረገ፣ ያቋረጠ ወይንም ያበላሸ እንደሆነ ይላል፡፡ ይሁንና እነዚህ ተግባራት በሰላማዊ እምብይተኝነት ላይ የተለመዱ ስልቶች በመሆናቸው ከሽብርተኝነት ይልቅ ለሰላማዊ ትግል አካል ናቸው፡፡ ይሁንና ከ1997 አብዛኛዎቹ ተግባራት ሲተገበሩ ያየው አሊያም ሊተገሩ ሲሉ ፈርቶ በሀይል ያስቆመው ኢህአዴግ ወደ ሽብር አስጠግቷቸዋል፡፡ አዋጁ በሰላማዊ ትግል፣ ሽብር፣ የትጥቅ ትግልና ተራ ወንጀል ላይ ግልጽነት ቢኖረው እና ከፖለቲካዊ ይልቅ ህጋዊ ትርጉም ቢሰጠው ፓርላማ በአሸባሪነት የፈረጃቸው የአገራችን ድርጅቶች እና አልቃይዳ መካከል በአንድ አውድ ውስጥ ሊቀመጡ እንደማይችሉ ግልጽ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ለጸረ ሽብር አዋጅ መሰረት የሆነችው አሜሪካ የኢትዮጵያ ፓርላማ መካከል ያለውን ልዩነት መግለጽ ተገቢ ነው፡፡ ኢህአዴግ በበላይነት የሚመራው ፓርላማ የኢትዮጵያዎቹ ድርጅቶችና ግለሰቦች እንዲሁም አልቃይዳና አልሻባብ በአንድ አውድ አጭቋቸዋል፡፡ በተቃራኒው አሜሪካ የኢትዮጵያዎቹና አልቃይዳ እጅጉን የተለያዩ መሆናቸው ለማመን የሚያስችላት ህጋዊ ማዕቀፍን የተላበሰ “ጸረ ሽብር ህግ” በማጽደቋ ኢህአዴግ ለሚያሳድዳቸው መጠለያ ሆናለች፡፡
መንግስታት ዜጎች፣ ቡድኖችንን በምርመራ፣ በእስራትና በመሳሰሉት ህዝቦችን በርዕዮታዊ፣ ሀይማኖታዊና ፖለቲካዊ አቋማቸው ከመፈረጅ ይድኑ ዘንድ የጸረ ሽብር ህጉን ግልጽ በሆነ መንገድ ሊተረጉሙ ይገባቸዋል፡፡ በሽብርተኝነት ምክንያት ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ለህዝብም ሆነ ለአገር ደህነነት ሲባል እንዲወሰን ግድ የሚለው ሀሳብን የመግለጽ መብት ርዕዮታለማዊ፣ ሀይማኖታዊ፣ ወይንም የተደራጀ ወንጀልን በማራመድ በመንግስትና ባለስልጣናት እንዲሁም በህዝብ ላይ “ሽብር” ይፈጥራል በሚል ነው፡፡
የጸረ ሽብር ህጉ ሽብርተኝነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚሳተፉትን ፈርጇል፡፡ ሆኖም ህጉ እንዲህ አከራካሪና ፖለቲካዊ አላማ በያዘበት ሁኔታ በአንቀጽ 6 ሽብርተኝነትን ስለማበረታታት፣ አንቀጽ 7 በሽብርተኝ ድርጅት ውስጥ ስለመሳተፍ፣ በአንቀጽ 8 ለሽብርተኝነት ድርጊት መፈጸሚያነት እንዲውል ንብረት መያዝ ወይም መጠቀም፣ በአንቀጽ 9 በሽብርተኝነት ድርጊት የተገኘን ንብረት ስለመያዝና መገልገል፣በአንቀጽ 10 ምስክር ማባበል ወይንም ማስፈራራትና ማስረጃ ማጥፋት፣ በአንቀጽ 11 በሀሰት የሽብርተኝነትን ድርጊት ስለማስፋፋት፣ በአንቀጽ 12 የሽብርተኝነት ድርጊቶችን አለማስታወቅ የሚሉት ከህጋዊ መሰረት ይልቅ አወዛጋቢና በህዝብ ላይ አሉታዊ መሆናቸው የማይቀር ነው፡፡
የሽብርተኝነትን ጉዳይ የሚከታተሉ ተቋማት ውስጥ (1) አቃቢ ህግና ፖሊስ፣ (2) የደህንነት ሰራተኞች፣ (3) የጸረ ሽብር አስተባባሪ ኮሚቴ፣ (4) በሽብርተኝነት ወንጀል የዳኝነት ስልጣን በሚል ሲቀመጥ ዳኞች በአራተኛ ደረጃ ላይ ነው የተቀመጡት፡፡ ምንም እንኳ ዳኝነቱም በገዥው መንግስት ቁጥጥር ስር የወደቀ ቢሆንም መጀመሪያ ሽብርተኝነትን ደህንት፣ የጸረ ሽብር አስተባባሪ ኮሚቴ የመሳሰሉት ከገዥው ፓርቲ ጋር ልዩነት የሌላቸው አካላት ስለ ሽብርተኝነት ቀድመው የመወሰን አቅም አላቸው ማለት ነው፡ ፡ ይህም የሚያሳየው ገዥው ፓርቲ ከተጽዕኖው ያልወጣውን ፍርድ ቤትም ቢሆን የደህንነትና የጸረ ሽብር ግብረ ኃይልን ያህል “አላማየን ያስፈጽምልኛል!” ብሎ እንደማያምነው ነው፡፡ ጌታቸው ሺፈራው (ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ)
http://www.goolgule.com/the-mystery-terrorism/

Sunday, April 13, 2014

በሞት አፋፍ ላይ ተቀምጠው እውነትን የፈሩ

ብሩክ ሲሳይ (አዲስ አበባ)

ያለወትሮዬ ሴንትራል ሆቴል ቁጭ ብያለሁ ከጎኔ ሁለት ሽማግሌዎች ተቀምጠዋል ብቻዬን በመሆኔ እና የሽማግሌዎች ወግ ስለምወድ እነዚህ ሁለት አዛውንቶች የሚያወሩት ወሬ ላይ ጆሮዬን ጥያለሁ፤ ከአገራችን ፖለቲካ ጀምሮ እስከ ልጅነት ህይወታቸው እና ሌሎችም ብዙ ነገሮችን እያነሱ ያወራሉ። ከወሬያቸው እንደተረዳሁት አንደኛው አዛውንት ከአሜሪካ ቨርጂኒያ ለእረፍት የመጡ ዲያስፖራ ናቸው ሌላኛው ደግሞ በኢህአዴግ የፖለቲካ ስልጣን በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃወች ያገለገሉ እና ኢህአዴግ መጥጦ መጥጦ የወረወራቸው አዛውንት ናቸው። ወሬያቸው ግሏል ግንቦት 7 እና የግብፅ እና የሻብያ ተላላኪዎች፣ የጨረቃ ቤቶች፣ የመተማ እና የሱዳን ጠረፍ መሬቶች፣ መለስ ዜናዊ፣ ብርሀኑ ነጋ፣ ሟች ጳጳስ ጳውሎስ፣ አልማ፣ የዲያስፖራው አክራሪነት ወዘተ አይነት ነገሮች እየተወሩ ነው። ጋባዥ ስለሆኑ ነው መሰለኝ ብዙ የሚያወሩት ዲያስፖራው አዛውንት ናቸው ተጋባዥ አዛውንት ደግሞ ራሳቸውን በመነቅነቅ ድጋፍ ይሰጣሉ።Russian old Lada's in Addis Ababa, Ethiopia
የጨረቃ ቤት መፍረስ ትክክል ነው አሉ ዲያስፖራው ብዙ ማብራሪያ በመስጠት ፣ ያኛው አዛውንት ደግሞ የተዋጠላቸው አይመስልም ወደ እኔ ዞሩ እኔ ደግሞ ያልሰማሁ ይመስል ሞባይሌን መነካካት ያዝኩኝ ግን ጆሮየም ልቤም ወሬው ላይ ነው። አዛውንቱ ዲያስፖራ የሚናገሩት በሙሉ ያበሽቃል ብቻ ግን እኔ እያዳመጥኩኝ ነው፤ በመቀጠል አልማ አሜሪካ ላይ ገቢ ማሰባሰቢያ ሲያደርግ ቶምቦላ እንደገዙ (ያኔ ደመቀ መኮነን፣ ህላዊ ዮሴፍ፣ ካሳ ተክለብርሀን ወዘተ ሲዋረዱ ማለት ነው)፣ ለአማራ ልማት ብር እንደለገሱ፣ አቡነ መርቀርዮስ የሚባሉት ጳጳስ መለስ ዜናዊ እና አቡነ ጳውሎስ የሞቱት በህዝብ እንባ እና በእግዚአብሄር ቁጣ ነው ብለዋል፣ ወደ ኤርትራም ሶስት ጊዜ በመሄድ አርበኞች ግንባርን አበራትተዋል የአሜሪካን ምዕምናንም ገንዘብ እየዘረፉ ነው በማለት ከላይ ከታች አብጠለጠሉ፣ ሙስሊም ኢትዮጵያውያንንም እንደ ኢራቅ ሊያደርጉን ነው አሏቸው፣ ሰ’ማያዊ ፓርቲዎችንም እነሱ ከእንጦጦ መጥተው ስለ መተማ መሬት ምና አገባቸው እና መንግሥት ያልሰጠውን መሬት ለሱዳን ሰጠ ብለው በውሸት አመፅ ሊያስነሱ የሚፈልጉት እያሉ ሲቀጥሉ አላስችለኝ አለ አቁነጠነጠኝ አፌን በላኝ እኚህ የሽማግሌ ወራዳ አናደዱኝ ከዚያም “ይቅርታ አድርጉልኝ በወሪያችሁ ጣልቃ ገባሁ” በማለት
“የመተማ እና ሌሎች የሱዳን አዋሳኝ መሬቶች እንዳልተሰጡ በምን አወቁ?” አልኳቸው እሳቸው ሲመልሱ
“መንግስት አልሰጠሁም እያለ ነው፣ ጠ/ሚኒስተሩ በቴሌቪዥን ውሸት ነው ብለዋል ይሄን የሚያወሩት ተቃዋሚዎች ናቸው በውሸት ህዝብን ሊያሳምፁ ነው” አሉኝ እኔ ደግሞ ጥያቄየን ቀጠልኩ
“መንግስት መሬት ቢሰጥስ በአደባባይ ሰጥቻለሁ ብሎ የሚያወራ ይመስልወታል? እንዴትስ መንግስትን እና የመንግስት ሜዲያን ያምናሉ? የኛ መንግስት ባለስልጣናት እና ሜዲያዎች እኮ መለስ ዜናዊ መሞቱ እየታወቀ የአዲስ አመት ዘመን መለወጫ ይመጣል የሚሉ ናቸው፣ የባድመ እና ዛላንበሳ መሬቶች በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ዳኝነት ለኤርትራ ተወስኖ እያለ ነገር ግን የኛ መንግስት በውሸት ለኢትዮጵያ ነው የተወሰነው በማለት ህዝብን ሰላማዊ ሰልፍ የሚያስወጣ ነው፣ በ97 ምርጫ የ14 አመት ህፃን ገድለው ባንክ ሊዘርፍ ሲል ነው የተገደለው የሚል መንግስት፣ ሜዲያ እና ማፍያ ባለስልጣናት እንዴት ያምናሉ? ከፈለጉ ደግሞ መሬቱ በሱዳን መንግስት የተወሰደበት ተማሪየን ላገናኘወት እችላለሁ………”
ሰውየው ትንሽ ረጋ አሉ እና “በድንበር አካባቢ ችግር ሊኖር ይችላል ነገር ግን ከግብፅ እና ሻብእያ ጋር በመላላክ እነ ግንቦት 7 እና ብርሀኑ ነጋ ኢሳትን በመጠቀም የሚያናፍሱት ወሬ ነው” አሉኝ። እኔም
“ለምንድን ነው ብርሀኑ ነጋ እና ግንቦት 7 ከሻቢያ ጋር የሚሰሩት?” ብዬ ስጠየቃቸው። እሳቸውም
“ብር ነዋ ሆዳም ስለሆኑ በግብፅ በኩል ገንዘብ ለማግኘት ነው” አሉኝ። እኔም
“ይህ ዶ/ር ብርሀኑ የሚባሉ ሰውየ አገር ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ባለሀብት ናቸው፣ ቤተሰቦቻቸውም እንደዚያው ናቸው። ታዲያ ይሄን ሰው ብር ፈልገው ነው ማለት አይከብድም ወይ? ደግሞስ ብር ቢፈልጉ ይህ ሰውየ ከኢህአዴግ ጋር ተሞዳሙደው አገሪቱን መዝረፍ ያቅታቸዋል ብለው ነው? ህሊናን ሽጦ ከዚህ መንግስት ጋር ተሞዳምዶ ሀገር መዝረፍ እኮ በጣም ቀላል ነገር ነው ምናልባት ለእርሰዎ ከብዶዎት ካልሆነ?” ስላቸው መልሳቸውን ወደ ምክር በማዞር
“እናንተ ወጣቶች እየተሸወዳችሁ ነው፣ በዚህ እድሚያችሁ መስራት፣ መማር፣ ገንዘብ መያዝ ነው ያለባችሁ እዚያ አሜሪካ ሁሉም ስራ ላይ ነው ታች ላይ የሚለው፣ እንደ እኛ ጊዜ አትሸወዱ እየው ሀገሪቱ እያደገች ነው በዚህ እድል መጠቀም አለባችሁ” አሉኝ እኔ ደግሞ ቀጠልኩኝ
“እርሰዎ ከአሜሪካ መጥተው የነፃ መሬት ከመንግስት ተበርክቶለዎት ለንግድ ቤት የሚሆን ህንፃ እየሰሩ ነው። እኔ ግን ህዝቤን እያገለገልኩ ለቤት መስሪያ የምትሆን ቁራጭ መሬት መንግስት ነፍጎኛል፣ ይህች አገራችን ለልጆቿ በቀላሉ የምታበረክተው ነገር ቢኖር መሬት ነበር ነገር ግን ይህንን ቀላሉን ነገር ተነፍገናል። ታዲያ የእርሰዎ ሀገር ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት ለእኔ አገሬ ናት ማለት እችላለሁን? ኢትዮጵያ ውስጥ በሀገሬ ያለኝ መብት ከአንድ ሱዳናዊ ወይም ህንዳዊ ግለሰብ ያነሰ ነው” ስላቸው “ተሳስተሀል መሬት ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለም ለዜጋው ለውጭ ሰዎች እየተሰጠ ነው ግን እኛ ሰነፎች ስለሆነ እና መስራት ስለማንወድ መሬቱን አንጠቀምበትም” አሉኝ። እኔም በመቀጠል
እርሰዎ ዕድሜዎ እየገፋ ነው፣ ከዚያ ላይ ሃይማኖት አለዎት እንደው ቢያንስ እንኳን በአይንዎት እያዩ ያሉትን ነገር እንዴት እንዳላዩ ይሆናሉ፣ ውስጠዎ ምን እያሰበ እንደሆነ እረዳዋለሁኝ እውነታውን በልበዎ ያውቁታል ነገር ግን እንደ እርሰዎ አይነት ሽማግሌ ሆኖ ያውም መረጃ በቀላሉ ከሚገኝበት አሜሪካ ተቀምጠው በዚህ ደረጃ ማሰብዎ ይገርመኛል” አልኩኝ።
ሌላ ተጋባዥ የእሳቸው ጓደኛ መጣ እና በሰላምታ ምክንያት ክርክሩ ተቋረጠ እኔም ተነስቸ ሄድኩኝ። ነገር ግን እስካሁን በህይወቴ እንደዚህ አይነት አይነ ደረቅ ሆዳም ሽማግሌ አጋጥሞኝ አያውቅም። ያውም እኮ እድሜው ወደ 70 አካባቢ ይሆናል። አገር ሲዘቅጥ እንደዚህ ነው በሞት አፋፍ ላይ ተቀምጠው እውነትን የፈሩ የሚያናድዱ ሽማግሌ ናቸው።
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11780/

አባይን ለመንከባከብ የጎሰኛነት አገዛዝ በዲሞክራሳዊ አገዛዝ መተካት አለበት (ዶ/ር አክሎግ ቢራራ)

አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)

Click here for PDF

Ethiopia's dam on Abbay/Nile river
ክፍል አንድ
“ለምንወደው ለዛሬው ሕዝባችንም ሆነ፤ ከዘመን ወደ ዘመን ለሚከተለው ትውልድም ጭምር፤ የዓባይን የውሃ ሃብት ለሕይወቱ ደህንነትና ለፍላጎቱ ማርኪያ እንዲውል ማድረግ፤ ኢትዮጵያ ከፍ ያለ ግምት የምትሰጠውና በቅድሚያ የሚያሳስባት ጉዳይ ነው።
አምላካችን ያበረከተላትን ይህን ሃብቷን ለሕዝባቸው ህይወትና ደህንነት በማዋል እንዲጠቀሙበት ከጎረቤት ወዳጅ አገሮች ጋር በለጋስነት በጋራ ለመካፈል ዝግጁ ብንሆንም፤ ይህን የውሃ ንብረቷን በቁጥር እየጨመረ ለሚሄደው ሕዝቧና በማደግ ላይ ላለው ኢኮኖሚ ጥቅም እንዲውል ማድረግ የኢትዮጵያ ተቀዳሚና የተቀደሰ ግዴታዋ ነው።”
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፤ ጥቅምት 1957 ዓም
“ወንዞችን በጋራ ፈሰስ የሚጋሩ አገሮች ሁሉ ውሃውን አግባብ፤ ፍትሃዊ፤ ለሁሉም ጠቃሚ በሆነ መንገድ የመጠቀም መብትና ግዴታ አለባቸው። ይህን ሲያደርጉ በተቻለ መጠን ለጋራ ጥቅም በመመካከርና አንዱ ሌላውን ሳይጎዳ፤ ውሃውንና አካባቢውን ዘላቂነት ባለው መንገድ በመንከባከብ ይሆናል።”
Convention on the Law of the Non-navigational Uses of International Watercourses, UN General Assembly resolution 43/52 of December 1994.
አባይን የመጠቀም ጥያቄ አጼ ኃይለ ሥላሴ ከላይ ከተናገሩት በበለጠ ደረጃ ዛሬ ወሳኝ ሆኗል። ባሁኑ ወቅት በዓለም አከራካሪ፤ አሳሳቢና ጦርነትን ፈጣሪ ከሆኑ አንኳር ጉዳዮች አንዱ ውሃንና ወንዞችን የመጠቀም መብት ነው። ከፍተኛ ሽሚያና ሴራ አለ። ጉዳዩን ያጠኑ ግለሰቦችና ተቋሞች እንዲህ ይላሉ። “የዛሬ አስራ ስድስት ዓመት (2030) የዓለም ሕዝብ ብዛት እየጨመረ፤ ፍላጎት እያደገ፤ ከተሜነትና ልማት እየተስፋፋ ስለሚሄድ፤ አራት ቢሊዮን ሕዝብ የውሓ እጥረት ያጋጥመዋል። ከዚህ ውስጥ ብዙ መቶ ሚሊዮን የሚገመተው በአፍሪካ ቀንድ፤ በሰሜን አፍሪካ፤ በሳሄል አገሮች ይገኛል።” ከሳሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ሕዝብ ዛሬ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ሲገመት፤ በተባበሩት መንግሥታት ስሌት፤ በ2050 ይህ ቁጥር ወደ ሁለት ነጥብ አራት ቢሊዮን ከፍ ይላል። የውሃ ተፋሰስ ተፎካካሪ ወደ ሆኑት ግብጽና ኢትዮጵያ ብናተኩር የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ዛሬ ካለው እጥፍ ይሆንና ቢያንስ መቶ ሰማንያ አምስት ሚሊዮን ይደርሳል። ቀድሞ የተባበሩት መንግሥታት ከገመተው ዝቅ ብሏል ማለት ነው። በአንፃሩ፤ የግብፅ ሕዝብ ብዛት መቶ ሃያ አምስት ሚሊዮን ይሆናል። ኢትዮጵያ በሕዝብ ብዛት ግብፅን በስድሳ ሚሊዮን ሕዝብ ትበልጣለች ማለት ነው። ሆኖም፤ ከግብፅ ጋር ለመወዳደር፤ የኢትዮጵያን ብሄራዊ አንድነት፤ የመላዊ ሕዝቧን ኢትዮጵያውይነት መቀበል ወሳኝ ነው። በተጨማሪ ሁሉም ኢትዮጵውያን የሚሳተፉበትና ክፍጹም ድህነት የሚላቀቁበትን ዘላቂና ፍትሃዊ ኢኮኖሚ መመስረት ያስፈልጋ። ማንኛውም አገር በአፈና፤ በጎሰኛንትና በስደት በተበከለ አገዛዝ ጠንካራ ሕብረተሰብና ጥንካራ አገር ለመመስረት አይችልም። ኢትዮጵያ ታሪክ ያላት፤ መነሻና መድረሻ ያላት፤ ታላቅ ለመሆን የምትችል፤ የብዙ ብሄር/ብሄረሰብ ደሴት መሆኗን ተቀብለን ከልዩነቶች በላይ የሚገልጻት ዋናው እሴት ኢትዮጵያ አንድ አገር መሆኗን መቀበል፤ ዜግነት ኢትዮጵያዊ እንጅ ጎሳዊ አለመሆኑን በማንኛውም ግንኙነት ማስተጋባት የወቅቱ ጥያቄዎች ናቸው እላለሁ። ይኼን የተቀደሰ መርህ እንደዋዛ ካየነው፤ ኢትዮጵያን ለሌሎች (ጥቂት ተጠቃሚዎችና ለፈረንጆች) እንደምናስተላልፋት በአይናችን እያየን ነው። ዛሬ ኢትዮጵያውያን በጎሳ ስለተከፋፈሉ፤ መብታቸውና ነጻነታቸው ስለታፈነ በሃገራቸው የተፈጥሮ ሃብት፤ በቤታቸው፤ በመሬታቸው፤ ብህይዎታቸ፤ በሃብታቸው፤ ለማዘዝ አይችሉም። ለመጀመሪያ ጊዜ ፈረንጆች ከኢትዮጵያዊን የበለጠ ተሰሚነትና መብት አላቸው። አስደናቂውና የሚያኮራው የመሰረታዊ ለውጥ ምልክት ወጣቱ ትውልድ “መብት ይጠየቃል፤ አይለመንም፤ ፍርሃት አልወለደንም፤ በህሊናየ አታዝም” እያለ በደሴ፤ በሃህር ዳር፤ በጎንደር፤ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች የሚያሰማው ድምፅ ነው። ሌሎቻችን እጆቻችን አጣጥፈን የምንመለከት ጊዜ ያለፈ ይመስለኛል። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11773/

Saturday, April 12, 2014

አንድ ባርያ ነጻ የሚወጣው መቼ ነው? ሲፈቅድ ነው? ወይስ ሲፈቀድለት?

መስፍን ወልደ ማርያም
መጋቢት 2006
በአለፈው ሳምንት (ፋክት ቁጥር 36) ወይዘሮ መስከረም የተለያዩ መጻሕፍትን በመጥቀስ በሴቶች ላይ ያለውን መጥፎ ጫና በደንብ ያስመሰከረች ይመስለኛል፤ ግን እኮ በሴቶች ላይ ያለው ጫና የቆየ፣ ክፉና ጎጂ መሆኑን ማንም ያውቀዋል፤ ቁም-ነገሩ ያለው ከዚያ የባህል ጭነት በራስ ጥረት ወጥቶ፣ ነቀፌታንም ሆነ እርማትን ለመቀበል ሳይፈሩና ሳያፍሩ እንደመስከረም በአደባባይ ሀሳብን በመግለጽ በአገርና በወገን ጉዳይ መሳተፍና ሌሎችም እንዲሳተፉ የተቻለን ሁሉ ማድረጉ ላይ ነው፤ ለዚህ ነው ይህንን መልስ የምጽፈው፤ ወይዘሮ መስከረም በአጋጠሟትና በምታያቸው እንቅፋቶች ላይ ማተኮርዋ እንደርስዋ መንፈሳዊ ወኔው የሌላቸውን ያስፈራራቸዋል እንጂ አያበረታታቸውም፤ የማንንም አፍአዊ ጫና ተቋቁመው በራሳቸው የውስጥ ኃይል እንዲመሩ እናድርግ።
አንድ መጽሐፍን በመጥቀስ ወይዘሮ መስከረም የሚከተለውን ጽፋለች፡–
ፈጣሪ የሠራውን  ውጫዊ  ገጽታን ማሽሞንሞን በቂ እንደሆነ ሲነገራት የኖረች ሴት፣ በምን ተነሳሺነት አእምሮዋን የሚመግብ  እውቀት ልትሻ ትችላለች? … በልጅነት እውቀትን  ወደመሻት ያልተገፋ ማንነት በጉብዝና ወራት አላዋቂ በመሆን ቢወቀስ ትርጉም አይኖረውም፤ …››
ወይዘሮ መስከረም ሔዋን ሲነገራት የማትሰማ የመጀመሪያዋ ሰው (ልብ በሉ ሴት አላልሁም፤) መሆንዋን እንዴት እስከዛሬ ሳታውቅ ቀረች? ባለመጽሐፉም ይሁን መስከረም የሔዋንን ታሪክ ሳያነሡ መቅረታቸው መሠረታዊ ስሕተት ነው፤ በተጠቀሱት ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ አንድም እውነትን የሚመስል ነገር የለም፤ መስከረም ‹‹የሔዋን ዘር›› ከማለት በፊት የሔዋንን ሥራ ቆም ብላ ብታስታውስ የጠቀሰችውን መጽሐፍ እኔ እንደምነቅፈው ትነቅፈው ነበር፤ የሔዋን ታሪክ የሚነግረን የሚከተለውን ነው፡ ‹‹ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፣ ለጥበብም  መልካም እንደሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ፤ የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፤›› ዘፍ. 3
የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ ማለት ‹‹እንደእግዚአብሔር መልካምንና ክፉን የሚያውቁ›› ሆኑ ማለት ነው፤ አሁንም ሔዋን መስከረምና ባለመጽሐፉ እንዳቀለሏት አለመሆንዋን መረዳት ይቻል ነበር፤ እንዲያውም ከዚህ በፊት እንደጻፍሁት ሔዋን የመጀመሪያዋ አብዮተኛና የነጻነት እናት ነች ለማለት ይቻላል! በአንጻሩ አዳም የፍርሃት አባት ነው፤ ‹‹ራቁቴን ስለሆንሁ ፈራሁ፤›› ያለው እሱ ነው! ስለዚህ ወይዘሮ መስከረም ‹‹የሔዋን ዘር›› የምትለውን በድላለችና ይቅርታ መጠየቅ ሳያስፈልጋት አይቀርም!
ሔዋን የተጠቀመችው ውጫዊ ገጽታን የሚያሽሞነሙን ሳይሆን የውስጥን የመንፈስ ኃይል ቆፍሮ በማውጣት ነበር፤ በዚህ የውስጥ ኃይል ለሚጠቀም ከውጭ ግፊት አይጠብቅም።
‹‹እውቀትን ወደመሻት ያልተገፋ ማንነት›› አይወቀስም፤ ትላለች ወይዘሮ መስከረም፤ እየተገፉ የሚገኘው ባርነት ነው፤ እውቀት የሚገኘው በነጻነት ነው፤ መገፋት ከእውቀት ያርቃል እንጂ ወደእውቀት አያስቀርብም፤ የመስከረም ዋናው መልእክት ሰላቢውን እንጂ ሰለባውን አትውቀስ የሚል ነው፣ ወይም የኔ ሀሳብ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ዓይነት ሆኖባታል፤ ለመሆኑ ሰለባ የሚሆን ከሌለ ሰላቢ ይኖራል ወይ? ሰለባ ከመሆን በፊት ሰለባ ላለመሆን መጣር አንዱ የኑሮ ዓላማ አይሆንም ወይ? ከዚህ በፊት ስለጨቋኝና ተጨቋኝ ደጋግሜ ጽፌ ነበር፤ ጭቆና የጨቋኙ ባሕርይ የሚሆነውን ያህል የተጨቋኙም ባሕርይ ይሆናል፤ ለጨቋኙ ጭቆና የሚጠቅመውን ያህል ለተጨቋኙም ጭቆና ይጠቅመዋል፤ ለጨቋኙ ጭቆና የኑሮው መሠረት የሆነውን ያህል ለሚርመሰመሱት የጨቋኝ ሎሌዎች ጭቆና የኑሮ መሠረታቸው ነው፤ እንዲህ እያለ ወርዶ ወርዶ የጭቆና ጠቃሚነት ለሎሌው ሎሌ፣ ለሎሌው ሎሌ ሎሌ … በኢትዮጵያ ምናልባትም የመጨረሻዋ የጭቆና ሰለባ ሚስት ትሆናለች፤ ወይም ልጆች ይሆናሉ! ጨቋኝና ተጨቋኝ የባሕርይ ቁርኝት አላቸው፤ አንዱ ያላንዱ አይኖርም፤ ወይዘሮ መስከረም ይህ እውነት ያልሆነበት ሁኔታ ወይም አጋጣሚ የምታውቀው ካለ ብታጋራን ደስ ይለኛል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ሙታናቸውንም እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤›› የሚለው ኢየሱስ ክርስቶስ የሞቱትንና በቁማቸው የሞቱትን ሲያመሳስላቸው ነው! ለእኔ የሚታየኝ እንዲህ ነው።
መስከረም ብዙ ታላላቅ ሴቶችን ጠቅሳለች፤ በእስዋ ግምት ሁሉም በአባታቸው ወይም በባላቸው እየተገፉ ወደትልቅነት መድረኩ የወጡ ናቸው፤ አዙራ ብታየው የጠቀሰቻቸውን ሴቶች ገፉ የምትላቸው ወንዶች መጀመሪያውኑ በሴቶቹ ተገፍተው እንደነበረስ ሊታሰብ አይገባም? ምናልባት ከጠቀሰቻቸው ሴቶች ይልቅ መስከረም የሄለን ኬለርን ታሪክ ብታስታውስ ኖሮ መገፋትን አታነሣም ነበር፤ ሄለን ኬለር በሕጻንነትዋ ዓይኖችዋም ጆሮዎችዋም ሥራቸውን አቆሙ፤ የሄለን ኬለር የመንፈስ ጥንካሬ ከውስጥዋ አዲስና የተሻሉ ዓይኖችንና ጆሮዎችን እንድታበቅልና እንድትማር፣ ከታወቀ ዩኒቨርሲቲም የመጀመሪያዋ ሴት ምሩቅ ለመሆን እንድትበቃ አድርጓታል፤ ይህች አስደናቂ ሴት ከመቶ ሠላሳ ዓመታት ግድም በፊት ማኅበረሰቡ በሴቶች ላይ የነበረውን አጥር ሰብራ፣ ዓይኖችዋ ባለማየታቸውና ጆሮዎችዋ ባለመስማታቸው የገጠማትን እክል አሸንፋ ራስዋን ከወንዶች በላይ ለማድረግ በቅታለች።
መገፋትን የሚፈልግ ሁሉ፣ ካልገፉት የማይነቃነቅ ሁሉ፣ ሬትን ሲግቱት ይጣፍጣል እያለ የተቀበለ ሁሉ፣ ዶሮ ማታ፣ ዶሮ ማታ፣ እያሉ አታልለው እንኳን ዶሮ የለም ሹሮ ሲሉት የማይናደድ ሁሉ፣ ምኞቱ ልደግ ልመንደግ እያለ ሲነዘንዘው በአፈና ጭጭ የሚል ሁሉ ለወቀሳ ብቻ አይደለም ለውርደትም ክፍት ነው፤ ስለዚህም ተወቅሶ ከውርደት ከዳነ ወቀሳው ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ማለት ነው፤ ዞሮ ዞሮ የሰው ልጆች ሁሉ — ሴት፣ ወንድ፣ ወጣት ሽማግሌ-አሮጊት፣ ባለሥልጣን ተራ፣ ገበሬ ነጋዴ፣ ወታደር ፖሊስ፣ አስተማሪ አስተዳዳሪ፣ ዳኛ ጠበቃ፣ ሀኪም መሀንዲስ፣ … — የፈለገውን ቢሆን ላለበት ሁኔታ ኃላፊነቱ የራሱና የግሉ ነው፤ ራሱን የሚገነባው ወይም ራሱን የሚንደው ራሱ ነው፤ ሰበብ እየፈለጉ ከዚህ ኃላፊነት መውጣት ቀላል ቢመስልም ተመልሶ እምቦጭ ነው፤ ዳገቱን ለመውጣት የሚመረውን እውነት መቀበል ያሻል።
በመጨረሻም በማናቸውም መንገድ፣ በማናቸውም ጊዜ፣ በየትኛውም ቦታ ወደቁልቁለት የሚገፉትን ወይም የሚነዱትን ‹‹እምቢ!›› ብሎ ድምጹን ያላሰማ ገደል ገብቶ ሲንፈራፈር ከራሱ በቀር የሚወቅሰው የለም፤ አቅመ-ቢስነት ከውጭ አይመጣም።
Ze-Habesha 

ስለፍትሕ ሲባል፤ ሥርዓቱ ይፍረስ! (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ )

ባለፉት አራት አስርታት ሀገሪቱ አያሌ ተግዳሮቶችን መጋፈጧ ባይዘነጋም፤ በተለያየ ጊዜ ሚሊዮኖችን ካረገፈው አሰቃቂው ረሃብ በማይተናነስ መልኩ ሕዝቦቿን ዋጋ ያስከፈለ ጉዳይ ቢኖር የፍትሕ አለመከበር ያስከተለው ሁለንተናዊ ምስቅልቅሎሽ ነው ብሎ ለመናገር የሚያስደፍሩ በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡ የየካቲቱን አብዮት ጠልፎ ሥልጣኑን የተቆጣጠረው ወታደራዊው ደርግ፣ የፍርድ ቤት ደጆችን በጓጉንቸር ቆልፎ ሲያበቃ፣ የራሱ አባላት እጃቸውን እያወጡ ድምፅ በመስጠት በአፄው ባለስልጣናትንም ሆነ ግብረ-አበሮቹ በነበሩ መኮንኖች ላይ የሞት ቅጣትን ያህል የመጨረሻ ከባድ ውሳኔ የማሳለፍን አስደንጋጭ ክስተት ጨምሮ፤ ከከተማ እስከ ገጠር ያደራጃቸው የአብዮት ጠባቂዎችና የገበሬ ማሕበራት ከየቤቱ አንቀው እያወጡ “ነፃ እርምጃ” እንዲወስዱ፣ ከየእስር ቤቱ እየለቃቀሙ በጅምላ እንዲረሽኑ በአዋጅ የፈቀደበት ጊዜ የፍትሕ ምኩራቡ ፈርሶ በግላጭ የተቀበረበት ዕለት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በርግጥ ይህ የማን-አለብኝነት አረመኔያዊ አገዛዝ የታቃውሞውን ጎራ በማጠናከር ታሪካዊ ውድቀቱ እንዲፋጠን ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ እንደነበር ለመረዳት 17 ዓመታትን መውሰዱ አይዘነጋም፡፡

Temesgen Desalegn "Fact" Ethiopian Amharic newspaper editor
“ፍትሕ አልባው አምባ-ገነናዊ የደርግ ስርዓት አማርሮ በርሃ ያስወጣንና ብሶት የወለደን የለውጥ ሃዋርያት ነን፤ በመቃብሩም ላይ ፍትሕ-ርትዕ የሰፈነባት ዲሞክራሲያዊት አገር እንመሰርታለን” በማለት ከበሮ ይደስቁ የነበሩት የያኔው “ነፃ አውጪዎች”፣ ደርግ አፍርሶ የቀበረውን የፍትሕ ምኩራብ አመዱን አራግፈው ቢያነሱትም፤ ባነበሩት አስመሳይ ሥርዓት በኩል በዘውግ ማንነት፣ በሙስናና በሙያ አልባ ዜጎች በክለው ክብር የለሽ ሲያደርጉት በጣት የሚቆጠሩ ወራት እንኳ አልፈጀባቸውም፡፡ ‹‹አዲስ ንጉስ አንጂ ለውጥ መቼ መጣ!›› እንዲል ከያኒው፤ ካስወገዱት የደርግ መንግስት ጋር ልዩነታቸው-ደርጉ ያልቻለበትን የተቃውሞ ድምፆች በአዋጅ እንዲንቀሳቀሱ በአንድ በኩል ፈቅደው፣ በሌላ በኩል መልሶ ለመጨፍለቅ የፍርድ ቤቶችን ባረኮት የመጠቀም ባለ ሁለት ገፅ ብልጠታቸው ብቻ ነው፡፡
ይህ አይነቱ አገዛዝም ሥልጣን በያዘ ማግስት ሀገሪቱን እንዳሻው ለመርገጥ ሲቪል ቢሮክራሲውን ብቻ ሳይሆን የፍትሕ ስርዓቱንም በአምሳሉ አፍርሶ መስራት ነበረበት፡፡ ይሁንና ተቋሙን በዚህ መልኩ ለማዋቀር ጊዜ እንደሚያስፈልግ በመረዳቱ አሁን ድረስ በቂ መከራከሪያ ሊቀርብላቸው የማይችሉ ጉዳዮችን ከፍትሕ ሥርዓቱ ነጥቆ ሕገ-መንግስቱ ውስጥ በመዶል ለሌሎች ሰጥቷል፡፡ ለዚህ ደግሞ በቂ ማሳያ የሚሆነው፤ ሕገ-መንግስታዊነትን አስመልክቶ የሚነሱ የማጣራት ኃላፊነቶችን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት መስጠቱ ነው፡፡ በርግጥ አንዳንድ የወቅቱ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ሕገ-መንግስቱ በተረቀቀበት ሰሞን፣ ከሕገ-መንግስቱ የሚጣረሱ አዋጆች፣ ክሶች አሊያም ኩነቶች ሲፈጠሩ፣ የማጣራቱ ኃላፊነት የፍርድ ቤት መሆን አለበት ሲሉ የተከራከሩ ድምፆች ነበሩ፡፡ ዳሩ ውሎ-አድሮ ምን እንደሚሰሩ አስቀደመው የሚያውቁት ታጋዮች፣ በዛ ካድሬ-ዳኞች ባላፈሩበት ወቅት እንዳሻቸው ሕገ-መንግስቱን እየናዱ ቢያስሩ፣ አዋጅ ቢያወጡና ቢያስፈርዱ ድጋፉን የሚሰጣቸው ተቋም፣ በኢሠፓውያን እንደተሞላ የሚጠረጥሩት ፍርድ ቤት ሳይሆን፣ እንደ ልብ ሊቆጣጠሩት የሚችሉት የፌዴሬሽን ምክር ቤት መሆኑን በመረዳታቸው፣ በፓርላሜንታዊ ሥርዓት ትመራለች በተባለች ሀገር ብዙም ባልተለመደ አኳኋን ሕገ-መንግስታዊ ትርጉም የሚሻቸውን ጉዳዮች የማጣራት ስራን ለዚሁ ምክር ቤት ሰጡት፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎንም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የፍትሕ ተቋሙን በፓርቲ ፖለቲካ የተተበተበ፣ ለጉልበተኛ የሚገብር፣ ገንዘብ ሊገዛው የሚችል፣ ተቀናቃኝ ድምፆችን የማፈኛ መሳሪያ… አድርጎ የመቅረፅ ዓላማቸውን ማሳካት ችለዋል፡፡ በውጤቱም ተቋሙ የህግ የበላይነት የተደፈጠጠበት አድሎአዊና በየጊዜው ደካሞችን የሚያጠቃ ከሆነ እነሆ ከሁለት አስርት በላይ አስቆጥሯል፡፡
የሆነው ሆኖ የሥርዓቱን ፍትሕ ረጋጭነት በተጨባጭ ፍፃሜዎች አስደግፎ ለማቅረብ ሁለት አብነቶችን እጠቅሳለሁ፡፡ ቀዳሚው የበርካታ ግፉአንን እሪታ ሲወክል፤ ተከታዩ ደግሞ የገዥዎቹን የሙስና እና የጓዳ ፖለቲካ ትስስሮች ይጠቁመናል ብዬ አምናለሁ፡፡
የሞገስ ወልዱ-ጩኸት
ሰማይ ከመፍገጓ በፊት፣ ሁሌ ንጋት ላይ ኮተቤ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ተነስቶ፣ በእግሩ ሰከም ሰከም እያለ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ግድም ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይደርስና ዋናው በር ፊት ለፊት ቆሞ ከአንድ ሰዓት ላላነሰ ጊዜ ‹‹ሌባ ዳኛ!›› እያለ ይጮኻል፡፡ ያፏጫል፡፡ ‹‹እናንተ ገላችሁኛል፤ ቀብራችሁኛል፤ አምላክ ፍርዱን ይሰጣል!›› በማለትም ተስፋው በሰማያዊው መንግስት ላይ ብቻ እንደሆነ ያውጃል፡፡ …ይህ ሰው እንደምን ያለ ከባድ በደል ቢደርስበት ይሆን ምሬቱ እንዲህ ጣራ የነካው?
አሳዛኙ የሞገስ ታሪክ እንዲህ ይጀምራል፡- በ1997 ዓ.ም የወላጅ እናቱን ወ/ሮ አስካለ ቢፋ ህልፈት ተከትሎ፣ ወንድሙ ኃይሉ ወልደአማኑኤል የወራሽነት ድርሻውን እንዲያካፍለው ክስ መስርቶ ሲያበቃ፤ ሶስት ጥያቄዎችን ለፍርድ ቤቱ ያቀርባል፡-‹‹ንብረትነቱ የእናታችን የሆነ ቀበሌ 14/15 ውስጥ የሚገኝ 250 ካሬ ሜ. ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት፣ ሁለት ማሳ የእርሻ መሬት እና በንግድ ባንክ አራት ኪሎ ስላሴና መገናኛ ቅርንጫፍ የተቀመጠ መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብን ያካፍለኝ፡፡››
የከሳሽ ወንድም የሆነው ኃይሉም ፍርድ ቤት ቀርቦ ‹‹ቤትም ሆነ የእርሻ መሬት የሚባል ነገር የለም፤ በባንክ አለ ስለሚባለው ገንዘብም አላውቅም፤ እናታችን በሞተችበት ወቅት ስሟን ለማስጠራት ስል የእርሷ የነበረውን መሬት በ30 ሺህ ብር ሸጬ፤ ለአርባ፣ ለመንፈቅ፣ ለተስካር 10 ሺህ ብር ያወጣሁ ሲሆን፤ ቀሪውን 20 ሺህ ደግሞ ለወንድሜ ማረፊያ የሚሆን ቤት ሰርቼበታለሁ›› ሲል ምላሽ ይሰጣል፡፡ ችሎቱም ‹ቤቱንና የእርሻ መሬቱን በተመለከተ የቀረበ ማስረጃ አለመኖሩን› ገልፆ ‹የ30 ሺህው ጉዳይ ግን ያለይግባኝ ባይ ፍቃድ ወጪ የተደረገ ስለሆነ፤ የገንዘቡ ግማሽ 15 ሺህ ብር ድርሻው ስለሆነ እንዲሰጠው› በማለት ወስኖ መዝገቡን ይዘጋል፡፡ በውሳኔው እጅግ በጣም የተበሳጨው ሞገስ፣ ጉዳዩን በይግባኝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይወስደዋል፤ ይግባኝ ሰሚውም ‹‹ቤቱ ይገኝበታል›› የተባለው ቀበሌ የእናታቸውን ማህደር እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ግና፣ ሀገሪቷ ኢትዮጵያ ናትና፤ ቀበሌው ማህደሩ መጥፋቱን፣ ሟችም በተከሳሽ ቤት ይኖሩ እንደነበረ በደብዳቤ ያሳውቃል፡፡ ሆኖም ቀበሌው ይህንን ምላሽ ከሰጠ ከ14 ቀን በኋላ ‹የቀድሞውን አስተዳደር ጠይቄ ያገኘሁት መረጃ ነው› በማለት ለፍርድ ቤቱ እንዲህ የሚል ሌላ ደብዳቤ ይልካል፡- ‹ወ/ሮ አስካለ የግል መኖሪያ ቤት የነበራቸው ሲሆን፣ ቤቱ ያረፈበት መሬት ለ‹‹ሪል እስቴት›› በመሰጠቱ፤ ምትክ ቦታና ስድስት ሺህ ብር ወስደዋል›፡፡
የሰው ምስክሮችም ቀርበው ሟች እናት ቤት ሰርተው እንደነበረ ያረጋግጣሉ፡፡ ይህም ሆኖ የወ/ሮ አስካለ ማህደር ከቀበሌው ‹‹ጠፍቷል›› በመባሉ ምንም አይነት ማስረጃ ስላልቀረበ የቀድሞው ውሳኔ በይግባኝ ሰሚው ችሎትም ሊለወጥ አልቻለም፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ላለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛው ፍርድ ቤት በር ላይ ቆሞ መጮኽን ስራዬ ብሎ ይዞታል፡፡ በርግጥ ከቀን ቀን አካላዊ መዳከም እየበረታበት መሄዱ በግልፅ ቢታይም የ40 ዓመቱ ጎልማሳ ሞገስ ወልዱ ዛሬም ከፍርድ ቤት ደጅ ቆሞ መጮኹና ማፏጨቱ የበርካታ ግፉአንን ድምፅ የሚወክል ይመስለኛል፡፡
ይህ ጉዳይ የሚያሳየው፣ የመንግስት ደመወዝ እየተከፈላቸው በዜጎች ሕይወት ላይ ሊወስን የሚችል እንዲህ አይነቱን ማስረጃ ያለአንዳች ጭንቀት ‹‹ጠፋ›› ብሎ ለመናገር የሚደፍሩ፣ ስለሕዝብ ብሶትና ችግር ምንም ግድ የሌላቸው ካድሬዎች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም እንደ ሞገስ ያሉ የፍትሕ እጦት ረመጥ ሆኖ ያንገበገባቸው ምስኪኖች በአደባባይ ሲጮኹ ውለው፤ ሲጮኹ ቢያድሩ ‹‹ምን ይሆን ችግራቸው?›› ብሎ ለማድመጥ የሚሞክር አንድ እንኳን ባለሥልጣን መታጣቱንም ጭምር ነው፡፡
‹‹ሳይሰሙ ቀርተው ይሆናል!›› ማለቱን ከባድ የሚያደርገው ደግሞ፣ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አካባቢ የሚተላለፉ መንገደኞችም ሆኑ ወደ ተቋሙ የሚመጡ ባለጉዳዮች ክስተቱን የማወቃቸው እውነታ ነው፡፡ ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ሰዎችን የችሎት ውሎ ለመሰለል ከተከሳሾች ቀድመው የሚደርሱ የደህንነት ሰራተኞችም ሞገስን ለማወቃቸው እኔው ራሴ ምስክር ነኝ፡፡
በአናቱም ከዚህ ቀደም በሸገር ራዲዮ ‹‹ኧረ በሕግ›› የሚል ፕሮግራም ያዘጋጅ የነበረውና በአሁኑ ወቅት በ97.1 ኤፍ.ኤም ‹‹የእኔ መንገድ›› የተሰኘ በተመሳሳይ ጭብጥ ዙሪያ የሚያተኩር ፕሮግራም የሚያዘጋጀው በሳሉ የሕግ ባለሙያ ሰለሞን ጓንጉል፣ ይህንን ታሪክ ከአንዴም ሁለቴ ለአድማጭ አድርሶታል፡፡ እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ተደማምረው ነው ከቀበሌ አንስቶ ላይ ድረስ ያሉ መንግስታዊ መዋቅሮችን የዘረጋውና የሚቆጣጠረው የኢህአዴግ አመራር አባላት፣ የሞገስን ጩኸት ‹‹አልሰሙም›› ማለቱን ከባድ ያደረገው (በነገራችን ላይ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ግቢ ለአስር አመት ያህል በየቀኑ እየተመላለሱ የሚቆሙ አንዲት አዛውንት እና በፍትሕ ሚኒስቴር በር ላይ ቆማ መዋል ከጀመረች ስድስት ዓመት ያለፋት ራሄል የተባለች አቤት ባይ እንስት… መኖራቸውን አልዘነጋሁም)
ሙስና እና የጓዳ ፖለቲካ ትስስሮሽ
አገሪቷ በዚህ ሁሉ መፍትሔ እጦትና በፍትሕ መዛባት እየተመሰቃቀለችና በሕዝቦቿም ዋይታ እየተናወፀች ቢሆንም፤ መጽሐፉ ‹‹ዓይን አላቸው አያዩም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙም›› እንዲል፤ ገዥዎቻችን ይህን መሰሉን የድሆችና የአቅመ ደካሞች ብሶት መስማትን ፍፁም አይሹም፡፡ እነርሱ የታጋሉትም ሆነ የሚሰሙት አለቆቻቸውንና ባለፀጋዎችን ብቻ እንደሆነ ከሚያሳዩን በርካታ ማስረጃዎች መሃል ለአብነት አንድ ምሳሌ ላቅርብ፡-
ጉዳዩ በሙስና ተጠርጥሮ በእስር ላይ ከሚገኘው የቀድሞ ገቢዎችና ጉምሩክ ዳይሬክተር መላኩ ፈንቴ ጋር ይያያዛል፡፡ ከዚህ ሰው ሃያ አንድ ገፅ ከፈጀ የእምነት ክህደት ቃል ውስጥ ኮነ ምህረቱ የተባለ ግለሰብ በአራጣ ማበደር ተጠርጥሮ ከተያዘ በኋላ ‹‹እነአየለ ደበላ ለዳኛ ጉቦ ሰጥተው በዋስ ከእስር ተፈትተው፣ ከሀገር ለመውጣት ያስባሉ›› የሚል ‹‹መረጃ›› በመስጠት መተባበሩን ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ እንደነገረው ገልፆ፣ ከእስር እንዲለቀቅ መደረጉን እናገኛለን፡፡ መቼም በሙስና ወንጀል ከተጠያቂነት የሚድን ተከሳሽ የሚሰጠው መረጃ ተጠርጣሪዎችን በሕግ ለመጠየቅ የሚጠቅም ሲሆን እንጂ፤ እንዲህ ባለ ከዋናው ክስ ጋር በማይዛመድ ተራና የአሉ-ባልታ ወሬ አለመሆኑን እነገብረዋህድና እነመላኩ ቀርቶ ማንኛውም መንገደኛ እንኳ ሊጠፋው አይችልም፡፡ አውቆ የተኛ… እንደሚባለው ካልሆነ በቀር፡፡
የሆነው ሆኖ ከመላኩ ፈንቴ የእምነት-ክህደት ቃል ትኩረት የሚስበው፣ ግለሰቡ በዚህ መልኩ ከሱ ተነስቶለት ከእስር ከተፈታ በኋላ ንብረቱና የባንክ ሒሳቡ መታገዱን አስመልክቶ የተፈጠረው ኩነት ነው፡፡ አቶ መላኩ ጉዳዩን ለመርማሪዎቹ ሲያብራራ ቃል-በቃል እንዲህ ነበር ያለው፡-
‹‹አቶ አባይ ፀሀዬ እና አቶ ደመቀ መኮንን ደውለው ‹ግለሰቡ አቤቱታ እያቀረበ ነው፡፡ ለምን አታዳምጡትም? ሲሉኝ፤ እኔም ከዚህ በኋላ ነው ግለሰቡን እቢሮዬ አግኝቼ ከላይ በገለፅኩት ሁኔታ እንዲስተናገድ ያደረኩት፡፡
እነዚህ ሰዎች ‹‹ነፃ አወጣነው›› የሚሉትን ሕዝብ ለስቃይ ዳርገው፣ ጥቂት ባለፀጎችን ብቻ ለማገልገል የቆሙ መሆናቸውን ለማስረገጥ ከዚሁ የእምነት-ክህደት ቃል አንድ ማሳያ ልጨምር፡- ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ የተባለ የአዲስ ልብ ህክምና ክሊኒክ ባለቤት ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው የሕክምና መሳሪያዎች (የልብ ፒስ ሜከር ተብሎ ተጠቅሷል) በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያስገባ በቦሌ ኤርፖርት ጉምሩክ ሠራተኞች እጅ ከፍንጅ ከተያዘ በኋላ መለቀቁን በተመለከተ የህወሓት ከፍተኛ አመራር አባል የሆነው ዶ/ር ቴዎድሮስ አድህኖም ስልክ ደውሎ ‹‹ክሱን ብታነሱላቸውና በአስተዳደራዊ መፍትሔ ብትሰጧቸው›› ብሎ ከመንገሩም በላይ የግለሰቡ ክስ እንዲቋረጥ የሚጠይቅ ደብዳቤ እንደፃፈላቸው መላኩ ፈንቴ ለመርማሪዎቹ መናገሩ በመዝገቡ ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ ይህንን ሁናቴም ከወቅቱ የፖለቲካ አሰላለፍ አኳያ ስንተነትነው አቶ መላኩ ‹ዶ/ር ቴዎድሮስን መስማት፤ ህወሓትን እንደመታዘዝ ነው› የሚል እምነት አድሮበት የተባለውን ፈፀመ ብለን ብንደመድም ተምኔታውያን አያሰኘንም፡፡
እነዚህ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ያውም ሀገር በሚጎዳ ወንጀል የተከሰሰ ተጠርጣሪን በተመለከተ ከሥልጣን ገደባቸው አልፈው ‹‹አድምጥ!›› እያሉ የማዘዛቸው ምስጢር ሥርዓቱ ለፍትሕ ያለውን ግድየለሽነት እና በዚህ ሥርዓት የሕግ የበላይነት ብሎ ነገር እንጦሮጦስ መውረዱን ፍንትው አድርጎ ያሳያል ብዬ አምናለሁ፡፡ በርግጥ ይህንን ጉዳይ ለጥጠን ከተመለከትነው ‹‹…ለምን አታዳምጡትም?›› የምትለዋን ቃል ሰምና ወርቅ የለበሰች ቅኔ አድርገን በመውሰድ ልንፈታት እንችላለን፤ በተለይም መላኩ ፈንቴ ከዚህች ጥያቄ መሰል ትዕዛዝ በኋላ ግለሰቡን ቢሮ ጠርቶ ማስተናገዱን ስናስተውል፡፡
ምንም እንኳን አባይ ፀሀዬ በጊዜው በጉዳዩ ላይ መላኩን ሊያዝበት የሚያስችል መንግስታዊ ሥልጣን /የዕዝ ተዋረድ/ ባይኖረውም፤ አንጋፋ የህወሓት አመራር አባልና የበለጠ የፖለቲካ ጉልበት ያለው መሆኑ፤ ደመቀ መኮንን ደግሞ በብአዴን በኩል የአለቃነቱ ነገር ሲታሰብ፣ አሁንም መላኩ ፈንቴ የተጠየቀውን ‹‹ጥያቄ›› ከማስተናገድ ውጪ ሌላ አማራጭ አይኖረውም ወደሚል ጠርዝ ይገፋናል፡፡ በርግጥ እውነታው ይህ ቢሆንም፣ መላኩ ዛሬም እስር ቤት ውስጥ ሆኖ የቀድሞ አለቆቹንም ሆነ ራሱን ተጠያቂ ለማድረግ አልደፈረም፡፡ በግልባጩ ለቀረቡበት ክሶች በሙሉ ተጠያቂው ገብረዋህድ እንደሆነ ከመናገሩም በላይ እንዲህ በማለት ወንጅሎታል፡-
‹‹የአያት ባለቤት በግብር ማጭበርበር ተከሶ በነበረበት ወቅት የተከሳሹ ቤተሰብ የሆነ ሰው እቢሮዬ መጥቶ ‹ገብረዋህድ ምንም ጥፋት ሳያጠፋ ነው የአያት አክሲዮን ማሕበር ባለቤትን ያሳሰረው፤ አሁንም አንድ ሚሊዮን ብር ካመጣችሁ ከእስር ይፈታል ብሎናል› የሚል ጥቆማ አመጣልኝ፡፡ …ገብረዋህድ እና ነጋ ገ/እግዚአብሔር (የነፃ ትሬዲንግ ባለቤት ነው) ጓደኛሞች ናቸው፡፡ ነጋ ዕቃ ሲያስመጣ አያስፈትሽም፤ የነጋም ጓደኞች እነ አልሳም፣ ጌት አስ የመሳሰሉት ድርጅቶች ዕቃ በቀላል ቀረጥና ታክስ እንዲሁም አልፎ አልፎ ሳይፈተሹ ያልፋሉ፤ …ባለቤቱ ሃይማኖትም፣ በነጋ ድርጅት ውስጥ ትሰራለች…››
መላኩ ፈንቴ ይህንን ጉዳይ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ መናገሩንና ጠቅላይ ሚኒስትሩም፣ ፀጋዬ በርሄን ‹‹ተከታተል›› ብሎት እንደነበረ ከአስረዳ በኋላ እንደሚከተለው ይቀጥላል፡-
‹‹ገብረዋህድ በኋላ እንደነገረኝ ባለቤቱን ከነጋ ድርጅት አስወጥቶ በአዜብ ትዕዛዝ መሰረት ኤፈርት ውስጥ ያስቀጠራት መሆኑን ገልፆልኝ ‹አንተም ላይ የሚወራው ስለምትታገል ነው ብላኛለች አዜብ› ሲለኝ እኔም ተከታትዬ ፀጋዬ በርሄ ከምን እንዳደረሱት አልጠየኩም፡፡ መጠየቅ ነበረብኝ፤ ጥፋት ነው፡፡ በአጠቃላይ ገብረዋህድ ላይ ብዙ ነገር ይባል ነበር፡፡››
መቼም ይህ ምላሽ በ1981 ዓ.ም ከአስመራ ዩንቨርስቲ በኢኮኖሚክስ ዲግሪውን፣ ከአውስትራሊያ በገቢ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪውን፤ ከለንደንም በቢዝነስ አስተዳደር በተመሳሳይ መልኩ ትምህርቱን ካጠናቀቀና የረዥም ዓመታት የስራና የፖለቲካ ተሞክሮ ካለው ሰው የተሰጠ መሆኑን ስናስተውል፤ ሀገሪቱ የአምባገነን ባለሥልጣናት መቀለጃ ብቻ ሳትሆን፤ የሰዎቹንም የአቅም ማነስ ያመላክታል፡፡ እንዲሁም እነሞገስ ሰሚ ያላገኙበትን ምክንያትም ሆነ በዚህች ሀገር ገንዘብ ያለው የፈቀደውን መፈፀም የመቻሉን ምስጢር ይገለፅልናል፡፡
ኢህአዴጋዊ ዕድሜ ማራዘሚያ…
ገዥው ስብስብ የፍትሕ ስርዓቱን ተቋማዊነት ሳይነካ፣ ለጨቋኝነቱ መጠቀሚያ የሚያደርግበት አንዱ መንገድ ከጠቅላይ እስከ ታች በተዋረድ የሚገኙ ፍርድ ቤቶች ድረስ ያሉ ዳኞችን የሚመድብበት አካሄድ ነው፡፡ በርግጥ እንዲህ አይነቱ ሀገርና ሕዝብ አልያም ሞራላዊ ልዕልና እና የሕግ-የበላይነት የማያስጨንቀው አገዛዝ፣ የፍትሕ ስርዓቱ ቅጥ የለሽ ተባባሪነት ሳይታከልበት የሥልጣን ዕድሜውን ማራዘም እንደማይችል መረዳት አይሳነውም፡፡ ይህን ለማድረግም ያለው ብቸኛ ምርጫ ዳኞቹን ከስሩ መሰብሰብ ይሆናል፡፡ ለዚህ ደግሞ ኢህአዴግ መሩ-መንግስት ሁለት አካሄዶችን ለመተግበሩ ያሳለፋቸው ሁለት አስርታት በሚገባ ያሳያሉ፡፡
የመጀመሪያው የሚሾሙት ዳኞች፣ የግንባሩ ከፍተኛ የካድሬ ማሰልጠኛ እንደሆነ ከሚነገርለት ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ተማሪዎች መካከል ማድረጉ ነው፡፡ ከዚህ ‹‹የትምህርት›› ተቋም ውስጥ የሚወጡ የሕግ ምሩቃን ደግሞ ስለጥልቅ ዘመናዊ የሕግ ፅንሰ-ሃሳብ ለማወቅ ከመትጋት ይልቅ፤ የኢህአዴግ ፖሊሲዎች እና አብዮታዊ ዲሞክራሲ ሕግን እንዴት ‹‹ለመደብ ጠላት›› መጠቀም እንደሚያስችሉ በሚሰብኩ መምህራን ስር እንዲያልፉ ይገደዳሉ (ስለመምህሮቹ ምሁራዊ ልሽቀት ለመረዳት የሕዝብ ሙስሊሙን ጥያቄ በሽብር ተግባር ለመፈረጅ እና ማሕበረ ቅዱሳንን በአክራሪነት ለመወንጀል በ‹‹ጥናታዊ ጽሑፍ›› ስም የተጓዙበትን ርቀት ማየቱ ብቻ በቂ ይመስለኛል)፡፡ ተማሪዎቹም በዚህን መሰሉ የካድሬ ተቋም ስልጠና ስር ሰንብተው ሲወጡ፤ በፍፅምና ሊታመኑላቸው ይገቡ የነበሩትን ፍትሓዊ ዳኝነትና ህሊና የሚባሉ ጉዳዮችን ጨፍልቀው፣ በተለይም ፖለቲካዊ ነክ በሆኑ አይረቤ ክሶች ፊታቸው በሚቆሙ ንፁሀን ዜጎች ላይ መከራን የሚያዘንቡ አሽከሮች ይሆናሉ፡፡ ይህንን አስነዋሪነት ካለመታከት የሚፈፅሙትም፣ ሥልጣንን እና ተያያዥ ጥቅማ-ጥቅሞችን እያጋበሱ ወደ ከፍታ ሲወጡ ተመልክተናል፡፡
ሁለተኛው የግንባሩ አካሄድ ከካድሬ ማሰልጠኛውም ሆነ የተሻለ ነው ከሚባለው የአ.አ.ዩ. የሕግ ፋካሊቲ የሚመረቁትን፣ በተከታታይ ርዕዮተ-ዓለማዊ ጠመቃ የሥርዓቱ ጋሻ-ጃግሬ ማድረግ ላይ ያተኮረው ነው፡፡ በሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ሲያገለግሉ ቆይተው ስደትን የመረጡ ዳኞችና ዐቃቢ-ህግያት በተለያየ ጊዜ እንደ መሰከሩትም አሰልቺ የርዕዮተ-ዓለም ጠመቃ የፍትሕ ሥርዓቱን ነፃነት ጽልመት ካላበሱት ሂደቶች በዋነኛነት ተጠቃሽ ነው፡፡ በአንድ ወቅትም ሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ የሀገሪቱን ዳኞች ሰብስቦ ስለሕገ-መንግስት እና ሕገ አተረጓጎም መርህ ሲያስተምር ለማየት የተገደድነው የዚሁ የጠመቃው አንድ አካል በመሆኑ ይመስለኛል፡፡ ዳሩስ፣ ይህማ ባይሆን ኖሮ እስክንድር ነጋ ላይ 18 ዓመት መፍረድ ሕሊና እንዴት ይፈቅድ ነበር? ኦልባና ሌሊሳንስ ለ11 ዓመታት ወህኒ ያስወረወረው ጥፋት ምን ተብሎ በአሳማኝ መልኩ ሊጠቀስ ይችል ይሆን?
… ቀሪው ለሳምንት ይቆየን!
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11734/

ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ (ነገረ ኢትዮጵያ)

አዲስ አበባ፡- ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹የተነጠቁ መብቶችን እናስመልስ!›› በሚል መሪ ቃል ሚያዚያ 19/2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከአሁን ቀደም የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ምላሽ እንዲሰጣቸው ቢጠይቅም ጥያቄዎቹ ምላሽ ያልተሰጣቸው ከመሆኑም ባሻገር ጭራሹን እየተባባሱ በመምጣታቸውና ህዝብም እየተማረረ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፉን መጥራት እንዳስፈለገ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

Ethiopia's blue party called for rally in Addis Ababa
ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 2005 ዓ.ም ያደረገውን ጨምሮ በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፎችንና ህዝባዊ ስብሰባዎችን ባደረገበት ወቅት የኑሮ ውድነት፣ የእምነት ጣልቃ ገብነት፣ ሉዓላዊነት፣ ዜጎችን ከቀያቸው ማፈናቀልና ሌሎችም መሰረታዊ ጥያቄዎችን አንስቶ የነበረ ቢሆንም ጥያቄዎቹ ምላሽ ሊያገኙ እንዳልቻሉ የህዝብ ግንኙነቱ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ በእስልምና እና ኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ የሚደረገው ጣልቃ ገብነት፣ ዜጎችን ከቀያቸው ማፈናቀሉ፣ የኑሮ ውድነት፣ ሙስና አሁንም ድረስ ተባብሰው መቀጠላቸው ሰላማዊ ሰልፉን በመጥራት ህዝቡ እነዚህን የተነጠቁ መብቶች እንዲያስመለስ ማስተባበርና ማታገል የግድ በማለቱ ነው ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ ለገዥው ፓርቲ ስልጣን እንጅ ለህዝብ አገልግሎት የማይጨነቁት ተቋማት ስራቸውን በሚገባ ባለመስራትቸው ህዝብ ለከፈለው ክፍያ የሚገባውን አገልግሎት እያገኘ አለመሆኑም ሌላኛው ሰላማዊ የሰልፉ ምክንያት መሆኑን ተገልጹዋል፡፡ በተለይ የውሃ፣ የመብራት፣ የቴሌኮሚኒኬሽንና የትራንስፖርት አገልግሎቶች ህዝብን እያማረሩ መቀጠላቸው መፍትሄ ስለሚያስፈልገው የሰላማዊ ሰልፉን አስፈላጊነት እንዲሚያጎላው ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡
ምንም እንኳ ‹‹የህዝብ መብት መነጠቅና የአግልግሎቶች እጦት ሰላማዊ ሰልፉን ወቅታዊ ቢያደርገውም የሰማያዊ ፓርቲ በአመት ውስጥ ከያዛቸው ፕሮግራሞች መካከል አንዱ ህዝብ የተቀማቸውን መብቶች ማስመለስ መሆኑንና ይህም በተደጋጋሚ በተለያዩ ሚዲያዎች መገለጹን›› አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ገልጸዋል፡፡
ሰላማዊ ሰልፉ እሁድ ሚያዚያ 19 ከቀኑ 4 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ካሳንቺስ ከሚገኘው የፓርቲው ጽህፈት ቤት እስከ ጃን ሜዳ እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን ጃን ሜዳ የተመረጠበት ምክንያትም መብቱን የተነጠቀውና ማህበራዊ አገልግሎቶችን በሚገባ ማግኘት ያልቻለው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ጥያቄዎቹን እንዲያነሳ ሰፊ ቦታ በማስፈለጉ ነው ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በየክፍለ ከተማው የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሰላማዊ ሰልፉን ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ የገለጹት ኃላፊው ‹‹በሀይል የተቀሙትን መብቶችን ለማስመለስ በሚደረገው ጥረት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ ሚዲያውና እያንዳንዱ ዜጋ ተሳትፎ በማድረግ አገራዊ ግዴታውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Source: – ነገረ ኢትዮጵያ
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11765/

ሒላሪ ክሊንተን ጫማ ተወረወረባቸው


clinton


በመጪው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ይቀርባሉ እየተባሉ የሚጠበቁት ሒላሪ ክሊንተን ንግግር በሚያደርጉበት ጊዜ ጫማ ተወረወረባቸው፡፡ ጉዳት ባይደርስባቸውም ዜናው ግን የበርካታ ሚዲያዎችን ቀልብ ስቧል፡፡
አሶሺየትድ ፕሬስ እንደዘገበው የቀድሞው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሒላሪ ክሊንተን በላስ ቬጋስ በተጠራ የመልሶ መጠቀም ኢንዱስትሪዎች (Scrap Recycling Industries) ስብሰባ ላይ ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ባላሰቡት እና ባልጠበቁት ሁኔታ ከአዳራሹ ጫማ ተወርውሮባቸዋል፡፡
ጫማው ሳይመታቸው ቢቀርም ወርዋሪዋ ግለሰብ አስተካክላ ብትወረውር ግን ክፉኛ ጉዳት ልታደርስባቸው ትችል እንደነበር የቪዲዮው ምስል ያመለክታል፡፡ ምክንያቱም በወቅቱ አዳራሹ ጨለምለም ያለ በመሆኑ ክሊንተን ጫማው ከተወረወረ በኋላ ነው ያስተዋሉትና ደበቅ ለማለት የሞከሩት፡፡
ሒላሪ ክሊንተን በጉዳዩ ላይ ቀልድ በማከል አስተያየት የሰጡበት ቢሆንም የስብሰባው ኃላፊዎች ግን ታላቅ ይቅርታ ጠይቀዋቸዋል፡፡ ጫማ ወርዋሪዋ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር የዋለች ከመሆኗ በላይ ማንነቷ ገና አልተገለጸም፡፡
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን ሚስት ሒላሪ ከፍተኛውን የፖለቲካ ሥልጣን ለመቆናጠጥ በዝግጅት ላይ እንደሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በነበሩበት አራት ዓመታት ያከናወኗቸው በርካታ ሥራዎች እንዳሉ ደጋፊዎቻቸው ቢጠቀሱም የጋዳፊ ግድያ ከዚያም ጋር ተያይዞ የተከሰተው የቤንጋዚው ቀውስ እና የአሜሪካው አምባሳደር መገደል፣ በግብጽ የተካሄደው ለውጥና ከዚያም በአሜሪካና ምዕራባውያን ግፊት ለውጡ መቀልበሱ፣ በአፍጋኒስታንና ፓኪስታን ላይ የወሰዱት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ በአፍሪካ እንደነ መለስ ካሉ አምባገነኖች ጋር በመሞዳሞድ ግብረሰዶማዊነት እንዲስፋፋ አሜሪካ የተከተለችው ፖሊሲ፣ ወዘተ በጣም ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ሒላሪ ኪሊንተን በቅርቡ በውጭ ጉዳይ ሚ/ርነት ዘመናቸው ስላከናወኑት የሚያወሳ “የሚኒስትር ማስታወሻ” በገበያ ላይ ያውላሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡
የዛሬ ስድስት ዓመት አካባቢ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ በኢራቅ ከጠ/ሚ/ር ኑሪ አልማላቂ ጋር ንግግር ሲያደርጉ አገሩ በአሜሪካ ወራሪነት መፍረሷ ያናደደው ኢራቃዊ ጋዜጠኛ የጫማ ሚሳኤል ወርውሮባቸው እንደነበር አይዘነጋም፡፡
http://www.goolgule.com/shoe-thrown-at-hillary-clinton-at-vegas-speech/