FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, December 28, 2012

የኢትዮጵያውያን ግጭት በሳውዲ


በዋና ከተማዋ በሪያድ ና በሌሎችም ከተሞች በሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል የሚነሳው ግጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች አስታወቁ ። ነዋሪዎች ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሳውዲ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን በብሔር ተከፋፍለው እንዲሁም በቂም በቀል በሚፈጥሩት ግጭት ለሞት ለከፋ የአካል ጉዳት እየተዳረጉ ነው ።

በህጋዊ መንገድ ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚሄዱት ኢትዮጵያውያን አያያዝ አሳሳቢነት ተደጋግሞ በሚነሳበት በአሁኑ ወቅት በዋና ከተማዋ በሪያድና በሌሎችም ከተሞች በሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል የሚነሳው ግጭትና መዘዙ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች አስታወቁ ። ነዋሪዎች ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሳውዲ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን በጎሳ ና በብሔር ተከፋፍለው እንዲሁም በቂም በቀል በሚፈጥሩት ግጭት ለሞት ለከፋ የአካል ጉዳት እየተዳረጉ ነው ። ለዚህም ነዋሪዎቹ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያውያን መካከል በተፈጠረ ፀብ ሞቱ የተባለውን ኢትዮጵያውን በቅርብ ጊዜ ምሳሌነት ያነሳሉ ። የጅዳው ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።

ነብዩ ሲራክ

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

                 contentId_16486558_mediaId_16486552

No comments:

Post a Comment