(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)
በሲዳማ ህዝብ እያመጸ ነው
ሚያዚያ 6 ቀን 2005 ዓ ም ኢህአዴግ ብቻውን ሊያካሂደው የነበረውን ምርጫ አንቀበልም በማለት ከተለያዩ ወረዳ በትስስር የተቃወሙ የሲዳማ ብሔረሰብ አባላት መታሰራቸውን የጎልጉል ምንጮች አስታውቀዋል። ምንጮቹ እንዳሉት በአካባቢው ከፍተኛ ድጋፍ ያለው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ከምርጫው ራሱን ማግለሉ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንዳገኘም አመልክተዋል።
በቀበሌ የመሰብሰቢያ አዳራሾች የታጎሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው የብሔረሰቡ አባላት እንዲፈቱ በሚጠይቁና በታጣቂ ሃይሎች መላከል የተካረረ ግጭት ይነሳል የሚል ፍርሃቻ እንደነበር ያመለከቱት ምንጮች የሲዳማ ተወላጆች የታጠቁ ስለሆነ ኢህአዴግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ አንጋቾችን ማሰማራቱን አመልክተዋል።
ለምርጫው አንድ ቀን ሲቀረው እጩዎቼ፣ ታዛቢዎቼና አባላቶቼ በእስር፣ በድብደባና ከሥራ በመባረር እየተንገላቱ ነው በማለት ራሱን ከምርጫው ያገለለው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ፤ ከምርጫው በኋላም እስሩና እንግልቱ መቀጠሉን ማስታወቃቸውን፣ በአንድ ሳምንት 26 አባላቱ እስር እንደተፈረደባቸው፣ በሲዳማ ዞን በየወረዳው ጊዜያዊ ፍርድ ቤቶችና ሸንጎዎች እየተቋቋሙ የፓርቲው እጩዎች፣ ታዛቢዎችና አባላት ከ400 ብር በላይ የገንዘብ ቅጣትና ከ3ወር እስከ አንድ ዓመት ከስድስት ወር የሚደርስ እስራት እየተፈረደባቸውና ፍርደኞቹ ወህኒ መውረዳቸውን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የደርጅቱ ጉዳይ ሃላፊ ዶ/ር አየለ አሊቶ በመጥቀስ ኢሳት ዘግቧል። የኢህአዴግ አመራሮች ከሳሽም ፈራጅም በሆኑበት ሁኔታ ዜጎቻችን እየተንገላቱ ነው፤ ከምርጫው ብንወጣም ትግላችን ይቀጥላል ማለታቸውን የኢሳት ዘገባ ያስረዳል። (ፎቶ: worancha blogpost)
የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ታስረው ተፈቱ
በስፍራው ተገኝተው አንዳንድ ሰዎችን በማናገር ያዘጋጁት ቪዲዮ በወረዳው ባለስልጣናት ትዕዛዝ እንዲደመሰስ መደረጉን ኢንጂነሩ ተናግረው፣ ይሁን እንጅ በአይናቸው ያዩት፣ በጆሮዋቸው የሰሙት በቂ መረጃ እንደሰጣቸው ኢሳት በዘገባው አመልክቷል።
ታሪካዊ የሪፖርተር አንደበት
ምንጭ፤ የሪፖርተር ጋዜጣ ዘጋቢ ታምሩ ጽጌ “ከለቅሶ ቤት” እንደዘገበው (10 April 2013)
አርበኞች ግንባር ማርኬ ገደልኩ አለ
የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ልዩ ስሙ ሰቋር እና አምቦ ጠበል በተባለ ስፍራ በሁለት ተከታታይ ቀናት ከአገዛዙ የፈጥኖ ደራሽ ሃይል ጋር ባካሄደው የፊት ለፊት ውጊያ ወታደራዊ የበላይነትን ስለመቀዳጀቱ ለጎልጉል በላከው መግለጫ አስታወቀ።
ግንባሩ ካደረሰው ሰብአዊ ጥቃት በተጨማሪ የተለያዩ የቡድንና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎችንም ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መማረኩን አስታውቋል። የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር አገኘሁ ስላለው ድልና ተቀዳጀሁት በሚል በይፋ የገለጸውን ዜና አስመልክቶ ከመንግስት በኩል እስካሁን በይፋ የተሰጠ መልስ የለም። ግንባሩም ቢሆን ሪፖርቱን በምስል አላስደገፈም።
የአውሮፓ ህብረት አቋም አልጠራም
የሰብአዊ መብት ማስከበር የህልውናችን ጉዳይ ነው
በኢትዮጵያ ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ያደነቁት የህብረቱ ሊቀመንበር፣ “ይህ ዕድገት ቀጣይነቱ ሊረጋገጥ የሚችለው ፣ የአገሪቱ ሕዝብ መሠረታዊ መብቶች፣ የመናገርና ሐሳብን የመግለጽ ነፃነቶች ሲከበሩ ብቻ ነው” ብለዋል። በጋራ በተዘጋጀው መግለጫ አቶ ሃይለማርያም “የሰብአዊ መብቶች መከበር ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው” አያይዘውም “የመሬት ወረራ ብሎ ነገር የለም፣ ሊኖርም አይችልም፤ አንድም ጋዜጠኛ ሃሳቡን በመግለጹ አልታሰረም “ሲሉ የተለመደውን የመለስን ዓይነት መልስ በመመለስ ሸምጥጠዋል።
No comments:
Post a Comment