ይሁን እንጂ “ክቡር የሠው ልጅ ቀርቶ እንስሳ እንኳ ጉዞውን የሚጀምረው ከቤቱ ወይም ከመኖርያ አድራሻው ነው” ያለው ፓርቲው፤ ሠልፉን ከፅ/ቤቱ አካባቢ ከመጀመር ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለው ገልጿል፡፡ “ሠላማዊ ሠልፈኛ ዜጐቻችን የራሣቸው መሬት በስንዝርና በጭልፋ ተለክቶላቸው የሚሠጣቸው መሆን የለበትም” ያለው ፓርቲው፤ መስቀል አደባባይን ጨምሮ ሌሎች በአማራጭነት ያቀረባቸው የነበሩ ቦታዎች ከባቡር ግንባታው ጋር በተያያዘ ሣይፈቀድለት መቅረቱንና በሣር፣ በሙጃ እንዲሁም በሠንበሌጥ በተሞላው ጃንሜዳ ውስጥ ብቻ ሠላማዊ ሠልፉን እንዲያከናውን ትዕዛዝ እንደተላለፈለት አስታውቋል፡፡ የአስተዳደሩ ትዕዛዝ አግባብነት አለው ብለን አናምንም ያለው ኢራፓ፤ የሠላማዊ ሠልፉ መነሻ ብሄራዊ አካባቢ ከሚገኘው የፓርቲው ፅ/ቤት ሆኖ፣ መዳረሻው ጃንሜዳ ይሆናል ብሏል፡፡
No comments:
Post a Comment