በአዕምሯችን ሲደቀኑብን ለዓመታት ኖረናል፡፡ አሁንም ያ አካሄድ እንደቀጠለ መሆኑን በተለያዩ ነገሮች ማየት እንችላለን፡፡ ነገር ግን፣ ግለሰቡ መለስና ተቋሙ ኢህአዴግ በተለያየ ዓለም ውስጥ ሆነው፣ እንደ አራምባና ቆቦ ተራርቀው አንደበታቸው አንድ ቋንቋ መናገር የተሳነበትን የታሪክ አጋጣሚ በዚህ ፅሁፌ ላስታውስ ወደድኩ፡፡ መነሳቱም ተገቢ ነው የሚል ዕምነት አለኝ፡፡
[በቅድሚያ ከተሳሳትኩኝ እታረማለሁ] የቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት፣ በተለያዩ ጋዜጣዊ መግለጫዎች፣ ሀገራዊና ዓለምአቀፋዊ መድረኮች፣ ስብሰባዎች፣ ውይይቶች፣ ቃለ-መጠይቆች… ወዘተ ላይ አብዝተው እንዲህ ማለትን ይመርጡ ነበር፡- “ፓርቲያችን ኢህአዴግ…”፣ “የኢህአዴግ ራዕይ…”፣ “የኢህአዴግ ዕቅድና ስትራቴጂ…”፣ “ያወጣናቸው ደንቦች…”፣ “በፓርቲያችን ዕቅድ መሠረት…”፣ “ኢህአዴግ የሚከተለው አቅጣጫ…”፣ “የመንግሥታችን ዕምነት…”፣ “የኢህአዴግ አቋም….”፣“እኛው መሀንዲስ ሆነን….”፣ “ገዢው ኢህአዴግ..”፣ “የልማት ጀግኖቻችን…”፣ “መንግሥታችን የሚጓዝበት አቅጣጫ…”፣ “ሲቪል ሰርቪሳችን…”፣ “ኢኮኖሚያችን…”፣“የኢንዱስትሪ ዘርፋችን…“፣ “የግብርና ልማታችን”፣ “መከላከያ ሰራዊታችን/ኃይላችን…”፣ “መንግስት ዓይንና ጆሮ አለው…ያያል ይሰማል”፣ “ጀግኖች ታጋዮቻችን…”፣ “ህገ-መንግሥታችን”፣ “የምንከተለው ርዕዮተ-ዓለም…”፣ “ታግለን የመጣንበት ዓላማ…”፣ “የመንግስታችን ፖሊሲ…“፣ “የሀገራችን ህዝቦች…”፣ “ልማታዊ መንግስታችን…”፣ “የልማት እንቅስቃሴዎቻችን…” የመሳሰሉት ንግግራቸው ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
የአቶ መለስ አደባባያዊ የንግግር መሠረተ-ድንጋዮች “መንግሥታችን፣ፓርቲያችን፣ ራዕያችን፣ ዕቅዳችን፣ ዕምነታችን፣ አቋማችን፣ ሕገ-መንግስታችን፣ርዕዮተ-ዓለማችን፣ልማታችን፣ ህዝባችን”…የሚሉ ተቋማዊነትንና ብዝሃነትን የተላበሱ ነበሩ እንጂ በእኔነት የታጀቡ ቃላቶችን ሲጠቀሙ አይስተዋሉም፡፡ ይሄ እንግዲህ የብልጥ ‘smart’ ፖለቲከኛነት አካሄድ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡
እንዲያውም በአንድ ወቅት ከአንድ ጋዜጠኛ ስለስልጣን ዘመናቸው መርዘም ተጠይቀው፣ አቶ መለስ ስልጣናቸውን ለቅቀው ማረፍ እንደሚፈልጉ ተናግረው ነበር፡፡ ነገር ግን፣ የፓርቲያቸውን ውሳኔ ማክበር ስለነበረባቸው በፓርቲያቸው ውሳኔ መሠረት በአመራርነቱ መቀጠላቸውን በብልህ ዘዴ አስረድተዋል፡፡ …በአጭሩ አቶ መለስ በንግግሮቻቸው ውስጥ የወከሉትን መንግስትና ፓርቲ ስም ፈጥነው መጥራት ይመርጣሉ ብል አላጋነንኩም፡፡
ግንባሩ ኢህአዴግ ወይስ መለስ?
ከላይ በጥቂቱ ከዘረዘርኳቸው የአቶ መለስ አነጋገሮች በተቃራኒው ያለውን ማድመጥ የጀመርነው ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ለዓመታት በሚጠቀምበት ሚዲያው ተጠቅሞ የጠ/ሚ/ሩን ዜና እረፍት ባሳወቀበት ከነሐሴ 16 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም. ንጋት ወዲህ ነበር፡፡ ይኼንን የሀዘን ዜና ‘እንባ እየተናነቀው' በሚመስል መልኩ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጆሮ ያደረሠው ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ፣ ኢትዮጵያ ታላቅ መሪዋን ማጣቷን ከተናገረ በኋላ በቀጥታ ያመራው “እሳቸው ትተውልን የሄዱትን ዕቅድ፣ ስትራቴጂ፣ ፖሊሲ፣….” ወዘተ እንዲሁም እሳቸው ያስጀመሯቸውን የልማት እንቅስቃሴዎች፣…. መንግስት ከህዝብ ጋር ተባብሮ እንደሚያስጨርስ አስደመጠን፡፡
ውድ አንባቢያን፣ እንግዲህ እዚህ ጋር ልብ በሉ! ከላይ እንደጠቀስኩት አቶ መለስ በህይወት ሳሉ ስለመንግሥታቸውና ፓርቲያቸው እንቅስቃሴ ጠንከር ብለው፣ ዘርዝረው እና አስረግጠው ሲናገሩ፣ ከሞቱ በኋላ ያለው መንግስታቸው ግን ‹‹የእሳቸው ራዕይ››፣ ‹‹የእሳቸው ዕቅድ››፣ ‹‹የእሳቸው ዓላማ››፣ ‹‹የእሳቸው ስትራቴጂ››፣ ‹‹የእሳቸው ፖሊሲ›› ‹‹የእሳቸው…የእሳቸው…የእሳቸው…››.. እያለ በአደባባይ ተነተነልን፡፡
አቶ መለስ በመንግስት ወንበር ላይ ሆነው ‹‹መንግስቴ…››፣ ‹‹ፓርቲዬ…››፣ ‹‹ዕቅዴ…››፣ ‹‹ስትራቴጂዬ…››፣ ‹‹ዓላማዬ…››፣ ‹‹ርዕዮት-ዓለሜ…››፣ ‹‹አቋሜ…››፣ ‹‹ቀያሽነቴ…››፣ ‹‹የህዳሴ መሃንዲስነቴ…››፣ ‹‹ዕምነቴ…››፣ ‹‹አባይን ደፋሪነቴ…››” ‹‹ልማቴ…››፣ ‹‹ኢኮኖሚስትነቴ…›› ወዘተ ሲሉ በግሌ ማድመጤን አላስታውስም፡፡ መቼም ሰው ስለ ራሱ ሥራ መናገር የለበትም ቢባል እንኳ ሥራውን ስለሚያውቀው በድንገት አንድ ቀን አምልጦት ሊናገር ይችላል፡፡ ግን ይኼንን በአቶ መለስ አልተመለከትንም፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ከእሳቸው ሞት በኋላ ያለው መንግስት፣ ሁሉም ነገር የእሳቸውና የእሳቸው ሀሳብ ብሎም የስራ ውጤት መሆኑን በአደባባይና በራሱ ሚዲያ መሠከረልን፡፡ ያም ስላልበቃ አሁንም ድረስ ያለማቋረጥ እየነገረን ይገኛል፡፡ …አልተገናኝቶ! ይልሃል እንዲህ ነው፡፡
መንግስት እንደመንግስትነቱ መናገር ያለበት መንግስታዊ ቋንቋን ነው፡፡ ኢህአዴግ የሚባል፣ ለ21 ዓመታት ሀገር እየመራ የሚገኝን ግንባር ድርጅት በግለሰቡ መለስ ተበልጦ ተመለከትን፡፡ ጠ/ሚ/ሩ በሞቱ ጊዜ ኢህአዴግ እንደመንግስትነት መናገር የነበረበት የጠ/ሚ/ሩ “ራዕይ”፣ “ዕቅድ”፣ “ስትራቴጂ”፣… ሳይሆን “የመንግስት ራዕይ” “የኢህአዴግ ዕቅድና ስትራቴጂ”….ወዘተ ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡ በዚህ ረገድ አቦይ ስብሃት ሳይሻሉ አይቀርም፡፡ ‹‹ፋጡማ ሄደች መጣች››… ያሉትን ማስታወስ ነው፡፡
ገዥው ፓርቲ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ ደጋግሞ በሚነግረን መልኩ ካየነው ከግንባሩ በላይ የገዘፉትና የሰሩት ሠውየው መሆናቸውን ነበር፡፡ በዚህ መሠረት ስንረዳው ‹‹ግንባሩ ኢህአዴግ ወይስ መለስ?›› የሚለውን ጥያቄ ያስነሳል፡፡ መልሱን ለግንባሩ ትተን እንለፍ፡፡
አቶ መለስ እንደከፍተኛ የመንግስት አስፈፃሚ አካል ኃላፊነት፤ መንግስታዊ ቋንቋን ደጋግመው ሲነግሩን ከእሳቸው በኋላ ያለው አዲሱ መንግስት ደግሞ ግለሰባዊ ቋንቋን ለመናገር መገደዱ ትልቅ ትዝብትና ትችት ላይ ጥሎታል፡፡ “ይሄን ሁሉ ረዥም ዓመት ኢህአዴግ ምን ሲሠራ ነበር?”፣ “ሌሎች ባለሥልጣናትስ ምን ሲሰሩ ከረሙ?”፣ ‹‹ባለስልጣናቱ በእሳቸው ትከሻ ነበር ሲኖሩ የነበሩት?››፣ ‹‹የቀሩት አመራሮች ራሳቸውን በአደባባይ አጋልጠው አሁን ምን ሊውጣቸው ነው?››፣ ‹‹አዲስ ነገር መፍጠር ይችሉ ይሆን?››፣ ‹‹ሁሉም ሥራ የአቶ መለስ ብቻ እንዴት ሊሆን ቻለ?”፣ ‹‹ፓርቲው ለአቶ መለስ ለዓመታት ዕረፍት ስላልሰጣቸው ለሞታቸው ተጠያቂነት አለበት…›› የሚሉ አስተሳሰቦችንና ንግግሮችን አድምጠናል፡፡ ለነገሩ ኢህአዴግ ‹‹ሚስጢራዊ ድርጅት ነው›› ይባላል እንጂ ገመናውን ገልጦ በአደባባይ የሚያሳየው ራሱ ነው፡፡ ዳሩ እውነትን እንዴት መደበቅ ይቻላል?!
“ጀግንነት” አይሞትም በሉ
አቶ መለስ የመንግስታቸውና የፓርቲያቸው ሁለ-ነገር፣ ፈጣሪ፣ ቀማሪና ተግባር ሰጪ መሆናቸውን እያወቁ እንኳን “እኔ” ሳይሆን “መንግስታችንና ፓርቲያችን…እንዲሁም አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመራችን…” የሚል ያጌጠ ልብስ አልብሰው ለ21 ዓመታት ሲነግሩን ኖረዋል፡፡ የዋሃንም አምነናቸው ኖረን ነበር፡፡ ይሄ ግን ለእኔ ፖለቲከኝነታቸውን፣ ብልጣብልጥነታቸውን እና ኢህአዴጋዊያንን [ኢትዮጵያውያንን አላልኩም] ረዥም መንገድ ልቀው መሄዳቸውን አስረጅ ነው፡፡
ከሙታቸው በኋላ ያለው መንግስታቸው ግን ዛሬም ድረስ “እሳቸው… እሳቸው…እሳቸው…” እያለ እረፍት በሌለው መልኩ፣ የሚያሰለች ንግግርን ውስጣችን ሊያሰርፅብን ይታትራል፡፡ ፓርቲው የ‹‹አቶ መለስን ራዕይ፣ ዕቅድ፣ ስትራቴጂ… አስፈፅማለሁ፣ አስጨርሳለሁ፣ ዳር አደርሳለሁ›› ቢልም ከአቶ መለስ ተምሮ እንደመንግስት መነገር ያለባቸውን ንግግሮች እንኳ ተግባራዊ በማድረግ ለህዝብ ጆሮ ለማድረስ ተስኖታል፡፡ በይፋና በስውር የሚባለውን ቀላቅሎታልና፡፡
መቼም ከእየሱስ ክርስቶስ በስተቀር ከሙታን የተነሳ የለም እንጂ አቶ መለስ ከሞት መነሳት ቢችሉና ከሞታቸው በኋላ የነበረውን የመንግስታቸውን ሁኔታና ትዕይንት መመልከት ቢችሉ ተገርመው በአዘኔታ አንገታቸውን እንደሚያወዛውዙ አስባለሁ - የሚደሰቱባቸው ነገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉም ታሳቢ ይደረግልኝ፡፡
ስለዚህ ኢህአዴጐች እባካችሁ! ዛሬ መንግሥት ናችሁና መንግስታዊ ቋንቋን ተናገሩ፡፡ መንግስታዊ ንግግርን አስደምጡን፡፡ “ጀግና አይሞትም!” ሳይሆን “ጀግንነት አይሞትም!”›› በሉ፡፡ ‹‹ራዕይህ ህያው ሆኖ የሚኖር የሀገር ሀብት ነው!››፣ ‹‹ቃላችንን እንጠብቃለን፣ ቃልህን እናሳካለን!››፣ ‹‹የጀመርከው ትልቅ፣ ብሩህና ቅርብ ነው፡፡ ተግተን በመስራት እንጨርሰዋለን!››፣ ‹‹ልማታዊ ራዕይህን ለማሳካት እና የሰጠኸን አደራ ለመፈፀም ቃል እንገባለን!››…ወዘተ እየተባለ ነው፡፡ ይኼን ሁሉ ከሚባሉት መለስ በላይ ፓርቲው አይተልቅም? አይገዝፍም? አለበለዚያ ፓርቲያችሁ የነበረው አቶ መለስ እንጂ ኢህአዴግ አይደለም ማለት ነው፡፡ መቼም ኩረጃ ጠቃሚ ነገር አለመሆኑን ማንም ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡ መኮረጅ ደግሞ የግድ ከሆነ እንደ አቶ መለስ አሪፍ ኮራጅ መሆን ነው፡፡ አለበለዚያ ቢቀር ይሻላል፡፡
አቶ መለስ ይረፉበት፣ ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያምን እንጠንቀቃቸው!
‹‹ራሱን መሆን አቅቶት ሌላውን ለመምሠል የሚጣጣር ወይም የሚታትርን ሠው ያህል በምድር ላይ የሚሠቃይ የለም!›› የሚል አባባል ማንበቤን አስታውሳለሁ፡፡ አባባሉ ትክክልነት አለው፡፡ ምንም እንኳን እንደሠው ሁላችንም የምንጋራቸው የጋራ አፈጣጠር ቢኖረንም እያንዳንዳችን ለዚህች ምድር የተለየን ነን፡፡ ማንም ማንንም ሆኖ አልተፈጠረም፣ አይፈጠርምም፡፡
…ወርሃ-መስከረም 2ዐዐ5 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ምድር አዲስ ሁነትን አስተናግዷል፡፡ የሟቹን ጠ/ሚ/ር መለስ የረዥም ዓመታት የሥልጣን ወንበር ለተተኪው አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ገዢው ፓርቲ ማስረከብ ግድ ሆነበት፡፡ ምክትል ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያምም በፓርላማ ቀርበው ቃለ-መሃላ ፈፀሙ፡፡ አዲሱ ጠ/ሚ/ር መሆናቸውንም በሕግ አግባብ አወቅን፡፡
በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት፣ በጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ፊትአውራሪነት የሚመራው አዲሱ መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ ቀርቦ ከም/ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስና ማብራሪያ በጥቅምት ወር ሰጥቶ ነበር፡፡ እኔም አቶ ተሻለ ወዳጅ ከሚባል የቀድሞ የአውራምባ ታይምስ የሥራ ባልደረባዬ ጋር ለሥራ ጉዳይ መቀጣጠራችንን መሠረት አድርጌ በዕለቱ ጥዋት ጐፋ ማዞሪያ አካባቢ ደርሻለሁ፡፡ የፓርላማውን ሁኔታ በቴሌቪዥን ለመከታተል ቀዳሚ ትኩረት ስለሰጠሁት ወደአንድ ሬስቶራንት ጎራ ብዬ ፊቴን ቴሌቪዥን መስኮት ላይ አነጣጠርኩ፡፡ የኢህአዴግ የፓርላማ ተወካዮች ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማብራሪያ ፍለጋ ጥያቄ ይሠነዝራሉ፡፡ አቶ ኃይለማርያምም ማብራሪያና መልስ ሲሰጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ታዩ፡፡ የም/ቤቱ ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉም፣ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተው ከጠ/ሚ/ሩ ምላሽ ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ በዕለቱ መብራት ኃይል መብራት የማጥፋትና የማብራት ልምዱ አልተለየውም ነበር::
በዚህ የም/ቤት ውሎ የሚያስገርም ነገር መስተዋሉ አይዘነጋም፡፡ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚሰጡት ምላሽ፣ ማብራሪያ፣ እንቅስቃሴ /የእጃቸው በተለይ/፣ ቃላቶች፣ ጠንከር ያሉ ንግግሮች፣ቀልዶች…. ከአቶ መለስ መቀዳታቸውን በግልፅ አየን፡፡ መቼም አቶ መለስ ላለፉት 21 ዓመታት የሚወዳቸውም ሆነ የሚጠላቸው ሕዝብ፣ በፓርላማ ቀርበው የሚሰጡትን መንግስታዊ ምላሽ በመደሰት፣ በመማረክ፣ በንዴት፣ በመሰላቸት ተመልክቷቸው፤ አዳምጧቸው አልፈዋል፡፡ ዛሬ የሟቹን ጠ/ሚ/ር መለስን ንግግር ግልባጭ ለማድመጥ ከልቡ የሚሻ ጤናማ ሠው አለ ብዬ አላስብም፡፡ አቶ መለስ ጠ/ሚ/ር በነበሩበት ዘመናቸው በፓርላማ ቀርበው የሚናገሩት መልስ እውነትንና ውሸትን ቀላቅሎ የያዘ ቢሆንም በራሳቸው መንገድ የመሰላቸውን፣ያመኑበትን፣ እውነት ነው ያሉትን፣ እውነት ሳይሆን ለፖለቲካዊ ትርፍ የቀመሩትን በድፍረት ራሳቸውን ሆነው ይናገሩ እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ ሆኖም የሠውን አነጋገር ለመኮረጅና ለማስመሰል ሲንቀሳቀሱ በግሌ አላስታውስም፡፡ ይክፋም ይልማም፤ የራሳቸውን ቀለምና አሻራ በፓርላማውም ውስጥ ፈጥረው ይህቺን ዓለም በሞት ተሰናብተዋል፡፡
መለስን የመምሰል አባዜ
(ከሺህ ምላስ አንድ መለስ!)
በአንፃሩ ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ገና ከጅምሩ፣ አቶ መለስን ለመምሰል፣ ከመሞታቸው በፊት የሚናገሯቸውን ቃላቶች እና ንግግሮች ሁሉ ሆን ተብሎ በተኮረጀ መልኩ ሊነግሩን ጥረዋል፡፡ በግሌ ጠ/ሚ/ሩ አጥንተውና ተዘጋጅተው የገቡ መስሎኛል፡፡ ይሄ በየትኛውም አግባብ ትክክል ነው ተብሎ አይታሰብም፡፡
አዲሱ ከፍተኛ የመንግስት አመራር የመንግስትን አቋም በጠራ ቋንቋ፣ በራሳቸው ቅላፄ፣ በተፈጥሯዊ አካላዊ እና ኃይለማርያማዊ እንቅስቃሴ በፓርላማ ለሚነሱ ጥያቄዎች እና ማብራሪያዎች መልስ ሊሰጡን ይገባ ነበር፡፡
የብዙ ማንነቶች ባለቤት - መለስ
ከንግግራቸው ውጪ አቶ መለስም ቢሆኑ እኮ አንድ ራሳቸውን መሆን አቅቷቸው ነበር፡፡ ለእኛም ወጥ ባህሪያቸውን ለማወቅ ይከብደን ነበር፡፡ በረዥሙ የሥልጣን ዘመናቸው ብዙ ማንነቶች (Multiple personality) ን ማዳበራቸው አይዘነጋም፡፡ ሰውየው ብዙ ማንነቶችን እንዲያዳብሩና እንዲያሳዩን ያስገደዳቸው በሌሎች አመራሮች እምነት ማጣት ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ፡፡ የአቶ መለስ የማንነታቸው መብዛት ደግሞ በእሳቸው ላይ እምነት ለማጣት የተገደደ ህዝብንም ፈጥሯል፡፡ የተለያዩ ማንነቶቻቸው የወታደራዊውን፣ የሲቪሉን፣ የፖሊሲ ማውጣቱን፣ የምህንድስናውን፣ የግብርናውን፣ የኢኮኖሚክሱን፣ የውጭ ጉዳዩን፣ የጤናውን፣ የኢንዱስትሪው፣ የሕግ፣ የአዋጅ፣ የደንብና የረቂቆች፣ የትህምርቱን፣ የማዕድኑን፣ የውሃ ሀብቱን፣…. ዘርፎች በአንድም ይሁን በሌላ አጥጋቢ ባልሆነ ደረጃ ነካክተውታል፡፡ ለዚህም ነው፣ በሞታቸው ሀዘን ወቅት አቶ መለስ በተለያዩ ስሞች ሲሞካሹ የነበረው፡፡ ከስሞቹም መካከል “የጦር መሃንዲስ”፣ “የህዳሴው ቀያሽ”፣ “ኢኮኖሚስት”፣ “ስትራቴጂስት”፣ “የርዕዮተ ዓለም ተንታኝ”፣ “የአየር ንብረት ተደራዳሪ”፣ “ዓባይን የደፈረ መሪ”፣ “ባለራዕዩ መሪ”፣ “ጀግና”፣….ከብዙ በጥቂቱ ናቸው፡፡
ብዙ ማንነት የነበራቸው የቀድሞ ጠ/ሚ/ራችን አንድ እና ወጥ የሆነውን መለስን ሳያሳዩንና ሳይነግሩን ነበር በሞት የተለዩን፡፡ ጥሩ መሪ ለመሆን የተለያዩ ማንነቶች እና የባለ ብዙ ተሰጥዖዎች ባለቤት መሆንን የግድ አይጠይቅም - የብዙ ተሰጥዖዎች ባለቤት መሆን መልካም ቢሆንም፡፡
ታላቅ መሪ በቅድሚያ ራሱን አውቆ፣ ራሱን ማሳወቅና ማንፀባረቅ ይጠበቅበታል፡፡ ያለመታደል ሆኖ ብዙ ኢትዮጵያውያኖች እውነተኛውን መለስ አላወቅናቸውም፡፡ እሳቸውም ቢሆኑ ራሳቸውን ያወቁት አይመስለኝም፡፡ በዚህም ሳቢያ ሕዝብም የተለያየ መለስን ለማወቅ ተገደደ፡፡ ለዚህም ነው፣ ገሚሱ “ታላቅ መሪ”፣ “ባለራዕይ”፣ “ሕዝብን የሚያስጠሩ ጀግና”፣ “ቆራጥ”፣ “ለሕዝብ ኖረው ለሕዝብ የሞቱ”፣ “መልዓክ”፣ “ደግ”፣ “ቀና”፣ “ለነገሮች የጠለቀ ዕውቀት ያላቸው”፣ “በሳል”፣ “አገርን ያለማ”… በማለት መሆናቸውን ያምናል፤ ይናገራል፡፡ ከፊሉ ደግሞ “ቀሽም መሪ”፣ “ራዕይ አልባ”፣ “እንደጊዜው ተቀያያሪ”፣ “ፈሪ”፣ “ለሕዝብ ንቀት ያላቸው”፣ “አቋም የሌላቸው”፣ “ለትውልድ መበላሸት በር የከፈቱ”፣ “ጨካኝ”፣ “ክፉ”፣ “ሴረኛ”፣ “ለፖለቲካ ትርፋቸው የሚጠቅማቸውን ዕውቀት መርጠው የሚጠቀሙ”፣ “ያልበሰሉ”፣ “አገርን የገደሉ”… በማለት ስማቸውን በአሉታዊ ጐን የሚጠሯቸው ወገኖች አሉ፡፡ ይሄም በሕዝብ ዘንድ ድብልቅልቅ ያለ ስሜትን ፈጥሯል፡፡ …ስለዚህ ለቀድሞ ጠ/ሚ/ራችን ያልበጀ የተለያዩ ማንነቶችን ማንፀባረቅ ለአዲሱ ጠ/ሚ/ራችንም ይጠቅማል ብዬ አላምንም፡፡ እስከነአካቴው ራስን ትቶ ሌሎችን ለመምሰል የሚደረግ ጥረትም አደጋው የከፋ ይሆናል፡፡ ቀውሱም ከፍተኛ ነው፡፡
መረጋጋት እና ወደ ልቦና መመለስ
ስለ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፉት ሁለት ወራቶች ውስጥ የተለያዩ ሃሳቦች በተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘገቡ ከርመዋል፡፡ በትምህርት ቤት፣ በማኅበራዊ ህይወት፣ በእምነት፣ በመምህርነት እና በዩኒቨርሲቲ ዲንነት፣ በቤተሰባዊ ህይወታቸው መልካም ሠው መሆናቸው ሲነገርም ነበር፡፡ የተማሩና ጨዋነትም እንደሚገልፃቸው በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ምስክርነት ሰጥተዋል፡፡ ይሄ ጥሩና አስደሳች ነገር ነው፡፡
ነገር ግን፣ በነሐሴ ወር 2ዐዐ4 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የአቶ መለስ መሞት የፈጠረው ድንጋጤ፣ በዚህም የሥልጣን ክፍተት ተፈጥሮ ሀገር ያለመሪ ለረዥም ቀናቶች መጓዟ፣ በሀገሪቷ የተስተዋለው የተደበላለቀ የሀዘን ስሜት፣ ወደ አዲስ ከፍተኛ የመንግሥት እና የሀገር ስልጣን መሸጋገር፣ የሚዲያውና የሕዝብ ትኩረት ወደ አቶ ኃይለማርያም በአጭር ጊዜ ውስጥ መሸጋገር፣ በአቶ ኃይለማርያም ማንነት ላይ ድንገተኛ ለውጥ አምጥቷል ብዬ አስባለሁ፡፡
አዲሱ ጠ/ሚ/ራችን በድንገት በተፈጠረ ማንነት ላለፉት ሁለት ወራት ሲንቀሳቀሱ እንደነበረ ይሰማኛል፡፡ በእነዚህ ጊዜያቶች ውስጥ ደግሞ ያለመረጋጋቱ ሁኔታ ሊኖር የሚችልበት ዕድል የሠፋ ነው፡፡ አቶ ኃይለማርያምም ቢሆኑ ለራሳቸው ጊዜ አልሰጡም ይሆናል፡፡ በዚህ ቀውጢ ወቅት ለራስ ጊዜ መስጠትም ይከብዳል፡፡ ማንኛውም ሠው ካልተረጋጋ ደግሞ ከልቦናው ሊርቅ እንደሚችል ይታመናል፡፡ ከልቦናችን ስንርቅ ደግሞ ነገሮችን የምናይበትና የምንረዳበት ሁኔታ ይለያያል፡፡ በዚህ ውስጥ የሚወሰኑ ውሳኔዎች ስህተት ይበዛባቸዋል፡፡ በተፈጠሩ ሳይሆን ባልተፈጠሩ ሁነቶች ላይ መልስና እርምጃዎች ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡ አቶ ኃይለማርያም ድንገት ስለ ሀገራዊ ጉዳዮች ሲጠየቁ ያልታሰበና ዝግጁነት ያልተዋሃደው ምላሽና ውሳኔ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ሌላም ሌላም…
በመሆኑም አቶ ኃይለማርያም፣ ከወራቶች በፊት አቶ መለስ በመሞታቸው በፊት ወደነበራቸው የተረጋጋ ማንነት ተመልሰው ውስጣቸውን ቢያደምጡት የተሻለ ነው፡፡ የተሰጣቸው የመንግስት አስፈፃሚነት የሥራ ኃላፊነት እንደሚበዛ ቢታወቅም ለራሳቸው ጊዜ ሰጥተውና ተረጋግተው ልቦናቸውን ሊመረምሩት ይገባል፡፡ የራሳቸው ሰው መሆንም አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው፡፡ ኢትዮጵያን የምታክል ሠፊ፣ ከ8ዐ በላይ ብሔር-ብሔረሰቦች፣ የተለያየ አስተሳሰብና ባህል ያለውን ሕዝብ የያዘች፣ በርካታና ዘርፈ-ብዙ ችግሮች ላሉባት ሀገር ቃላቅ መሪ ለመሆን ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም አሁን ነኝ ከሚሉት ውጪ ያለውን እውነተኛውን ኃይለማርያም መልሰው ማግኘት አለባቸው፡፡ አለበለዚያ በመለስ ባርኔጣ ስር ሆነው ኃይለማርያማዊ አመራርን እሰጣለሁ ቢሉ ከሚያለሙት የሚያጠፉት ሊበልጥ ይችላል፡፡
አቶ ኃይለማርያም፣ ራስዎትን ይሁኑ!
አቶ ኃይለማርያም፣ ዛሬ ‹‹ራስዎትን ይሁኑ!›› ስል በግልፅ ሀሳቤን እነግርዎታለሁ፡፡ ለእርስዎም ሆነ ለመንግስትዎ የሚያዋጣው እሱ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የመንግስትዎን ራዕይ፣ ዕቅድና ስትራቴጂ፣ ሥራ እና አቋም በራስዎት ትክክለኛ ማንነት የተቀነባበረ ንግግር፣ ገለፃና ማብራሪያ ባልተኮረጀ ቋንቋ ከአሁን በኋላ እንዲሰጡን በአክብሮት እጠይቅዎታለሁ፡፡ ማንም ከራሱ ውጪ ማንንም ሆኖ አልተፈጠረም፡፡ ማንንም ሊሆን ስለማይችሉም ራስዎትን ሆነው የተሰጥዎትን የመንግስት ኃላፊነት በአግባቡ ይወጡ ዘንድ ትልቁ ምኞቴ ነው፡፡ አሊያ መዘዙን ለመወጣት ይከብድዎታል፡፡ ራስዎትን መሆን ካልቻሉ ደግሞ ልንጠነቀቅዎት ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡
…አቶ መለስም ቢሆኑ በቃ ይረፉበት! ለረዥም ዓመታት ያለዕረፍት ፓርቲያቸውን እና የወከላቸውን መንግስት ሲያገለግሉ በድንገት ታመው ተለይተዋል፡፡ “የእሳቸውን ራዕይ እናሳካለን”፣ “ያስጀመሯቸውን ነገሮች እናስጨርሳለን”…. በማለት ለወራቶች በተደጋጋሚ መንግስት እየነገረን ይገኛል፡፡ ስለእሳቸው መባል ያለበት ሁሉ ከሚገባው በላይ ተብሏል፡፡ አሁን ተግባራዊ ስራችሁን ሥሩ፡፡ ለአፍ፣ለንግግር፣ለገለፃ፣ለፅሁፍ ቀልሎ የተናገራችሁትን በተግባር ማሳየት እስኪ ጀምሩ?
አቶ መለስን ለማስታወስ እየተባለ በሰበብ አስባቡ ለቢልቦርድ፣ለባነር፣ለቲሸርት፣ለተለያዩ የህትመት ውጤቶች፣ለኘሮግራሞች፣ለኘሮፖጋንዳ ቅስቀሳ የሚወጣው በሚሊዮን የሚቆጠር የሀገር ሀብትና ገንዘብ ያለአግባብ እየባከነ ይገኛል፡፡ የሚደረጉት ነገሮች ሁሉ የአቶ መለስን ህይወት መመለስ እንደማይችሉ ነፍስ ያወቀ ህፃን ልጅም ቢሆን አይስተውም፡፡ ለታይታ የሚደረጉና ብዙ ብር እየፈሰሰባቸው የሚገኙ ወጪዎችን በከተማም ሆነ በገጠር በረሀብ፣ በችግር፣ በኑሮ ውድነት፣ በበሽታዎች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ለምን አይውሉም? ሌሎች አንገብጋቢ የልማት ስራዎች የሉም እንዴ?! “ጐጂ ባህል ነው”፣ “ኢኮኖሚን ያቃውሳል”፣ “ቦታ ያጣብባል”፣ “ሠው ከሞተ በኋላ የሚደረግለት ነገር ምንም አይጠቅመውም” በሚል አስተሳሰብ በየመቃብር ስፍራዎች ኃውልት የማስገንባት ሥራ እየቆመና ተሰርተው የነበሩትም እየፈረሱ በሚገኙበት ወቅት በአቶ መለስ ፎቶግራፍ በተለያዩ የህትመት ውጤቶች በየአደባባዩ በየከተሞቹ መስቀል፣ ማሰቀል፣ መለጠፍ፣ ማስለጠፍ እርባናው ምንድን ነው?! ለመታሰቢያቸው አንድ ታሪካዊ ሀውልት ማቆም አይሻልም?!....ግራ ያጋባል!!! ግራ የመጋባት ውጤት ይሆን እንዴ?!
ኤልያስ ገብሩ የሁለት ዓለማቱ መለስና ኢህአዴግ

No comments:
Post a Comment