1 አስተያየት
(ፊቱ ጠቋቁሮና የንዴት መንፈስ ተላብሶ የሕግ ክፍል ኃላፊው ክቡር ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቢሯቸው ገባ) – ምነው በደህና?
- ዛሬስ በደህና አይደለም ክቡር ሚኒስትር፡፡ በጣም ተናድጄና አዝኜ ነው እርስዎ ጋ የመጣሁት፡፡
- ምነው?
- በጥዋቱ እኔ ጋ አንድ ስልክ ተደወለ፡፡
- ከማን?
- ማንነቱን አልነገረኝም፡፡ ነገር ግን በቀደም ለአንድ ሰው አንድ ሥራ እንዲጀምር የብቃት ማረጋገጫ ሰጥተነው ነበር፡፡
- እና?
- እናማ ስልኩ የሰውዬውን የብቃት ማረጋገጫ እንድንሰርዝ የሚያዝ ነው፡፡
- የ – ሚ – ያ – ዝ?
- አዎን፡፡
- ማን ነኝ አለህ?
- ‹‹እሱን ለወደፊቱ ታውቀዋለህ ግን በአስቸኳይ ዕርምጃ ወስደህ፣ ማረጋገጫውን ቀምተህና ሰርዘህ ሥራ ውስጥ እንዳይገባ አድርግ፤›› የሚል ትዕዛዝ ነበር፡፡
- እና እኔ እዚህ እንደ ሚኒስትር ተቀምጬ እያለሁ እኔን ትተውና ንቀው አንተን ያዙሃል?
- እኔን ከማነጋገር ይልቅ ክቡር ሚኒስትሩን አነጋግሩ አልኩ፡፡
- ምን አለ?
- ማንን እንደምናነጋግር አንተ አትወስንም፣ አትነግረንም፡፡ ያልኩህን ካልፈጸምክ ይቆጭሃል አለኝ፡፡
- ለመሆኑ ያ የብቃት ማረጋገጫ የሰጠነው ሰውዬ ብቃት ያለውና ሕግን ያሟላ ነው?
- አዎን ብቃት አለው፡፡ አሟላ ያልነውን ሁሉ አሟልቷል፡፡ አቅርብ ያልነው ማስረጃም ከሚያስፈልገው በላይ አቅርቧል፡፡ በሰጠነው የብቃት ማረጋገጫ መሠረትም አስፈላጊውን የሥራ ፈቃድ አውጥቶ ሥራ ጀምሯል፡፡
- ታዲያ ለደዋዩ ይህን ሁሉ ነገርከው?
- ነገርኩት፡፡
- ምን አለህ?
- ፈቃድ የሰጡትም እንዲሰርዙ ተነግሯቸው እየሰረዙት ነው፡፡ ‹‹አልገባህ ያለህ ደደብ አንተ ብቻ ነህ›› አለኝ፡፡
- ሕግ ካከበረ ለምን ይሰረዛል አትለውም?
- አልኩት፡፡
- ምን አለህ?
- ‹‹ሕግን የማክበርና አለማክበር አይደለም፣ ብቃት የመኖርና አለመኖር አይደለም፣ ሥራ የመጀመርና ያለመጀመር ጉዳይ አይደለም፤›› አለኝ፡፡
- ይህ እንደ ምክንያት ካልቀረበ ታዲያ ይህን የሚያስወስነው ሌላው ምክንያት ምንድን ነው ብለህ አትጠይቀውም?
- ጠየቅኩት፡፡
- ምን አለህ?
- የፖለቲካ ውሳኔ ነው፡፡
- ምን?
- የፖለቲካ ውሳኔ ነው!
- ማነው ይህ ደዋይና የፖለቲካ ወሳኝ?
- ማንነቱን ብጠይቀው፣ ‹‹የሚነገርህን ብቻ ፈጽም፣ ይቆጭሃል›› አለኝ፤ ለክቡር ሚኒስትሩ እነግራቸዋለሁ አልኩት፡፡
- ‹‹እሳቸውም ካደናቀፉ ይቆጫቸዋል›› አለኝና ስልኩን ዘጋው፡፡
- ምን እናድርግ?
- እንዴ ክቡር ሚኒስትር፣ ማንም ወሮበላ ደወለ ብለን አሠራራችን እንቀይራለን እንዴ? ይህ’ኮ ወንጀል ነው፡፡ ፖሊስ እንዲመረምረውም እናመልክት፣ ለደኅንነትም እናሳውቅ፡፡
- የተደወለው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ይሆን እንዴ?
- እርግጠኛ ነኝ አይደለም፡፡ እነሱ ቢሆኑ ኖሮ በአካል ያነጋገሩን ነበር፣ ደብዳቤም ይጽፉ ነበር፣ በስልክ ለማነጋገር ከፈለጉም ማንነታቸውን ይገልጹ ነበር፡፡
- ከደኅንነት ይሆን እንዴ?
- እንዴ ክቡር ሚኒስትር እነሱ ቢደውሉም ማንነታቸውን ይገልጹ ነበር፡፡
- ከፖሊስም አይሆንም፡፡
- ከፖሊስ ነው ይሉ ነበር፡፡
- ከሌሎች ሚኒስትር መሥሪያ ቤቶችስ?
- እንዴ ክቡር ሚኒስትር ከንግድ ሚኒስትር ቢሆኖ ኖሮ ይህ አልተሟላም ይሉን ነበር፡፡ ደዋዩ እንዳለው ከሆነም እነሱንም ፈቃዱን አቋርጡ ብሎ አሰፈራርቶ አቋርጠውታል ነው ያለኝ፡፡
- ብቻ እስቲ ጠንቀቅ እንበል፡፡
- እንዴት እንጠንቀቅ ክቡር ሚኒስትር?
- ጥቃቱ ወደ እኛ እንዳይመጣ ብዬ ነዋ!
- እንዴ እንዴት ወደእኛ?
- የሰውዬውን የብቃት ማረጋገጫ ካስቀሙ፣ የተሰጠው ፈቃድ ሰርዝ ብለው የሚያስፈራሩ ከሆነ’ኮ የሚኒስትሩን ጉዳይ እንዲህ አድርጉ፣ የሕግ ክፍል ኃላፊውን አንሱና አባርሩ እያሉም ማስፈራራት ይችላሉ ማለት ነው፡፡
- እና ማፍያዎች እንዲህ እያሉ አስፈራሩና ሕግና ሥርዓት፣ መብትና ግዴታ ሊተውና ሊሰረዝ ሊጣስ ሊረገጥ ነው ማለት ነው፡፡
- እንደው ስለፈራሁ ነው፡፡
- ሚኒስትር ከፈራና ከሕግ፣ ከሐቅና ከኃላፊነት ከሸሸ ሌላ ታዲያ ማን ሊያከብርና ለሕግና ለሕዝብ ሊቆም ነው?
- ግድ የለህም፣ ጠንቀቅ ማለቱ ይበጃል፡፡
(የሕግ ክፍል ኃላፊው ከክቡር ሚኒስትሩ ቢሮ ወጣ፡፡ ከግማሽ ሰዓት በኋላ ደብዳቤ ይዞ ተመለሰ)
- ይኼ ምንድነው?
- የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ምነው አንተ ልትለቅ?
- አዎን!
- ለምን? በምን ምክንያት?
- ሕግ እየተጣሰ መሆኑን እያወቅኩ፣ የሰው መብት እየተረገጠ መሆኑን እያየሁ፣ በሕገወጥ መንገድ በማስፈራሪያ እየታዘዝኩ መሆኑን እየተረዳሁ፣ ያውም አዛዥና ደዋይ ማን እንደሆነ ሳላውቅ ማስፈራሪያ እየደረሰኝ፣ ለሕግ ወጥነትና ማብራሪያ የሚገዛ ህሊና የለኝም፡፡ ሕዝብ የሰጠኝ አደራ ይህ አይደለም፡፡
- የእኔ አቋም ምን እንደሆነ ገብቶሃል?
- አልገባኝም፤ አቋሞ ምንድን ነው?
- ‹‹ጠንቀቅ››
- የእኔ አቋም ምን እንደሆነ ገብቶዎታል?
- አልገባኝም?
- ‹‹መልቀቅ››
(ማመልከቻውን ጠረጴዛ ላይ ትቶ የሕግ ክፍል ኃላፊው ወጣ፡፡ ከሳምንት በኋላም ለቀቀ፡፡ ከሳምንት በኋላም የመሥሪያ ቤቱ የቅሬታ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር ሚኒስትሩ ቢሮ ውስጥ ገባ)
- እሺ ምን አዲስ ነገር አለ?
- አዲስ ነገር አለ ክቡር ሚኒስትር፡፡ የብቃት ማረጋገጫ ስለሰጠነው የሥራ ፈቃድ አውጥቶ ሥራ የጀመረ ዜጋ ነበር፡፡
- እህ…
- አሁን የብቃት ማረጋገጫውን ሰረዝንበት መሰለኝ ፈቃዱም ተሰረዘ፡፡
- እህ ቀጥል፡፡
- አሁን የቅሬታ ደብዳቤ ይዞ ወደ እኔ ቢሮ መጥቶ ነበር፡፡
- ምን የሚል ደብዳቤ?
- ‹‹የብቃት ማረጋገጫ የተሰጠኝ የተጠየቀውን ብቃት ስለማሟላና ሕጉን ተከትዬ ስለምሠራ ነው፤ አሁን መሰረዙ ግን ሕጋዊ አይደለም፤ ስለዚህ እንደገና ይሰጠኝ›› የሚል፡፡
- ያንተ አስተያየት ምንድን ነው?
- ሰውዬው ሕጋዊ ነው፡፡ ሰውዬው ብቃት አለው፡፡ ከሚጠበቀው በላይ መረጃና ማስረጃ አቅርቧል፤ ሊበረታታ እንጂ ሊከለከል አይገባም የሚል አቋም ነው ያለኝ፡፡
- እ…
- እና አሁን እንደገና ሊሰጠው ይገባል ባይ ነኝ፡፡ በእርግጥ አቋሜን በጽሑፍ እንዳቀርብ የቅሬታ ኮሚቴ ስብሰባ አሁን ጠርቼአለሁ፡፡ አስቀድመው እንዲያውቁት ብዬ ነው የመጣሁት፡፡
- እሺ ተሰብሰብና በጽሑፍ አቅርብልኝ፡፡
- እሺ ዛሬ እናቀርባለን፡፡
(የቅሬታ ኮሚቴው ተሰበሰበ፡፡ አንድ ዓይነት አቋም ያዘ፡፡ የተሰረዘው ትክክል ስላልሆነ እንደገና ይሰጠው የሚል በጽሑፍ ሰፈረ፡፡ ለክቡር ሚኒስትሩ ደረሰ፡፡ በመሀል ግን አንድ ነገር አጋጠመና የቅሬታው ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር ሚኒስትሩ ጋ ገባ)
- ምነው በደህና?
- ምን በደህና ክቡር ሚኒስትር፣ አንዱ በስልክ ደውሎ አስፈራራኝ፡፡
- ምን ብሎ?
- ‹‹ልጆችህን ማሳደግ አትፈልግም፣ ትዕዛዝ ትዕዛዝ ነው አርፈህ ተቀመጥ፡፡ የሰውዬው የብቃት ማረጋገጫ ተሰርዟል በቃ፡፡ ቅሬታ ሰሚ እያልክ የምትወስደው ዕርምጃ በመንግሥት ላይ ቅሬታ እየፈጠረ ስለሆነ ተጠንቀቅ እረፍ፤›› አለኝ፡፡
- አንተ ምን አልከው?
- እኔን ማዘዝ አትችልም ለመሆኑ ማን ነህ? አልኩት፡፡
- አንተን ማዘዝ የምችል የበላይ አካልህ ነኝ አለኝ፡፡
- ምን አልከው?
- የበላይ አካል ከሆንክ አለቃዬን ክቡር ሚኒስትሩን አነጋግር አልኩት፡፡
- ምን አለህ?
- ‹‹እሳቸውማ ትዕዛዛችን ገብቷቸው አርፈው ተቀምጠዋል፤ አላርፍ ያልከው አንተ ነህ፡፡ ለመሆኑ ለምን እንደ ሕግ ክፍል ኃላፊው ሥራህን አትለቅም?›› አለኝ፡፡ የሕግ ክፍል ኃላፊው የለቀቀው በዚህ ምክንያት ነው እንዴ?
- አዎን፡፡
- እንዴ ክቡር ሚኒስትር ምን ሆኑ?
- ምን ሆንኩ?
- ከውጭ ማስፈራሪያ ደረሰን ተብሎ መሥሪያ ቤታችን እጁን ይሰጣል እንዴ? እኛ’ኮ ከእነሱ በላይ የሕዝብ ኃላፊነት የተሸከምን ሰዎች ነን፡፡
- ሸክሙን ከቻልከው ጥሩ፡፡
- ምን ማለትዎ ነው አልገባኝም?
- ሰዎቹ እያስፈራሩ ጥቃት ሊያደርሱብን ይችላሉ ማለቴ ነው፡፡
- እና እኛ እንዳንጠቃ ብለን ሕዝብና አገር ሲጠቃ ዝም ብለን እናያለን? እጃችን እንሰጣለን? እንለምናለን? ባለሥልጣን የሚያሰኘን ታዲያ የቱ ጋ ነው?
- እነሱ ከእኛ በላይ ባለሥልጣን ከሆኑስ?
- ክቡር ሚኒስትር ከእኛ በላይ ባለሥልጣን ማን እንደሆነ በሕግ የተቀመጠና በሕገ መንግሥት የሰፈረ ነው፡፡ በስልክ የሚያስፈራራ ማፍያ ከሕጋዊ መንግሥትና ከሕገ መንግሥታዊ ሥልጣን በላይ ሊሆን አይችልም፡፡
- እ…
- እሺ ክቡር ሚኒስትር እኔም መልቀቄ ነው፡፡
- ምንድን ነው የምትለቀው?
- ሥራዬን፤ አሁን የመልቀቂያ ደብዳቤ አመጣለሁ አመሰግናለሁ፡፡
(እንደ የሕግ ክፍል ኃላፊው የቅሬታ ኮሚቴ ሰብሳቢውም ሥራውን ለቀቀ፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ ተሸማቀው ቢሯቸው ተቀምጠዋል፡፡ እየሠሩት ያለው ትክክል እንዳልሆነ ገብቷቸዋል፡፡ ማስፈራሪያው ደግሞ ከብዷቸዋል፡፡ ጨነቃቸው፣ ጠበባቸው አንድ ሐሳብ ግን መጣላቸው፡፡ አንዱን ሰው ማግኘት፡፡ ደወሉለት)
- አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡
- እንግዲህ ሚኒስትር ነኝ ብዬ የማዝህ ነገር አይደለም፡፡ ዘመድ ቤተሰብ ነኝ ብዬ ግን የምትተባበረኝ ነገር አለና ልለምንህ፡፡
- ምንድን ነው እሱ?
- በስልክ አይሆንም ለእራት ቤት እንገናኝ፡፡
- እሺ፡፡
(እራት እየበሉ ጥብቅ ሚስጥር የያዘ ወሬ ጀመሩ)
- መሥሪያ ቤት ውስጥ እየደወሉ የሚያስፈራሩ ሰዎች አሉ፡፡ ይኸውልህ በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች ናቸው የሚደወሉት፡፡ የተደወለላቸው ሰዎች ደግሞ ድምፃቸውን በሞባይል ቀርፀውታል ይኸው፡፡ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን መስለው የሠራነውን ‹‹የፖለቲካ ውሳኔ ነው›› እያሉ እያስፈራሩ እንዲሰረዝ ያዛሉ፡፡
- እና እናንተ የወሰናችሁትን ቀየራችሁ?
- አዎን ፈርተን ቀይረናል፡፡ አንቀይርም ብለው የተቃወሙን ደግሞ የሕግ ክፍል ኃላፊውና የቅሬታ ኮሚቴ ሰብሳቢው አንሠራም፣ አንስማማም ብለው ሥራ ለቀዋል፡፡
- እነማን ናችሁ ስትልዋቸው ምን ይላሉ?
- አትጠይቁን ማዘዝ የምንችል ነን ይላሉ፡፡
- እስቲ ስልክ ቁጥሩን ልየው፡፡
- ይኸው (አየው)
- እስቲ ቴፑን ላዳምጠው፡፡
- ይኸው (አዳመጠ)
- ሃ – ሃ – ሃ
- ምነው ሳቅክ?
- እኔ’ኮ የጠራሁህ ቤተሰቤ ነህ ዘመዴ ነህ እንድጠቃ አትፈልግም ብዬ ነው፡፡
- እኮ አሁንም አንተም የብቃት ማረጋገጫና የሥራ ፈቃድ የተነጠቀውም እንድተጠቁ አልፈልም፡፡
- ታዲያ ለምን እኔ ስሰቃይ አንተ ትስቃለህ?
- ደዋዮቹን ማን እንደሚያዛቸው ስላወቅኩ ነው የሳቅኩት፡፡
- እንዴት አወካቸው?
- ከሥራዬ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እናንተ ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ያስፈራራሉ፣ ያስቆማሉ፣ ያስጀምራሉ፣ ያስፈቅዳሉ፣ ያሳስራሉ፣ ያስፈታሉ ሌላም ሌላም፡፡
- ይህን እያወቃችሁ ታዲያ ለምን ዕርምጃ አትወስዱም?
- ቀላል አይደለም፡፡ ነገር ግን አሁን መረን ስለለቀቀ ዕርምጃው አይቀሬ ነው፡፡
- ማን የሚሉት ባለሥልጣን ነው ግን እንዲህ የሚያደርገው?
- የባለሥልጣኖች ባለሥልጣን ነኝ ባይ በሕግ ባለሥልጣን ያልሆነ ሰው ነው፡፡
- በሕግ ባለሥልጣን ካልሆነ ታዲያ ምንድን ነው? ማነው?
- ባ – ለ – ሀ – ብ – ት!!!

source: http://www.ethiopianreporter.com/
No comments:
Post a Comment