ዶ/ር ቴዎድሮስ ኢትዮጵያ ነብዩ ሙሀመድና ተከታዮቹን ተቀብላ ያስተናገደችበትን የሁለቱን ሀገራት ጥንታዊ የታሪክ ግንኙነት፣ በሃገሪቱ ስላለው የኢኮኖሚያ እድገትና የኢንቨስትመንት አማራጮች ለሳውዲ አረቢያው አቻቸው አብራርተዋል፡፡
ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ በሳውዲ አረቢያ ለሚገኙ ከ40ሺ በላይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ ለመስጠት በመፍቀዷ አመስግነው፣ህጋዊ ፈቃድ ለማገኘት ያልቻሉ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በመኖራቸው የተሰጠው ህጋዊ የመሆኛ ቀነ ገደብ እንዲራዘምም ለሳወዲው አቻቸው ጥያቄ አቅረበዋል፡፡
የሳውዲ አረቢያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሳውድ አል ፋይሳል በበኩላቸው በህገወጥ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵዊያን እድሉን እነዲጠቀሙበት መንግስታቸው ቀነ ገደቡን ለ4 ተጨማሪ ወራት እንደሚያራዝም ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለችውን እድገት ሚንስትሩ አድንቀው፣ በኢኮኖኖሚ ልማት፣ እርዳታና ኢንቨስትመንት መስኮች ሁለቱን ሀገራት ትብብር ለማጠናከር ተስማምተዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ በቀጠናው ባሉ ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል፡፡የኢትጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለሳውድ አረቢያው አቻቸው ሳውድ አል ፈይሰል የጉብኝት ግብዣ አቅርበውላቸዋል፡፡
ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጠቅሶ ኢዜአ
No comments:
Post a Comment