ኢሳት ዜና :- ባለፈው ረቡዕ 78 ሰዎችን አሳፍሮ ከአዲስ አበባ ወደ አክሱም ይበር የነበረው ቦምባርዴር ኪው 400 አውሮፕላን ማረፊያ ቦታው ላይ ሊደርስ ደቂቃዎች ሲቀሩት የጭስ መቆጣጠሪያው በመጥፋቱ፣ ፓይለቱ አውሮፕላኑን በአስቸጋሪ ሁኔታ በማሳረፍ የሰዎችን ህይወት እና የአየር መንገዱንም መልካም ስም ታድገዋል።

ከባለቤቱዋና ከአንድ አመት ልጇ ጋር ትጓዝ የነበረችው እርጋት ሀይለገብርኤል ” ከአውሮፕላኑ ክንፍ ጭስ ሲወጣ እንመለከት ነበር፣ ሁላችንም በጣም ፈርተን ነበር ” ስትል ለጋዜጣው ዘጋቢ ገልጻለች።
የአየር መንገዱ ኤክስፐርቶች ጭሱ ከ5 ደቂቃ በፊት ተከስቶ ቢሆን ኖሮ አውሮፕላኑ ሙሉ በሙሉ ይጋይ ነበር በማለት ተናግረው፣ አብራሪው የወሰደውን ፈጣን እና ፕሮፌሽናል እርምጃ አድንቀዋል። ተሳፋሪዎችም ህይወታቸውን የታደገላቸውን አብራሪ ማመስገናቸውን ጋዜጣው ዘግባል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንድ ሳምንት ውስጥ ተመሳሳይ ችግር ሲገጥመው ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
በጉዳዩ ዙሪያ አየር መንገዱ ይፋዊ መግለጫ አልሰጠም።
No comments:
Post a Comment