FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Sunday, September 7, 2014

የአፋርን ሕዝብ ወኃ ጠማው

አኩ አብን አፋር ለዘ-ሐበሽ አንደዘገበው፦
በአፋር ክልል በ32 ወረዳዎች ህዝብ በውኃ ጥም በከፈተኛ ችግር ውስጥ ይገኛል። ባለፉት 5 አመታት ለኢህአዴግ ባለስልጣናት ኢንቨስትመንት ተብሎ ከህዝቡ የተቀማው የአፋር ህዝብ መሬት ለህዝብ በከፍተኛ ደረጃ የውኃ እጥረት አስከተሏል!! በአዋሽ ወንዝ ዳር ሲኖሩ የነበሩ አርብቶ አደሮች በግዴታ በመንደር በማሰባሰብ ከፍተኛ ኪሳራ በህዝቡ ላይ አድርሷል።
(ፎቶ ፋይል)
(ፎቶ ፋይል)

ለምሳሌ ፦ በግብርና አስተዳደር የነበረው ህዝብን በግዴታ በመንደር በመሰብሰብ ለከፍተኛ አደጋ እያጋለጡ ነው። ትምህርት ፣ ህክምና፣ ኤሌክትሪክ፣ ውኃ እና የመሳሰሉትን ነገሮች ሳይዘጋጀላቸው ህዝብን እያፈናቀሉ ነው። በአሁኑ ወቅት በጭፍራ ወረዳ «በወአማ» ቀበሌ የሚገኙ ህዝቦች በመጀመሪያ በመንግስት የተሰበሰቡ ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት ግን ከመንግስት ልያገኙ የሚገባቸውን ነገሮች እንደማያገኙ ይናገራሉ። ከጭፍራ ፣ከሚሌ፣ ከገዋኔና አካባቢው ወጣቶች ለስደት ወደ ጅቡቲ እንዲሁም ወደ አረብ ሃገራት እየተሰደዱ መሆናቸው ይደመጣል።
በጣም ነው የሚያሳዝነው በሎግያ አካባቢ አንድ ጄርካን ውኃ በ17 ብር እየገዙ የሚጠጡ አሉ! «የክልሉ መንግስት ምን እየሰራ ነው? እኛ መንግስት የለንም! መንግስት የራሱን የስልጣን እድሜ ለማራዘምና ለቤተሰቦቻቸውን ብቻ ለመርዳት የሚሰራ የሙስና ቡድን እንጂ መንግስት የለንም» ሲሉ ብዙዎች ይናገራሉ!! ህክምና ለማግኘት ወደ ደሴ መሄድ አለባቸው ወደ ደሴ በመሄድ መንገድ ላይ የሚሞቱም አሉ! ከ4 ወር በፊት አንዲት አዛውንት በእባብ ተነድፈው ወደ ደሴ ሆስፒታል እየወሰዷቸው መንገድ ላይ ህይወታቸው አልፏል! «እውነት ለመናገር የአፋር ክልል ችግር ከሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች የተለየ ነው» ሲሉ ነዋሪዎች ብሶታቸው ይናገራሉ። «ክልሉ እየተመራ ያለው ኃላፊነት በማይሰማቸው መሀይሞች በመሆኑ ነው ከአሁን በኋላ የምንጠበቀው እድገት የለም» ይላሉ ነዋሪዎቹ።
በአፋር ክልል 32 ትላልቅ ወረዳዎች ይገኛሉ፣ በመላው የአፋር ክልል ብቸኛው እና እድሜ ጠገብ የሆነው አንድ ሆስፒታል አለ፤ እሱም የተገነባው በደርግ ጊዜ ነው። በዱብቲ የሚገኘው ይህ ሆስፒታል ለህዝብ የሚሰጠው አገልግሎት በጣም አነስተኛ ነው! የወባ መድኃኒት እንኳን አይገኝበትም የዱብቲ ወረዳ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ለሆስፒታሉ የሚሰጠው ማቴሪያልና መድኃኒቶች ለግል ፋርማሲዎች ይሸጣሉ።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/34404

ከንግድ ባንክ ከሰባት ሚሊዮን ብር ላይ በመመዝበር የተጠረጠሩ ኃላፊዎች ተከሰሱ

- ተጠርጣሪዎቹ በጋብቻና በሥጋ ዝምድና የተሳሰሩ ናቸው ተብሏል
CBE_SAበኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መሥሪያ ቤት በሒሳብ ማስታረቅ ሥራ ክፍል የደንበኞች አገልግሎት ሥራ አስኪያጅና የሒሳብ አስታራቂ ሲኒየር ኦፊሰርን ጨምሮ 13 ተጠርጣሪዎች፣ ከሰባት ሚሊዮን ብር በላይ ከባንኩ የውስጥ ሒሳብ በመመዝበር ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡
የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ክስ ያቀረበባቸው፣ የንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት የሒሳብ ማስታረቅ የደንበኞች አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ አቶ ታምርአየሁ ተክሌና የሒሳብ አስታራቂ ከፍተኛ ኦፊሰር አቶ ኤፍሬም ወልደተንሳይ ናቸው፡፡
የአቶ ታምራየሁ አማች ናቸው የተባሉት አቶ ንብረት ማሞና እህቶቻቸው ወ/ሮ ትንሳኤ ማሞ (የአቶ ታምራየሁ ሚስት)፣ ወ/ሮ ውዳሴ ማሞ፣ የአቶ ኤፍሬም ወንድም አቶ ሔኖክ ወልደተንሳይና የአቶ ታምራየሁ አክስት ልጅ ናቸው የተባሉት ተጠርጣሪ አቶ ዓለሙ አብርሃም (ያልተያዙ) በዋና ወንጀል አድራጊነት የተጠረጠሩ ናቸው፡፡ በአቶ ንብረት ማሞ ሥራ አስኪያጅነት የሚመሩና አድራሻቸው በሐዋሳ የሆነ ጂቢሲ ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ማኅበር፣ ንብረት ማሞ ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ድርጅት፣ በአቶ ታምራየሁ ሥራ አስኪያጅነት የሚመራው አዳነና ቤተሰቦቹ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ አከራይ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ በአቶ ሔኖክ ሥራ አስኪያጅነት የሚመራው ሔኖክ ወልደተንሳይ ኮንስትራክሽን ማሽነሪ አከራይ ድርጅትና በአቶ ዓለሙ ሥራ አስኪያጅነት የሚመራ ወንድገማኝ ዴዛ ሕንፃ ሥራ ኮንስትራክሽን ድርጅትም በክሱ ተካተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መሥሪያ ቤት፣ በሒሳብ ማስታረቅ ሥራ ላይ የነበሩት ኃላፊዎች አቶ ታምራየሁና አቶ ኤፍሬም፣ ከሌሎቹ ተጠርጣሪዎች ጋር በሥጋና በጋብቻ ዘመዳሞች መሆናቸውን የሚጠቁመው የዓቃቤ ሕግ ክስ፣ ይኼም ግንኙነታቸው ወንጀሉን ለመፈጸምና ሚስጥሩን ለመጠበቅ መልካም አጋጣሚ ስለፈጠረላቸው፣ የማይገባ ጥቅም ለማግኘትና ለሌሎች ለማስገኘት በማሰብ፣ ከባንኩ የውስጥ ሒሳብ ላይ 7,064,857 ብር መመዝበር በመንግሥት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ክሱ ያብራራል፡፡
ገንዘቡ ሊመዛበር የቻለው ሁለቱ የባንኩ ኃላፊዎች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በመጠቀም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መሥሪያ ቤት የውስጥ ሒሳብ ላይ በመቀነስ፣ በተለያዩ የባንኩ ቅርንጫፎች መተላለፍ የሚገባቸውን የሒሳብ ማስታረቅ ሥራዎች፣ የሥራ ኃላፊነትን ወደ ጎን በመተው ለጥቅም ሲሉ መመሳጠራቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡
በመሆኑም ገንዘቡን በስውር ለመመዝበር እንዲያስችላቸው ከአቶ ንብረት ማሞና ከአቶ ዓለሙ አብርሃም ጋር በጥቅም በመመሳጠር የአቶ ኤፍሬምን የግል መግቢያ ቃል (User Name) እና የሚስጥር ቃል (Password) በሕገወጥ መንገድ በመጠቀም ወጪ ማድረጋቸውን ክሱ ይዘረዝራል፡፡
ሁለቱ የባንኩ ኃላፊዎች የክሬዲት ሒሳብ ትኬት አዘጋጅተው በመፈረምና የባንኩን ሠራተኞች የባንክ ሲስተም የግል መግቢያ ቃልና የሚስጥር ቃል በመጠቀም፣ ገንዘቡን በተለያየ መጠን ወጪ ማድረጋቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡
ከባንኩ የውስጥ ሒሳብ ላይ ያላግባብ ወጪ በማድረግ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሐዋሳ ዲስትሪክት ታቦር ቅርንጫፍ፣ አቶ ንብረትና ወ/ሮ ውዳሴ መሥራች በመሆን ባቋቋሙት ጂቢሲ ጠቅላላ ኮንስትራክሽን ስም በተከፈተ አካውንትና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ በሚገኘው ወንድማገኝ ዴዛ ሕንፃ ኮንስትራክሽን ስም በተከፈተ አካውንት፣ በድምሩ 7,064,857 ብር በሕገወጥ መንገድ እንዲዛወር ማድረጋቸውን ክሱ ያብራራል፡፡
አቶ ንብረት የተባሉት ተጠርጣሪ ከወ/ሮ ውዳሴ ጋር በጋራ ባቋቋሙት ድርጅት ስም፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መሥሪያ ቤት ሒሳብ ላይ እየተቀነሰ ሐዋሳ በሚገኘው የባንኩ ታቦር ቅርንጫፍ በሁለቱ የባንኩ ኃላፊዎች አማካይነት ሲተላለፍላቸው እንደነበር፣ በአቶ ኤፍሬም ስም በኅብረት ባንክ መስቀል ፍላወር ቅርንጫፍ በከፈቱት ሒሳብ ሲያስተላልፉ እንደነበር፣ በአቶ ሔኖክ ስም በዳሸን ባንክ መስቀል ፍላወር ቅርንጫፍ ሲተላለፍ እንደነበር፣ በወ/ሮ ትንሳኤ ስም በዳሸን ባንክ ዓቢይ ቅርንጫፍ በተከፈተ ሒሳብ ሲተላለፍ እንደነበርና በሌሎቹም ግለሰቦችና ድርጅቶች ስም በተለያዩ ባንኮች በተከፈቱ አካውንቶች ገንዘቡን ሲያስተላልፉ እንደነበር ክሱ ይገልጻል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለያዩ አካውንቶች ወጥቷል የተባለውን ከሰባት ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች፣ ደረቅ የጭነት ማመላለሻ ገልባጭ መኪና፣ ጅምር ቤት፣ የቤት አውቶሞቢሎችና ሌሎች ንብረቶችን መግዛታቸውንና በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስለው በማቅረብ ሲገለገሉበት እንደነበር ክሱ ያስረዳል፡፡
በአጠቃላይ ተጠርጣሪዎቹ ሁለት ክስ የቀረበባቸው ሲሆን አቶ ታምራየሁ፣ አቶ ኤፍሬም (ያልተያዙ)፣ አቶ ንብረት፣ አቶ ሔኖክ፣ ወ/ሮ ትንሳኤ፣ ወ/ሮ ውዳሴ (ያልተያዙ)፣ አቶ ዓለሙ (ያልተያዙ) በመንግሥት ላይ ጉዳት በማድረሳቸውና ያላግባብ ተጠቃሚ በመሆናቸው በዋና ወንጀል አድራጊነትና በልዩ ወንጀል ተካፋይነት በፈጸሙት በሥልጣን ያላግባብ መገልገል ወንጀል መከሰሳቸውን ክሱ ያብራራል፡፡
በሌላ በኩል ሁሉም ተጠርጣሪዎች ያገኙትን ገንዘብ ሕገወጥ አመጣጡና ምንጩን በመደበቅና በመሸፈን፣ ሕጋዊ አስመስሎ ለማቅረብና ከወንጀል ተጠያቂነት ለማምለጥ፣ የገንዘቡን እንቅስቃሴ ሰውረው በማዘዋወር በፈጸሙት፣ በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የሙስና ወንጀልም መከሰሳቸውን ክሱ በዝርዝር ያስረዳል፡፡
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/34394


ሶስት ጋዜጠኞች አገር ለቀው ወጡ

የወያኔው መንግስት አላሰራ ያላቸው እና ጫናውን ያሳረፈባቸው ሶስት ጋዜጠኞች አገር ለቀው መውጣታቸው ታውቋል።
በዚህም መሰረት
1ኛ/ ሚሊዮን ሹሩቤ – የማራኪ መጽሄት ባለቤት እና አዘጋጅ
2ኛ/ ኤሊያስ ጉዲሳ – የቃልኪዳን መጽሄት ባለቤት እና አዘጋጅ
3ኛ/ መድሃኒት ረዳ – የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ሪፖርተር
በገዛ አገራችው መስራት ስላልቻሉ እናት አገራቸውን ኢትዮጵያን ለቀው ተሰደዋል። የወያኒው መንግስት ከምርጫ 2007 ቀደም ብሎ ነጻ ፕሬሶችን በማጥፈታ በራሱ አምሳል አዳዲስ ፕሬሶችን በመቅረጽ በ97 የደረሰበትን ሽንፈት አሁን እንዳይደርስበት በስፋት እየሰራ ሲሆን ሕዝብ የመረጃ ደሃ ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት በዚህ አመት ብቻ ወደ 30 የሚጠጉ ጋዜጠኞች እንዲሰደዱ ሌሎችን ደሞ ወደ እስር ቤት እንዲገቡ አድርጓል።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/34414

  • 576
     
    Share

Saturday, September 6, 2014

“ሕወሀት ኢሕአዴግ” በቅርብ ጊዜ የብሔራዊ እርቅ ተማጻኝ!

(ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

reconciliation truth


ብሔራዊ እርቅ (National Reconciliation) በተለይ በእርስ በእርስ ግጭት ደም የተቃባንና የከፋ አደጋ የተጋረጠበትን ኅብረተሰብ ወይም የመበታተን አደጋ የተጋረጠባትን ሀገር በይቅር ለእግዚአብሔር ይቅር አባብሎ ሰላም ለማውረድና የቂም በቀልን ዶሴ ዘግቶ በአዲስ መንፈስ  ብሔራዊ መግባባትን (National Consensus) ፈጥሮ የአንዲት ሀገርን ሕዝብ በአንድነት አስተባብሮ ለማንቀሳቀስና ህልውናውን ከመረጋጋቱ ጋራ ለማስቀጠል ዓይነተኛ መንገድ ነው፡፡
በሕወሀት ኢሕአዴግ የአገዛዝ ዘመን የዚህ የብሔራዊ እርቅ (National Reconciliation) ጥያቄ በተለያዩ አካላት በተደጋጋሚ ሲቀርብ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን የአገዛዝ ሥርዓቱ ይህ እርቅ ቢፈጸም የመጀመሪያውና ዋነኛው ተጠቃሚ እሱ መሆኑን እስከአሁንም ቢሆን መረዳት ባለመቻሉ ምክንያት የተለያዩ የእብሪት ኃይለ ቃሎችን በመሰንዘር ከተለያዩ ወገኖች ለሚቀርብለት ጥያቄ ቀና ምላሽ መስጠት ሳይችል ቀርቷል፡፡ የዚህም ምክንያቱ አንደኛ የሥርዓቱ ባለሥልጣናት የሌላው ጉድፍ እንጅ የራሳቸው ግንድ ስላልታያቸው ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ቀኑ ለእነሱ “ሁልጊዜም ፋሲካ” እንደሆነላቸው የሚኖርና አይቀሬው ነገር ማለትም ቀን ተለውጦ ትላንት በሌላው እጅ የነበረው ዛሬ በእነሱ እጅ ያለው ነገ ደግሞ በሌላው እጅ እንደሚገባ ያለመረዳትና ዘለዓለም በእነሱ እጅ የሚኖር ስለመሰላቸው የፈጠረባቸው መዘናጋት ናቸው፡፡
በእኔ እምነት ይህ ትንሽዬ አገዛዝ የቀረበለትን ወርቃማ እድል ሊጠቀምበት ሳይችል ቀርቶ በማባከኑ ከጉዳዩ ተጠቃሚ ሊሆን የሚችልበትን እድል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዳመለጠው አስባለሁ፡፡ አርቀው ማሰብ ቢችሉ ወይም የያዙትን የኃላፊነት ቦታ የሚመጥን ጭንቅላት ቢኖራቸውና ነገ ሌላ ቀን ነው ብለው ጥያቄውን በቀናነት ተቀብለው አስተናግደውት ቢሆን ኖሮ ለሁሉም መልካም ተአማኒ ሰላም ለሀገርም የጸና መሠረት ያለውና ትክክለኛ የዲሞክራሲ (የበይነ-ሕዝብ) ሥርዓት ለመመሥረት በተቻለ ነበር፡፡
ይህ እድል በወያኔም ባይሆን በሌላ ለሀገሪቱና ለሕዝቧ እንደሚኖር አትጠራጠሩ፡፡ ለወያኔ ግን ኃጢአቱን ሊያሥተሰርይለትና በኢትዮጵያ ታሪክ መልካም ስም ሊያሰጠው የሚችለውን መልካም ታሪክ ሠርቶ ማለፍ የሚችልበት ቀን አለፈ፡፡ እስከዛሬ ይህ ትንሽዬ አገዛዝ ተለማኝ ሌሎች ወገኖች ማለትም የሲቢክ (ሕዝባዊ) ማኅበራትና ፖለቲካዊ (እምነተ-አሥተዳደራዊ) ማኅበራት ደግሞ ለማኝ ነበሩ፡፡ እመኑኝ አትጠራጠሩ ከዚህ በኋላ ግን ለማኙ ወያኔ ተለማኙ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሆናል፡፡ አዲሱን ዓመት 2007ዓ.ምን ጨምሮ ቀጣዩ ዓመት ለወያኔ ጭንቅና ጥብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ ተስፋን ይዘው መጥተዋል፡፡
ከዚህም የተነሣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወያኔ ይሄንን ብሔራዊ እርቅ እሱ በሚመቸው መንገድ አጠናቆ ከጉድ ከውርደትና ሞት ለመዳን የሚችልበትን ስልት በመንደፍና ጭንቅ በገጠመው ቁጥር እየሰበሰበ የሚያሠማራቸውን ከጭንቁ የሚታደጉትን “የሀገር ሽማግሌ” ተብየዎችን ቀሳጢ ጉዳይ አስፈጻሚዎች በማሠማራት ውትወታውን እንደሚያጧጡፈው “ምናለ አምሳሉ በሉኝ” ጠብቁ፡፡ በእኔ እምነት ሕወሀት ኢሕአዴግ ይሄንን ታላቅ ብሔራዊ ቁምነገር መከወን የሚችልበት አቅም ትከሻ ቅድስናና ሰብእና ቅንጣቱ እንኳን የለውም፡፡ በሕወሀት ኢሕአዴግ ከዋኝነት አስተናጋጅነት ኃላፊነት ኢትዮጵያ ውስጥ ሊመጣ ሊገኝ የሚችል መሠረት ያለው እውነተኛና ትክክለኛ ሰላምና እርቅ አይኖርም፡፡ ምክንያቱም አንዴ ሁለቴ ሦስቴ ብቻም አይደል ለቁጥር ለሚያዳግት ጊዜ መንግሥት ነኝ ከሚል አካል ፈጽሞ በማይጠበቅ ነውረኛነት ብልግና እብለትና ክህደት ማጭበርበር ማወናበድም የኢትዮጵያ ሕዝብ በተደጋጋሚ ጊዜያት ስለተካደና ስለተሞኘ ስለተወናበደና ስለተጭበረበረ ወያኔ መታመንን መልሶ ላያገኘው አጥቶታልና ብቻ ሳይሆን ወያኔ ይሄንን ማድረግ የሚችልበት ተፈጥሮ ወይም ሰብእና እንደሌለው ሕዝቡ በሚገባ ያውቃልና ነው፡፡
አሁንም እርግጠኛ ነኝ ወያኔ ይሄንን አስመሳይ እንቅስቃሴ በሚጀምርበት ጊዜ በተቃውሞና በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ያሉ የሥልጣን ጥማት ያስቸገራቸው ዜጎች በአገዛዙ በመደለል የእንቅስቃሴው አባሪ ተባባሪ ሆነው በመራኮት በሀገርና በሕዝብ ዘላቂ ጥቅም ላይ ከባድ ስሕተትና በደል የሚፈጽሙ ግለሰቦችና ቡድኖች እንደሚኖሩ አትጠራጠሩ፡፡ ምን አለፋቹህ የምታዩት ታላቅ ድራማ ይኖራል፡፡ ከዚህ በኋላ ከምሁራንም በሉ ከፖለቲከኞች እንዲሁም ከሀገር ሽማግሌዎች ባጠቃላይ ከሀገሪቱ ልኂቃን የብሔራዊ እርቅን ጥያቄ ለወያኔ አቀረቡ የሚባሉ ዜጎች ቢኖሩ ያለውንና የነበረውን የተፈጠረውንና የሚፈጠረውን ሁሉ ጨርሰው የማያውቁ ያልተረዱና የማይረዱ የዋሀን እንደሆኑ ልነግራቸው እወዳለሁ፡፡
ይሄንን ሐሳብ ያለ ምንም ግላዊና ከሀገር ጥቅም ጋር ከማይቃረን ምክንያት ከቀናነት ብቻ የሚያስቡ ዜጎች ካሉ እንደምኞታቸው ቢሆን ምንኛ መልካም በሆነ ነበር፡፡ ያለው ሀቅ ግን ከሚያስቡት እጅግ የራቀና የተለየ ነው፡፡ የሥርዓቱ ባለሥልጣናት በብዙ ቢሊዮን (ብልፍ) የሚቆጠረውን ከሀገሪቱ የመዘበሩትን ገንዘብ ቢመልሱም እንኳ፣ ለሀገር ለወገን በተቆጩ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት በታተሩ እየታፈኑ ተወስደውባቸው ልጆቻቸው ወላጆቻቸው በግፍ ተገለውባቸው ለመቅበር እንዲችሉ አይደለም ሞታቸውን እንኳን እንዳያውቁ ተደርገው እርማቸውን እንዲበሉ የተደረጉ ወገኖችን “ግድ የላቹህም ከሁሉም ነገር ሀገር ትበልጣለችና ስለ ሀገር ብላቹህ ይቅር በሉ” ብለን ማሰመን ብንችልም እንኳ፣ “በገደሉኝ በተሻለኝ” የሚያሰኙ ግፍና በደል የተፈጸመባቸውን ወገኖችንም እንደዚያው ማሳመን ብንችልም እንኳ፤ ሀገር ይቅር የማትለው ለይቅርታ የማይመች በርካታ የሀገር ክህደት ወንጀሎች አሉና ይህ የብሔራዊ እርቅ ሐሳብ ከወያኔ ጋራ ምንም የሚሆን አይደለም፡፡ በወያኔ የተደለሉ የተወሰኑ ወገኖች ተወናብደውና አወናብደው እንዲሆን ቢያደርጉ ግን ሀገሪቱ በኢፍትሐዊ መንገድ በወያኔ ያጣቻቸውን ብሔራዊ ጥቅሞቿን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀን በወጣለት ጊዜ ሥልጣንን በእጁ ባደረገ ጊዜ እንዲመለሱለት ጥያቄ የማቅረብና ማስመለስ የሚችልበትን መብት እንዲያጣ ያደርገዋልና ከወያኔ ጋራ በዚህ መልኩ መሸኛኘት የማይታሰብ ነው፡፡
በየዋህነት እንደሚያስቡት ወገኖች በወያኔ እጅ ይሄ ቢፈጸም በኋላ ላይ ለማይወጣላቸው ጸጸት እንደሚዳረጉ ነገሩ እርግጥ ነውና ከወዲሁ መጠቀሚያ ከመሆን እንዲቆጠቡ ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ ለነገሩ የፈለገውን ያህል ቢባል በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች በወያኔ ተሹመው እያገለገሉ እንደምናያቸው የትምህርታቸውንና የእድሜያቸውን ያህል የማያስቡ እንደ እንስሳ ያለ ሆዳቸው ምንም ነገር የማይታያቸው፤ ካለባቸው የአድር ባይነት ርካሽና ወራዳ ሰብእናቸው የተነሣ የዐፄ ኃይለሥላሴን የደርግን አሁንም ደግሞ የወያኔን ሥርዓት ወይም ደግሞ ደርግን ሲያገለግሉ ቆይተው አሁን ደግሞ የወያኔ ሹመኛ ሆነው ያለ አንዳች የአቋም ችግር እንደሚያገለግሉት ሆዳቸው አምላካቸው ክብራቸው በነውራቸው የሆኑ ግልሰቦችን እንደባዶ ብርጭቆ የሞሉባቸውን ሁሉ የሚሞሉ፣ በዚህ ርካሽና ወራዳ ማንነታቸውም ከሰው ፊት ሲቀርቡ ቅንጣትም እንኳን ሐፍረትና መሸማቀቅ የማይታይባቸውን ግለሰቦች አግኝቶ መንቀሳቀሱ አይቀርም፡፡ ምን ቢሠራ ምን ቢያደርግ ግን የሕዝብ አመኔታን አያገኝም እንጅ፡፡
ነገር ግን አገዛዙ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንቅሮ እንደተፋው አውቆ ምንም ቢያደርግ ተአማኒነት አግኝቶ ተጠቃሚ በሚሆንበት መንገድ የሚያደርገውን አስመሳይ ብሔራዊ እርቅ (National Reconciliation) መከወን እንደማይችል ከተረዳ ግን ጡንቻው ሊያቆየው እስከቻለለት ጊዜ ድረስ እየተንገታገተ ይቆይና የፍጻሜው ሰዓቱ ሲደርስ በየመቀመጫችን የቀበረብንን የዘርና የሃይማኖት የሰዓት ፈንጅዎች (Time Bombs) በማፈንዳትና ሀገሪቱን በማፈራረስ ለፍርድ የሚያቀርብ ጠያቂና ከሳሽ አካል እንዳይኖርበት ለማድረግ እንደሚሞክር ካላቸውና ከምናውቀው “ከእኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” ተፈጥሯቸውና ከእስከዛሬው ፀረ ኢትዮጵያ ሸራቸው በመነሣት መረዳት ይቻላል፡፡ ወያኔ ሁለቴና ሦስቴ አይደለም ሽህ ጊዜ እንኳን በምርጫ ቢሸነፍም ተሸንፌያለሁ ብሎ ሥልጣን የማያስረክብበትም ዋነኛው ምክንያት ይሄ ነው፡፡ ሥልጣን በለቀቀ ማግሥት በፈጸመው ግፍ፣ ሙስና፣ ወንጀልና የሀገር ክህደት ሁሉ እየታነቀ ለፍርድ እንደሚቀርም አሳምሮ ስለሚያውቅ፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ ወያኔ ከደገሰበት የጥፋት ድግስ አንጻር ሊጠነቀቃቸው የሚገቡ በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም ይህ የወያኔ ሀገሪቱን አፈራርሶ የመጥፋት ሰይጣናዊ ተግባር እውን ይሆናል ብሎ ግን ቅንጣት ታክል እንኳን እንዳይጠራጠርና ሥጋት እንዳያድርበት ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ ይህች ሀገር መቸም ጊዜ ቢሆን ባላት የሠራዊት ብዛትና ኃይል ብቻ በመመካት ከጥፋት የዳነችበት ወይም የተረፈችበት ዘመን ኖሮ አያውቅም፡፡ ይልቁንም በየበረሀው በየገዳሙ በየዋሻው በየፍርኩታው በየበዓታቸው ጤዛ ልሰው ቅጠል ቀምሰው ዳዋ ጥሰው ድንጋይ ተንተርሰው ግርምዓ ሌሊቱን ፀብአ አጋንንቱን ታግሰው በአስጨናቂ ጾም ጸሎት ሥግደትና የተለያዩ የመከራ ትሩፋት ስለ ተወዳጅ ሀገራቸውና ሕዝባቸው መከራ በመቀበል በሚያለቅሱት በቅዱሳኖቿ ጸሎትና ምልጃ እንጅ፡፡ ይሄንን ያህልም የተፈተነውና መከራ እያየን ያለነውም የእነሱን ጸሎት ፈጣሪ ስላልሰማ ወይም ስለማይሰማ አይደለም፡፡
የዚህ ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በዕብ. 12፤5-11 ላይ ይገኛል “ልጀ ሆይ የጌታን ቅጣት አታቃልል በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል፡፡ ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታቹሀል፡፡ ለመቀጣት ታገሡ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርጋቹሀልና፡፡ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኗልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃሎች እንጅ ልጆች አይደላቹህም፡፡ ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋ አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይዎት ልንኖር በተገባን? እነሱ መልካም ሆኖ እንደታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል፡፡ ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጅ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል” ይላል ቃሉ፡፡ “የእስራኤል ልጆች ሆይ! እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላቹህምን? ይላል እግዚአብሔር” ትን. አሞ. 9፤7 በመሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን ልጆች እንጅ ዲቃሎች አይደለንምና ምንም ቢበድሉ የቱንም ያህል ቢረክሱ ቢያምፁበትም ምንም እንደማይላቸው እንደ ሌሎች ሀገራትና ሕዝቦች ዝም አይለንም እሽ እስክንልና እስክንመለስ ድረስ ይቀጣናል፡፡
ትናንትና በቅዱሳኖቿ ጸሎትና ልመና እንደሚመጣባትና እንደሚደርስባት የፈተናና የመከራ ክብደትና ብዛት ሳያደርግባት እንደአመጣጡ እየመለሰ ከብዙ መከራና ጥፋት የታደጋት አምላክ ዛሬም አለ፡፡ በእርግጥ ቃሉ “እሽ ብትሉ ለኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላቹህ እንቢ ብትሉ ግን ብታምፁም ሰይፍ ይበላቹሀል” ትን.ኢሳ. 1፤19-20 እንዳለው ይህ ሁሉ ጉድ የመጣብንና የተሰበርነው እንቢ በማለታችን መሆኑን ሁሉም እያንዳንዱ ወደሌላው ሳይሆን ወደ ራሱ ወደ ውስጡ በመመልከት ምን ያህል እንዳመፅን እንደረከስን እንደበደልን ከውስጡ ከሚያገኘው መልስ የሚረዳው ነገር ቢሆንም ምን ብንበድለው ምን ብናሳዝነው እንዲህ ወያኔ ላሰበብን ለደገሰብን ዓይነት ጥፋት አሳልፎ ይሰጠናል ብላቹህ ቅንጣት ታክል እንኳን እንዳትሠጉ፡፡ “እመኑ እንጂ አትፍሩ”
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በእግዚአብሔር ቸርነትና በራሱ በልጆቹ ጥረት ቀድሞ በመንቃት ከጫፍ እስከ ጫፍ ወያኔ የተከለብንን የዘርና የሃይማኖት ፈንጅዎቹን በማምከን ሌሎች እሾሆቻችንም በመንቀል በአዲስ መንፈስ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ ሆኖ በመነሣት ከጥፋት ይድናል የሚል የጸና እምነት አለኝ፡፡ ለወያኔ የምንሰጠው ወይም የማንነፍገው ነገር ቢኖር ፍትሕና ሕትህ ብቻ ነው፡፡ ሁሉም የዘራውን ማጨዱ ግድ ነው፡፡ ቃሉም እንደሚል “ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና” ገላ 6፤7 ፡፡ እናም በብዙ ነገር የቆሰለውን የደማውን ያመረቀዘውን የሀገር አንጀት የሚያጠግገው ቂም በቀልን የሚሽረው ፍትሕ ብቻ ነው፡፡ ለዚህች ከቅርብ እርቀት ላለች ትንሣኤያችንን ለምታረጋግጠው ብሩህ ቀናችንም ታጋዩ አርበኛው ወታደሩም በጽናት ይታገል፣ ሁሉም ዓይነት ሠራተኛ በትጋት ይሥራ፣ ገበሬውም በብርታት ይረስ፣ ካህኑም በንጽሕና ይጸልይ ይቀድስ፣ እናቶችም ያለ እረፍት ይማለሉ፣ ሁሉም ዜጋ እጁ ላይ ባለው ነገር ሁሉ የመጨረሻ ይበርታ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
http://www.goolgule.com/tplfeprdf-pleading-national-reconciliation/