አዎን አውቃለሁ፣ የምን ምርጫ ነው ትሉ ይሆናል፡ ይህም የኔም ጥያቄ ነው የእናንተ ብቻ ሳይሆን። የህውሃት/ወያኔ አገዛዝ እስካለ ድረስ በኢትዮጵያ ዳግም ትክክለኛ የሆነ ምርጫ ሊደረግ እንደማይችልና እንደማይኖር ብዙዎች የተነበዩት ነው። የሕዝብን ድምፅ አክብሮ በተሸናፊነት አምኖ ወያኔ ሥልጣኑን የመልቀቁ ጉዳይ ያከተመለት ይመስላል።
ህውሃት/ወያኔ አሁንም ስለምርጫው በሰፊው በማውራት ላይ ይገኛል፡ ሕዝብን በእህልና በምግብ አቅርቦት፡ በሥራ እድልና በመሳሰሉት እንደ ቀብድ በማስያዝ፡ በፓርቲው ስር ካልታቀፉ በሐገሪቱ ውስጥ ሊያገኟቸውና ሊጠቀሙባቸው የሚገባቸውን ሰብዓዊ መብቶች በመግፈፍ በውዴታ ሳይሆን በግዴታ የፓርቲውን የአባልነት ፎርም በማስሞላት ላይ ይገኛል። በቀደመው ምርጫ ድምጻቸውን ለተቃዋሚዎች የሰጡትን ግለሰቦች ከስራቸው እንዲባረሩ ወይም ሐገር ለቀው እንዲወጡ ለመጪውም ምርጫ እንቅፋት የማይሆኑበትን መንገድ በመቀየስ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል፡
ለማንኛውም ባለፈው የክልል ምርጫዎች እንደተደረገው አሁንም ምርጫው የሚካሄደው ወያኔ ከራሱ ከወያኔ ጋር ይሆናል እንጂ በዚህ ሁካታና የመብት መጣስ በሰፊው በተንሰራፋበት ሁኔታ ጠንካራ ተቃዋሚ ገብቶ ሥነሥርዓት ባለው ሁኔታ ምርጫ ይካሄዳል ማለት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው። ለዚህም ነው 2002 ምርጫ ሲሉን የምን ምርጫ የሚለው ጥያቄ ሲያስተጋባ የምንሰማው።
እውነት ግን የምን ምርጫ ከአሁን በኋላ?
No comments:
Post a Comment