FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, December 13, 2013

ወጣቱ የሰሜን ኮሪያ መሪ አጎታቸውን ገደሉ!

ለቀሪዎቹ “መቀጣጫ” ነው ተብሏል

jang5
jang3
መካከል የሚታዩት ጃንግ ሶንግ-ታዬክ በቀኝ ያሉት ወጣቱ መሪ ኪም ጆንግ ኧን ናቸው
ሰሜን ኮሪያን ለረጅም ዓመታት ሲመሩ የነበሩትንና ሥልጣናቸውን ከመጀመሪያው የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት ኪም ኤል ሱንግ የተረከቡት ኪም ጆንግ ኢል ባልተጠበቀ ፍጥነት ሲሞቱ ወጣቱ ኪም ጆንግ ኧን ሥልጣን መንበር ላይ ተቆናጠጡ፡፡ በወቅቱ በሃያዎቹ መጨረሻ ዕድሜ ላይ የሚገኙት ኧን ከልምድ ማነስ ችግር ውስጥ እንዳይገቡ በማሰብ አባታቸው ኪም ጆንግ ኢል አስቀድመው ከጎናቸው የሚሆኑ ሞግዚትና አለማማጅ አዘጋጅተው ነበር፡፡
ኪም ጆንግ ኢል የጤናቸው ሁኔታ እየተቃወሰ መምጣቱን በአብዛኛው ይፋ ሆኖ ባይታወቅም ለእርሳቸው ግን የተሰወረ ባለመሆኑ የሥልጣኑን መንበር ሲያዘጋጁና ሲመቻቹ ከአንድ ዓመት በላይ አልፏቸዋል፡፡ በመንግሥት ውስጥ ያለውን አመራርና አሠራር እንዲያስተምሯቸው አጎት ጃንግ ሶንግ-ታዬክ ተመደቡ፡፡ ኪም ጆንግ ኢል ከሞቱም በኋላ ልጃቸው ኪም ጆንግ ኧን በፕሬዚዳንትነት ሥልጣኑን ቢረከቡም ወሳኝ የሆነው የአገሪቱ ሥልጣንና አስተዳደር በሞግዚታቸው አጎት ጃንግ የተያዘ ነበር፡፡ ሰሞኑን ከሥልጣን እስኪወገዱ ድረስ አጎት ጃንግ ከታላቁ መሪ ወሳኝ ፖሊሲ አማካሪነት በተጨማሪ የብሔራዊ መከላከያ ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ነበሩ፡፡Jang2
የአጎት ጃንግ ወንጀል ይፋ ከሆነ በኋላ በድንገት ከፖሊት ቢሮ ስብሰባ ላይ በወታደሮች እንዲወገዱ ተደረገ፡፡ ከዚያም ወደ ወታደራዊ ፍርድቤት እንዲቀርቡ በመደረግ በሞት እንዲቀጡ ተወሰነባቸው፡፡ የሞት ቅጣቱ ከተፈጸመ በኋላ የሰሜን ኮሪያ ዜና አገልግሎት አጎት ጃንግ “አሳፋሪና አጸያፊ ህይወት ሲመሩ” የነበሩ መሆናቸውን በመግለጽ ረጅም ዘገባ አወጣ፡፡ “ስኳሮቻቸው” ምን እንደነበሩ በዝርዝርም ተነገረባቸው፡፡ ገንዘብ አባካኝ፣ አደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚ፣ ለህክምና ወደ ውጭ አገር ተልከው በርካታ ገንዘብ ያባክኑ፣ ቁማርተኛ፣ ሴት አውል (ሴሰኛ)፣ ሙሰኛ፣ … ፡፡ ወዲያውም በሰሜን ኮሪያ ታሪክ ተፈጽሞ በማያውቅ መልኩ በይፋ ከፖሊት ቢሮ በወታደር ታጅበው ዘብጥያ ወረዱ፤ ከማንኛውም መንግሥታዊ ሥልጣናቸውም ተገፈፈ፡፡ ሰሜን ኮሪያ ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት “የማጽዳት ሥራ” አካሂዳ ታውቃለች ነገር ግን በዚህ መልኩ በይፋ ተደርጎ አያውቅም፡፡
jang6
በግራ በኩል በሚታየው ፎቶ ጃንግ ሶንግ-ታዬክ የነበሩ ሲሆን እርምጃው ከተወሰደባቸው በኋላ በሰሜን ኮሪያ ቲቪ ምስላቸው ተቆርጦዋል
የክሱ መዝገብም ዳጎስ እንዲል መንግሥት ለመገልበጥ የሞከሩ የሚል ተጨመረበት፡፡ ባስቸኳይ የጦር ፍርድቤት ተወስደው ሞት ተበየነባቸው፡፡ ተገደሉ፤ የኮሪያ ዜናም ሃተታውን አወጣ፤ ከዚያም አልፎ በፊት በሞግዚትነት ከሚረዷቸው ኧን ጋር የተነሱት ፎቶዎች በሙሉ የአጎት ጃንግ ምስል በፎቶ ማረሚያ ጥበብ እንዲወገድ ተደረገ፡፡ አጎት ጃንግ ከሰሜን ኮሪያ ታሪክ፣ አመራር፣ ህይወት፣ … ተሰረዙ፡፡ ማንነታቸውም ጭምር ተወገደ፡፡ ግን ይህ ሁሉ ለምን መደረግ አስፈለገው? ታላቁ መሪ ኧን ለምን በሞግዚትና አጎታቸው ላይ ይህንን ዓይነት አሰቃቂ ፍርድ ፈረዱ?
በኮሪያ ጉዳይ ላይ አጥኚ የሆኑት አንድሬ ላንኮቭ ሦስት ምክንያቶችን ያቀርባሉ፡-
  1. ሞግዚቶች ብዙውን ጊዜ ሥራቸው ሲጠናቀቅ ይወገዳሉ፡፡ ወጣቱ ኧን ወደ ሥልጣን መንበር ሲመጡ ብዙ ልምድ ስላልነበራቸው በአጎት ጃንግ ትዕዛዝና አመራር ነበር በርካታ ጉዳዮችን ሲፈጽሙ የቆዩት፡፡ አሁን ግን ሰላሳዎቹን ደፍነዋል በሚባበት ወቅት ላይ ስለሚገኙ የአመራር ብቃታቸውንም ሆነ በግላቸው የሚወስኑ መሆናቸውን ለማሳይት ይፈልጋሉ፡፡ ከዚህም በላይ በፊት እንደ አለቃ ይህንን አድርግ ይህንን አታድርግ ሲሏቸው የነበሩትን ሰው ማስወገድ ቀዳሚ ተግባራቸው መሆን አለበት፡፡ ተፈሪ ለመሆን ይህንን ማድረግ የግድ ሆኖባቸዋል፡፡ የዚያኑ ያክልም ይኸው ድርጊት በሌላ አቅጣጫ ኧን ራሳቸውን መቆጣጠር የማይችሉና አሁንም ብስለት የሌላቸው አድርጎ ሊያስገምታቸው ይችላል፡፡
  2. ኧን የተከፈለው ተከፍሎ የራሳቸውን የአገዛዝ መስመር ለመጀመር ፈልገዋል፡፡ የበፊቱ ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኢል ከአባታቸው ኪም ኤል ሱንግ ሥልጣን በተረከቡ ጊዜ በአገሪቱ ላይ ረሃብ በመንገሡ ሥልጣን ለመረከብ ብዙም ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡ የወደፊቱን አስተዳደራቸውን ለመገንባትም የግድ የአባታቸውን ባለሟሎች በሥልጣናቸው ማካተት ነበረባቸው፡፡ በአንጻሩ ኪም ጆንግ ኧን እንዳባታቸው ሥልጣኑን ላለመረከብ የፈለጉ አይመስሉም፡፡ በሥልጣን መንበር ላይ ከተቀመጡበት ጊዜ ጀምሮ በሚዲያ ላይ በደጋጋሚ በመቅረብ የተለያዩ የልማት ሃሳቦችን በማቅረብ ሲታዩ ከርመዋል፡፡ በመሆኑም አሁን አዲስና የራሳቸው የሆነ ሥርዓት ለመገንባት በሚያደርጉት ጥረት የቀድሞ ባለሥልጣናትን ማስወገድ መፈለጋቸው እሙን ነው፡፡ አጎት ጃንግ ዓይነት መጠጥ ያሉ ባለሥልጣናትን ለማስወገድ በሚደረገው እርምጃ ተቃውሞ ሊኖር እንደሚችል ስለሚገመት አስቀድሞ ትልቁን ግንድ መገርሰስ ለሌሎቹ የሚሰጠው ትምህርት አለ፡፡ ለዚህም ነው በአጎት ጃንግ ላይ የተወሰደው እርምጃ በይፋ እንዲታይ የተደረገውም ለዚህ ነው፡፡
  3. በኮሪያ አመራር ውስጥ ያሉ አዛውንት አመራሮችን ሰጥ ለጥ ብለው እንዲገዙ ለማድረግ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ሰሜን ኮሪያ በርካታ በዕድሜ የገፉ አመራሮች በሥልጣን ላይ የሚገኙ በመሆናቸው አዲሱንና ወጣቱን መሪ ለመታዘዝ ያላቸው ተነሳሽነት ዝቅተኛ እንደሚሆን ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም ሁሉንም ታዛዥ እንዲሆኑና ለኧን ሥልጣናቸውን በሙላት እንደለማመዱ ለማድረግ አዛውንቶቹን አመራሮች ማስደንገጥ የግድ ይላል፡፡ በሰሜን ኮሪያ ሁለተኛ በነበሩት አጎት ጃንግ ላይ እንዲህ ዓይነት እርምጃ ከተወሰደ ሌሎች ለመገዛት መዘጋጀት አለባቸው አለበለዚያ የአጎት ጃንግ ዕጣ የእነርሱም ይሆናል፡፡
አፋኝ ሥርዓት በሕዝባቸው ላይ የደነገጉ አገዛዞች ተመሳሳይ አካሄዶችን እንደሚከተሉ በሙያው ላይ ጥናት ያደረጉ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ በሚገዛት ኢትዮጵያም በተመሳሳይ የሥጋ ዝምድና ያላገደው መበላላት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ የማርክሲስት ሌኒንስት ሊግ ትግራይ (ማሌሊት) ፈጣሪ የነበሩትና ሞት የቀደማቸው አቶ መለስም ኮሚኒስት እንደመሆናቸው በተቀናቃኞቻቸውና በወደፊት ባላንጣዎቻቸው ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ሲወስዱ ቆተዋል፡፡(ዜናውን ከተለያዩ የዜና አውታሮች የተጠናቀረ)

No comments:

Post a Comment