FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, June 13, 2013

ኢትዮጵያ በግብፅ ላይ ተመጣጣኝ የኃይል እርምጃ ለመውሰድ 1ሺ 500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል መታጠቅ ብቻ ይበቃታል Ethiopia may need missile that travels 1,500 KM

sendekየግብፅ ፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲ የሕዳሴውን ሃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን በተመለከተ ሁሉም አማራጮች በጠረጴዛ ላይ ናቸው ማለታቸውን ተከትሎ፣ አንድ የቀድሞ መንግስት ከፍተኛ ወታደራዊ ኤክስፐርት የግብፅ መንግስት ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ 1ሺ 500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል መታጠቅ ብቻ በቂ ነው ሲሉ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለፁ።
ኤክስፐርቱ እንደገለፁት “ግብፅ የሕዳሴውን ኃይል ማመንጫ ግንባታ ግድብ በጦር መሣሪያ ለመምታት ካስቀመጠቻቸው አማራጮች አንዱ መሆኑን በመጠቆም ግብፅ የሕዳሴውን ኃይል ማመንጫ ግድብ ስትመታ ለኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ በአፀፋው የአስዋን ግድብን እንዲመታ ሕጋዊ ፍቃድ መስጠቷን ልታውቅ ይገባል” ብለዋል።
አያይዘውም፤ “ግብፅ በወታደራዊ እቅዷ ከገፋችበት በኢትዮጵያ በኩል አማራጭ መንገዶችን መመልከት ተገቢ ነው። ለምሳሌ፤ ከሰሜን ኢትዮጵያ መነሻ አድርገህ ላቲቲውዱን በ14.3000 ዲግሪ እና ሎንግቲውዱን በ36.6167 ዲግሪ ብትወስደው እንዲሁም አስዋን የሚገኝበት ላቲቲውድ 23.9706 ዲግሪ እና ሎንግቲውዱን 32.8779 ዲግሪን አቀናጅተህ ብታሰላው በአየር ላይ ያለው ርቀት ከ1100 እስከ 1500 ኪሎ ሜትር የአየር ርቀት ነው ያለው። በዚህ ውጤት መነሻ የኢትዮጵያ መንግስት ከ1500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ የስከድ ሚሳኤሎችን መታጠቅ ብቻ በግብፅ አሰዋን ግድብ ላይ ተመጣጣኝ ሃይል ሊፈጥር ይችላል።” ብለዋል።
ወታደራዊ የአየር ርቀቱን ለመለካት የተሄደበትን አሰራር ቢያብራሩት ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ “ይህ ሮኬት ሳይንስ አይደለም። Movable Type በሚለው ድረ ገጽ ዲግሪውን በመጠቀም ማስላት ይቻላል። ቁም ነገሩ ግን ወታደራዊ አማራጭ ሁለቱንም ወገኖች ተጠቃሚ አያደርግም። ብቸኛው አማራጭ በዲፕሎማሲ ደረጃ ለመፍታት መሞከር ነው” ሲሉ ኤክስፐርቱ አሳስበዋል።
በአሁን ሰዓት በዓለማችን ላይ ከ1ሺ 500 ኪሎ ሜትር እስከ 15ሺ ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል የታጠቁ ሀገሮች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ ፈረንሳይ፣ ሕንድ፣ ኢራን፣ እስራኤል፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ቻይና፣ ፓኪስታን፣ ሩሲያ፣ ሳዑዲአረቢያ እና አሜሪካ ይገኙበታል።

No comments:

Post a Comment