FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Sunday, June 2, 2013

በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ወጥታችሁ ድምጻችሁን ላሰማችሁ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ምስጋና እናቀርባለን


ነፃነት በነፃ እንደማይገኝ አውቃችሁ ለሀገራችሁ እና ለህዝባችሁ መስዋእትነት ለመክፈል ለቆረጣችሁና ፍርሀትን ለሰበራችሁ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች በመላው አለም ተበትነን የምንገኝ የኢትዮጵያ ወቅታዊ መወያያ መድረክ (ECADF) ታዳሚዎች አድናቆታችንና ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በተጨማሪም ይህንን ህዝባዊ ሰልፍ ለጠራው እና ላስተባበረው የሰማያዊ ፓርቲ፣ አባላቱና ደጋፊዎቹ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲን ጥሪ ለደገፉና ለተባበሩ የፖለቲካና ሲቪክ ድርጅቶች፣ በማህበራዊ መገናኛ መረቦች ስትቀሰቅሱና ስታስተባብሩ ለነበራችሁ ለውጥ አራማጆች ያለንን አድናቆት ልናስተላልፍ እንወዳለን።ECADF Statment regarding Addis Ababa's demonstration
እንደተለመደው  እኛ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ (ECADF) የምንሰባሰብ ኢትዮጵያውያን ምንግዜም ከለውጥ አራማጅ ኢትዮጵያውያን ጎን ተሰልፈን የሚጠበቅብንን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደምንቀጥል በድጋሜ ቃል-እንገባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
ሀገራችን ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ
Ethiopian Current Affairs Discussion Forum (ECADF)

No comments:

Post a Comment