FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, June 8, 2013

የሕዝብ ድሎች ሲመዘገቡ-ሲጣጣሙ፤

በቅድሚያ ድል ሲባል ምን አይነት ድሎች አሉ ብሎ ማስተዋሉ ተገቢ ነው። በመሰረቱ በትእግስት፤በመቻል፤በሰላም፤በዝምታ የሚገኙ ድሎች አሉ። በትእግስት ዝም ብሎ ማስጨረስ ማሸነፍ ማለት ነው። ቀጥሎም ታግለው፤በሁለገብ አይነቱ ማለት ነው፤የሚገኙ ድሎች አሉ። ከዚህም ባሻገር እነዚህ መንገዶች አላስኬድ ሲሉ በግፊት የሚመጡ በጦር የሚገኙ ድሎች አሉ። በየአይነቱም አሽንፎ ማሸነፍ፤ተሸንፎም ማሸነፍ አለ። በተስተካከለ የትግል መስክ ማሸነፍና መሸነፍ፤ድል መንሳትና መነሳት አለ፤ ባልተስተካከለ መስክ ደግሞ አሸንፎ ማሸነፍ ተሸንፎ ማሸነፍም አለ።
እነዚህን መግቢያ ሓሳቦች ካስቀመጥን፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለው የት ነው? የትኛው ምእራፍ ለይ ደርሷል? ድሎቹስ ምን ይመስላሉ ብሎ ማስተዋልና መመርመር ለሚቀጥለው እርምጃ የሚበጅ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ታጋሽ ነው ሲባል በተግባር እንዳስመሰከረ የሓያ ሁለት አማታትን ውጣውረድ በትእግስት፤ በመቻል፤ በሰላም በዝምታ መወጣቱና መዝለቁ በቂ ምስክር ነው። ይህን አስተዋይና አዋቂ ሕዝም የተገላቢጦሽ ትእግስቱን እንደ ፍረሀት፤ አስተዋይነቱን እደደሞኝነት፤ ብስለቱን እነደድክመት ቆጥረው ለዘመናት መከራ ሲያዘንቡበት የቆዩትን ስርአት እንዳስቆጠረና አሁንም እየተደገሙ ናቸው። እዚህ ላይ ሕዝቡ ባሳያቸው አስተዋይነትና ትእግስት በታሪክ ምእራፍ ቅድሚያ ቦታ ይዞ መጠቀስ ያለበት አይነተኛ ድል ለመሆኑ አጠያያቂ አይሆንም። ባጭሩ ሕዝቡ በትእግስቱ በሰላማዊነቱና በአስተዋይነቱ ብዙ ድሎችን አስመዝግቧል። በወቅቱ-አሁንም። “እሰኪ እንያቸው” አለ እንጂ-ለዘመናት ተከመሩብን አላለም። አሁን መከራው ትእግስቱን አሟጧታል። ትእግስቱም መጠን ነበረውና። ይቀጥላል…

No comments:

Post a Comment