FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, June 26, 2013

በቤተመንግስት ግቢ ዙሪያ አንድ ሰው ተገድሎ ተገኘ

ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሀሙስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ጽህፈት ቤት ጀርባ ሁለተኛው በር ከ150 እስከ 200 ሜትር ባለ ርቀት ላይ አንድ ጎልማሳ አንገቱ ተቆርጦ  መገኘቱን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል።  
እማኞች እንደሚሉት  ሟቹ እድሜው ከ45 እስከ 53 የሚጠጋ ጸጉር አልባ ጎልማሳ ነው። የሟቹ የራስ ቅል ባእታ ክሊኒክ አቅራቢያ ባለ አንድ ቦታ ላይ ተጥሎ መገኘቱን የጠቆሙት ነዋሪዎች፣ ፖሊስ በአካባቢው ተገኝቶ አስከሬኑ እንዲነሳ ከአደረገ በሁዋላ ለአስከሬን ምርመራ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል እንዲወሰድ አድርጓል።
የአይን እማኞች ” አካባቢው 24 ሰአት ሙሉ በስለላ ካሜራዎች የሚጠበቅ በመሆኑ ድርጊቱ በቤተመንግስት ጠባቂዎች ካልተፈጸመ በስተቀር በሌሎች ዜጎች ተፈጽሟል ብሎ  ለማመን አስቸጋሪ ነው” ይላሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ የሚኒሊክ ሆስፒታልንና አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ለማነጋገር ላለፉት 5 ቀናት በተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም የሚኒሊክ ሆስፒታል ዛሬ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር፣ የህዝብ ግንኙነት እና የወንጀል ምርመራ ክፍሎች ስልኮች አይነሱም። ሚኒሊክ ሆስፒታል የአስከሬን ምርመራ ውጤቱን በተመለከተ መውሰድ የሚችለው ፖሊስ በመሆኑ ፖሊስን መጠየቅ አለባችሁ የሚል መልስ ሰጥተዋል።
የአካባቢውን ሁኔታ በደንብ የሚያውቁ አንድ ሰው እንደገለጹት አስከሬኑ በተገኘበት አካባቢ፣  በምሽት  ሰዎች እንደሚይዘዋወሩ ገልጸው ግድያው የተፈጸመው ምናልባትም በጠባቂዎች ሊሆን ይችላል ብለዋል። ያም ካልሆነ ግን መንግስት በመገናኛ ብዙሀን መረጃውን ይፋ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል ግለሰቡ ።

No comments:

Post a Comment