FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Sunday, November 10, 2013

ባለስልጣናት እና በተቃዋሚ ፓርቲ ውስጥ የተሰገሰጉ ሰላዮች ተጠያቂዎች ናቸው

በየትም አገር የአሸባሪነት ህግ አለን የሚሉ ዜጎቻቸውን አያጠምዱበትም::
ባለስልጣናት እና በተቃዋሚ ፓርቲ ውስጥ የተሰገሰጉ ሰላዮች ተጠያቂዎች ናቸው::
አሜሪካ ውስጥ ያፈነዳ የገደለ የተኮሰ የፈጀ …. አሜሪካዊ ዜጋ አሸባሪ ተብሎ ሲከሰስ ሲዘለፍ አላየንም ይልቅ እብድ ነክ ምናምን በሚል ከእስር ቤት ወደ ፍርድ ቤት እና ምርመራ ይሄዳል:: አሜሪካንም እኮ የአሸባሪዎች ህግ አላት:: ሆኖም ዜጎቿን አታጠምድበትም:: ከሌላ አገር ዜጋ ጋር አያይዛ ቲለጥፈዋለች … የአሜሪካ ዜግነት እንኳን ቢኖረው ኦሪጂኑን ነው የምትጠራው እንጅ አሜሪካዊ አሸባሪ ብላ አደባባይ ዜጎቿን በንዝህላልነት አታስርም አትገልም አታንገላታም:: ሌሎችም አገራት እንዲሁ …በአሸባሪነት ህግ ዜጋን አያጠምዱም :: የአሸባሪነት ህግ ከምንጩ በአሸባሪነት አሜሪካን የመዘገበቻቸውን አሸባሪ ድርጅቶች (ሕወሓትን ይጨምራል) ለመዳኘት የወጣ ነው::
እዚህ ጋ ግን ሲመጡ እኛ አገር የህጉ ትርጉም ለየት ብሎ እያየነው ነው::በዚህ ህግ ይዳኛሉ የተባሉት እነ አልቃይዳ እና የታጠቁ መሰሎቹ ሳይሆኑ የተዳኙበት የራሳችን ዜጎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ያውም ያልታጠቁ ብእር እና ወረቀት ያነገቡ የህዝብን ነጻነት እና መብት ያስተማሩ ወዘተ… ናቸው:: በአለም አቀፍ ደረጃ አሸባሪነትን ለመቆጣጠር የተባለው ዜጎችን ማጥመድ መሆኑ አሳሳቢነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በሃገራችን አሸባሪነ የተባሉት ግን የማናውቃቸው ሰዎች ሳይሆኑ መንግስትን በይፋ የተቃወሙ ለውጥ የጠየቁ የፖለቲካ መሪዎች ጋዜጠኞች እንዲሁም ሃይማኖታዊ ነጻነታቸውን የጠየቁ የሃይማኖት ምሁራን ናቸው::እንዲሁም የሰብኣዊ መብታቸው ተጥሶ ከህጉ ውጪ በላያቸው ላይ ከባድ እና አደገኛ የሆነ ፕሮፓጋንዳ እየተካሄደባቸው ሳይመሰከርባቸው እና ማስረጃ ሳይቀርብባቸው ወንጀለኛ ተደርገው እንዲታዩ ተደርጓል::
ይህ የሽብር ህግ በተለያየ ጊዜ እንዲስተካከል እና እንዲለወጥ እንዲሻሻል ዜጎችን ማጥመድ እንዲያቆም .. የተለያዩ ቡድኖች አገሮች እና ኢትዮጵያውያን የገዛ የወያኔ ስርኣት አባላት ሳይቀሩ እየተናገሩ ነው :: ግን የወያኔው ጁንታ ይህንን ለስልጣን ማስረዘሚያ እና ለተቃዋሚዎች ማፈኛ እየተጠቀመበት ነው::በአለም አቀፍ ደረጃ አሸባሪ እንደሆነ የሚታወቀው ሕወሓት ምእራባውያን እየነቁ እንዳይነቁ አድርጎ እያጭበረበራቸው በሚያገኘው የብድር እና የእርዳታ ገንዘብ ዜጎችን ለማፈን እና ለመግደል እየተጠቀመበት ነው::ይህ የሽብር ህግ የማያፍናቸው አፋኞቹን የአገሪቱ ባለስልጣናት እና በተቃዋሚ ውስጥ የተሰገሰጉ ባላንጣዎችን የሚያሳፍኑ ብቻ ነው::
ይህንን ህግ በተመለከት መፍትሄ ከማምጣት ይልቅ በየጊዜው ለማፈኛነት መጠቀምን የመረጠው የወያኔ ጁንታ ከትግራይ እስከ ሞያሌ ከጋምቤላ እስከ መልካጀብዱ እና ጎደ በሃገሪቱ በተለያዩ ማእዘናት ዜጎችን በማሳደድ ሰርተው እንዳይኖሩ እንዲፈናቀሉ የፖለቲካ እምነታቸውን እንዳያራምዱ እንዳይጽፉ እንዳያነቡ በማድረግ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ሽብርን እየነዛ አሸባሪ እያረገ በማሰር ከአገር ተሰደው እንዲወጡ በማድረግ እና በመግደል ጭምር ወንጀል እየፈጸመ ስለሚገኝ ህዝቦች በጋራ ታግለን ስርኣቱን መቃብር ልንከተው ይገባል::

No comments:

Post a Comment