FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, November 14, 2013

ከካሌብነት ወደ ከልብነት

በእውቀቱ ሥዩም

ethio saudi6


ኢትዮጵያ እመ-መከራ
የግዜር መመራመሪያው የስቃይ ቤተ-ሙከራ
መውደቅማ ነበር ያባት
እንደ ያሬድ እስከ ሰባት
እንደ በላ ብላቴና፣ የእንክርዳድ ሙልሙል እንጎቻ
የትውልዴ እጣ ፋንታ ፣ መውድቅ መውድቅ መውድቅ ብቻ…
አጤ ካሌብ የተባለ የኢትዮጵያ ንጉሥ ባንድ ወቅት በቅድመ-እስልምና የመን የሚኖሩ ክርስቲያኖች ባንድ ያይሁድ ገዥ መዳፍ ስር መማቀቃቸው አስቆጥቶት ቀይ ባሕርን ተሻግሮ ተበቅሎላቸዋል። የዛሬውን አያድርገውና፣ እንኳን ለቤት ለጎረቤት ጥቃት የሚቆረቆር ንጉሥ ማፍራት ችለን ነበር፤ አንኳን ለቤት ለጎረቤት እርዳታ የሚበቃ ጉልበት ማካበት ችለን ነበር። ዛሬ ግን ጊዜ ከካሌብነት ወደ ከልብነት ደረጃ አውርዶናል። (“ከልብ” በግዕዝ ውሻ ማለት ሲሆን በአማርኛ ዘይቤ አንድ ሰው ያለ ካሳ ያለ ጉማ ደሙ ፈሶ ሲቀር ደመ ከልብ ሆነ ይባላል)።
አቅመ-ቢስ ሕዝቦች በጉልቤ ሕዝቦች መዳፍ ስር ገብተው መከራ ማየታቸው በታሪክ ብርቅ አይደለም። እኔን የሚገርመኝ በፋንታችን መከራ ማየታችን አይደለም፤ እኔን የሚገርመኝ ከዚህ ሁሉ መከራ በሁዋላ ከመከራ የሚታደገን የኑሮ መላ አለማፍለቃችን ነው። ከመከራ መደራረብ በሁዋላ ያፈለቅነው የስልጣኔ ፍሬ የሙሾ ግጥም ብቻ መሆኑ ያስደንቃል።
አይሁድ በሁለተኛው ያለም ጦርነት ግፍ ከደረሰባችው በሁዋላ አንሰራርትው በርትተዋል፤ እንደ ኒቼ “ጨርሶ የማያጠፋኝ ሁሉ ያበረታኛል” ብለዋል። ዛሬ በነዳጅ መስክ ላይ የበቀሉ አረሞችን (አረቦችን) ያርበደብዳሉ ። ጀርመኖች በሁለተኛው ያለም ጦርነት ማክተሚያ ላይ በጠላቶቻቸው ከስክስ ጫማ ደቀዋል። ግን በአጭር ጊዜ አንሰራርትው ሃይላችውን እንደ ንስር አድሰዋል፤ እኛስ ይሄን ማድረግ ያቅተናል? አያቅተንም። ያገራችን አስተዳዳሪዎች፣ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ሀያል መንግስቶች ከመከራ ዶፍ የማይታደጉን ነዳላ ጃንጥላ መሆናችውን አይተናል። የራሳችን አዳኞች ራሳችን መሆናችንን አንርሳ፤ ጎበዝ የዳይኖሰርን ፈለግ ከመከተላችን በፊት ትንሽ መላ እንምታ::
- በእውቀቱ ሥዩም ፌስቡክ የተወሰደ (November 11, 2013)

No comments:

Post a Comment