FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Sunday, November 10, 2013

በውሸት የሚያሸብረው አሸባሪ መንግስት!

እለቱን ባላስታውሰውም ግንቦት 20ቀን1983ዓ.ም ወያኔ አዲስ አበባ ሲገባ በቦታው ሆኘ ያለውን ቆራጥነት ለዚያች ቀን መብቃታቸውን ለህዝቡ ጥሩ ነገር ይዘው ይመጣሉ ብዬ ባላስብም ግን ጽናትና ብርታታቸውን ግን ከሚያደንቁ አንዱ ነበርኩ‘። እውነተኞች ውሸት የሌለባቸው ሌብነት የሚጸየፉም ሆነው ሲቀርቡ ይበል አልን እንጂ የተቃወመም አልነበረ ፤ እዲያውም እዲያውም ከማስታውሰው መርካቶ ተክለሃይማኖት አካባቢ ግልጽ መኪና ላይ ሆነው ሰው ከቦ ሲያወራቸው ከመኪናው ላይ ኩንታል ስኮር ተሰርቀው ዋይ ዋይ ሲሉ ምስኪኖች ብዬ ስቄ ነበር ። ከዚያም በመቀጠል ሌባ ሲሰርቅ ከተያዘ ይገደል ሲሉ እረ ጎበዝ ይህ ነገር ተባለ፤ ግና በሌባው አጀብ የሚፈልጉትን በማስወገድ  ሌብነቱና  ውሸቱም ተያይዞ ቀጠለ።                                

ይቅርታ ብዙም እዳልዘባርቅ እንዲያው ለመንደርደሪያ ብዬ እንጂዛሬ እዲያው ያአሸባሪው ታሪክና አካሄዱ የሚያስቅ የውሸት ድራማ ላወጋችሁ ነው ። ባለፈው ጊዜ የኢትዩጵያ ብሔራዊ ቡድን ከናይጀሪያ አቻው ጋር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ቀን በቦሌ ክፍለ ከተማ አሸባሪወች በስታዲየም ባሉ ንጹሀን ዜጎች ላይ ፈንጂ ለማንጎድ ሲዘጋጁ በራሳቸው ላይ ፈንድቶ  አሸባሪወች በፍንዳታው ሰውነታቸው በቃጠሎ አረው ሲሞቱ በቤቱ ላይ ከፍተኛ ቃጠሎ ተነስቶ ንብረት እንደጠፋ ወያኔ እደፈለገ የሚአደርገው ቴሌቨዝንና ሬድዮ ሲናገር ተከትሎም የፌደራል ፖሊስ መግለጫው ስታዲየም ገብተው ሊያፈነዱ እደነበረ ከቤቱም የኢትዮጵያ ባንዲራ እዳገኙና ሁለቱም የሱማሌ ዜጎች እንደሆኑ ነገሩን ውሸት ይላሉ………እንደዚያ ነው ባንዲራው ከምን ተሰርቶ ነው ሳይቃጠል የቀረው አንድ አትሉም ፤ አሁን ደግሞ በቤንሻንጉል ክልል አሸባሪዎች የቀበሩት ፈንጂ መለስተኛ አውቶቡስ በላዩ ላይ ቆሞ ነው አደጋው የደረሰው ነው ያሉን ? ይገርማል የነሱን የድንቁርና አባባል ህዝብ ይሰማናል ማለታቸው፤ ፈንጂ ላይ የቆመ መኪና አካሉ ይቆራረጣል፤ ይፈናጠራል ቢያንስ የቆመበት ጎማ ይበተናል በሚዲያ ተለቆ ያየነው ምስል የሚያሳው ከመኪናው ውስጥ ቃጠሎ እንደሆነ በትክክል ያሳያል ሃያ አመት ውሸት የተማረን መንግስት እውነት እንዴት ይቀበላል ነው የምትሉት ታዲያ??
Terror in Ethiopia

No comments:

Post a Comment