FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, November 28, 2013

ፍትህ የጎደለው ስደት እስከ መቼ!

ከሀና ሰመረ (ኖርዌይ)
hannasemere@yahoo.com


የምንሰማውና የምናየው የኛው ከልክ ያለፈ አሳዛኝ ዜና አላስችል ቢለኝ እንደው ትንሽ የውስጤን ሀዘን እና ብሶቴን
ቢገልፅልኝ ብዬ ብዕሬን አነሳው::

እኔ የምላቹ እንደው የሰው ልጅ እንዲህ እንዴት ከፋ? አምላክ በራሱ አምሳል የፈጠረውን ሰውን የሚያህል ክቡር
ፍጡር ለማጥፋት እንዲህ መሯሯጥ ምን የሚሉት ነው? እኛ ኢትዮጵያኖች ለምን ይሆን እንዲህ በየቦታው
ስቃያችን የበዛው? እውነት ግን የምላችሁ ወገኖቼ አያት ቅድመ አያቶቻችን አገራችንን ከወራሪ ጠላት ጠብቀው
ያስከበሩ እና እንዳስከበሩ ሲነገር የቆየው የጀብዱነት ታሪክ በደመ ነፍስ በሚወዛወዘው በወያኔ ድርጅት ከስር
መሰረቱ ለማፍረስ የታለመ ነው:: ይህንን እኩይ ተግባር በቸልተኝነት መመልከት ከታሪክ አጥፊው ጎራ አብሮ
ከመሰለፍ ተለይቶ አይታይም:: ግን እስከመቼ ብለን የጊዜ ቀጠሮ ይዘን ነው አያቶቻችን ደምና አጥንት ከፍለው
ባስረከቡን ሀገር ላይ ነፃነታችንን ተነፍገን ተራ እየጠበቅን የስደትን መራራ ፅዋ የምንጎነጨው ግን እስከመቼ?
ይህንን ጥያቄዬን ልብ ያለው ለራሱ ይመልስ::

ኢህአዴጋውያንን ሳይሆን በመላው አለም ያሉ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ያሳዘነና ያስቆጣው በሳውዲ አረቢያ
የሚኖሩ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ላይ የሚደርሰውን በርካቶችን እስከ ሞት ፤ ሴት እህቶቻችንን እስከ መደፈር
፡ እንዲሁም ወንድሞቻችንን ለከፍተኛ ድብደባ ከዳረገውም በላይ የህወሀት አባላት በሳውዲ አረቢያ ልጅም
ዘመድም ስለሌላቸው ወገኖቻችንን ካሉበት ችግር ለማውጣት የተከፈለ አመርቂ እንቅስቃሴ የለም:: እንዲያውም
በተገላቢጦሽ አረቦቹ በመለስ ዜናዊ ለብዙ ዓመታት በሊዝ የሰጣቸውን መቶ ሺህ ሄክታር የኢትዮጵያውያኑ መሬት
ላይ ህይወታቸውን ላጠፉ ፤ ሰብዓዊ መብታቸውን ለገፈፉ ፡ እንዲሁም ደማቸውን ላፈሰሱት ለሳውዲ አረቢያ
ህዝብ ቀለብ ሩዝ እያመረቱ ነው::

ይህም አልበቃ ብሎ ኢትዮጵያኖች ፍትህን ፍለጋ
በተሰደዱበት ዓለም ሁሉ በሙሉ ነፃነት
የወገኖቻቸውን በደል እልህ በተሞላበት ተቃውሞ
ሲያሰሙ ፤ ህዳር 6 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ
5:00 ሰዓት በተለምዶ ወሎ ሰፈር ተብሎ
በሚታወቀው አካባቢ ከአይቤክስ ሆቴል
ፊት ለፊት በሚገኘው የሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ
ደጃፍ ላይ የተቃውሞ ድምፃቸውን ሊያሰሙ
የተሰበሰቡትን በተወለዱበት እና በገዛ ሃገራቸው
የወገኖቻቸውን ስቃይ እንዳይቃወሙ
በፖሊስ የመባረርና ከፊሉም ለእስር ተዳርጓል::

ግን ማን ይሆን ስደትን ሐሴት አድርጎ ቀዬውን ጥሎ በባዕድ ሀገር የሚንከራተት? ፍትህ ቢጓደልበት፤የብልሹ
አስተዳደር ግፍና የጭቆና ቀንበር ከአቅሙ በላይ ቢሆንበት እንጂ፤ ለዚህ ሁሉ ችግሮች ተጠያቂው ለዜጎቹ
ህልውናና ክብር ግድ የለሽ የሆነው መንግስት ተብዬው ነው:: ለነገሩ ወያኔ ብዙ ትንንሽ አድርጎ ከፋፍሎ የወሰነውን
እኛ ካላፈራረስነው ችግራችንም ማብቂያ አይኖረውም የወያኔም አላማ ግብ ይመታለታል ስለዚህ ወገኖቼ “ህዝብ
መንግስትን ሳይሆን መንግስት ህዝብን” አገልጋይ የሚሆንበትን ስርዓት ለመገንባት እንዲሁም ለዚህ ያበቃንን
ስርዓት ለማስወገድ ድክመታችንን በጋራ መፍታት የትግሉ ቅድመ ሁኔታ መሆን አለበት::

ኧረ ማንን ይሆን እንክርዳዱን ከስንዴው አንጓሎ እንዲያስወግድልን የምንጠብቀው?

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

http://addisvoice.com/wp-content/uploads/2013/11/Hanni-file-21.pdf

No comments:

Post a Comment