FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Sunday, November 10, 2013

የመፀሃፍ ግምገማ “ዴሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ” ደራሲ ብርሃኑ ነጋ

የመፀሃፍ ግምገማ

“ዴሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ”
ደራሲ ብርሃኑ ነጋ
ግምገማ በጥላሁን አፈሣ
ብርሃኑን ከ ፳፭ አመታት ላላነሰ ግዜ በቅርብ የማውቀው ጓደኛየ ነው። ለሥራ ትጋቱ፣ ለቆመለት አላማ ፅናቱ፣ የማይረግበው የይቻላል መንፈሱ፣ ካወቅኩት ግዜ ጀምሮ ያልተለዩት መላያ ባህርዮቹ ናቸው። በእነዚህ አመታት ውስጥ፣ የአገሩን ጉዳይ በሚመለከት የተሳተፈባቸውንና ያከናወናቸውን መጠነ ሰፊ ተግባሮች መዘርዘር ይህ ቦታው ባይሆንም፣ በዚህ አጋጣሚ፤ እንደው በጥቅሉ ብርታቱን የሰጠው ግለሰብ መሆኑን በጨረፍታ ገልጬ ማለፍ እወዳለሁ። ሌላው ቢቀር ፣ የራሱን የግል ነፃነት ተነፍጎ፣ የነፃነት ጭላንጭል በማይታይበት በቃሊቲ ወህኑ ቤት ነዋሪ በነበረባቸው በነዛ ሁለት ፈታኝ ዓመታት ውስጥ፣ “የነፃነት ጎህ ሲቀድ” በሚል ርዕስ በቁርጥራጭ ወረቀቶች ላይ ከትቦ ገና ከቃሊቲ ሳይሰናበት ለህትመት አብቅቶ ያቋደሰንን ከ ፮፻ ገፆች በላይ ያካተተውን መጸሃፉን በማንበብ ብቻ፣ በእርግጥም ብርታቱን የሰጠው ሰው መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም። በተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ላይ ሆኖ በፃፋት በዛች ድንቅና ተስፋ ጫሪ መጽሃፉ መግቢያ ላይ፣ “ከአሜሪካ ኑሮዬ የተገነዘብኩት የነፃነት እና የኢኮኖሚ ብልፅግናን ጠንካራ ግንኙነት ነበር”፤ አገር ቤት ከተመለሰኩ በሗላ በጻፍኳቸው የተለያዩ ጽሑፎቼም “የዴሞክራሲ እና የኢኮኖሚ እድገት ትስስርን በሚመለከት በአጠቃላይና በተለይ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ብልፅግና የዜጎች ነፃነትና ዴሚክራሲያዊ ስርዐት አስፈላጊነትን መክሪአለሁ” በማልት በጽኑ የሚያምንበትን መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳብ አስምሮበት አልፎ ነበር። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]
Dr. Berhanu Nega's New book

No comments:

Post a Comment