FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Sunday, November 17, 2013

መቋጫ ያጣው የወገኖቻችን ስቃይ እና በደል በሳውዲ አረቢያ አሁንም ቀጥሏል!


ethio saudi 10


ትላንት አመሻሹ ላይ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገርሽቶ በዋለው ተቃውሞ የሞተ ባይኖርም ኢትዮጵያውያኑ ድምጻቸውን ከፍ አድረገው አማራው አንድነን … ትግሬውም አንድነን … ጉራጌው አንድነን … መብታችን ይከበር … እኛም ሃገር አለን ወዘተ… በሚል መፈክር ታጅበው ብሶታቸውን ሲያሰሙ መዋላቸውን የሚገልጹ የአይን እማኞች የሳውዲ የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞውን ለመበተን በከፈቱት ተኩስ አካባቢውን ወደ ጦርነት አውድማ ለውጦት ማምሸቱን ይገልጻሉ።
የጸጥታ ሃይሉ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ተጨማሪ ልዩ ፈጥኖ ደራሽ፡ ኮማንዶዎች በመታገዝ የኢትዮጵያውያኑን ተቃውሞው መግታት ተችሏል ብለዋል። እነዚህ ምንጮች ትላንት ተቀስቅሶ በነበረው ሁከት ጥቂት ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን በማውሳት ሰሞኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በውጭ ሃገር ነዋሪዎች ላይ ያወጣው ህግ የጊዜ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያውያኑ ላይ እየወሰዱ ባሉት የተናጠል እርምጃ አያሌ ወገኖቻችን ወደ ሃገሩ ለመመለስ ከየመኖሪያ ቤቱ ነቅሎ አደባባይ ቢወጣም ወደ ሃገር መግባት የሚያስችሉት ነግሮች በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ባለመመቻቸቱ ከሳውዲያኑ ወረበሎች አሰቃቂ ግድያ ተርፈው ወደ እስርቤት የተጓጓዙ ከ20 ሺህ የሚበልጡ ወገኖቻችን በምግብ ውሃ እና የመጸዳጃ ቦታ እጦት ቁም ስቅላቸውን እያዩ መሆኑ ተግልጾል።
ለሰው ልጅ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች ያልተሟሉበት ማጎሪያ ውስጥ 4 ቀናቸውን እንዳስቆጠሩ የሚነገርላቸው ኢትዮጵያዊያን እና ሪያድ መንፉሃ ጅዳ እና መካ እስከነ ልጆቻቸው በየመንገዱ ላይ ወድቀው ለመንገድ ላይ አዳሪ የተዳረጉ በመቶሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን ብሶት ለማድመጥም ሆነ ለማየት ከሃገር የመጣ የመግስት ባለስልጣን አለመኖሩ ታውቋል። ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ ጅዳ ከተማ ውስጥ ኢትዮጵያውያኑ የሚኖሩበት አካባቢ በሳውዲ የጸጥታ ሃይሎች እና በኢትዮጵያውያን መሃከል በተነሳ ግጭጥ 76 ሰዎች መቁሰላቸውን የሚገልጹት ምንጮች በዛ ቀውጢ የተኩስ እሩምታ በጥይት ተደብድቦ የተገደለ ኢትዮጵያዊ ሊኖር እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
ተቀማጭነታቸው ሪያድ እና ጅዳ ከተማ በሆኑት በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አምባሳደር እና የቆንስላው ጽ/ቤት ዲፕሎማቶች ላይ ተስፋ የቆረጠው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ወገናችንን ለማየት በኢትዮጵያ መንግስት መገናኛ ብዙሃን ወደ ሳውዲ አረቢያ ተጉዘዋል የተባሉት የልኡካን ቡድን አባላት እሰከአሁን ምንም አይነት የሚጨበጥ ነገር መስራት ባለመቻላቸው ኢትዮጵያውያኑ ለከፋ አልቂት በመዳረግ ላይ መሆናቸው ተገልጾል።
ሰሞኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያውያኑ በሳውዲ አረቢያ እየተፈጸመባቸው ያለውን የጅምላ ግፍ እና በደል ይሄን ያህል የሚጋግነን እና ቦታ የሚሰጠው አለመሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ትላንት ምሽት መንፉሃ አካባቢ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከ17 በሚበልጡ አውቶብስ ተጭነው እንደተወሰዱ የሚነገርላቸው ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ህጻናት ሴቶች አረጋውያን የሚገኙበት አያሌ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ከሪያድ የ6 ሰአታት ጉዞ በኋላ ያልታወቀ ምድረ በዳ የሆነ አካባቢ እንዲወርዱ መገደዳቸውን እና እስካሁንም ያሉበት ሁኔታ በውል እንደማይታወቅ ተገልጾል።
(Ethiopian Hagere ከጅዳ በዋዲ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በፌስቡክ በኩል የላኩት)

No comments:

Post a Comment