ማስተዋል ለማያቅተው
አንዳንዴ፣ ጊዜና ሁኔታውን ከጠበቁ አንድ ሁለት ቃላት፣ ከሺ ዓ/ነገሮች የበለጠ በአእምሮ ውስጥ ይገቡና እውነቱን ቁጭ ያደርጉታል።
አውሮፓውያን መቼም በዘረኝነት የተጠመቁበት ጊዜ አለፎና ተመክሮዋቸውን ሰብስበው ለራሳቸው፣ በተለይ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወዲህ፣ በሰላም ለመኖር ይሞክራሉ፤ የኋላኋላ ተባብረው፣ ቀደም ሲል ደግሞ ቢያንስ በየራሳቸው መንግሥታት ሥር። በተለይም ጀርመን ስለዘረኝነት ተመክሮ ያውራ ቢባል፣ ይህ እንደማይሳነውና እንደሚችል ማንንም አያጣላም። ይህም ሆኖ ግን አሁንም ህዝቡ ከዳር እስከ ዳር፣ ከዚህ በሽታ ነጻ ነው ማለት አይደለም። ስለሆነም በስፖርት ሜዳ ላይ ሁሉ በተለይም እግርኳስ ጨዋታ ላይ ይህ የዘረኝነት በሽታ ደጋግሞ ይንጸባረቃል። አልፎ አልፎም ከአፍሪቃ በመጡ ወይንም እዚህ በተወለዱ ጥቁር ተጫዋቾች ላይ የዘረኝነት ስድቡ ሲበዛ፣ አእምሮ ያለው ዳኛ ጨዋታውን አልመራም ብሎ እስቲያቋርጥ ድረስ ሁሉ ያጋጥማል። በቅርቡ እንደሆነው። በዚህ ዓይነት ሁኔታ፣ በአንድ የጠዋት የቴሌቪዥን የስፖርት ሪፖርት ላይ እንደተዘገበው፣ አንድ የክለቡ ባልደረባ የሆነው ተጫዋች፣ አንድ ጀርመን ሀገር የተወለደ ጥቁር ጓደኛው ላይ የሚሰነዘረውን ዘረኝነት አስመልክቶ፣ በፌስቡክ(Facebook) ላይ፣ ለአስነዋሪዎቹ የዘርኝነት ስድቦቹ እንደሚከተለው ይመልሳል (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
No comments:
Post a Comment