FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, August 1, 2013

ሰበር ዜና


በወላይታ የኢህአዴግ አባላት፣ፖሊስና ደህንነቶች በአንድነት አባላት ላይ ድብደባና ዝርፊያ እየፈፀሙ ነው
ፍኖተ ነፃነት
አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በሶዶ ከተማ ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ የነበሩ የአንድነት አባላትን ፖሊሶችና ደህንነቶች በመደብደብና ያሰባሰቡትን የህዝብ ፊርማ በመንጠቅ ላይ መሆናቸውን የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ የአንድነት የወላይታ ዞን አመራሮችም እንዳረጋገጡት ታርጋ ያልለጠፉ ባጃጆችንና ሞተር ሳይክሎችን የያዙ ፖሊሶችና ደህንነቶች በተደራጀ ሁኔታ የሚበተኑ በራሪ ወረቀቶችንና የፀረ ሽብር ህጉ እንዲሻር እየተሰባሰበ የሚገኘውን ፊርማ በመቀማት ላይ ናቸው፡፡
Fenote Nesant
አንድ ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ የወላይታ ዞን ፖሊስ አባል ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፀው የዞኑ አስተዳደሮች “የአንድነት አባላትን በእጃቸው ያለውን በራሪ ወረቀትና የፊርማ ማሰባሰቢያ ቅፅ ቀሙዋቸው እነሱን ማሰር አንዳች አይፈይድም” ተብለዋል፡፡
የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ሰብሳቢ አቶ ወኖ መንአሳ ለፍኖተ ነፃነት “ኢህአዴግ ያሰማራቸው ግለሰቦች ከአንድነት አባላት ላይ በራሪ ወረቀት ከመቀማት አልፈው ቦርሳ ፣ጫማ ፣በፌስታል የተያዘ ፍራፍሬ ሳይቀር በመቀማት ላይ ናቸው” ብለዋል፡፡ አያይዘውም ለስብሰባ ስራ የተዘጋጁ ቁሳቁሶችም እንደተዘረፉ አስረድተዋል፡፡

No comments:

Post a Comment