FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, August 6, 2013

ከእሁድ እስከ እሁድ

(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)




መንግስት በምእራብ አርሲ ዞን የተገደሉትን ሙስሊሞች ቁጥር መቀነሱን የአካባቢው ሰዎች ገለጹ
በምእራብ አርሲ ዞን በኮፈሌና አካባቢዋ የፌደራል ፖሊሶች በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ በወሰዱት እርምጃ 3 ሰዎች መገደላቸውና 7 ሰዎች መቁሰላቸውን የኦሮምያን ፖሊስ በመጥቀስ የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ቢዘግቡም የኢሳት ምንጮች በበኩላቸው የሟቾች ቁጥር ከ18 እስከ 25 ይደርሳል ይላሉ።
በአካባቢው የሚገኝ አንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የሟቾችን ቁጥር 18 መሆኑን ሲገልጽ፣ ወደ ኮፈሌ እና ዋቢ ከተሞች ለመግባት ሙከራ አድርጎ በፖሊሶች ፍተሻ ተንገላቶ ሳይሳካለት የቀረው ዘጋቢያችን ከከተሞች ሲወጡ ያገኛቸውን ሰዎች አነጋግሮ እንዘገበው የሟቾች ቁጥር ከ15 እስከ 20 ሊደርስ እንደሚችል ገልጿል።
beni-mosqueመንግስት ሙስሊሞቹ የጦር መሳሪያዎችን እንደያዙ አድርጎ ያቀረበው ዘገባ ትክክል አለመሆኑና የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ለግድያው ተጠያቂዎች መሆኑን የአካባቢውን ሰዎች አስተያየት በማሰባሰብ ዘጋቢያችን ገልጿል።
በዛሬው እለትም ውጥረት ሰፍኖ መዋሉንና ምናልባትም ለሁለተኛ ጊዜ ግጭት ሊከሰት እንደሚችል አክሎ ተናግሯል።
ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ በርካታ ቁጥር ያላቸው የፌደራል ፖሊሶች የኮፈሌ ጎረቤት ከተሞች ወደ ሆኑት አሳሳ ፣ ዶዶላና ኮሬ አምርተዋል። ከፍተኛ ውጥረት በሚታይበት ቢዘህ አካባቢ ግጭት ከተነሳ በቀላሉ ላይበርድ እንደሚችል ዛሬ ከሰአት በሁዋላ ወደ አካባቢው የተጓዘው ዘጋቢያችን ገልጿል።
በሙስሊም ወገኖች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችም እያወገዙት ነው። በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ የህወሀት ኢህአዴግ የፌደራል ፖሊስ አባላት የሀይማኖት መሪዎቻቸው ወይም ኢማሞቻቸው መታሰራቸውን በተቃወሙ ዜጎች ላይ የፌዴራል ፖሊሶች በከፈቱት ተኩስ  25ቱን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውንና በመቶዎች የሚቆጠሩትን  ማቁሰላቸውን ገልጾ፣ ድርጊቱን በጽኑ ኮንኗል።
ህወሀት ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ የኦሮሞን ህዝብ በተለይም የአርሲ ኦሮሞዎችን ኢላማ ማድረጉን የገለጸው ኦነግ ፣ በአካባቢው ህዝብ ላይ የሚፈጸመው የሽብር ጥቃት ህወሀት ህዝቡን የማፅዳት አጀንዳ እንዳለው የሚያሳይ ነው ብሎአል።
ህወሀት የኢትዮጵያን ህዝብ ለማስተዳደር የሞራል ብቃት የሌለው መሆኑን የገለጸው ኦነግ፣ ህዝቡ  ባገኘው መሳሪያ ሁሉ ራሱን እንዲከላከልና አገዛዙን ለማስወገድ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርቧል።
ግንቦት7 “ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ወያኔን እናስወግድ!!” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ “በወያኔ ፋሽስታዊ እርምጃ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻች” የተሰማው መሪር ሀዘን ገልጿል።
“ወያኔ በሥልጣን መንበር ላይ ውሎ ባደረ መጠን እንዲህ ዓይነቱ መርዶ  መስማታችን የማይቀር ነው ” የሚለው ግንቦት7፣ገዳዮች ለፍርድ መቅረብ እንዳለባቸውም ገልጿል።
በአገራችን ሰላም እንዲሰፍን እና መሠረታዊ  መብቶቻችን ተከብረውልን መኖር እንድንችል ወያኔን ለማስወገድ ህዝቡ ቆርጦ እንዲነሳም ግንቦት 7 ጠይቋል።
መንግስት የድምጻችን ይሰማ አባላትን በሙሉ አሸባሪ ብሎ እንደሚፈርጃቸው ይገልጻል። (ምንጭ: ኢሳት)
ከአርባ ምንጭ – የአንድነት ቅስቀሳ መኪና 4ቱም ጎማዎቿ ተንፍሰው ተገኙ
ለአርባምንጭ ሰላማዊ ሰልፍ በቅስቀሳ ላይ መሰማራቷ ያልተወደደላት መኪና እንቅስቃሴዋን ለመግታት ከ6 የቱሪስት መኪናዎች ተለይታ car4ቱም ጎማዎቿ ተንፍሰው ተገኙ ለሴቻ ወረዳ ፖሊሶች ሪፖርት ቢደርሳቸውም የበላይ አካል ካላዘዘን መጥተን ልንመለከት አንችልም የሚል ምላሽ በመስጠት የአለቆቻቸውን ትዕዛዝ እየተጠባበቁ ነው፡፡ (ምንጭ: ፍኖተ ነጻነት)
ኦሊምፒያ አካባቢ የሚገኘውን የቀበሌ መዝናኛ እሳት በላው
ባለፈው ዓርብ ረፋድ ላይ በአፍሪካ ጎዳና (ቦሌ መንገድ) ከደምበል ሲቲ ሴንተር ሕንፃ ጀርባ የሚገኘው ቀበሌ 20/21 መዝናኛ (17 መዝናኛ) በተከሰተ ድንገተኛ እሳት አደጋ ጉዳት ደረሰበት፡፡
መዝናኛ ማዕከሉ ለምሳ ምግቦች እየተዘጋጁ ባሉበት ከረፋዱ 4፡30 ላይ ከሥጋ መጥበሻ ቤት ተነሳ በተባለ እሳት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ የመዝናኛ ማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ አልቤ ለሪፖርተር እንደተናገሩትና ሪፖርተር በቦታው ተገኝቶ መመልከት እንደቻለው የመዝናኛ ማዕከሉ የምግብ ማብሰያ፣ የሠራተኞች ልብስ መቀየርያ፣ ማብሰያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች፣ ጄኔሬተር፣ የምግብ ግብዓቶችና በዕለቱ ሜኑ መሠረት ለምሣ የተዘጋጁ የተለያዩ ምግቦች ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል፡፡
‹‹ለምሳ የተዘጋጁ ምግቦች እስከ ሰባት ሺሕ ብር ድረስ ሽያጭ ነበራቸው፤›› ሲሉ አቶ ብርሃኑ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
Dembelቅፅበታዊው የእሳት አደጋ ከ35 እስከ 40 ደቂቃዎች ውስጥ መዝናኛ ማዕከሉ 300 ሺሕ ብር የገመተውን፣ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ኤጀንሲ 150 ሺሕ ብር የገመተውን ንብረት አውድሟል፡፡
ብዙዎችን ያስገረመው መዝናኛ ማዕከሉ የወደመበት ንብረት 300 ሺሕ ብር ሲገመት ሊጠፋ ይችል የነበረ ሁለት ሚሊዮን ብር መትረፉን መግለጹ ሲሆን፣ የእሳና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ኤጀንሲ በበኩሉ የወደመውን ንብረት በግማሽ ቀንሶ 150 ሺሕ ብር ሲያደርግ ሊወድም የነበረውን ንብረት ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ አድርጎታል፡፡ ይህ የግምት መፋለስ በወቅቱ መከሰቱ ጉዳዩን ለተረዱ ሰዎች አስገራሚ ሆኗል፡፡ የዕለቱን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር በአቶ ቁምላቸው ንጉሴ የሚመሩ 22 የኤጀንሲው አባላት ተሰማርተዋል፡፡
አቶ ቁምላቸው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ እሳቱን ለማጥፋት 13,500 ሊትር ውኃ ተጠቅመዋል፡፡ የእሳት አጥፊው ኤጀንሲ ወትሮ ከሚደርስበት ወቀሳ ነፃ መሆኑን ሪፖርተር ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎችና የመዝናኛ ማዕከሉ ሠራተኞች ገልጸዋል፡፡
ኤጀንሲው በአምስት ደቂቃ ውስጥ በቦታው መድረሱ ሲነገር፣ አቶ ቁምላቸው በዚህ ጊዜ ውስጥ ለመድረስ ከፍተኛ የተሽከርካሪ መጨናነቅ እንደነበር ጠቅሰው፣ የግድ እሳቱን መቆጣጠር ስለነበረባቸው ሕገወጥ ጉዞ አድርገው በስፍራው መገኘታቸውን አልሸሸጉም፡፡
በየጊዜው እየተከሰተ የሚገኘው የትራፊክ መጨናነቅ እሳት የማጥፋት ሒደቱን አስቸጋሪ እንዳደረገው አቶ ቁምላቸው አስረድተዋል፡፡  የቀበሌ 20/21 መዝናኛ ማዕከል 50 ሠራተኞች አሉት፡፡ ማዕከሉ መሿለኪያ አካባቢ የሚገኘው ቀበሌ 15 መዝናኛ ማዕከል በሥሩ ይገኛል፡፡
መዝናኛ ማዕከሉ በአሁኑ ጊዜ በሸማቾች የኅብረት ሥራ ማኅበር ሥር የሚገኝ ሲሆን፣ በሥራ አመራር ቦርድ ይተዳደራል፡፡ በደረሰበት ድንገተኛ አደጋ ላልተወሰነ ጊዜ ከአገልግሎት ውጭ የሚሆን በመሆኑ በማዕከሉ ሥር የሚተዳደሩ ሠራተኞች በዕጣ ፈንታቸውና በቀጣዩ የማዕከሉ አደረጃጀት ላይ የሥራ ኃላፊዎቹን በማነጋገር ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ (ምንጭ: ሪፖርተር)
“ህገ-መንግስታዊ መብታችንን ሳንገል እየሞትን እናስከብራለን!”
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ሰኔ 13 ቀን 2005 ዓ.ም በጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቆ ወደ ንቅናቄው ከገባ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ህዝባዊ ድጋፍና በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃት እና የነፃነት ጥያቄ ድምፅ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች በመደመጥ ላይ ይገኛል፡፡
በአንፃሩ ገዥው ፓርቲ የህዝቡን የነፃነት ድምፅ ለማፈን ንቅናቄያአችንን ከጀመርን እለት ጀምሮ በርካታ መሰናክሎችን እየፈፀመ ይገኛል፡፡
በጎንደርና በደሴ ያደረግነውን ሰላማዊ ሰልፍ በተደራጀ መንግስታዊ ሽብር ለማደናቀፍ የተሞከረውን ሙከራ በህዝቡ ንቁ ተሳትፎ ከሽፎ የህዝቡን የነፃነት ድምፅ ማሰማታችን የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ይህንን የነፃነት ድምፅ በሌሎች ከተሞች ተቀጣጥሎ እንዳይዘልቅ ከሼክ ኑር ኢማም አሟሟት ጋር በማያያዝ ገዢው ፓርቲ ይህ መግለጫ እስከወጣበት ቀን ድረስ በተለያዩ ከተሞች ህዝቡን በማስገደድ አንድነት ፓርቲን እንዲያወግዝ በየቀኑ ሰልፍ በማስወጣት ላይ ይገኛል፡፡
ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም በጂንካ ፣ ወላይታ ፣ ባህርዳር ፣ አርባምንጭ እና መቀሌ ሰላማዊ ሠልፍ እና ህዝባዊ ስብሰባ እናደርጋለን ብሎ አንድነት ካሳወቀ ጊዜ ጀምሮ በአካባቢው በሚገኙ አባሎቻችን ላይ ማዋከብና ከፍተኛ ጫና ማሳደሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡andinet -UDJ
ሐምሌ 27 ቀን 2005 ዓ.ም ወላይታ ለቅስቀሳ የገባው የአዲስ አበባ ልዑክ በአካባቢው ባለስልጣኖች መንግስታዊ ውንብድና ተፈፅሞበታል፡፡ ታርጋ የሌላቸው ሞተር ሳይክሎች በብዛት በማሰማራት ለቅስቀሳ በተንቀሳቀሱ አባሎቻችን ይዘው የወጡትን በራሪ የቅስቀሳ ወረቀቶችንና የፀረሽብር ህጉን ለማሰረዝ የተሰባሰቡ ፊርማዎችን ከእጃቸው ላይ ነጥቀዋቸዋል፡፡ የፀጥታ ኃይሎችም ዘራፊዎችን ለማስቆም ፍቃደኛ አልነበሩም፡፡ ለቅስቀሳ የተሰማራውንም መኪና አራቱንም ጎማ በማተንፈስና ሹፌሩን በመደብደብ ከተማውን ለቆ እንዲወጣ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል ፡፡ በድምፅ ማጉያ መሳሪያም ቅስቀሳ እንዳናደርግ ተከልክለናል፡፡
የአንድነት ፓርቲ የወላይታ የዞን አመራር አባል የሆነችው ወ/ሮ ሀድያ መሀመድ ከትላንት ሐምሌ 26 ቀን 2005 ዓ.ም እለት ጀምሮ በግፍ ታስራ ትገኛለች፡፡ በእስር ቤትም የማታምንበትን ሰነድ እንድትፈርም መገደድዋን ለማወቅ ችለናል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ህዝበ ሙስሊሙን ለአመፅ እንደሚያነሳሳ አድርገው ያቀረቡትን ሰነድ አልፈርምም ፓርቲዬም ይህንን አልፈፀመም በማለት ፓርቲውን ለመወንጀል በተዘጋጀው የሀሰት ሰነድ ላይ ሳትፈርም ቀርታለች፡፡ በአጠቃላይ የመንግስት የፀጥታ ኃላፊዎች እና የአስተዳድር ኃላፊዎች የህገ-መንግስት ጥሰት በአንድነት ፓርቲ ላይ ፈፅመዋል፡፡ በዚህ አስጨናቂ ሁኔታ ላይ ሆነንም በወላይታ ህዝባዊ ስብሰባውን በነገው ዕለት ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም በተያዘለት እቅድ መሰረት በህዝባችን ድጋፍ ይከናወናል፡፡
በጂንካ ፣ በአርባምንጭ እና በባህርዳር ቅስቀሳው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ህዝቡም ድጋፉን በአደባባይ እየገለፀ ይገኛል፡፡ በተለይም በባህርዳር የባጃጅ ሹፌሮች በግል ተነሳሽነት የቅስቀሳው አካል በመሆናቸው የባህርዳርን ህዝባዊ ሰልፍ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል፡፡
በአንፃሩ በመቀሌ ከተማ ከሐምሌ 25 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ቅስቀሳ ለማድረግ ጥረት ሲያደርግ የሰነበተው ልዑክ ምንም ዓይነት የድምፅ ማጉያ መሣሪያ እንዳይጠቀም ከመታገዱም በላይ ለቅስቀሳ ያዘጋጀውን ሞንታርቮ በአደባባይ በፖሊስ ተቀምቷል፡፡ በቅስቀሳ ላይ የነበሩት የአንድነት ፓርቲ ብ/ም/ቤት አባል አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ እንዲሁም የትግራይ ዞን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች የሆኑት አቶ ክብሮም ብርሃነ እና አቶ አርአያ ፀጋይ በቀዳማይ ወያኔ ፖሊስ ጣቢያ በአሁኑ ሰአት በዕስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህንን በደል በተቀነባበረ መልኩ እየፈፀሙ ያሉት የከተማው አስተዳደር እና የፀጥታ ዘርፍ ክፍሉ በጋራ ሲሆኑ ህገ-መንግስቱን በጉልበት በመናድ በመቀሌ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳናደርግ በኃይል አደናቅፎናል፡፡ ይህንን የህገ-መንግስት ጥሰት አንድነት ፓርቲ በፍፁም በዝምታ አይመለከተውም፡፡ የጀመርነውን ሠላማዊ ትግል አጠናክረን ከሰፊው የትግራይ ህዝብ ጋር በመሆን እንቀጥላለን በቅርብ ቀን በድጋሚ በመቀሌ ከተማ ሠላማዊ ሰልፍ የምንጠራ መሆናችንን እያሳወቅን ገዢው ፓርቲ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በግፍ ያሰራቸውን የፓርቲያችንን አመራሮች በአስቸኳይ እንዲፈታ እንጠይቃለን፡፡ የመቀሌ ነዋሪዎች መንግስት በአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ የፈፀመውን አፈና ፊት ለፊት በመቃወም ያሳዩትን አጋርነት ሳናደንቅ አናልፍም፡፡ አንድነት ፓርቲ ሳይገድል እየሞተ ህገ-መንግስቱን የማስከበር ትግሉን አጠንክሮ ዛሬም ወደፊትም ይቀጥላል፡፡
መንግስት ህገ-መንግስቱን ያክብር!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ባለ 4 ኮከቡ የቀነኒሳ ሆቴል ነገ ሥራ ይጀምራል
200ሚ. ብር የወጣበት ሆቴል በአዲስ አመት ይመረቃል
የዓለምና የኦሎምፒክ የ5 እና የ10ሺ ሜትር ሩጫ ሪከርድ ባለቤት ቀነኒሳ በቀለ፤ በ200 ሚሊዮን ብር ያስገነባው ባለ 4 ኮከብ ዘመናዊ ሆቴል ነገ አገልግሎት ይጀምራል፡፡
ከቦሌ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት የተሰራውና በጀግናው አትሌት ስም የተሰየመው ቀነኒሳ ሆቴል፤ ባለ 7 ፎቅ ሲሆን 51 የመኝታ ክፍሎች እንዳሉት ታውቋል፡፡
ሆቴሉ፣ ሱዊት፣ ጥንድ፣ ሲንግል፣ የቤተሰብና ለአካል ጉዳተኞች ታስቦ የተሰሩ ክፍሎች ሲኖሩት፣ ሱት የሚባሉትን 10 ክፍሎች ጨምሮ 22 ክፍሎች ጃኩዚ እንዳላቸው የሆቴሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሪት ሮማን ታፈሰወርቅ ገልፀዋል፡፡
ሥራ አስኪያጇ አክለውም፣ ሆቴሉ በአሁኑ ወቅት ለመቶ ሠራተኞች የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ጠቅሰው ሠራተኞቹ ቀደም ሲልም በሆቴል ሙያ እውቀትና ልምድ ቢኖራቸውም የአንድ ወር ሥልጠና እንደተሰጣቸውና ሥልጠናው ወደፊትም እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
በቂ የመኪና ማቆሚያ ስፍራ መኖሩ ልዩ ያደርገናል ያሉት ወ/ት ሮማን፤ የደንበኞቻቸውን ምቾት ለመጠበቅ፣ ለክፍሎቹ ብቻ ሳይሆን ለሆቴሉ በአጠቃላይ የአየር ሙቀትና ቅዝቃዜ መቆጣጠሪያ መሳሪያ (ኤሲ) መገጠሙን ገልፀዋል፡፡ ከሁሉም በላይ የእንግዶቻቸውን ደህንነት ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፣ ሁሉም ክፍሎች ጭስ ጠቋሚ (አነፍናፊ) መሳሪያ፣ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከያ ሲስተም (ማምለጫ ደረጃዎች)፣ በየቦታው የውሃ መርጫና ጠቋሚ ካሜራዎች መገጠማቸውን አስረድተዋል፡፡
kenenisa hotelየድምፅ ብክለትን ለመከላከል በሮቹና መስኮቶቹ ድምፅ የማያስተላልፉ (ሳውንድ ፕሩፍ) መሆናቸውንና ዕቃዎቹ በሙሉ የባለ 5 ኮከብ ሆቴል መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ሰፊና ዘመናዊ ሎቢ ባር፣ ካፊቴሪያ፣ የባህላዊና ዘመናዊ ምግቦች ሬስቶራንት፣ ቪአይፒ ላውንጅ፣ እንግዳው በንፁህ አየር እየተዝናና ፒዛ መብላት፣ ቢራና ድራፍት መጠጣት እፈልጋለሁ ቢል ምቹ (ኦፕን አየር) ስፍራ ተዘጋጅቷል፡፡
ሆቴሉ፣ ሁለት የእንግዶችና አንድ የሠራተኞች መጠቀሚያ አሳንሰር (ሊፍት) ሲኖረው፣ ፈጣን ብሮድ ባንድ ኢንተርኔትና ሽቦ አልባ (ዋየርለስ)፣ ሳውና ባዝ፣ ስቲም ባዝ፣ ጃኩዚ፣ ሁለገብ ጂምናዚየም፣ ኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ መቀበያ ካርድና የተለያዩ የንግድ ማዕከላት ሲኖሩ 24 ሰዓት አገልግሎት እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ ወ/ሪት ሮማን ታፈሰወርቅ፤ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሆቴል ማኔጅመንት የመጀመርያ ዲግሪ ሲኖራቸው፣ ለሁለተኛ (ማስተርስ) ዲግሪያቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ማርኬቲንግ ማኔጅመንት እየተማሩ ናቸው፡፡ (ምንጭ: አዲስ አድማስ)
“ዝናብ ያልበገረው የባሕር ዳር ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል” ፍኖተ ነጻነት
አንድነት ፓርቲ በባህር ዳር የጠራው ሰላማዊ የተዋውሞ ሰልፍ በድምቀት ተጠናቋል። በመጨረሻም የምዕራብ ጎጃም የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ማሩ እና ሌሎችም አመራሮች በሰልፉ ላይ ንግግር እድርገዋል፡፡ በዕለቱ ከ 50 ሺህ በላይ የሚሆን ሰልፈኛ መሳተፉ ተገልጿል። ቨሌላ በኩል በሰ፤ፉ መካክል አንድ የቀበሌ አመራር ሰዎችን ለማስፈራራት ሲሞክሩ በሕዝብ ትብብር ከሰልፉ እንዲገለሉ የተደርገ ሲሆን ሕብረተስቡም የግለሰቡን ማስፈራራት አጣጥሎታል።
ዛሬ በባህርዳር ከተማ ዝናብ እየዘነበም ቢሆን ሰላማዊ ሰልፍ ሳይቋረጥ የተካሄደ ሲሆን በወቅቱም የሚሰሙ የነበሩ መፈክሮች
ያማራው ህዝብ ጨዋ እንጂ ፈሪ አይደለም!
ለሱዳን ተቆርሶ የተሰጠው መሬታችን ይመለስ!
የሙስሊም መፍት ሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ባስቸኩዋይ ይፈቱ!
እስክንድር ነጋ ጋዜጠኛ እንጂ አሸባሪ አይደለም።!
የታሰሩ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ይፈቱ!
መንግስት ህገ-መንግስቱን ያክብር!
መንግስት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ያቁም!
መንግስት ለብሄራዊ መግባባት ባስቸኳይ መልስ ይስጥ!
ውሸት ሰልችቶናል! ይቁም!!!
የጸረ – ሽብር ህጉ ባስቸኳይ ይሰረዝ!
ዘርን መሰረት ያደረገ ማፈናቀል ባስቸኳይ ይቁም!!udj bahirdar
ሙወስና የስርአቱ መገለጫ ነው!!
የአባይ ጉዳይ የኢትጵያ ሕዝብ ነው!
ለተከሰተው የኑሮ ውድነት ተጠያቂው መንግስት ነው!!
የዜጎች ሰብአዊ መብታቸውን የማግኘት መብታቸው ይከበር!!
ዜጎች በሀገራቸው ስራ የማግኘት መብታቸው ይከበር!!
በአባይ ጉዳይ ወሳኙ የኢትጵያ ሕዝብ እንጂ ግብጾች ይደሉም!!
የፓርቲ አባልነት በፍላጎት መሆን አለበት!!
የመሳሰሉት መፈክሮች ተሰምተል!
በተያያዘም ዜና በባህር ዳር የመንግስት ካላት አረንጓዴ ሽብር የሚል ወረቀት እየተበተነ እንደነበረ ተረጋገጧል፤ “አረንጓዴ ሽብር” የሚል በነጭ ወረቀት የተባዛ እና የአንድነትን የስልክ ቁጥር የያዘ በራሪ ወረቀት እየተበተነ መሆኑ ታውቋል፡፡ አንድነት ፓርቲ የበተነው በራሪ ወረቀቶች ቢጫና ቀይ ብቻ ናቸው፡፡ (ምንጭ: ፍኖተ ነጻነት)
ጉቦ እየተቀበለ የፈተና ውጤት የጨመረ መምህር በሙስና ተከሰሰ
ከ10 ዓመት በላይ እስር ሊያስቀጣ ይችላል
በአየር ጤና ሁለተኛና መሰናዶ ት/ቤት ለ11 የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ጉቦ እየተቀበለ የፈተና ውጤት በመጨመር ከክፍል ወደ ክፍል እንዲዘዋወሩ አድርጓል የተባለው የባዮሎጂ መምህሩ አቶ ፈቃዱ ቢጀጋ በሙስና ወንጀል ክስ ተመሠረተበት፡፡
የፌደራሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ፣ የክስ ዝርዝር እንደሚያስረዳው፤ በመምህሩ ላይ ሁለት ክሶች የቀረቡበት ሲሆን በአንደኛው ክስ በ2005 የትምህርት አመት የ9ኛC ክፍል የክፍል ሃላፊ ሆኖ የተመደበበትን ስልጣን ያለአግባብ በመጠቀም፣ ከሰኔ 28 እስከ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ለአስራ አንድ ተማሪዎች ዘጠኝ የሚደርሱ የትምህርት አይነቶች ላይ ለእያንዳንዱ የትምህርት አይነት መምህራን ሳያውቁ እስከ 91 ነጥብ በመጨመር ከክፍል ወደ ክፍል ማለፍ የማይገባቸው ተማሪዎች እንዲያልፉ ለማድረግ በማሰብ፣ ከስልጣኑ በላይ በሆነ አሠራር በመንግስት የትምህርት ጥራት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ፣ በፈፀመው በስልጣን ያለአግባብ መጠቀም የሙስና ወንጀል እንደተከሰሰ ተመልክቷል፡፡
bribe mበሁለተኛነት በቀረበው ክስ ላይም ሃላፊነቱን ያለአግባብ በመጠቀም የግል ተበዳይ የሆነ አንድ ተማሪ ካርድ እንዲሰጠው ሲጠይቀው “ውጤትህ የተሟላ አይደለም፤ የተሟላ ውጤትህን የያዘ ካርድህን እንድሰጥህ ከፈለግህ ገንዘብ አምጣ” በማለት ጠይቆ፣ ሐምሌ 8 ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰአት ሲሆን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4፣ አንድ ግሮሰሪ ውስጥ ከግል ተበዳይ 200 ብር ተቀብሎ “ካርድህን እልክልሃለሁ፤ ገንዘብ ግን ስለሚያንስ ትጨምራለህ” በማለት በነጋታው ከምሽቱ 12 ሰዓት ሲሆን ተጨማሪ 150 ብር ከዚሁ ተበዳይ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ በመያዙ በሙስና ጉቦ በመቀበል ወንጀል ተከሷል፡፡
ክሱ እንደደረሰው ለፍ/ቤቱ ያረጋገጠው ተከሳሽም፣ በችሎቱ በተገኙና ሊረዱት በፈለጉ ጠበቆች አማካይነት የተከሰሰበት የህግ አንቀጽ ዋስትና የማያስከለክል በመሆኑ፣ “ፍ/ቤቱ ጉዳዬን በዋስ ሆኜ እንድከታተል ይፍቀድልኝ” ሲል የጠየቀ ሲሆን አቃቤ ህግም በዋስትና ጥያቄው ላይ ተቃውሞ እንደሌለው አመልክቷል፡፡
ይሁን እንጂ ተከሳሹ ከ10 አመት በላይ በሚያስቀጣ ወንጀል የተከሰሰ በመሆኑ የዋስትና ጥያቄውን ባለመቀበል፣ መዝገቡን ለነሐሴ 3 ቀን 2005 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡ (ምንጭ: አዲስ አድማስ)

No comments:

Post a Comment