FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, August 8, 2013

በመንግሰት የችግር አፈታት ዘዴዎች ዛሬም አዝነናል፧ አፍረናልም!!!!


ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ከሁሉም በማሰቀደም ሰማያዊ ፓርቲ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳቹ፣ በዓሉ የሰላምና የደሰታ እንዲሆንላቹ ኢድ ሙባረክ በማለት ምኞቱን ይገልፃል ::Blue Party Ethiopia
ኢሕአደግ መራሹ መንግሰት ተቋማትን የመቆጣጠር አባዜው ከግዜ ወደ ግዜ እየባሰባት በመምጣቱ ዛሬም እጁን ያላሰገባበት ምንም አይነት ተቋምና አሰተሳሰብ ባይኖርም በተለይ ባለፈው አንድ አመት ተኩል ጀምሮ ከእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር በፈጠረው እሰጥ አገባ መፍትሔ አጥቶ እሰከ አሁኗ ሰአት ቀጥሏል:: ሰማያዊ ርቲ የመንግሰትን በሐይማኖት ጣልቃ መግባት አጥብቆ በመቃወም የራሳቸውን የእሰልምና እምነት መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እንዲፈታና ችግሩም በውይይት እንዲፈታ በተደጋጋሚ ግዜ ጥሪውን አቅርቧል::
ነገር ግን መንግሰት ችግሮችን በሐይል ጨፍልቄ እፈታለሁ የሚል የተለመደ አካሔድ ለፓርቲያችን ጥሪ የሰጠው ምላሽ ካለመኖሩም በላይ የፓርቲያችንን ሰም በማጉደፍ የሀገር ጠላትና አሸባሪ ፓርቲ አድርጎ ለማሳየት ጎምበስ ቀና በማለት ላይ ይገኛል::
መንግሰት ከእሰልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን ጋር በፈጠረው ችግር ባለፈው አንድ አመት ተኩል ብዙ ችግሮች ተፈጥረዋል፣ ሀብትና እውቀት የሚያድግበት ግዜ ባክኗል፣ በሰው አካልና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፣ ሕይወት ጠፍቷል:: ችግሩ ግን አሁንም አልተፈታም፧ እንደውም እያደገና እየከረረ ሔዷል:: በዛሬው ነሐሴ 2 ቀን 2005 ዓ.ም የኢድ አልፈጥር በአል አከባበር ላይ በመላው ኢትዮጵያ በሕብረት የመሰገጃ ቦታዎች በተሳተፉ የእምነቱ ተከታዮች ላይ በመንግሰት ታጣቂዎች በተወሰደው እርምጃ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች አሰቃቂ ድብደባና የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል:: በአሰር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ደርሞ የማረሚያ ቦታዎች እና ፕሊሰ ጣቢያ አልበቃ ብሎ በጋራዦች ጭምር ታሰረዋል:: ባልተረጋገጡ መረጃዎችም የሰው ሕይወት ጠፍቷል:: በዚህም ነገር ፓርቲያችን ከልብ አዝኗል::
ሰላማዊ ፓርቲ አሁንም መንግሰት ችግሮቹን በሐይል ለመፍታት የሚወሰደውን እርምጃ አጥብቆ እያወገዘ በቀላሉ መፍትሔ ሊሰጣቸው የሚችሉ የመብት ጥያቄዎችን በማፈን ዜጎች ተገደው ወደማይፈልጉት መንገድ እንዳይሄዱ በጥብቅ ሊታሰብበት እንደሚገባ ማሳሰብ ይፈልጋል:: ሐገራችን ያለችበትን ቀጠናና ታሪካዊ መሰተጋብርም በውል የሚረዳ መፍትሄ ባሰቸኳይ እንዲሰጥ አሁንም አሁንም አጥብቀን እንጠይቃለን::
ነሐሴ 2 ቅን 200 ዓ.ም
አዲሰ አበባ
Blue Party Ethiopia

1 comment:

  1. ሚስተር ቤንጃሚን የኢሜል ዝርዝሮችን እነሆ ፣ Lfdsloans@outlook.com ፡፡ / ወይም ደግሞ ንግዴን ለመጀመር በ 90,000.00 ዩሮ ብድር የረዳኝ WhatsApp + 1-989-394-3740 እና እኔ በጣም አመስጋኝ ነኝ ፣ እዚህ አንድ ነጠላ እናት ነገሮች እንዳላደረጉ መንገድ ለመፍጠር እየሞከርኩ ነው ፡፡ ከእኔ ጋር ቀላል ይሁኑ ግን ንግዴ እየጠነከረ ሲመጣ እና እያሰፋ ሲሄድ እያየሁ በሚስተር ሚስተር እርዳታ ፊቴ ላይ ፈገግታ አሳየኝ ፡፡ የገንዘብ ድጋፍን መፈለግ ወይም በዚያ ንግድ ውስጥ መከራን ማለፍ ወይም የመነሻ የንግድ ሥራ ፕሮጀክት መጀመር መፈለግ ይህንን ማየት እና ከችግራቸው ለመውጣት ተስፋ ሊኖረው ይችላል ... እናመሰግናለን ፡፡

    ReplyDelete