FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, August 3, 2013

የኢትዮጵያ ወጣቶች ያስተሰርያሉ!


እንቁ መጽሄት
Professor Alemayehu G. Mariam teaches political science at California State University, San Bernardino.
ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም
ለብዙ ዓመታት በኢትዮጵያና በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ አስተያየት ሳቀርብ ጽሑፎቼን የማቀርበው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነበር። እርግጥ ነው ብዙዎቹ የእንግሊዘኛ ጽሑፎቼ ወደአማርኛ ቋንቋ ተተርጉመዋል። በእንግሊዘኛም የምጽፈው በዓለም ላይ ያሉ አንባቢዎቼን በሰፊው ለመድረስ በሚል ምክንያት ነው። ምናልባት አንዳንድ አንባቢዎች፣ ‹‹የአማርኛ ጽሑፍ ችሎታ ስለሚያንሰው ይሆናል በእግሊዝኛ የሚጽፈው›› ብለው ሊገምቱ ይችላሉ። ነገር ግን በመጠኑም ቢሆን በአማርኛ የመጻፍ ችሎታ አለኝ። አንድን ክህሎት ለረዥም ጊዜ ካልተጠቀሙበት ሊኖር የሚችለው ‹‹ዝገት›› እንዳለ ሆኖ ማለት ነው፤ ምናልባትም አለፍ ሲል ስሕተት። የሆኖ ሆኖ ‹‹ከሰው ስሕተት…›› እንደሚባለው፣ ይህን ለመጀመሪያ ጊዜ በአማርኛ ቋንቋ የጻፍኩትን መጣጥፍ በተመለከተ፣ አንባቢዎች የቋንቋ አጠቃቀሜን ‹‹ቀለል›› አድርገው እንዲገነዘቡልኝ በቅድሚያ እጠይቃለሁ።
ነገር በምሳሌ…
አበው ሲተርቱ፣ ‹‹ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ›› ይላሉ። …የዛሬ ሰባት ወር ገዳማ (የአውሮፓውያን አዲስ ዓመት መግቢያ ወር አካባቢ)፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሀከል ስለተፈጠረ ግጭት አንድ መጣጥፍ ጸፌ ነበር። ጉዳዩን አስመልክተው የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እንዳተቱት፣ በተማሪዎቹ መሀከል የተነሳው አምባጓሮ መነሻ ምክንያት፣ ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች (የዩኒቨርሲቲው ተማሪች አልያም ቅጥረኛ ነገር ጫሪዎች…)፣ በተለይ የአንድን ዜጋ ሰብዓዊ ክብር የሚያንቋሽሹና የሚዘልፉ ጸያፍ ቃላትን በመታጠቢያ ቤቶች፣ በቤተ-መጽሐፍትና በመኝታ ክፍሎች ውስጥ መለቅለቃቸው ነበር ሲሉ ተናግረዋል። በሌላ በኩል ደግሞ፤ በወቅቱ እንደተናፈሰው ወሬ፣ የተማሪዎቹ ጸብ የተጫረው ‹‹በኦሮሞና በትግራይ ብሔር ተወላጅ ተማሪዎች መሀከል›› እንደሆነና በጸቡም ሃያ የሚሆን ተማሪዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውና ብዛታቸው ከተጎዱት የማይተናነሱ ተማሪዎች ባለተጠቀሰ ወንጀል ለእስር እንደተዳረጉ የሚገልጽ ነበር። ይህን ጉዳይ በሰማሁበት ወቅት፣ መንፈሴን ያወከና የበጠበጠ ስሜት ነበር የተሰማኝ። ‹‹እንዴት ሆኖ የኢትዮጵያ ብርቅዬ ልጆች፣ የኢትዮጵያ ብርሃኖች እንደዚህ ባለ አስከፊ፣ አሳፋሪና አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ?›› በማለት ከሕሊናዬ ጋር ሙግት ገጠምኩ።…

No comments:

Post a Comment