FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Sunday, February 23, 2014

ወያኔን ተሸክሞ መኖር ይብቃን!

በዳዊት መላኩ ( ከጀርመን)

የሰው ልጅ ካመረረ ቀጥሎ ምን እንደሚመጣ ማሰብ አይችልም፡፡ ለነፍሱም ፈጽሞ አይሳሳም፡፡ ወቅቱ 1998 ዓ.ም ነው፡፡ የ97 ሰባቱን ምርጫ ተከትሎ በተነሳው ብጥብጥ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ ይኖር የነበረ ስሙን ለጊዜው የማላስታውሰውን ወጣት ሁኔታ ላካፍላችሁ፡፡ በእለቱ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ረባሻ ነበር፡፡ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብጥብጡ ተዛምቱዋል፡፡ ቀደም ብሎ ተማሪዎች ወደ ክፍል እንዳይገቡ ስጋት ተፈጥሩዋል፡፡ ግቢው በፌዴራል ፖሊስ ተከቡዋል፡፡ የከተማው ወጣቶች  ወደ ዩኒቨርሲቲው ገብተው ተማሪዎችን ይዘው መውጣት ያፈልጋሉ፡፡ ተማሪዎችም ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው ድምጻቸውን ማስማት እና ተቃዉሞአቸውን መግለጽ ይፈልጋሉ፡፡ በመሀል ዙሪያውን የከበበው የፌዴራል ፖሊስ በታጠቀው መሳሪያ በማስፈራራት እየተከላከለ ያገኛል፡፡ ከውጪ ወደውስጥ እንዳይገቡ ሲከላከሉ ከውስጥያ ያለው ደግሞ ወደ ውጪ እንዳይወጣ በመሀል ሆነው  ይከላከላሉ፡፡ ማሪዎች ያሳደባሉ፤ ይጮሀሉ፡፡ በዚህ መሀል በአዲሱ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንጻ በኩል አንድ ረዘም ያለ  መልካማ ወጣት መሳሪያ ደግነው ለግዳይ የሚጠባበቁትን ወታደሮች ከምንም ሳይቆጥር ከወደ ስላሴ ቤተክርስቲያን አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት እየሮጠ መጣ፡፡ ወታደሮች ተመለስ! ተመለስ! ትሞታለህ እያሉ ይጮሀሉ፡፡ በለው! በለው! ያባባላሉ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ያ ነፍሱ ፍትህ የተጠማች ወጣት ግቡ ወደ ግቢው በመምጣት ድምጹን ማስማት  በመሆኑ  የወታደሮችንም ጩኸት ሆነ የተደቀነውን መሳሪያ ከምንም አልቆጠረውም፡፡
የወጣቱን ድፍረት ላየ ሰው ሞት የሚባል ነገር ከምድር  እንደሌለው የተረዳው ይመስል ነበር፡፡ ሩጫውን ቀጠለ፡፡ መግደል የተካኑት ወታደሮችም በሁለት ጥይት አከታትለው መቱት፡፡ እንደኛው ጥይት ትክሻውን የመታው ሲሆን ሁለተኛው ጥይት ኩላሊቱን አካባቢ ነው የመታው፡፡ እንደዚህም ሁኖ ወጣቱ አሁንም እየሮጠ በሸቦ ከታጠረው የዩኒቨርሲቱው አጥር ሲደርስ አጥሩን አልፎ መግባት አልቻለም፡፡ ሽቦው አጥር ስር ወደቀ፡፡ በዚህ ጊዜ ተማሪዎች የወደቀውን ወጣት ለማንሳት ከያሉበት  ተሯሯጡ፡፡ የሽቦውን አጥርም ፈልቅቀው ወደ ውስጥ ይዘውት ገቡ፡፡ወዲያው ወደተማሪዎች ክሊኒክ ይዘውት ሄዱ፡፡ በዩኒቨርሲቲው ክሊኒክ የሚሰሩት ዶ/ር ታጀበ አለሙ እና ነርስ በላይነሽ እርዳታ ቢያደርጉለትም ማትረፍ አልቻሉም፡፡ ወጣቱ ህይወቱ አልፋለች፡፡ ግቢው ታመሰ፡፡ ለቂሶ ዋይታ እየዩ ሆነ፡፡ በመሀል የምሳ ሰሀት ስለደረሰ  የተወሰኑ ተማሪዎች ምግብ እንብላ ሲሉ ሌሎች ደግሞ እሬሳ አጋድመን መብላት የለብንም ሲሉ እንብላ የሚሉት ከላይ ትእዛዝ ተላለፎላቸው ኑሮዋል እናንተ ምን ትሰራላችሁ ለምን ዝም ብላችሁ ታያላችሁ ስለተባሉ ጉዳዩ ወደ ብሄር ጠብ ተቀይሮ  ተማሪዎች ጎራ ለይተው ድብድብ ተጀመረ፡፡ ከዚያም ግቢው ሙሉ በሙሉ በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ለተወሰኑ ቀናት ሽንት ቤት እንኩዋን ለመውጣት የወታደሮችን ፈቃድ ተጠይቆ ነው፡፡ ከዶርም እንዳይወጣ ተከለከለ፡፡ ትምህርትም ተቁዋረጠ፡፡ ከሳምንት በላይ በዚህ መልኩ ቀጥሎ ቀስ በቀስ ተረጋጋ፡፡
እንግዲህ እንድትረዱልኝ የፈለግሁት የሰው ልጅ ትዕግስቱ ገደብ እንዳለው ነው፡፡ ከዚያ ገደብ በላይ ማለፍ እንደማይቻል በዚህ ወጣት ታሪክ ይነግረናል፡፡ ማንኛውም ነገር ገደብ (tolerance limit) አለው፡፡ ለምሳሌ አንድ ላስቲክ ስንስበው እስከተወሰነ ደረጃ ይለጠጣል፡፡ ከዚያ ደረጃ በኃላ ይበጠሳል፡፡ ውኃ በፈሳሽነት ደረጃ የተወሰነ ሙቀትን ወይም ቅዝቃዜን ተቋቁሞ ይቆያል፡፡ ከዚያ ደረጃ ሲያልፍ ወይ  ይተናል ወይ ወደ በረዶነት ይለወጣል፡፡ የአንድ ብረት ጥንካሬው የተወሰነ ሀይልን ለመቋቋም ነው፡፡ የሀይል መጠኑ ሲበዛ ይጣመማል ወይም ይሰበራል፡፡ የወያኔ አፈና እስከተወሰነ ደረጃ ህዝቡን ለማስጎንበስ ረድቶታል፡፡ የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ያለፉትን ጊዜያት በስልጣን ተደላድሎ የሀገርን ሀብት እየዘረፈ እንዲቆያ አግዞታል፡፡ ነገር ግን ዘላልም ስልጣን ላይ እንዲቆይ አያደርገውም፡፡ ማንኛውም ነገር ከገደቡ ማለፍ ስለማይችል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔን መሸከም የሚችለውን  ያክል ታክሻው እስኪጎብጥ ግፍ እና በደሉን ችሎ ተሸክሞትል፡፡ ላለፉት 23 አመታት ሲያነቋሽሹት፤ ሲገድሉት፤ ሲዘርፉት፤ ከመኖሪያው፣ ከቤቱ ፣ከስራው ሲያፈናቅሉት፤ ከሀገር ሲያስወጡት፤ በእምነት በጎሳ እየከፋፈሉ ሲያጫርሱት ብዙ ብዙ ታግሷቸዋል፡፡ አሁን  ህዝቡ መሸከም ከሚችለው በላይ ስለሆነበት ከራሱ አሽቀንጥሮ መጣል ያፈልጋል፡፡ ዛሬ አንድነት እና መኢአድ  በጠሩት ሰልፍ የታየው የህዘብ ስሜት ምን ያክል እየገነፈለ እንደሆነ ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ የሚነግረን ህዝቡ ምን ያልክ ለውጥ እንደሚፈልግ ነው፡፡ እንግዲህ አወዳደቁ እንዳይከፋ ቀስ ብሎ ትንሸራቶ መውረድ ከቻሉ ለወያኔ እና ለደጋፊዎች እሰየው ነው፡፡ ካለሆነ ግን ህዝቡ በግድም ቢሆን አንኮታኩቶ ጥሎ መሰባባሩ የማይቀር ሀቅ ነው፡፡ ስለዚህ ወያኔ ወይ በራሳቸው ጊዜ ቀስ ብለው ይውረዱ ወይ  በግድ ይወገዱ፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝቦች!
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11204/

የሸፍጥ ክርክር የሃሰት ክምር የታሪክን እውነታ አይቀይርም! (ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ)

ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የካቲት 15 ቀን 2006 ዓ/ም ( February 22, 2014 )
I. መግቢያ:
የካቲት 3 ቀን 2006 ዓ/ም የወያኔ/ኢሕአዴግ ሊቀ-መንበርና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለአገር-ውስጥ ጋዘጤኞች በሰጡት መግለጫ ላይ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በድፍረት የሰጡት ምላሽ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴን ብቻ አይደለም መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በእጅጉ ያሳዘነና ያሳፈረ ሆኖ አግኝተነዋል። በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እግር የተተኩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተረከቡት የመንግሥት ሥልጣንን ብቻ ሣይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከበሬታ-አልባነትንም በሚመስል መልክ ነው ይህንን በጣም የተምታታ፤ በተቃርኖዎች የተሞላና በእጅጉ ኃላፊነት-የጎደለው ጋዜጣዊ-መግለጫ የሰጡት።
የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ባደረገው ያላሰለሰ ክትትል የወያኔ/ኢሕአዴግ መንግሥት ከሱዳን መንግሥት ጋር የሕዝብን መሠረታዊ-ሉዓላዊነት በሚዳፈርና ዘለቄታዊ ጥቅሙን ለባዕድ አሣልፎ በሚሰጥ ሁኔታ እየሸረበ ያለውን ደባና እየፈጸመ ያለውን አሣፋሪ ድርጊት በተገቢ ጥናትና በጠራ-መረጃ ላይ ተመሥርቶ በተከታታይ ባወጣቸው መግለጫዎች እንዲሁም በልዩ-ልዩ መገናኛ-ብዙኃን አማካይነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ለወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎችና ልዩ-ልዩ ተቋማት፤ ለሱዳን መንግሥትና ለዓለም-አቀፉ ማኅበረሰብ ጭምር ሲያሳውቅ መቆየቱ ይታወቃል። የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች ግን አሁንም በዚህ የአገር ድንበርን በሚያክል ከባድ ጉዳይ ላይ ከዋናው ባለ-ጉዳይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ የጀመሩትን እኩይ ተግባር እየገፉበት አንደሆነ ከራሣችው አንደበት እየሰማን ነው።
II. የመግለጫው ዓላማ፤
የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ በሚከተሉት ምክንያቶች ከላይ የተጠቀሰውን የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር በተመለከተ ይህንን መግለጫ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል።
ሀ). ከማንኛውም አገርና መንግሥት መሪ በተለይም የውጭ ግንኙንትን በተመለከተ የሚሰነዘር አስተያየትም ሆነ የሚሰጥ መግለጫ የአገር አቋም ተደርጎ የሚወሰድና በዋቢነትም የመጠቀስ መዘዝን ያዘለ በመሆኑ በዝምታ ሊታለፍም ሆነ ‘አጉል-መዘላበድ’ ተደርጎ ችላ ሊባል የሚችል ጉዳይ ባለመሆኑ፤
ለ). በዚህ የወያኔ/ኢሕአዴግ መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ እየፈጸመ ባለው በአገር-ክህደት የሚያስጠይቅ፤ ሕዝብን የናቀ የድፍረት አርምጃና ሕገ-ወጥ ድርጊት አገራችን ኢትዮጵያ አንጡራ መሬቷ ለባዕድ አሣልፎ እየተሰጠ መሆኑ ምንም ዓይነት ተቀባይነትም ሆነ አግባብነት የሌለው ብቻ ሣይሆን የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጉዳይና ሁሉም በግልጥ ሊረዳው የሚገባ መሆኑን ከአሁን በፊት በተደጋጋሚ መግልጫዎች የሰጠነበት ቢሆንም አሁንም በድጋሜ ማሳሰቡ አስፈላጊ ስለሆነ፤
ሐ). አፄ ቴዎድሮስ፤ ንጉሥ ተክለ-ኃይማኖትና አፄ ዮሐንስን የመሳሰሉ ታላላቅ መሪዎች እየታገሉና ክቡር መስዋዕትነት እየከፈሉ አስከብረውት የቆየውንና በአካባቢው ሕዝብ የመረረ ተጋድሎ ታፍሮና ተጠብቆ የኖረውን የሱዳን ወሰን በድብቅ ስምምነት ለባዕድ አሣልፎ ለመስጠት የሚደረግ ሕገ-ወጥ ውል ውሎ-አድሮ የሚያስከትለው መዘዝ በቀላሉ የማይታይ ከመሆኑም በላይ፤ ይህንን በመሰለ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ በተፈጸመ ውል ድንበር ለማካለል የሚወሰድ እርምጃ ሁለቱን እህትማማች አገሮች ወደ-አይቀሬ ጦርነት የሚወስድና ይህም ኢትዮጵያና ሱዳን በመልካም ጉርብትና መርኅ ተከባብረው እንዳይኖሩ፤ የውስጥ ሰላማቸውንና እድገታቸውን ወደሚያደናቅፍ ያላስፈላጊ ችግር ውስጥ ከማስገባት አልፎ ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ ጠንቅ እንደሚሆን ሁሉም ሊያውቀው ስለሚገባ፤
መ). የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች በሱዳን በኩል ያለውን የአገር ወሰን በተመለከተ በድብቅ የሚያደርጉትን የክህደት ተግባር በወቅቱ ማጋለጥና ማክሸፍ ተገቢና የማንኛውም ኢትዮጵያዊ የዜግነት ግዴታ እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚያሳስበውና የሚታገለው፤ ይህ ሕገ-ወጥ እርምጃ በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ድንበሮቻችን እንዲደፈሩና አገራችን ኢትዮጵያ አንጡራ መሬቶቿን በተመሣሣይ ሁኔታ እንድታጣ በር-ከፋች ማስረጃ ሊሆን እንዳይችል ለማድረግም ጭምር ስለሆነ፤
ሠ). ይህንን ድብቅ ሴራ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በትክክል እንዲያውቀውና በተለይም የአገሩን ዳር-ድንበር የማስከበር ኃላፊነት ያለበት የአገሪቱ የመከላከያ ኃይልና የአገር-ደኅንነት ክፍል አባላት የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች አሳፋሪ በሆነ መልኩ በተሳሳተ መረጃ ላይ ተመሥርተው የአገራቸውን አንጡራ መሬት ለባዕድ አሳልፈው ለመስጠት የሚያደርጉትን የአገር-ክህደት ተግባር በትክክል ተረድተው ከሕዝባቸው ጎን አንዲቆሙና የአገራቸውን ዘለቄታዊ-ጥቅም የማስከበር መሠረታዊ የሙያ፤ የተቋምና የዜግነት ግዴታቸውን አንዲወጡ ማሳሰቡ አስፈላጊ በመሆኑ፤
ረ). በአገራችን የሥርዓት-ለውጥ እንዲኖር የሚታገሉ ድርጅቶች ለዚህ ዓብይ አገራዊ ጉዳይ የተባበረ ምላሽ ለመስጠት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በአገራዊ አንድነት መንፈስና በተቀናበረ ሁኔታ እንዲሆን ለማሳሰብ፤…ነው።
III.  ጭብጦች፤
ሀ.) በአቶ ኃይለማርያም ደሳልኝ  / ኢሕአዴግ በኩል፤
1ኛ) አቶ ኃይለማርያም በዚህ መግለጫቸው ከእሳቸው በፊት የነበሩት የወያኔ/ኢሕአዴግ ጠቅላይ-ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ግንቦት 13 ቀን 2000 ዓም የሕዝብ-ተወካዮች ምክር-ቤት ፊት ቀርበው ምንም ዓይነት ታሪካዊ ማረጋገጫ ሳይኖራቸውና ያለ-አንዳች ሃፍረት ያሉትን በመድገም ከአፄ ምኒልክ ጀምሮ እስከ ደርግ የነበሩት የኢትዮጵያ መንግሥታት ሁሉም የሻለቃ ግዌንን መሥመር እንደተቀበሉና እንደተስማሙ፤
2ኛ) የእሳቸውም መንግሥት ወያኔ/ኢሕአዴግ ይህንኑ የግዌን የወሰን ክለላ መሥመር እንደሚቀበል፤ በተግባር የመተርጎም ግዴታ እንዳለባቸውና ለዚህም ዝግጁ መሆናቸውን፤
3ኛ) ይህን ተግባራዊ ለማድረግ በሚደረገው ሂደት አንድም የተፈናቀለ ኢትዮጵያዊ እንደሌለና ወደፊትም ሊኖር እንደማይችል፤
4ኛ) የሱዳንን ታጋሽነት በማወደስና የኢትዮጵያን ‘የተስፋፊነት’ አቋም በማውገዝ፤ ሃቁን በመካድና ታሪክን በማጣመም አሁን ሱዳን ይገባኛል የምትለውና የወያኔ/ኢሕአዴግ መንግሥትም ለማስረከብ የተዘጋጀው መሬት ቀደም-ሲል በሱዳን ይዞታ ሥር የነበረና የቀድሞው የግብፅ ፕሬዝደንት ሆስኒ ሙባራክ ኢትዮጵያን በሚጎበኙበት ወቅት በተካሄደው የግድያ ሙከራ ሳቢያ በኢትዮጵያና በሱዳን መኻል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ‘ሱዳኖች የለቀቁትን መሬት ኢትዮጵውያን ገበሬዎች አልፈው ሲያርሱት የነበረውን’ አንደሆነ፤
5ኛ) በሁለቱ አገሮች መኻል ያሉ ልዩ-ልዩ የጋራ ጉዳዮችን በተመለከተ ከሁለቱም አገሮች የተሰየሙ ኮሚቴዎች በቋሚነት እየተገናኙ ምክክር ከማድረግና ውሎችን ከመዋዋል ውጪ በአሁኑ ጊዜ የተከለለ መሬት እንደሌለ፤
6ኛ) ይህንን ኢትዮጵያ ለሱዳን መሬት አሳልፋ ሰጠች የሚለው ‘አሉባልታ’ በአገሪቱ በየአምስት ዓመት የሚደረገውን የምርጫ ወቅት እየጠበቀ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል በወያኔ/ኢሕአዴግ ላይ የሚነዛ ወሬ እንደሆነ፤…
የእሣቸውንና የመንግሥታቸውን አቋም ሲያሣውቁ፤ በአጠቃላይ የአቶ ኃይለማርያም ደሳልኝ መግለጫ ይዘት ከአሁን በፊት አቶ መለስ ታሪክን በመከለስና ሃቁን በማድበስብስ የተናገሩትን በአዲስ መልክ በመድገም የኢትዮጵያን አንጡራ መሬት ለሱዳን አሣልፎ ለመስጠት የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች ያላቸውን አቋምና እምነት፤ ይህንንም በተግባር ለመተርጎም የደረሱበትን ውሳኔ ይፋ ያደረገና በኢትዮጵያ ላይ ምስክርነት የሰጠ ሆኖ አግኝተነዋል።
ለ.) በኢትዮጵያ ሕዝብ በኩል
1ኛ) የአውሮጳ ቅኝ-ገዥዎች ያለ-አፍሪቃውያን ተሣትፎና ይሁንታ የአፍሪቃን ምድር እንዳሻችው ሲቀራመቱ በነበረበት ወቅት ሱዳንን ከግብፅ ጨምራ ትገዛ የነበረችው ቅኝ-ገዠዋ እንግሊዝ የኢትዮ-ሱዳን ድንበርን በተመለከተ በወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሠ-ነገሥት ከነበሩት ብልኁ መሪ አፄ ምኒልክ ጋር ድርድርና ውል ማድረጋቸው የተረጋገጠ ጉዳይ ነው።
አፄ ምኒልክም ሆኑ ሌሎቹ የኢትዮጵያ መሪዎች ከእነዚህ አውሮጳውያን ጋር ውል ሲዋዋሉና ሲደራደሩ በእነዚህ ባዕዳን የተውተበተቡ ብዙ ሴራዎችን እያከሸፉና የአገራቸውን ጥቅም ለአፍታም አሣልፈው ሳይሰጡ፤ አገራዊ ኃላፊነታቸውንና የመሪነት ግዴታዎቻቸውን በሚገባ የሚወጡ እንደነበር በኩራት የሚዘከር ነው።
በአንድ ወቅት አፄ ዮሐንስ አራተኛ “ምጥዋን ለጣሊያኖች አልሰጠኋቸውም፤ እንግሊዞች ናቸው የሰጧቸው፤ ምጥዋ የኢትዮጵያ ነው። እኔ በአግባቡ የኢትዮጵያ የሆነውን ማንኛውንም ግዛት የመተው ፍላጎትም ሆነ ሥልጣኑም የለኝም’’ ሲሉ እንዳረጋገጡት ሁሉ፤ በአገር-ወዳድነታቸው የታወቁት የኢትዮጵያ መሪዎች ከፈጣሪ በታች ጠያቂ የሌለባቸውና ምንም ነገር ለማድረግ ሙሉ-ሥልጣን የነበራቸው ቢሆንም አንኳ የሕዝብንና የአገርን ጥቅም አሣልፈው ያልሰጡ ብቻ ሣይሆን ጥንት የኢትዮጵያ ግዛቶች የነበሩና በልዩ-ልዩ ምክንያቶች ከኢትዮጵያ ይዞታ ውጪ የሆኑትን ለማስመልስ ያለ-መታከት የሚጥሩ፤ በዚህ ጥረትም ሕይዎታቸውን መስዋዕት ያደርጉ እንደነበር ይታወቃል።
አገራችን ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ያላትን ወሰን በተመለከተ አፄ ምኒልክ ከእንግሊዝ መንግሥት ጋር የተዋዋሉት ያ ውል ግን አሁን የኢሕአዴግ መሪዎች የሚሉትንና አጣምመው የሚያቀርቡትን ሻለቃ ግዌን የተባለ የእንግሊዝ መኮንን ያለ-ኢትዮጵያ ተሣትፎና እውቅና፤ በራሱ ፈቃድና ዓይን-ባወጣ አድሎዓዊነትብቻውንአሰመርኩት የሚለውን መስመር ፈጽሞ የሚመለክት እንዳልሆነ በተገቢ ግልጥ መሆን ይኖርበታል። ‘የግዌን መስመር’ የተባለውን ይህ የተናጠል ውሳኔ አንድም የኢትዮጵያ መንግሥት ሆነ መሪ እንኳን ሊገዛበት ሕጋዊ እውቅና የሰጠበትም ሆነ ትክክል ነው ብሎ አምኖ የተቀበለበት ጊዜ የለም። እንግዲህ የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች በግልጥ እያምታቱ ያሉት አፄ ምኒልክ አገራቸው ኢትዮጵያ በሱዳን በኩል ያለውን ድንበሯን በተመለከተ ከእንግሊዝ ጋር ያድረጉትን ስምምነትና ከዚያ በኋላ ግዌን ከላይ በተጠቀሰው ሁኔታ ብቻውን አካልያለሁ የሚለውንና በኢትዮጵያ በኩል ምናልባት ከአቶ መለስና ከምትካቸው ከአቶ ኃይለማርያም የተዛባና ሃቁን ያወናገረ ምስክርነት በስተቀር ምንም ዓይነት ሕጋዊ-ተቀባይነትም ሆነ አስገዳጅነት የሌለውን የአንድ-ወገን ውሳኔ ነው።
‘የግዌን መስመር’ የተባለውን ቅድመ-ወያኔ/ኢሕአዴግ የነበሩ የኢትዮጵያ መንግሥታት መቸውንም ያልተቀበሉት፤ ኢትዮጵያም ልታከብረውና መቀበል ልትገደድበት የማትችል በመሆኑ፤ ይህንን በተለየ መልኩ ለማቅረብ የሚከጅሉ መሠረታዊ በሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊና አገራዊ ጥቅም ላይ ከሚዘምቱ ባዕዳን ተለይተው ሊታዩ የማይችሉና በአገር-ክህደት ተግባር የሚያስጠይቃቸው እንደሆነ ለሁሉም ግልጥ መሆን ይኖርበታል።
2ኛ) አቶ ኃይለማርያም በዚህ መግለጫቸው የተረኩት ሌላው በጣም አስገራሚና መሠረተ-ቢስ አባባል ደግሞ በኢትዮጵያና በሱዳን መኻል እ.አ.አ. በ1996 ዓም በተፈጠረው ግጭት ሣቢያ ሱዳኖች የለቀቁትን መሬት ኢትዮጵያውያን ድንበር ዘልለው ሲያርሱ እንደነበርና ይህ መሬት የሱዳን በመሆኑ ሊመለስላቸው እንደሚገባ መንግሥታቸው እንደሚያምንበት፤ ይህንንም ተቀብሎ በተግባር ከመፈጸም ወደ-ኋላ እንደማይል የሚለው ህቶት ነው።
ሃቁን ገልብጦ ለመረዳት ካልተፈለገ በስተቀር እውነታው ግን የዚህ ተቃራኒ መሆኑ ግልጥ ነው። በመጀመሪያ በኢትዮጵያ የተያዘ የሱዳን መሬት የለም። እንደሚታወቀው በአፄ ኃይለ-ሥላሴ መንግሥትም ቢሆን ኢትዮጵያ በሱዳን ወሰኗ በኩል ጎላ-ብለው የሚታዩ የጦር-ሠፈሮች አልነበሯትም። በደርግ ጊዜም ቢሆን በዋናነት የውስጥ ተቃዋሚዎችን ለመፋለም ካልሆነ በስተቀር ለድንበር ጥበቃ የሚበቃ ሠራዊት በዚህ የአገሪቱ መሥመር አልነበረም። ድንበሩ ተከብሮ የኖረውና በሱዳኖች በኩል ይደረጉ የነበሩ አንዳንድ ድንበር-ዘለል መተናኮሶችን ሲከላከልና ሲያከሽፍ የኖረው የአካባቢው አገር-ወዳድ ሕዝብ እንደነበር ይታወቃል። በደርግ ጊዜም በተለይ በጎንደር ክፍለ-አገር ባለው ኢትዮጵያና ሱዳን በሚዋሰኑበት አካባቢ ከሕዝቡ በተጨማሪ የኢዴኅ (ኢዲዩ)፤ የኢሕአፓ፤ የአገር-ወዳድ ድርጅት፤ የከፋኝ አርበኞች ድርጅት፤ ወዘተ ታጣቂዎች ይንቀሳቀሱ ስለነበር፤ አሁን የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች ‘ቀድሞ የሱዳን ይዞታ የነበረና በኋላ ግን የኢትዮጵያ አራሾች የያዙት መሬት’ ብለው በድፍረት የሚናገሩት ከኢትዮጵያውያን ይዞታና ቁጥጥር-ውጭ ያልነበረ ነው። ደርግ እየተሸነፈ ወያኔ/ኢሕአዴግ ወደ አዲስ አበባ ሲያመራ ቀደም-ሲል ሕዝባቸውን እያስተባበሩ ድንበራቸውን ያስከብሩ የነበሩ የአካባቢው መሪዎች በሞት እየተለዩና ድንበር-ጠባቂዎችም የተለመደ የድንበር-ማስከበር ሥራቸውን መሥራት ያልቻሉበት ጊዜ ስለነበር፤ እንዲሁም በአካባቢው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ኢትዮጵያዊ ታጣቂ-ኃይሎች በልዩ-ልዩ ምክንያቶች በአካባቢው ያልነበሩበት ሁኔታ በመከሰቱ፤ ሱዳኖች ይህንን የተፈጠረ ክፍተት ተጠቅመው ድንበር እያለፉ የኢትዮጵያን መሬት መያዝና ጦር ማስፈራቸው ይታወቃል። እግር-በእግርም የሱዳን ገበሬዎችና ሃብታሞች ይህንኑ በሕገ-ወጥ መንገድና በጉልበት የተያዘ የኢትዮጵያ መሬት ማረስና ማሳረስ፤ ጫካውንም እንደፈለጉ ማውደምና መዝረፋቸው ግልጥ ነው። የአካባቢው ሕዝብ ይህንን የሱዳን ድፍረት ለመቋቋም ለአዲሶቹ ገዥዎች (ለወያኔ/ኢሕአዴግ) አቤቱታ በማቅረብ ጭምር የሚችለውን ሁሉ ከማድረግ አልተቆጠበም።
“ማን ይናገር የነበረ፤ ማን ያርዳ የቀበረ” አንዲሉ ነውና ምናልባትም ይህንን ጉዳይ በትክክል ግልጥ ለማድረግ በወቅቱ የአዲሱ መንግሥት የመከላከያ-ሚኒስትር የነበሩት አቶ ስዬ አብርሃ ግንቦት 23 ቀን 2000 ዓ/ም በወጣው ‘አዲስ ነገር’ ጋዜጣ ላይ ያሠፈሩትን ሃቅ በዋቢነት መጥቀሱ አስፈላጊ ነው። አቶ ስዬ የተባለውን የጽሑፍ ምስክርነት የሰጡት ግንቦት 13 ቀን 2000 ዓ/ም አቶ መለስ የሱዳንን የድንበር ጉዳይ በተመለከተ ሕዝብ-ተወካዮች ምክር-ቤት ፊት ቀርበው ለሰጡት የተዛባ ዘገባ ምላሽ ነው። አቶ ስዬ በዚህ ጽሑፋቸው ግልጥ ያደረጉት ነገር የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሣልፎ ለመስጠት በማስረጃነት ሊጠቀሙበት የሚሹትና እንደ-ምክንያት የሚያቀርቡት አንዱ ይህ አሁን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የደገሙትና ቀደም-ሲል አቶ መለስ ሃቁን ገልብጠው ያቀረቡት ለሱዳን ለመስጠት የወሰኑት ‘ቀደም-ሲል በሱዳን ይዞታ ሥር የነበረውንና በኋላ በግብፅ መሪ ላይ በተሰነዘረው የግድያ ሙከራ ሣቢያ ኢትዮጵያና ሱዳን መኻል የነበረው ግጭት በፈጠረው ክፍተት ኢትዮጵያውያን ድንበር ተሻግረው ያርሱት የነበረውንና ድሮም የሱዳን ይዞታ የነበረውን ነው’ የሚለውን የፈጠራ ትረካ ነው። አቶ ስዬ ስለዚሁ ጉዳይ በዚህ ጽሑፋቸው ያቀረቡትን በሰፊው እንጠቅሳለን።
“የሱዳን መንግሥት ይህንን የጥበቃ ኬላዎች ያለመኖር ሁኔታ በመጠቀም ሠራዊቱን ወደዚህ ቀጠናማስገባቱን ቀጠለ። ሱዳናውያን አራሾች የሠራዊታቸውን ኮቴ እየተከተሉ መጠጋት ጀመሩ። ባለቤት የሌለው መሬት አገኘን ብለው ደኑን ማጥፋት፤ የእርሻ መሬቱን እንዳሻቸው መያዝ ቀጠሉ። ይባስ ብለው በእርሻ ሥራ መቋቋም የጀመሩትን ኢትዮጵያውያን ገበሬዎች መተናኮልና መጋፋት ጀመሩ።ሁኔታው አየባሰበት በመሄዱ ውሱን የመከላከያ ኃይል በዚሁ አካባቢ በማስፈር ቀስ በቀስ ይህንኑ ማጠናከር ጀመርን። ሠራዊቱ ይህን በአራሾች ላይ የሚደርሰውን በደል እና በዓይናችን ፊት የሚደርሰውን ውድመት መቃወም ጀመረ። በአካባቢው የተመደበው የመከላከያ ሠራዊታችን አዛዥ የጽሑፍ መልእክቱን አስይዞ አቻው ወደሆነው የሱዳን ጦር አዛዥ አንድ የመላክተኛ ጓድ ይልካል። የተላከው ጓድ የተደረገለት አቀባበል የወዳጅ ሠራዊት አቀባበል አልነበረም። ኑ ብለው ተቀብለው ትጥቃችውን አስፈትተው አረዷቸው። ይህ ድፍረትና ጭካኔ እንደተፈጸመ ሠራዊታችን አይምሬ የአጸፋ እርምጃ ወስዶ በአካባቢው የነበረው ጦር እንደወጣ ቀረ። እኔ በኃላፊነት እስከነበርኩበት ጊዜ ድረስ ሱዳኖች ወደዚህ እካባቢ ተተኪ ሠራዊት አላኩም። አቶ መለስ ሠራዊታችን በ1995/1996 አካባቢ የወሰደው ማጥቃት ብሎ የገለጸው ይህንኑ የአጸፋ እርምጃ ነው። ይህንን አካባቢ ሠራዊታችን በወሰደው የአጸፋ እርምጃ ምክንያት በእጃችን የገባ የእኛ ያልሆነ መሬት አድርጎ ማቅረቡ ግን ትክክል አይደለም። የሱዳን ወታደሮች እና እነርሱን ተከትለው የመጡት የሱዳን አራሾች ወደዚህ ቀጠና የመጠጋታቸው ታሪክ ከፍ ብሎ ከገለጽኩት የነገሮች አንድነት ጋር የተያያዘ ነውና ድንበር ሳይካለል በፊት እንደዚህ ብሎ ፍርድ መስጠት አይገባውም ነበር።  አስቀድሞ በኢትዮጵያ ላይ እየመሰከረ ነው።”
ሲሉ ስለሁኔታው ምስክርነታቸውንና ትዝብታቸውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በይፋ አሳውቀዋል።
3ኛ) የወያኔ/ኢሕአዴግ መንግሥት ለሰባት ዓመታት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ሣይሆን እራሱ ከሚቆጣጥረው ፓርላማ ጀርባ በድብቅ ያቋቋማቸው ‘የኢትዮጵያና የሱዳን የጋራ ድንበር ኮሚሽን’ እና ‘የኢትዮጵያና የሱዳን የፖለቲካ ኮሚቴ’ የሚባሉ ሁለት ልዩ አካሎች መኖራቸውን ይፋ ያደረገው ይህን ድብቅ ሥራውን ማጋለጥ ከተቻለ በኋላ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች ከሱዳን ጋር በእነዚህ ድብቅ አካሎች አማካይነት በየጊዜው ስለሚደራደራቸው ኢትዮጵያን የሚጎዱ ውሎችና ስለሚፈጽማቸው የሕዝብን ሉዓላዊነት የሚዳፈሩ ተግባራት ማወቅ የቻለው በመንግሥት ስም ከተቀመጠው አካል ሣይሆን ጋፍኛ ከሱዳን መንግሥት ባለሥልጣናትና ከእነሱው መገናኛ-ብዙኃን ነው። የዚህ ድብቅ ሴራ ተጠቃሚ የሆኑት ሱዳኖች ከለጋስ የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች በየጊዜው ስለተቸሯቸው የኢትዮጵያ መሬቶች የምስራቹን ለሕዝባቸው ቢያበስሩና በአንፃሩ ከሕዝብ ጀርባ ተደብቀው አገርን የሚጎዳ የክህደት ተግባር ላይ የተሰማሩት የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች መሰሪ ሥራቸው እንዳይታወቅ ለመደበቅ ቢሞክሩ፤ ያ ደግሞ ሳያስቡት ይፋ ሲሆን ምንም ተቀባይነትም ይሁን ታሪካዊ እውነታ የሌላቸው የሃሰት ማስረጃዎችን ለመደርደር ቢማስኑ ላያስገርም ይችላል። የሚያስገርመውና የሚያሳዝነው ግን የባዕዳንን ተደጋጋሚ የቀጥታ ወረራዎች ጭምር ተቋቁማና ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሎ ተከብራ የኖረች ኢትዮጵያ አገራችን እንመራታለን በሚሉ በራሧ ልጆች ችሮታ ድንበሯ መደፈሩና አንጡራ መሬቷን እንድታጣ መደረጉ ነው።
እንደ ሱዳን ባለ-ሥልጣኖች ቀጥተኛ ዘገባ ከሆነ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ድንበር ለመካለል ከወያኔ/ኢሕአዴግ መንግሥት ጋር መስማማታቸውን ብቻ ሣይሆን ቋሚ የወሰን ምልክቶችን ለማስቀመጥ ቀኖች መቆረጣቸው፤ ተግባራዊ ለማድረግ ከሚጠይቀው ወጪ ሱዳን ሁለት-ሦስተኛውን ለመሸፈን ፈቃደኛና ዝግጁ መሆኗን፤ እንዲያውም ሥራው ከወዲሁ መጀመሩን ጭምር ያስረዳል። ይህ እውነታ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በተለያዩ መንገዶች ሲታወቅ ብቻ በአብዛኛው ጉዳዩን ለማስተባበል ሲባል አልፎ-አልፎ በወያኔ/ኢሕአዴግ የውጭ-ጉዳይ መሥሪያ ቤት የሚሰጡ መግለጫዎችና አሁን አቶ ኃይለማርያም ከሚናገሯቸው የተምታቱ ንግግሮች መረዳት የሚቻለው ቢያንስ በሱዳን በኩል የሚቀርቡ ዘገባዎችን ሃሰትነት በአስተማማኝ የሚያረጋግጡ አይደሉም። አንዲያውም እውነታውን ይበልጥ የሚያጋልጡ ሆነው ይገኛሉ።
4ኛ) ከአሁን በፊት ኮሚቴአችን ባወጣቸው መግለጫዎች እንዳሳወቀው ሁሉ፤ አቶ መለስ ግንቦት 13 ቀን 2000 ዓ ም ፓርላማ ቀርበው ‘አንድም የተፈናቀለ ኢትዮጵያዊ የለም’ ብለው በድፍረት ሲናገሩ ልክ ከአንድ ወር በፊት (በሚያዝያ 13 ቀን) ድንበር ተሻግሮ በመጣ የሱዳን ጦር በቋራ ወረዳ ውስጥ ነፍስ-ገበያ ከተባለ የእርሻ ሥፍራ 34 ኢትዮጵያውያን ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎና ተዘርፎ እነሱም ታግተው ወደ ሱዳን ተወስደው መታሰራቸው እንኳ ጥቂትም የወገናዊነት መቆርቆር ቀርቶ ሰብዓዊ ስሜት አልታየባቸውም። ይበልጥ ስሜታቸውን የነካውና የከነከናቸው ሱዳኖች ያሳዩት ታጋሽነት (ያውም የኢትዮጵያን መሬት ለመውሰድ) እንደሆነ በአንደበታቸው ገልጠውታል። በጣልያን ወራሪዎች የተፈጸመው ልዩ ሁኔታ እንዳለ ሆኖ፤ ምናልባትም እነ-ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስን አፍኖ ከአገራቸው ከኢትዮጵያ ወደ-እንግሊዝ ከወሰደው በናፒር የተመራው የእንግሊዝ የባዕድ ጦር ወዲህ ኢትዮጵያዊ ዜጎች በባዕድ ወራሪ ጦር ከአገራቸው ታፍነው ወደ-ባዕድ አገር ተወስደው የታሠሩት በዘመነ-ወያኔ/ኢሕአዴግ ብቻ ነው።
አሁንም ኢትዮጵያውያን አርሶ-አደሮች ከዘመን-ዘመን ከኢትዮጵያ ይዞታና ቀጥተኛ ቁጥጥር ውጭ ሆኖ ከማያውቀው እርሻቸው እየተፈናቀሉና እየተነቀሉ መሆናቸው፤ ሱዳኖች በወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች ሥልጣንና ችሮታ ተሰጥቶናል በሚሏቸው ሥፍራዎች ቁጥጥራቸውን ለማጠናከር እየተጣደፉ እንደሆነ የዓይን ምስክሮች እያረጋገጡት ያለ ጉዳይ መሆኑ ሊታውቅ ይገባል።
5ኛ) ስለ-አገር ድንበር ጉዳይ በማንኛውም ጊዜ ማንሳትና የሚከሰቱ ስጋቶችን መግለጥ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ የዜግነት ግዴታና የፖለቲካ ድርጅቶችም መሠረታዊ ኃላፊነት መሆኑን የዘነጉት አቶ ኃይለማርያም፤ ይህንን የድንበር ጉዳይ የሚያነሱ ወገኖችን (በተለይም የፖለቲካ ድርጅቶችን) ‘ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል የምርጫ ጊዜ ሲቃረብ እየተጠበቀ የሚቀርብ’ ተራ የፖለቲካ አጀንዳ አድርገው ለማሣየት ዳድተዋል። ጉዳዩን በዚህ መልክ ለማቅርብ የፈለጉበት ምክንያት ግልጥ ነው። አንድም የጉዳዩን ክብደት አቅልሎ ለማሳየትና ሕዝብን ለማደናገር ሲሆን፤ በዋናነት ግን አሁንም በተለይ ጉዳዩ በአግባቡ ያሳሰባቸውና ሕዝብን ሊያነሳሱብን ይችላሉ ብለው የሚሰጉባቸውን ድርጅቶች ከወዲሁ ለማሸማቀቅ በማሰብ ነው። የሚገርመው ግን በአንድ አፋቸው ከሱዳን ጋር ያለውን ድብቅ ድርድር ላለፉት አሥራ-ሦስት ዓመታት ሁለት ኮሚቴዎችን አቋቁመውና በየጊዜው እየተገናኙ ሥራቸውን እየሠሩ እንደሆነ እራሣቸው እየተናገሩ፤ እዚያው-በዚያው ይህንን እነሱ እያደረግን ነው የሚሉትንና ያልካዱትን ከሕዝብ የተደበቀ ሥራ ‘ሕዝብ እያወቀው ይሠራ፤ የምታደርጉት የአገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚጻረርና ሕገ-ወጥ ነው’ የሚሉ ወገኖችን ኃላፊነት-የተሞላበት አቤቱታ አምስት ዓመት ጠብቆ ከሚደረግና ውጤቱ አስቀድሞ ከተወሰነ የምርጫ ጨዋታ ጋር ለማያያዝ መሞከር ቢያንስ ተኣማኒነትም ሆነ ተቀባይነት የለውም።
IV. ማጠቃለያ:
የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳ ኮሚቴ አሁንም ለወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች ያለው መልእክት አንድ ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ ንቃችሁ ከሱዳን መንግሥት ጋር በድብቅ የምታደርጉት ማንኛውም ውል ሕገ-ወጥ እንደሆነ፤ የአገርን ብሔራዊ ጥቅም አሣልፎ የሚሰጥና እናንተንም በአገር-ክኅደት ተግባር የሚያስጠይቅ ከፍተኛ ወንጀል መሆኑን ከወዲሁ ያስታውቃል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ባልመከረበት፤ ባላወቀውና ባላመነበት ድርድር የሚደረግን ውሳኔ በለከት-የለሽ ዕብሪትና በተራ-ማምታታት ተግባራዊ ለማድረግ መሞከር አገርን ለባሰ አደጋ ማጋለጥ እንደሆነና ለውስጥም ሆነ ለአካባቢ አለመረጋጋት ምንጭ እንደሚሆን ልትገነዘቡት ይገባል። ስለሆነም በአገርና በሕዝብ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት በመገንዘብ፤ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጠውን ስምምነት ከመተግበር እንድትቆጠቡ እናሳስባለን።
የአገር-መከላከያ ክፍሎችና አባላት ለዚህ ዓብይ አገራዊ ጉዳይ የሚገባውን ክብደት ሰጥታችሁ ባዕዳን ድንበር ገፍተውና ተሻግረው በሕዝባችሁ ላይ ለሚደርስ ብሶትና ሰቆቃ የሚኖርባችሁን ሙያዊና የዜግነት ግዴታ ለመወጣት ብሔራዊ ኃላፊነት አለባችሁ።
ለሥርዓት ለውጥ የቆማችሁና የምትታገሉ አገር-ወዳድና ዴሞክራት ድርጅቶች የአገር ድንበር ጉዳይ በቀላሉ የሚታይም ይሁን ለጊዚያዊ የፖለቲካ ፍጆታ የሚመነዘር ሣይሆን መሠረታዊ የብሔራዊ ክብርና የጋራ ኅልውና መርኅ ነውና ተባብራችሁና ሕዝባዊ ኃይላችሁን አስተባብራችሁ ይህን እኩይ ሴራ ለማክሸፍ የጋራ እንቅስቃሴዎቻችሁን እንድታጎለብቱ እናሳስባለን።
ከአሁን በፊት በተደጋጋሚ አንዳስገነዘብነው ሁሉ ይህ ጉዳይ ለወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች ወይም ለተወሰኑ ክፍሎች የሚተው ሣይሆን የሁሉም የጋራ አገራዊ ጉዳይ በመሆኑ፤ ዞሮ-ዞሮ የዚህ አሣፋሪ ድርጊት ዕዳ ከፋዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ በመኻልህ ምንም ዓይነት የፖለቲካ አመለካከትም፣ የጎሣ፣ የሐይማኖትም ይሁን የአካባቢ ልዩነት ሳታሣይ ወዳጅ ቀርቶ ጠላት በመሰከረልህ የተለመደ የአገር መውደድና የአንድነት መንፈስ የጋራ ድምፅህን እንድታሰማና በጋራ እንድትቆም ወገናዊ ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን።
በኢትዮጵያ ላይ የሚሸረብ ደባ ይከሽፋል!
የኢትዮጵያ ዳር-ድንበር በሕዝቧ ኅብረትና አንድነት ተረጋግጦ ይቀጥላል!!
ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኑር!!!
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11119/

በአገሩ ሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ሆኖ ባለሙያው እንዲበሳጭና እንዲማረር እያድረጉ የኢትዮጵያን አየር መንገድ መንከባከብና ማሳደግ ይቻላልን?

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ስለተንሰራፋው መጥፎ የማኔጅመንትና ብሄረሰብ ላይ የተመሠረተ አስተዳደር ስለመኖሩ ብዙ ይነገራል። ታህሳስ 21፣ 1945 ተመሥርቶ: ረዥም ታሪክና ገና ከሥረ መሠረቱ በጥሩ የአስተዳደር ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ በመሆኑ፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የነበረው የተመቻቸ ሁኔታ ለጥንካሬው ዋነኛ ምክንያት ሆኖታል።
የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ አየር መንገዱ ሲቋቋም፡ ኢትዮጵያ በስሜንና በምሥራቅ የግዛት ክልሏ ራሱ እንኳ ገና አልተጠናቀቀም ነበር – የኤርትራ ሁኒታ አለየለትም። የዛሬይቱ ኦጋዴንም ተጠቃልላ ከእንግሊዝ ጋር በተደረገ በሕግ፡ በትሪቲ: ደንብና ድፕሎማቲክ ስምምነት ሙሉ የኢትዮጵያ አካል ለመሆን ገና ሁለት ዓመት ይቀረው ነበር።
ይህ የሚያሳየው አየር መንገዱና ኢትዮጵያ አብረው ያደጉና፡ ኢትዮጵያም ቀደም ሲል ለድህነንቷና ለግዛት አንድነቷ ታማኝነት በነበራቸው ሁለት መንግሥታት ሥር ለአየር መንገዱ የወደፊት ሕልውና እንደራሳቸው አካል ልዩ ትኩረት የሰጡት ኢንተርፕራይዝ ነበር። ባለፉት ሁለት አሥርተ ዓመታት ግን የሕወሃት የዘር ፖለቲካ አየር መንገዱንም እየተፈታተነው በመሆኑ፡ ውስጡ ያሉት ዜጎችም ሆኑ፡ ሌሎች ኢትዮጵያውንም የሚሰጉለት ድርጅት እየሆነ ነው።
ይህ ማለት ግን በእነዚህ ሁለት አሥርተ ዓመታት አየር መንገዱ አልተስፋፋም ማለት አይደለም – ብዙ ዕዳ ቢኖርበትም። ብዙ አውሮፕላኖች ተገዝተዋል፡ ብዙ የበረራ መስመሮች ተክፍተዋል። ነገር ግን የትኛውም ትክክለአኛ የማኔጅመንት ምሁር ሊያስረዳ እንደሚችለው፡ የአንድ ኢንተርፕራይዝ ጤንነትና አስተማማኝነት የሚለካው በዚህ ብቻ ቢሆንማ፡ ነገሮት ሁሉ ቀላል በሆኑ ነበር በዚህ በፉክክር በተወጠረ ኢንዱችትሪ ውስጥ።
CEO Tewolde Gebremariam during the Boeing award (Credit ENA)
CEO Tewolde Gebremariam during the Boeing award (Credit ENA)
አሁን ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት የዘነጋው ዋናው ካፒታሉና ኢንቬስትመንቶቹ ሠራተኞቹ መሆናቸውን ነው – espirit de corps መጥፋት – እንደሌሎቹ የአገራችን ድርጅቶችና ተቋሞች ሁሉ! ድርጅቱ በዘር ፓለቲካ በመወጠሩ፡ ሕወሃት የሚመለከተው የራሱ ሰዎች በአመራር ላይ መቀመጣቸውንና የዘር ፓለቲካቸውን ማራመዳቸውንና ድርጅቱን ጠቅመው እርስ በእርስ መጠቃቀማቸውን ነው። ይህ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የወደፊት ተስፋውን ሰባሪ ሸውራራ አስተሳስብ እንጂ ቅንጣት ለሀገር ታስቦ የሚደረግ አይደለም።
እንደዚያ ካልሆነማ ለምንድነው ነባርና አዲስ የኛ ፓይለቶች የሚወዱትንና የሚኮሩበትን ኩባንያ እየተዉ፡ በአፍሪቃ፡ በመካከለኛው ምሥራቅና እስያ ውስጥ ለመሥራት የሚገደዱት? ይህ በመሆኑ አይደል እንዴ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባጋጠመው የማኔጅመንት ችግሮች የኢትዮጵያዊ ፓይለቶቻችን ቁጥር መመናመን (መሠረቱ በሁሉም መስክ በታጠቀ በስለላ ድርጅት የተጠናከረ ዘረኝነት ነው)። ለዚህ አይደል እንዴ: በዚህ ረገድ ራሷን ችላ የኖረች አገርና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለሌችም ፓይለቶችና መካኒኮች ለማሠልጠን የበቃች አገር፡ አሁን የውጭ ፓይለቶች ለመቅጥር የተገደደችው?
ዘወትር አጥሩ ዝቅተኛ በሆነበት በኩል መዝለልን ልምዳቸውና ፓለቲካቸው ያደረጉት የሕወሃት ስዎች፡ አፋቸውን አሹለው የብቃት ማንስን አንድ ጉዳይ አድርገው እንዳያነሱ፡ ደግነንቱ ዛሬም ቢሆን፡ ረዳት ካፕቴን ኃየለመድህን ስኞ ዕለት በብቃት እንዳሳየው ሁሉ፡ hኢትዮጵያውያን ፓይለቶች በሄዱበት ሁል ስመጥርና ታዋቂዎች የመሆናቸው ጉዳይ ከሕወሃትም ልደት በፊት የታሪክ ምሥክርነት አለው።
On the grass at Dar airport (Credit: Richard Bodin, via Wolfgang Thome’s Blong)
On the grass at Dar airport (Credit: Richard Bodin, via Wolfgang Thome’s Blong)
እስከአሁን በምንሰማው እስከአምስት የሚደርሱ የውጭ ሃገር ፓይለቶች እንዳሉ ይነገራል። የመረጃውን እርግጠኝነት ባላጣራም፡ ቲውተር ላይ እንዳየሁት ከሆ፡ ታህሳስ 18፣ 2013 የበረራ ቁጥር ET 815 ማረፊያውን ናይሮቢን ስቶ ዳሬስላም ሣር ውስጥር ሜዳ ቆፍሮ እግሩን የቆለፈው የኢትዮጵያ አውሮፕላን አብራሪም የውጭ ስው እንደነበረ ይነገራል።
ሌላው ችግርም እንዲሁ መካኒኮቻችንን ይመለከታል። እነርሱም አገር እየጣሉ እየሄዱ ነው። ባለፈው ዓመት ተኩል አገሩንና ሥራውን ጥሎ ጥገኝነት ለመጠየቅ ያለሁበት አገር የመጣ ከዩኒቨርሲቲ ክአሥርታት በፊት በማኒጅመንት ተመርቆ ሲሠራ የነበረ የቀድሞ የድርጅቱ ባልደረባ አንድ የኢትዮጵያውያን ማኅበራዊ ስብስብ ላይ አግኝቼው እንዳጫወተኝ፡ ባጭሩ ሁኔታው እንደሚክተለው ነው:
በሠራተኛው እይታ፡ አየር መንገዱ የድሮ ጥላውን እንጂ የዛሬ ሪያልቲው ወንካራ ነው። ድሮ ለአየርመንገድ መሥራት ኩራት ነበር። ዛሬ ለአየር መንገዱ ለመሥራትና ታማኝ ነው ብሎ ለመታየትሙያችንን ማሸነፋችን፡ ሃላፊነታችንን መወጣታችንና ኢትዮጵያውያነታችን በቂ አይደለም። በሌላ በኩልደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ዜጎች መሆናችን እንዲታወቅ ሆን ተብሎ በሕወሃት ስዎች አያያዝና ተቀባይነት፡ታማኝነት ልዩነቱ መሠመሩ ነው
“አንተ አየር መንገዱንና አገርህን ትተህ እዚህ ስትመጣ ሌላ የገፋፋህ ነገር የለም” ወይ ብዬ ስጠይቀው፡ ትክ ብሎ ተመልክቶኝ፡ “አገሪቱ ስላምና ጤና ሆና ማየትና የራሴን የወደፊት ተስፋዬን መገፈፌ ነው በተደጋጋሚ የሚሰማኝ የነበረ” አለኝ።
በእርግጠኝነት መናገር ባልችልም፡ ምናልባትም ረዳት ካፒቴን ኃይለመድህንን ያንገፈገፈውም ይህ ሊሆን ይችላል። አልያ ጤነነቱ የተረጋገጠ፡ በቆንጆ ገቢ ደህና ኑሮ ይኖር የነበረ ኢትዮጵያዊ ይህንን ትቶ ራሱን መሥዋዕት ለማድረግ ምን ያስገድደው ነበር?
ይህ ሁኔታ እንዴት ይታረማል?
እስከዛሬ ያለውን የሕወሃትን አሠራር ስመለከት፡ ጠባቡና ጎጠኛው ቡድን ትምህርት በማግኘት የሀገራችን ሁኔታ በቀላሉ መለወጡን የሚጠራጠር ስሜት በየቀኑ ይዳስሰኛል። ስዎቹ ሥልጣን በእጃችን ወይንም ማንም አይኖርም ብለው የቆረጡ ይመስላል።
ለዚህ ነው ሁሉም ሃገራችን በስላምና በብልጽግና ለልጆቻችን የምትተላፍበትን መንገድ መቀይስ የሚያስፈልገው። 95 ከመቶ የሚሆነው ሕዝባችን በሁለተኛ ድረጃ ዜግነት፡ እንዲሁም በድምሩ አምስት በመቶ የሚሆኑት የሕወሃት ደጋፊዎችና አጫፋሪዎቻቸው ከሌሎቹ ብሄረስቦች የተውጣጡትን ጭምሮ በሃገራችን ላይ የጫኑት የአፈና ቀነበር አሽቀንጥሮ መጣል አለበት።
ረዳት ካፒቴን ኃይለመድህን በወሰደው እርምጃ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ለሶስት ተከፍለዋል። አንዱ ወገን የሕወሃት ሲሆን፡ እነርሱም እንደጠላት በመፈረጅ፡ “ከሃዲ” በማለት ረዳት ካፒቴኑን በሃገር ጠላትነንት ሲፈርጁት ይሰማሉ። ቤተስቦቹንም እያስቸገሯቸው መሆናቸው ይስማል።
ሁለተኛው ወገን፡ ሁኔታውን ሀገሪቱ ካለችበት የሥልጣን ብልግናና ከላይ እንደተገለእጽው የዘረኝነት ችግር ላይ መሆኗን ተናግረው ለፓይለቱ በጎ ይመኙለታል። ለኢትዮጵያ የነፃነት ሻማ አድርገው ይመስክሩለታል።
ሶስተኛው ወገን የሚጨነቀው፡ ለፓይለቱ ወይንም ሀገሪቱ ስላለችበት ሁኔታ ሳይሆን፡ አየር መንገዳችን ምን ዐይነት የወደፊት ሕልውና ያጋጥመው ይሆን የሚለው ሥጋት የሚያበስለስላቸው ናቸው።
ለማንኛውም፡ ለሕውሃትም ሲሉ ሳይሆን፡ የስዊስ መንግሥት ረዳት ካፒቴን ኃይለመድህን ላይ የረዥም ጊዜ እሥራት እንደሚፈርድበት አልጠራጠርም። አንዳንድ ስዎች ስለኤክስትራዲሽን ሲያወሩ ይስማሉ። በኔ እምነት፡ የሞት ቅጣትን በሃገሯ የሻረች ስዊትዘርላንድ፡ የሞት ቅጣትን የሕግ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የፓለቲካ መሣሪያ አድርጋ ለምትጠቀምበት ኢትዮጵያ ግለስቡን ለሞት አሳልፋ ትሰጠዋለች የሚል ቅንጣት ጥርጥር የለኝም።
ዋናው ጉዳይ ግን፡ ለረዥም ዓመታት ስዊትዘርላንድ ውስጥ እንዲታሰር መደረጉ ለኢትዮጵያውያን የታሪኩ ፋጻሜ ሊሆን አይገባም። በተለይም ይህንን እርምጃ አሁን እንደሚገመተው ፖለቲካ ከሆነ፡ እርሱን ያነሳሳው፡ ኢትዮጵያውያን የእርሱን የትግል አርማ ከፍ አድርገው ሕወሃትን ሊፋለሙትና የሃገር ጥፋት ፓለቲካውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊገድቡት ይገባል። አለዚያማ እርሱን በቃላት ብቻ ማሞካሸቱ ከሌላው ወገን እንደሚመነጨው የጥላቻና ቂም በቀል የተለየ አያደርገውም። የእነርሱ ከሳሾች የሚሉት እኮ፡ ስዎችን አደጋ ላይ ጣልክ አይደለም – ማንም አልተጎዳምና። የእነርሱ ብሽቀት አገዛዛችንን አጋለጠ፤ ሥልጣናችንን ለአደጋ አጋለጠ ነው። የቡድን ጥቅም ቧንቧችንን ሊደፍንብን ሞከረ ነው። ይህ ደግሞ እውነትና ትክክል ነው።
የስሞኑን ጫና ለመቋቋም፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት የመረጠው የአየር መንገዱን የወደፊት ማስብ ሳይሆን፡ የዛሬዋን እሳት ማዳፈን ላይ ነው። ለምሳሌም ያህል ለመጥቀስ፡ አየር መንገዱ ከአውሮፕላን ሻጭ ኩባንያና ከሚዲያ ጋር በመተባበር፡ ለራሱ የአይዞህ መልዕክትና ምሥጋና በማስባሰብ ላይ መሠማራቱ: ከላይ እንዳመለከቱት፡ እነዚህ ስዎች እሳቱ እስኪበላቸውና ሀገራችንንም እስኪጎዳ ድረስ እንደማይቀየሩ የሚያመላክት ነው።
ስሞኑን አየር መንገዱ ብዙ ለቅሶ ደራሽች ነበሩት
ከስሞኑ ለቅሶ ፈጥኖ ደራሽች መካከል ቦይንግ ግንባር ቀደም ነበር። ይዞ የመጣውም ፋና እንደዘገበው the 2013 “GOLD Level Boeing Performance Excellence Award” ነው።
ሌላው ለቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ታቦ ምቤኪ ነፃ ቲኬት: የፕሮቶኮል ወንበር ስጥቶና በግብዣ አምነሽንሾ የኢትዮጵያ አየር መንገድን እንዲጎበኙ ማድረግ ነበር – ጥቅሙና ግንኙነቱ ገሃድ ባይሆንም። ለማንኝውም አድረጉት። ታቦ ምቤኪም የድርጅቱን ከአቪዬሽን ማሰልጠኛ አካዳሚ እና የአለም አቀፍ አየር መንገዶች አውሮፕላን የመገጣጠሚያ ክፍሎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፡ ፕሬዝዳንት ምቤኪ ከጉብኝታቸው በኋላ በሰጡት አስተያዬት የአየር መንገዱ የማሰልጠኛ አካዳሚ አለም አቀፍ የአቪዮሽን ጥራትን ያሟላና በአህጉሪቱ ቀዳሚ የሆነ ተቋም ስለመሆኑ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
Welcoming at Ethiopian for Tabo Embeki (credit: ENA)
Welcoming at Ethiopian for Tabo Embeki (credit: ENA)
ስሞኑን ይህንን ጋጋታ በጽሞና ላዳመጠ ሰው፡ የአየር መንገዱ ዝና እንዳይጎዳ የሚወስድ እርምጃ መሆኑን መገመት ይቻላል።
አየር መንገዱ ባይጎዳ ደስ ይለኛል። ሕይወቱና ነፍሱ ተጠብቆ ከድል ወደ ድል እንዲሄድ በኢትዮጵያዊነቴ እመኛለሁ። ይህ ምኞት ግን ፋይዳ የለውም – የሕወሃት ስዎች ነገ ተመልስው የከአፕርታይድ ሊቀመኳስ Hendrik Frensch Verwoerd Verwoerd ካደረገው ባላነሰ በዘርና ጎጥ ላይ የተመሠረተ ኋላቀር ፖለቲካቸው ነገ ተመልስው የጥቅም ገበያቸውና ሌላውን ማተራመሻቸው ያደርጉታል! የዜጎችን ስሜት ሲጎዱና የሃገርን ስላምና ደህንነት መሠሪ በሆነው ፖለቲካቸው ሲመርዙት: በእነዚህ ድርጊቶቻችው፡ የሕዝቡን ምሬትም እያከረሩ፡ የታሪክ መንገድ አይታውቅምና በጥቂት የታሪክ ተጋባዦች አማካይነት በድንገት የሚቀሰቀሰው እሳት እንዲገላገለን ሁኔታውን እራሳቸው እያመቻቹት ነው!
ሃገራችን ወደፊት እንድትራመድ ከተፈለገ: በኢትዮጵያውያን እኩለነት ላይ የተመሠረተ የሁሉም ኢትዮጵያውያን አሰተዳደር መፈጠር የጊዜው ጥያቄ ነው። ይህ እስካልተቻለ ድረስ፡ በውንብድና በሃገርና ወገን ከሃዲዎች የውሸትና የተንኮል አመራር ላይ የተመሠረተ የሕወሃት አስተዳደርን ዕድሜ ለማሳጠር ብዙ ነገሮች ነገ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ሊፈጸሙ ይችላሉ!
ይህ ደግሞ በሚገባ ተቀነባብሮ ካልተካሄደ፡ ብሽቀቱን በቀላሉ መገላገል ካለመቻሉም በላይ፡ በየቦታው በተበታተነ መንገድ የሚደረገው የአልገዛም ባይነትም በአገር ደኅንነትና ዕድገትም ላይ ጉዳት ይኖረዋል።
ነገር ግን ክትርፍ አሳድጅ የውጭ ኩብንያዎችና የውስጥ አላዛኞች ባለፍ፡ ሌላው ዓለምም አሁን የኢትዮጵያን አፓርታይድ አገዛዝ የሃገሪቱና የቀጠናው የወደፊቱ የችግር ምንጭ መሆኑን በሚገባ የተገነዘቡት ይመስላል!
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11198/

የኢትዮጵያን ገጽታ አደባባይ ያወጣው አውሮፕላን አብራሪ ሃይለመድህን አበራ

ዳኛቸው ቢያድግልኝ

ልማታዊ ግስጋሴ እስከ ግድበ ህዳሴ በደረሰበት ታሪካዊ ወቅት፣ ኢትዮጵያ በፈጣን የእድገት መስፈርት ውስጥ ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም ከቻይና ቀጥሎ ሁለተኛ ነች እየተባለ በመሪዎቿ በሚነገርላት ጊዜ። አሸባሪዎችን ከመነሻቸው ለማምከን በአይነቱ ልዩ የሆነ የአንድ ለአምስት አደረጃጀት የሰዎችን ድርጊት ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብን ጭምር የሚመረምር ምትሃታዊ ሃይል ተደራጅቶ ባለበት ሁኔታ የዴርቶጋዳን ልብወለድ መሰል ነገር መታየቱ ብዙዎችን አስደምሟል። ለመሆኑ የዛሬ ልጆች ጀግና አይደሉም የሚል ማን ነው?
በውጭ ሃገር የዜና ማሰራጫዎች ወሬው እንደተሰማ አስተያየት ለመክተብ ጣታቸው እንደ ክላሺኒኮቭ ፊደል የሚያንጣጣ ሁሉ ፓይለቱ ጥገኝነት ለማግኘት ብሎ እንዲህ ማድረጉ አሳፋሪ ነው፣ አላዋቂ አፍሪካዊ መሆን አለበት፣ ይቀጣ! ይቀጣ! የሚሉ ሃረጎች በርክተው ነበር። እነዚህ በአብዛኛው አፍሪካ ማለት አንድ ሃገር የሚመስላቸው የእውቀት ብርሃን የጨለመባቸው ናቸውና ምንም ማድረግ አይቻልም።Ethiopian Airlines plane Co-Pilot Hailemedehin Abera Tagegn.
ሁለተኛው ሰሞኑን ነገረ ስራው አያምርም ነበር የሚልና አእምሮው ለየት ያለ ነገር የሚያሳየው ‘ሺዞፍሬንያ’ እሚሉት ነገር እየጀማመረው ነበር የሚለው ነው። እህት ሁሉም ይስማልኝ በማለት በመረጃ መረቦች በተነች የሚባለውን ያነበበ ሰው ለበረራ ብቁ ነው የሚለውን ፈቃድ ሰጪም ወፈፍ ያደረገው መሆን አለበት ቢል አላጋነነም። ይሄ እብድ እየመሰለ ሲሰልል የኖረ ወያኔ ወፈፌነትን በጣም ስለተለማመደው አማኑኤል ሆስፒታልን የደህንነት ማሰልጠኛ ኮሌጅ አድርጎ ቢመለከት አይፈረድበትም ብለን መሳቅም መብታችን ነው። ቁም ነገሩ ግን የበረራውን ደህንነት ለማስጠበቅ የአብራሪዎችንምጤናና ደህንነት መከታተል ስለሚገባው ያንንም ማድረግ ባለመቻሉ ወደ ትልቅ ስህተት ራሱን እየጨመረ ነው። በዚህ ሁኔታ ምን  ያህል ወፈፌ ፓይለቶች ይኖሩ ይሆን ብሎ መጠየቅም ያስፈልጋል። ከሆነም ምን አይነት አስተዳደር ቢኖር ነው ጨርቅ ጥሎ የሚያሳብደው፣ ሃገር ጥሎ የሚያስኮበልለው ብሎ መጠየቅም ተገቢ ነው። የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥ እንደሚባለው በአንድ-ለአምስት ተጋግዞ መዋሸት ይቻል ይሆናል ከዚያ መረብ ውጪ ላለነው ግን አስቂኝ ትዕይንት ነው።
እኔ አውሮፕላኑን ጠለፈ የሚለው አገላለጽ እጅግም አልተመቸኝም።  ረዳት አብራሪው ድምጼ ይሰማልኝ በማለት ማቆም የማይገባው ስፍራ ላይ አውሮፕላኑን አቆመ ለዚያውም ያለ ፍርሃትና ሽብር መደናገጥና መርበትበት ተሳፋሪውም ኮሽታ ሳይሰማ። አቅጣጫ በቀየረው አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ ሰራተኞች ለተሳፋሪዎቻቸው ቡና ሻይ እያቀረቡ ምቾታቸውን እየጠበቁ ዋናው አብራሪ ጋዜጣቸውን እያነበቡ ምቾታቸው ሳይጓደል አረፉ። ተሳፋሪዎች የሆነውን ሁሉ ሳያዩ ረዳቱ አብራሪ በገመድ ወርደው ለፖሊሶች እጃቸውን ሰጡ። እንግዲህ የአእምሮ በሽተኛ እንደዚህ ከሆነ ተጋግዘን ብንታመምስ ምን ነበረበት?
ረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራ ማስተላለፍ የፈለገው መልዕክት ስለመኖሩ መጠራጠር አውቆ መጨፈን ይሆናል። በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ የሀገሪቱ አስተዳደርን ገጽታ የሚያበላሽ ድርጊት ተከናውኗል። ስለምን የሃገሪቱን ገጽታ የሚያጎድፍ እንደሚባል አይገባኝም። የሀገሪቱን ገጽታ የሚያጠለሹት ጎጠኞችና አምባገነኖች ናቸው። የነርሱ አስተዳደር መበስበሱን፣ ሁሉንም ዘርፍ ማለትም ብዙሃኑን የሀገሪቱ ሕዝብ ማሳዘኑን በዚህም ምክንያት ምሬት መኖሩን ነው ይህ ወንድማችን አደባባይ ያወጣው። አዎ የአስተዳደሩን ብልሹነትና እንዳይድን ሆኖ መታመም ነው አደባባይ ያወጣው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ገጽታ ሳይሆን ዓለም የተመለከተው የአስተዳደሩን መጥፎነት ነው።
ቤተሰቦቹ ተገድደው የሚያወጧቸው መግለጫዎች ይበልጥ የሚያጋልጡት ይህ ማፍያ ቡድን እስከምን ድረስ ሊሄድ እንደሚችልና በቤተሰብ ችግርና ሃዘን ውስጥ እንኳን በመግባት ሊፈጽም የሚችለውን አረመኔያዊ ድርጊት ነው። ቤን የሚሉት ለማጅ ጋዜጠኛ ወሎ ሄዶ ባላቸውን አለቆቹ ገድለው እርሱ ደግሞ በሙስሊም አክራሪዎች እንደተገደሉ ለማስመሰል ሃዘንተኛዋን ባለቤት ሌላ ፖለቲካ ሲያሰራ እንደነበረው ያለ ዜናን ማስታወስ ተገቢ ነው። ያለንበት ዘመን የራሽያ አብዮት የፈነዳበት ጊዜ አይደለም በአይነቱ በተለይም በመረጃ ቅብብሎሹ ረገድ እጅግ በጣም የተለየ ዘመን ነው። የዚያን ጊዜ ታክቲክ በመጠቀም አሁን የሚታየውን አመጽ ማፈን አይቻልም። ይልቁኑ እብዶቹ መንግስት ነኝ ባዮችና ወፈፌዎቹ ጋዜጠኛና ካድሬዎች ከአሳፋሪ ተግባር ቢታቀቡ ነው የሚሻላቸው።
ረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራ ቃል ሳይተነፍስ ማለት የሚፈልገውን የተናገረ ይመስለኛል። የምቾት ህይወትን ትቶ ሙያውን ተሰናብቶ መሄዱ ጀግንነት ነው። የብዙዎችን ሰቆቃና ቁጣ ያለውን የአስተዳደር በደልና ዘረኛነት ማጋለጡ ጀግንነት ነው። ራሱን ከዚህ ጨቋኝ ስርዓት ነጻ ማውጣት ለርሱ ቀላል እጅግ በጣም ቀላል ነገር ሆኖ ሳለ በሙያው በክህሎቱ የአለምን ትኩረት የሚስብን ነገር የአንድ ሰው ሕይወት ሳያጠፋ ማስተላለፍ መቻሉ ጀግንነት ነው። ይልቁንም ደግሞ የታወከ አእምሮ ኖሮ(አዋኪውና አስቀዋሹ ምክንያት ምን እንደሆነ ይታወቃልና) በዚህ አይነት የተረጋጋ መንፈስ እንዲህ ያለ መልዕክት ማስተላለፍ መቻሉ ይበልጥ አስደናቂ ያደርገዋል። ምናልባትም በሽታ መሆኑ ቀርቶ ልዩ ስም የሚሰጠው የመንፈስ ጥንካሬ ተብሎ የሚታወስ ይሆናል።  ለወንድማችን ሃይለመድህን አበራ መልካም ጤንነትና ፍትህን እመኛለሁ። ቤተሰቡና ወዳጆቹ ተመሳሳይ የመንፈስ ጥንካሬ ያድርባቸው ዘንድም አሳስባለሁ።
biyadegelgne@hotmail.com
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11137/

Friday, February 21, 2014

“የረዳት አብራሪ ኃይለመድን እህት ታስራለች፣ ቤተሰቦቹ በግዳጅ ሊናገሩ ነው”

Tensay Abera (Co-pilot Hailemedhin's sister)
Tensay Abera (Co-pilot Hailemedhin’s sister)
ቦይንግ 767-300 ጄኔቭ አርፎ፣ መንገደኞቹ ወደየመድረሻቸው ተጉዘው አውሮፕላኑም ወደ ሀገሩ ተመልሷል። ነገር ግን የወሬው በረራ ማረፊያ ቦታ እንዳጣ ነው። የኃይለመድን ጉዳይ በየቦታው የመወያያ ርዕስ እንደሆነ ነው፣ ይቀጥላልም። የግምት ወሬዎች እዚህም-እዚያም እየተረጩ ነው። በተለይ የመንግስት ካድሬዎችን “ቢዚ” አድርጓቸዋል። በምን መልኩ የድራማውን ድርሰት እንደሚጽፉ ግራ ግብት ብሏቸዋል የአዕምሮ ሕመምተኛ ሊሉት ፈለጉ …ከዚያ ትዝ ሲላቸው አዕምሮ ታማሚ ሆኖ አየር መንገዱ መንግስት እንዴት እንዲያበር ፈቀደ፣ ለአብራሪዎቹ ምርመራ አያደርግም ወይ የሚሉት ጥያቄዎች ሊከተሉ ሆነ። ቀጥለው አባትዬው እቁብ ሰብሳቢ፣ አራጣ አበዳሪ… ተደርገው ተሳሉ። እእ..ደራሲዎቹ የቤተሰብ ጣጣ መሪ ተዋናዩ ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ አልታይ አላቸው። የኃይለመድን እህት ሆነው የተዋቀረ እና የተዋቃ ጽሑፍ በፌስቡክ ላይ አከታተለው ጻፉ…በርግጥ ይሄኛው የወጭ የዜና አውታሮች ዘንድ ደርሶላቸው ተራግቦላቸዋል። ተአማኒነት ባያገኝም።
በነዚህ መጨበጫ በሌላቸው ወሬዎቹ አንድ ሊገባን የሚችል ነገር ቢኖር ካድሬዎቹ ደራሲዎች የአበራሪው ስም እና ስብዕና በአሉታዊ ጎኑ ብቻ እንዲነሳ መፈለጋቸው ነው። ከአየር መንገዱ ይልቅ የመንግስታቸው ህልውና እንቅልፍ ነስቷቸዋል። ምክንያቱም ኃይለመድን የጠየቀው የፖለቲካ ጥገኝነት ነው፣ ዝርዝር ባይኖረውም ይቺ ቃል የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ስቧል። የHuman Rights Watch ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮው ስለክስተቱ ተጠይቀው የኢህአዴግ አምባገነናዊ እና ኢ-ሰብአዊነት የትኛውንም ዜጋ የሚያሰድድ እንደሆነ ሳያመነቱ ተናግረዋል። የእንግሊዙ Telegraphም በመረጃ አስደግፎ “ኢትዮጵያውን ያላማቋረጥ የሚፈልሱት በድኅነት እና በጭቆና ነው” ሲል ቁልጭ አደርጎ አስቀምጦታል። እና እንደዚህ ያሉ የኢህአዴግ መታወቂያዎች ከሀገሬው አልፈው ለተቀረው ዓለም እየደረሱ መሆናቸው ካድሬዎቹን አሰበርግጓቸዋል። አውሬ ደግሞ ሲበረግግ የሚያደርገውን አያውቅም።
አሁን የልጁን ቤተሰቦች አስገድደው እንደለመድነው ETV ላይ ድራማ ሊያሰሯቸው እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ነው። “ፌስቡኬ በሌሎች ሰዎች ጥቅም ላይ ውሏል” ያለችው እህቱም በእስር ላይ እንደምትገኝ ተሰምቷል።
እስኪ የሚያስብሏቸውን እንስማ መቼም ምንም ቢቧጥጡ እውነታዋ ያለችው ረዳት አብራሪ ኃይለመድን ጋ’ ስለሆነ ሊያጠፏት አይቻላቸውም። እኛም እሱ እስኪናገር ከይሆን-ይሆናል አሉባልታዎች ተቆጥበን በድርጊቱ መፈጸም በፊት ባንዲራችንን ተሸክሞ ከአድማስ አድማስ አውሮፕላናችንን እያበረረ ሀገሩን ሲያገለግል ለቆየው ኋይለመድን የምንሰጠው ክብር ይቀጥል።

“ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም” አቶ አለምነው መኮንን (አቤ ቶኪቻው)

አቶ አልምነው“ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም” አቶ አለምነው መኮንን

አንድነት እና መኢአድ የተሳዳቢው ባለስልጣን አቶ አለምነው መኮንን እንጀራ እናት የሆነችውን ብአዴንን ለመቃውም እሁድ በባህር ዳር ሰልፍ መጥራታቸው እንደተሰማ፤
በኬኒያ የስደት “ኬዝ” ጋገራ
እኒያ የአማራ ህዝብ ምንትስ ነው… ቅብርጥስ ነው… ብለው በሞቅታ ውስጥ ያለ ሰው እንኳ የማይሞክረውን የስድብ ውርጂብኝ “በመረጣቸው” ህዝብ ላይ ያወረዱት ሰውዬ፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው። “ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም… ይህ የተደረገው በኮምፒውተር ቆርጦ ቀጥል ቴክኖሎጂ ነው…” ብለው መግለጫ ሰጥተዋል መባሉን ስሰማ ሮጬ ወደ ኢቲቪ ድረ ገጥ ሄጄ ያሉትን ለመስማት ሞከርኩ።
“ድምጹ የእኔ ነው…” የሚለው ከንግግራቸው ውስጥ ተቆርጦ ወጥቷል። “ተሳደበ ይሉኛል… እንዴት እሳደባለሁ… መራጮቼን… ወላጆቼን… ዘመዶቼን… ወገኖቼን… ምን በወጣኝ እና ምን ቆርጦኝ እሳደባለሁ…???” ብለው እኛኑ ሲጠይቁ የሚያሳየው ንግግራቸውን ግን ሰማሁት።
እንግዲያስ አቶ አለምነህ፤
አንደኛ የብዙሃኑም ጥያቄ ይሄው ነው… ይሄ ህዝብ ቅጥ ባጣ ድህነት እንዲኖር የተፈረደበት አንሶ ምን በድሎ ምን አጥፍቶ ይብጠለጠላል… ምን በወጣውስ ይሰደባል…???
ሁለተኛ አዩት አይደል መቁረጫ እና መቀጠያ ቴክኖሎጂው ያለው ኢቲቪ ቤት ነው…! በአደባባይ ተናግረው ዞር ከማለትዎ “ድምጹ የእኔ ነው” የሚለው የእምነት ቃልዎ ተስረዘልዎ!
ሶሰት… አራት…አምስት…. መቶ፤ ይሄንን ለሁሉም ኢህአዴጎች ንገሩልኝ፤
ወይ ልቦና ግዙ! ንስሃም ግቡ እና ተንበርከካችሁ ይሄን ህዝብ ይቅርታ ጠይቁ፤ ወይ ደግሞ “ማስተዳደሩን” ርግፍ አድርጋችሁ ትታችሁ ማደሪያችሁን ፈልጉ!
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11096/

አንድነት እና መኢአድ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን በባህርዳር ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።

andent ena mead
አንድነት እና መኢአድ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን በባህርዳር ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።
የአማራ ክልሉ ባለስልጣን፤ “አማራው በባዶ እግሩ ነው የሚሄደው…” ብለው እጅግ የከፋ ዘለፋ ካሰሙ ብኋላ ህዝቡ በያለበት ስለ ሰውዬው ያፈረላቸው ቢሆንም እርሳቸው ግን ሳያፍሩ ትላንት በቴሌቪዥን መስኮት ተከስተው ሲያስቁን ነበር።
ዛሬ እንደሰማነው እና እንዳየነው፤ የመኢአድ እና አንድነት አባላት እሁድ ለጠሩት ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን ባደረጉት ቅስቀሳ “እኛም ጫማ የለንም፤ እኛም በባዶ እግራችን ነው የምንሄደው ቢሆንም ግን የሞራል ለዕልና አለን” የሚል ቅስቀሳ ሲያሰሙ ውለዋል።
በቅስቅሳው ወቅት ፖሊስ ጉልቤውን ሊያሳያቸው ቢሞክርም ህዝቡ ከበባ እያደረገ ሲከላከላቸው አንድነት ዛሬ ከለቀቀው ቪዲዮ አይተናል።
ድረ ገጻችን፤
…የምር ግን ህዘብ እየተዘለፈም እየተዘረፈም እንዴት ይችለዋል…. ???ብላ በትልቁ እየጠየቀች፤ አንድነት ያሰራጨውን ቪዲዮ ላላዩት እንደሚከተለው ታሳያለች።

Thursday, February 20, 2014

ዓለም ባንክ ኢህአዴግን በረበረው – ከዚያስ?

“ኢህአዴግ የተጭበረበረ ሪፖርት አቅርቦ” ነበር

world bank foto


ኢህአዴግ “አልመረመርም፣ አልበረበርም” በማለት ሲያንገራግር ከቆየ በኋላ በዓለም ባንክ ቀጭን ትዕዛዝ ለመበርበር መስማማቱን ገልጾ በተለያዩ አካላት ምርመራ ተካሂዶበታል። በተከታታይ ሲካሄድ የነበረው ምርመራ አካል የሆነው የመጨረሻ ምርመራ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ተጠናቋል። የጎልጉል ታማኝ ምንጮች እንደተናገሩት ስድስት አባላትን ያካተተው የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን ኢህአዴግን መርምሮ ተመልሷል። የሚጠበቀው የመጨረሻው ሪፖርትና ሪፖርቱ የሚቀርብለት የዓለም ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ ነው። በቅርቡ የሚወጣውን ውሳኔ አቅጣጫ ለማስቀየር በማሰብ ኢህአዴግ ለመርማሪው ቡድን ራሱ የፈጠረውን “የተጭበረበረ ሪፖርት” አቅርቦ ነበር፡፡
ኢህአዴግ ምርመራውን በተቀነባበረ የፈጠራ ሪፖርት ለማምለጥ ሞክሮ እንደነበር የጠቆሙት የመረጃው ምንጮች “የመርማሪዎቹ ቡድን ሪፖርቱን አንቀበልም፣ የችግሩ ሰለባዎችና ክሱን የመሰረቱት ክፍሎች በሚኖሩበት ቦታ በመገኘት ነዋሪዎችን በተናጠል ለማነጋገር እንፈልጋለን” በማለት ኢህአዴግን እንደሞገቱት አስታውቀዋል። ኢህአዴግ በልማትና በህዝብ ስም የሚያገኘውን ከፍተኛ የዕርዳታ ገንዘብ የጦር ሃይሉን ለማደራጀት፣ የደህንነትና የፖሊስ ሃይሉን ለማስታጠቅና ርዳታ በሚለመንባቸው ዜጎች ላይ የተለያየ ወንጀል ፈጽሟል፣ አሁንም እየፈጸመ ነው በሚል መወንጀሉ ይታወሳል።
የምርመራው መነሻ ከዛሬ አስር ዓመት በፊት በቀድሞው ጠ/ሚኒስትርና የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ፣ የህወሃትና የኢህአዴግ ሊቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝና በየደረጃው ያሉ አስፈጻሚዎች በጋምቤላ ክልል የተከናወነው የጅምላ ጭፋጨፋ ነው። በወቅቱ የተካሄደው ጭፋጨፋ ከ400 በላይ የተማሩ የአኙዋክ ወንዶች ላይ ያተኮረ እንደነበር በተለያዩ ጊዜያት የወጡ ዓለም አቀፋዊ ሪፖርቶችና የጉዳዩ ሰላባዎች ይፋ ያደረጉት ጉዳይ ነው። አቶ መለስ ሞት ቀደማቸው እንጂ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የቀረበባቸውን የክስ ማስረጃ ተቀብሎ ክስ እንዲመሰረትባቸው ከድምዳሜ መድረሱም ይፋ ሆኖ ነበር። ኢህአዴግ በዚሁ ፍርድ ቤት ላይ የአፍሪካ መሪዎችን የማስተባባርና የፍርድ ቤቱን አካሄድ ማውገዝ የጀመረው አቶ ኦባንግ የሚመሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ አቶ መለስ ላይ የመሰረተው ክስ እንዲከፈት መወሰኑን ተከትሎ እንደሆነ በወቅቱ ከየአቅጣጫው አስተያየት የተሰጠበት ጉዳይ ነው።
ከዚህ “ዘግናኝ” እንደሆነ ከሚነገርለት ጭፍጨፋ በኋላም በጋምቤላ ሰፋፊ ለም መሬትን በኢንቨስትመንት ስም ነዋሪዎችን በሃይል እያፈናቀለ በመሸጡ ኢህአዴግ ይከሳሳል። በተለይም የኦክላንድ ተቋምና (Oakland Institute) ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት (Human Rights Watch) ያቀረቡዋቸው ሪፖርቶች ኢህአዴግ በስድብና “የአብዮታዊ ዴሞክራሲ መንገድ ተጻራሪዎች፣ ርዕዮተ ዓለሙ ላይ የተነሱ፣ አይኗ እየበራ ያለችውን ኢትዮጵያን ለማጥፋትና ወደኋላ ለመጎተት ልዩ ተልዕኮ ያላቸው፣ የነፍጠኛውን ስርዓት መልሶ ለመትከል የሚሰሩ፣ ጸረ ልማቶች፣ ወዘተ” በማለት ቢያጣጥላቸውም ቀን ጠብቀው ስራቸውን እየሰሩ ስለመሆናቸው እየተነገረ ነው።
ጎልጉል ጥቅምት2፤ 2005 ዓም /October 12, 2012/ ኢህአዴግ ከዓለም ባንክ ያገኘውን 600 ሚሊዮን ዶላርና በተመሳሳይ ፕሮጀክት ወደፊት ሊያገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ገንዘብ በተመለከተ አደጋ ላይ መውደቁን፣ ኢህአዴግ የቀረበበት ውንጀላ ከተረጋገጠ የሚያጣው inspection panelገንዘብ በቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ፣ ዓለምአቀፉ ሁሉን ያካተተ የልማት ተቋም /Inclusive Development International (IDI)/ የተባለውን ተቋም ጠቅሰን “ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ” በሚል ርዕስ መዘገባችን ይታወሳል።
ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትን፣ በልማት ስም የሰብዓዊ መብት በመጣስ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ማስረጃ በመያዝ፤ በስፍራው በመገኘትና ከመሠረቱ ዘልቆ በመግባት አደራጅቶ በመሰብሰብ ተጠያቂ የሚያደርገው IDI ከሰለባዎቹ ውክልና የተሰጠው ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቆም ነበር፡፡
የኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊት የሚያደርሰውን እስራት፣ ግርፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ከመኖሪያ ቦታ ማፈናቀል፣ የግዳጅ ሰፈራ ወዘተ በማምለጥ ወደ ኬንያ የተሰደዱ የጋምቤላ ነዋሪዎች ይህ ሁሉ ግፍ የሚፈጽምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ስም ከዓለም ባንክ በሚያገኘው የዕርዳታ ገንዘብ በመሆኑ ለባንኩ በላኩት የአቤቱታ ደብዳቤ ተመልክቷል። ዝርዝሩ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡
አቤቱታው ከቀረበ በኋላ ሁኔታውን ለማጣራትና ውሳኔ ላይ ለመድረስ ያመች ዘንድ ኢንስፔክሽን ፓናል በኢትዮጵያ በመገኘት ምርመራውን አካሂዶ ነበር፡፡ በክሱ መሠረት ፓናሉ በእርግጥ “የዓለም ባንክ ለልማት ሥራዎች የሚሰጠው የእርዳታ ገንዘብ በኢትዮጵያ በተለይም በጋምቤላ ክልል የሚኖሩትን ዜጎች ሰብዓዊ መብት በመጣስ ላይ” እና ለደኅንነትና ወታደራዊ ጥቅሞች ላይ አውሎታል በማለት የምርመራውን ውጤት የዓለም ባንክ ቦርድ ውሳኔ እንዲሰጥበት አቀረበ፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የውሳኔውና ሃሳብ አስመልክቶ “ኢህአዴግ በሩን እንዲከፍት የዓለም ባንክ አዘዘ” በሚል ሐምሌ 11፤ 2005ዓም /July 18, 2013/ በዘገብንበት ወቅት ከውጪ በሚመጣ ዕርዳታ ላይ ህልውናው የተመሰረተው ኢህአዴግ ገመዱ እየከረረበት መምጣቱን ጠቁመን ነበር፡፡
ኢህአዴግ የዓለም ባንክ ቦርድ ውሳኔውን እንዳያስተላልፍ የተለያዩ የውስወሳ (ሎቢ) ሥራዎችን ሲሰራ እንዲሁም የዓለም ባንክ የራሱን ማጣራት እንዳያደርግ ለማደናቀፍ ሲሞክርና ሲከላከል አምስት ወራት አስቆጠረ፡፡ በመጨረሻም ሐምሌ 11፤ 2005ዓም (July 18) ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ከአዲስ አበባ፤ እንዲሁም በዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘው ኤምባሲ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በመሆን የዓለም ባንክን አመራሮች ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው እያለ ባንኩ ከአንድ ቀን በፊት ሙሉ ምርመራ እንዲካሄድ አዘዘ። ውሳኔው ባንኩ በራሱ ገንዘብ ማንም ሊያዝበት እንደማይችል ያሳየበትና ለኢህአዴግም እጅግ አሳፋሪ ውሳኔ መሆኑ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለው ዓለምአቀፉ ሁሉን ያካተተ የልማት ተቋም Inclusive Development International (IDI) እና ሌሎች ክፍሎች አስተያየት ሰንዝረው ነበር። የዜናው ዝርዝር እዚህላይ ይገኛል፡፡world-bank
ከዚህ ውሳኔ በኋላ የኅልውናው ጉዳይ ያሰጋው ኢህአዴግ የባንኩ መርማሪ ቡድን ሙሉ ምርመራ እንዳያካሂድ የተቻለውን ሁሉ ሲያደርግ ቆይቶ ነበር፡፡ ምርመራው ተካሂዶ ኢህአዴግ በእርግጥ ከዓለም ባንክ የሚሠጠውን ገንዘብ ለሰብዓዊ መብት ረገጣ ማዋሉን ቡድኑ ካረጋገጠ፤ ኢህአዴግ በትንሹ 600 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያጣ፣ ጉዳቱ ከከፋም እስከ ቢሊዮኖች እንደሚደርስ ጎልጉል በዚሁ ዜናው ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል።
ከዚህ ሁሉ በኋላ ከሁለት ሳምንት በፊት ላይ ወደ አዲስ አበባ አቅንቶ የነበረው የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን ሥራውን በትክክል እንዳያካሂድ ኢህአዴግ የራሱን “የተጭበረበረ ሪፖርት አዘጋጅቶ” እንደጠበቃቸው ለጎልጉል መረጃ ደርሶታል። በዚሁ ሪፖርት መሰረት “ችግሩ ካለበት ጋምቤላ ክልል መሔድ አያስፈልግም” በማለት ኢህአዴግ የባንኩን መርማሪ ቡድን ተከራክሮ ነበር። የምርመራው ቡድን አዲስ አበባ ከመግባቱ በፊት አገር ጥለው የኮበለሉትን የቀድሞ የጋምቤላ ክልል መሪ አቶ ኦሞት ኦባንግን የተኩት አዲሱ ፕሬዚዳንትም ረዳቶቻቸውን በመያዝ አዲስ አበባ ተገኝተው ኢህአዴግ የያዘውን አቋም “እኛን እመኑ፤ ነዋሪውን ማነጋገር አያስፈልግም” በማለት ለዓለም ባንክ ቡድን አባላት አቅርበው ነበር።
ለጊዜው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉና ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ከአዲስ አበባ ለጎልጉል እንዳሉት ሶስት ቀን የፈጀ ክርክር ከተደረገ በኋላ የዓለም ባንክ መርማሪ ቡድን በቅድመ ሁኔታ ጋምቤላ የተፈቀደለት ቦታ ብቻ እንዲሄድ ከስምምነት ላይ ተደረሰ። ኢህአዴግ ባዘጋጀው “የተጭበረበረ ሪፖርት” ላይ እንደገለጸው አስቀድሞ ሰፈራን የሚያካሂደው የጤና አገልግሎት፣ ትምህርት ቤት፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ፣ መንገድ፣ የመኖሪያ ቤትና አስፈላጊ መስረተ ልማቶችን እንዳሟላ በስፋት ዘርዝሮ ነበር። በተመረጡት ቦታዎች ምስክርነት እንዲሰጡ የራሱን ሰዎች አዘጋጅቶ እንደነበርና በእድሜ የገፉ አባቶችና እናቶች አስተያየት እንዳይሰጡ ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ነበር። በእድሜ የገፉት ሰላባዎች “የመጣው ይምጣ በማለት እውነቱን ለመናገር አይፈሩም፣ በቀላሉም አይደለሉም” የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን የሚናገሩት እኚሁ ሰው “የመርማሪው ቡድን በቀላሉ የሚታለል አልነበረም” በማለት የዓለም ባንክ ቡድን በቅርቡ ከሚያወጣው የውሳኔ ሪፖርት በፊት ዝርዝር ጉዳዮችን ከመናገር ተቆጥበዋል።
ከምርመራው ቡድን አባላት መካከል ሁለቱ በኬኒያና በደቡብ ሱዳን ስደት ላይ የሚገኙ የአኙዋክ ተወላጆችን በግንባር ተገኝተው ማነጋገራቸውን ጎልጉል አረጋግጧል፡፡ በተለይ አንደኛዋ እንስት መርማሪ ጭፍጨፋውን አምልጠው የተሰደዱትን ሰዎች ባነጋገሩበት ወቅት እንባቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው ሲያለቅሱ እንደነበር የሚያስታውሱት የጎልጉል የመረጃ ምንጮች፣ “ኢህአዴግ displaced anuaksለማጭበርበር ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት፣ የመርማሪዎቹ ቡድን አስፈላጊው መረጃ እንደነበረው፣ ጉዳዩን አስቀድመው ለዚህ ሂደት እንዲበቃ ያደረጉት ክፍሎች የያዙት እውነትና ውክልናውን ወስዶ የክስ ማመልከቻውን ያዘጋጀው ተቋም በቂ ልምድና ሚዛን የደፋ ተግባር ያከናወነ በመሆኑ ኢህአዴግ በተለያዩ ጊዜያት የተዘገቡት ኪሳራዎች ይደርስበታል፣ አሊያም በቀድሞው መንገድ የመቀጠሉ ጉዳይ አሳሳቢ ይሆናል” ሲሉ ግምታቸውን ሰጥተዋል።
ከተለያየ አቅጣጫ አጣብቂኝ ውስጥ እየገባ ያለው ኢህአዴግ፤ አሜሪካ እንደ ቀድሞው ባዶ ቼክ እንደማትሰጥና ካሁን በኋላ ሁኔታዎችን እየመረመረች ገንዘብ እንደምትለቅ መወሰኗ ይህንንም በህግ ማጽናቷ በቅርቡ ሊያካሂድ ካሰበው “ምርጫ” አኳያ የሰሞኑ ራስ ምታት ሆኗል፡፡ ይህ የአሜሪካ ውሳኔ በአውሮጳውያኑም ዘንድ ተግባራዊ እንዲሆን እየተሰራ ባለበት ባሁኑ ወቅት ኢህአዴግ ፊቱን ወደ ቻይና የማዞር አዝማሚያ ሊያሳይ የፈለገ ቢመስልም የማያዋጣው እንደሆነ በስፋት ይታመናል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አቅጣጫው የጠፋበት አካሄድና ውጥረት በአገዛዙ ውስጥ ራሱን የቻለ የፖለቲካ ገመድ ጉተታ ፈጥሮ ችግሩን ሊያባብስ ይችላል እየተባለ ባለበት ወቅት የዓለም ባንክ ከዕርዳታና ድጎማ ጋር በተያያዘ የሚሰጠው ውሳኔ ሊፈጥር የሚችለውን ውጥረት ለመገመት ኢህአዴግ ምርመራው እንዳይካሄድ የተጠቀመውን ማደናቀፊያ መመልከቱ ብቻ በቂ እንደሆነ ይታመናል፡፡
የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን ለምርመራ አዲስ አበባ ከመግባቱ በፊት ኢህአዴግ የቀድሞውን የክልሉን መሪ አቶ ኦሞት ኦባንግን በቁጥጥር ስር በማዋል ለሚከሰስበት ጉዳይ መስዋዕት አድርጎ ሊያቀርባቸው ዝግጅቱን አጠናቆ እንደነበር፣ አቶ ኦሞት ከደህንነትና ከቀድሞ ታጋይና የአሁኑ “ልማታዊ ኢንቨስተሮች” ጋር ባላቸው ትስስር የተነሳ መረጃ ደርሷቸው እንደኮበለሉ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።
በአሁኑ ወቅት አውሮጳ እንደሚገኙ የሚነገረው አቶ ኦሞት ኦባንግ ከዓለም ባንክ ጋር በመገናኘት ከአኙዋኮች ጭፍጨፋ ጀምሮ እስከ አሁኑ ጊዜ ድረስ ለዘመናት የሚያውቁትን ምስጢር ሁሉ ለዓለም ባንክ በማጋለጥ ለራሳቸው ርካሽ የስደተኛ ጉዳይ መጠቀሚያነት ያውሉታል እየተባለ ከቅርብ ወገኖቻቸው ዘንድ ይሰማል፡፡
ኢህአዴግ በየመንደሩና በየክልሉ በተመሳሳይ የሚፈጽማቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና ህገወጥ ተግባራት በተደራጀ መልኩ በማሰባሰብ ዱካውን እየተከተሉ መታገል፣ ዓለም አቀፍ መስመሮችን በመከተል ትግልን ማሳለጥ፣ ኢህአዴግ በሚፈልገው መልኩ ደረጃን ዝቅ በማድረግ አላስፈላጊ ንትርክ ውስጥ አለመግባትና አልሞና አስተውሎ መራመድ የወቅቱ ጥያቄ እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚናገሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መሪ አቶ ኦባንግ ሜቶ የዓለም ባንክ እዚህ ደረጃ የመድረሱ ዜና የአንድ ቀን ሥራ ውጤት እንዳልሆነ ሲናገሩ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡
ሐምሌ 11፤2005ዓም /July 18, 2013/ “ኢህአዴግ በሩን እንዲከፍት የዓለም ባንክ አዘዘ” በሚል በዘገብንበት ወቅት አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ኦባንግ “እኛ በመሠረቱ ልማትን አንቃወምም፤ ሆኖም ግን በልማት ስም የሚሠጠው ዕርዳታ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ለመርገጥ የሚውል ከሆነ ህወሃት/ኢህአዴግ ተጠያቂ መሆን ይገባዋል፤ የግልጽነትና ተጠያቂነት ዕጥረት እንዲሁም የሙስና በሽታ እንዳጠቃው በራሱ መሪዎች የሚነገርለት ኢህአዴግ፤ የፈለገውን ነገር እንደፈለገው የማድረግ አምባገነናዊ አሠራሩ ራሱን አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚከተው” በመጥቀስ ድርጅታቸው በጥናትና በዕቅድ ከሚያካሂደው ሁሉን ዓቀፍ ትግል መካከል ይህ አንዱ እንደሆነና “በተጠናከረ መልኩ በመንቀሳቀስ ጉዳዩን ዳር በማድረስ የተጎዱ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን መከራ” እንደሚታደጉ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ይህንን የዓለም ባንክ ጉዳይ አስመልክቶ ከአንድ ዓመት በላይ ሲዘግብበት የቆየ ሲሆን በየጊዜው የወጡት የዜና መዘርዝሮች ለአንባቢው ግንዛቤ መስጠት ይችሉ ዘንድ በቅደምተከተል አቅርበናቸዋል፡፡
ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል! ጥቅምት 2፤2005ዓም/October 12, 2012
ዓለም ባንክ ርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ደርሷል – የካቲት 9፤2005ዓም/February 16, 2013
የማነቂያው ገመድ ከርሯል፤ “ትግሉ ይቀጥላል” ኦባንግ ሜቶ – ሐምሌ 11፤2005ዓም/July 18, 2013
http://www.goolgule.com/world-bank-investigated-eprdf-whats-next/