FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, February 6, 2014

ጐፋ ገበያ ማዕከል ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ 19 መደብሮች ወደሙ

በገበያ ማዕከሉ የእሳት ቃጠሎ ሲደርስ ለዘጠነኛ ጊዜ መሆኑ ታውቋል

goffa


በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ቄራ ጐፋ የገበያ ማዕከል ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ 19 መደብሮች ሙሉ በሙሉ ወደሙ፡፡
ጥር 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ከሌሊቱ 7፡15 ሰዓት ላይ የእሳት ቃጠሎው እንደተከሰተ የገለጹት፣ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ኦፊሰር አቶ ንጋቱ ማሞ ናቸው፡፡ የእሳቱ መነሻ ምክንያትና በንብረት ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡
በቄራ ጐፋ የገበያ ማዕከል ውስጥ ቁጥራቸው 500 የሚደርሱ ነዋሪዎችና ነጋዴዎች መኖራቸውን የገለጹት አቶ ንጋቱ፣ ከቤቶቹና ከሱቆቹ አሠራር አኳያ ሲታይ 19 መደብሮችና መኖሪያ ቤቶች ብቻ ተቃጥለው ሌሎቹ መትረፋቸው አስገራሚ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቤቶቹ ከተሠሩበት ግብዓትና መቀራረብ አኳያ መሆኑን አክለዋል፡፡
ከ53 ሺሕ ሊትር በላይ ውኃ በመርጨትና ሌሎች የማጥፊያ ዘዴዎችን በመጠቀም በ1፡30 ሰዓት ውስጥ እሳቱን ለመቆጣጠር መቻሉን ኦፊሰሩ ተናግረዋል፡፡ ቤቶቹ ቆርቆሮ በቆርቆሮ ሆነው ከመሠራታቸው በተጨማሪ፣ እጅግ በጣም የተጠጋጉና መደብሮቹም ውስጥ ለእሳት መቀጣጠል ምቹ የሆኑ ሸቀጣ ሸቀጦች በመኖራቸው ምክንያት ለማጥፋት አስቸጋሪ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡
ባለሥልጣኑ የግምት ባለሙያ ባይኖረውም ከተረፈው ንብረትና በአካባቢው ካሉት የንግድ ባንክና ሌሎች ድርጅቶች መትረፍ አንፃር በእሳቱ የወደመው ንብረት ትንሽ መሆኑን አቶ ንጋቱ አክለዋል፡፡ (ሪፖርተር)
http://www.goolgule.com/goffa-market-placed-burned-down/

No comments:

Post a Comment