FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, February 21, 2014

“ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም” አቶ አለምነው መኮንን (አቤ ቶኪቻው)

አቶ አልምነው“ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም” አቶ አለምነው መኮንን

አንድነት እና መኢአድ የተሳዳቢው ባለስልጣን አቶ አለምነው መኮንን እንጀራ እናት የሆነችውን ብአዴንን ለመቃውም እሁድ በባህር ዳር ሰልፍ መጥራታቸው እንደተሰማ፤
በኬኒያ የስደት “ኬዝ” ጋገራ
እኒያ የአማራ ህዝብ ምንትስ ነው… ቅብርጥስ ነው… ብለው በሞቅታ ውስጥ ያለ ሰው እንኳ የማይሞክረውን የስድብ ውርጂብኝ “በመረጣቸው” ህዝብ ላይ ያወረዱት ሰውዬ፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው። “ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም… ይህ የተደረገው በኮምፒውተር ቆርጦ ቀጥል ቴክኖሎጂ ነው…” ብለው መግለጫ ሰጥተዋል መባሉን ስሰማ ሮጬ ወደ ኢቲቪ ድረ ገጥ ሄጄ ያሉትን ለመስማት ሞከርኩ።
“ድምጹ የእኔ ነው…” የሚለው ከንግግራቸው ውስጥ ተቆርጦ ወጥቷል። “ተሳደበ ይሉኛል… እንዴት እሳደባለሁ… መራጮቼን… ወላጆቼን… ዘመዶቼን… ወገኖቼን… ምን በወጣኝ እና ምን ቆርጦኝ እሳደባለሁ…???” ብለው እኛኑ ሲጠይቁ የሚያሳየው ንግግራቸውን ግን ሰማሁት።
እንግዲያስ አቶ አለምነህ፤
አንደኛ የብዙሃኑም ጥያቄ ይሄው ነው… ይሄ ህዝብ ቅጥ ባጣ ድህነት እንዲኖር የተፈረደበት አንሶ ምን በድሎ ምን አጥፍቶ ይብጠለጠላል… ምን በወጣውስ ይሰደባል…???
ሁለተኛ አዩት አይደል መቁረጫ እና መቀጠያ ቴክኖሎጂው ያለው ኢቲቪ ቤት ነው…! በአደባባይ ተናግረው ዞር ከማለትዎ “ድምጹ የእኔ ነው” የሚለው የእምነት ቃልዎ ተስረዘልዎ!
ሶሰት… አራት…አምስት…. መቶ፤ ይሄንን ለሁሉም ኢህአዴጎች ንገሩልኝ፤
ወይ ልቦና ግዙ! ንስሃም ግቡ እና ተንበርከካችሁ ይሄን ህዝብ ይቅርታ ጠይቁ፤ ወይ ደግሞ “ማስተዳደሩን” ርግፍ አድርጋችሁ ትታችሁ ማደሪያችሁን ፈልጉ!
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11096/

No comments:

Post a Comment