FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, February 5, 2014

ትምህርት ቤታችን እና ኮሚኒቲውን የከበበው አደጋ …!


school


የመምህራን ማስጠንቀቂያ …
ሰሞነኛው የጅዳዎች ጉዳይ የመኖሪያ ፈቃድን በማስተካከል ዙሪያ ቢሆንም ከ 3000 (ከሶስት ሽህ) በላይ ታዳጊዎችን የሚያስተናግደው የጅዳው አለም አቀፍ ት/ቤት አሁንም አደጋ ላይ መሆኑን እየሰማን ዝም ብለናል!  ከሳምንታት በፊት መምህራን አመጽ አድርገው ነበር። ከቀናት በፊትም  25 መምህራን ስብሰባ ተቀምጠው፣ በአንድ አቋም ጸንተው ጠንከር ያለ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል። ላለፉት 8 ወራት በትምህርት ቤቱ ባለቤት በኮሚኒቲው ጉዳያቸው ቢያዝም እስካሁን ከወሬ ያላለፈ እርምጃ አለማየታቸውን ገልጸዋል።  25 ቱ school letterመምህራን ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር፣ ለኮሚኒቲው፣ ለጅዳ ቆንስልና ለወላጅ መምህራን ህብረት ባስገቡት ደብዳቤ እስከ ቀጣዩ ሳምንት የሁለተኛው የትምህርት አጋማሽ መጀመሪያ የመኖሪያና የስራ ፈቃዳቸው ተስተካክሎ ካልተሰጣቸው  በማስተማር መደበኛ ስራቸው እንደማይገኙ በላኩት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ማስጠንቀቃቸውን በእጀ የገባው ሰነድ ያመላክታል!
የወላጅ መምህራን ህብረት ስብሰባ ጥሪ …
“ወላጅና መምህራን ህብረት” በሚል ካች አምና በመንግስት ትዕዛዝ የወላጅ ኮሚቴን የተካው ኮሚቴ በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ለመምከር ለወላጅ ስብሰባ ጠርቷል። ኮሚቴው የሳውዲን የምህረት አዋጅ ማለቅ ተከትሎ የጅዳ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት ለሳምንት ሲዘጋ የሚወክለውን ወላጅም ሆነ መምህራኑን ብሎ ድምጹን አላሰማም። ትምህርት ቤቱ ካንድም ሁለት ሶስቴ በመምህራን ስራ ማቆም አድማ ሲናጥ፣ ከፍተኛ የማህበረሰቡ መዋዕለ ንዋይ ከመጋረጃ ጀርባ ለሚደረጉ የመምህራን እና ሰራተኛ ዝውውር መባከኑ ሲሰማ የዝሆን ጀሮ ስጠኝ ማለቱ አይደንቅ ይሆናል። የመንግስት ሃላፊዎች ትኩረትና ጥበቃ የማይደረግለትን  የትምህርት ማዕከል ህልውና ለማስጠበቅ ስብሰባ መጥራትና ወላጁን ባለማማከሩ ተወቃሽ ከመሆን ግን አላመለጠም። ለሚታየው እንግዳ፣ ለሚሰማው ባዳ መሆናቸው ያስከፋው ወላጅ ከትናንትም ዛሬ ተስፋ ቆርጧል።
ዛሬ የወላጅ መምህራን ህብረት ተብየውን ምን እንዳሰናከለው፣ ምን እንዳሽመደመደው መስማት ባያጓጓም የወደፊት የወላጁን፣ የመምህራንንና የታዳጊዎችን ትምህርት ቤት አደጋ ላይ መውደቅ  እያየ ስለያዘው አቋም መስማት ጓጉተናል። ማስታወቂያ ባወጣ በሳምንቱ፣ ስብሰባውን ሊያደርግ ቀናት ሲቀሩት ደግሞ ዛሬ ምሽት የህብረቱ አመራሮች በጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ሃላፊዎች ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርተዋል። አሁንም ኮሚቴው በዚህ ስብሰባ ምን በል ሊባልም ሆነ ከወላጅ መምህራን ጋር በሚደረገው ስብሰባ ላይ እንዳይነካ የሚፈለገውን ቦታና  እንዳይታለፍ የሚፈለገው የቀይ መስመር ገደብ ምን ሊሆን እንደሚችል አንገምትም።  ብቻ ሁነኛ ባለቤት አጥቶ አንደ ስደተኛው ተገፊ ወገን ለሚከላተመው የ3000 ታዳጊዎች ትምህርት ቤት መጻኢ ህይዎት ወላጁ በስብሰባው በመሳተፍ መምከር ይኖርበታል።sch letter
በመግስት ሊደራጅ ያታቀደው ኮሚኒቲ …
ዛሬ ያለው ኮሚኒቲ በአዲስ የመተኪያው የምርጫ ጊዜ በቆንስል መስሪያ ቤቱ ትዕዛዝ ተላልፏል። የሚተካው ኮሚቴ ደግሞ የሚደራጀው በመንግስት እንደሆነ እየተነገረን ነው። የምርጫው መዘግየትም ዋናው ምክንያት ይህ እውነት መሆኑ ቆንስል መስሪያ ቤቱ ከመካከለኛው ምስራቅ አገኘሁ ያለውን ሞዴል የኮሚኒቲ ህግና ደንብ ረቂቅ ጊዜውን ለጨረሰው ኮሚኒቲ ይፋ አድርጎታል። ቅንነት በሌለበት መንደር በወረቀት ላይ በሰፈረ ህግና መመሪያ ለወጥ ያመጣ ይመስል የማይገባ ስራ መሰራት ተጀመሯል። የሚጠፋውን ጊዜና የሚባክነውን የማህበረሰብ ንብረት ብክነት ነዋሪው ህብረት ፈጥሮና ማህበሩን ከፖለቲካና ከድርጅት አደረጃጀት ጣለቃ ገብ ሂደት በማስቆም ነጻ ካላወጣው አደጋው የከፋ እንደሚሆን ጥርጣሬው ያየለብኝ ለእኔ ብቻ ቢሆን መልካም ነበር ። ግን አይደለም። ብዙ ነዋሪ አዲሱን አካሄድ አልወደደውም!
ኮሚኒቲውን በአንድ ባንዴራ ስር ከማደራጀት ተወጥቶ በብሔር ብሔረሰብ ስብጥርና የፖለቲካ ድርጅት ሰወች በኮሚኒቲው በማሰግሰግ የሰራነው ስራ እንዳላዋጣን እናስተውለው። ወላጁም ሆነ አብዛኛው የጅዳና አካባቢው ነዋሪ ለአመታት የራቀው ኮሚኒቲ የጥቂቶች መፈንጫ ከሆነ ወዲህ የሆነውን ቆም ብለን እናስብ! እናም ቢያንስ በልጆቻችን ትምህርት ቤትን ህልውና ለማስጠበቅ ኮሚኒቲውን ሊውጠው ከተዘጋጀ ክፉ አውሬ አፍ ለማዳን እንረባረብ!  በኮሚኒቲውና በትምህርት ቤቱ ዙሪያ በሚደረጉ ስብሰባዎች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የልጆቻችን ትምህርት ቤት ለመታደግና ለህልናው ወሳኝ የሆነውን ኮሚኒቲ ከወደቀበት አዘቅት አውጥተን ለብሩህ ተስፋ ሂደቱ እንታደገው፣ እናጎልብተው!  ወላጅና መምህራን ህብረት በጠሩት ስብሰባ ተሳታፊ እንሁን፣ በነጻነት ሃሳባችን እናንሸራሽር! የልጆቻችን ትምህር ቤተችን ከአደጋ እንታደገው!  ይህ ማንም የማይገሰው መብታችን ነውና!
ጀሮ ያለው ይስማ!
ነቢዩ ሲራክ
http://www.goolgule.com/to-save-the-school-and-community-in-saudi-arabia/

No comments:

Post a Comment