FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Sunday, February 23, 2014

በአገሩ ሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ሆኖ ባለሙያው እንዲበሳጭና እንዲማረር እያድረጉ የኢትዮጵያን አየር መንገድ መንከባከብና ማሳደግ ይቻላልን?

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ስለተንሰራፋው መጥፎ የማኔጅመንትና ብሄረሰብ ላይ የተመሠረተ አስተዳደር ስለመኖሩ ብዙ ይነገራል። ታህሳስ 21፣ 1945 ተመሥርቶ: ረዥም ታሪክና ገና ከሥረ መሠረቱ በጥሩ የአስተዳደር ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ በመሆኑ፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የነበረው የተመቻቸ ሁኔታ ለጥንካሬው ዋነኛ ምክንያት ሆኖታል።
የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ አየር መንገዱ ሲቋቋም፡ ኢትዮጵያ በስሜንና በምሥራቅ የግዛት ክልሏ ራሱ እንኳ ገና አልተጠናቀቀም ነበር – የኤርትራ ሁኒታ አለየለትም። የዛሬይቱ ኦጋዴንም ተጠቃልላ ከእንግሊዝ ጋር በተደረገ በሕግ፡ በትሪቲ: ደንብና ድፕሎማቲክ ስምምነት ሙሉ የኢትዮጵያ አካል ለመሆን ገና ሁለት ዓመት ይቀረው ነበር።
ይህ የሚያሳየው አየር መንገዱና ኢትዮጵያ አብረው ያደጉና፡ ኢትዮጵያም ቀደም ሲል ለድህነንቷና ለግዛት አንድነቷ ታማኝነት በነበራቸው ሁለት መንግሥታት ሥር ለአየር መንገዱ የወደፊት ሕልውና እንደራሳቸው አካል ልዩ ትኩረት የሰጡት ኢንተርፕራይዝ ነበር። ባለፉት ሁለት አሥርተ ዓመታት ግን የሕወሃት የዘር ፖለቲካ አየር መንገዱንም እየተፈታተነው በመሆኑ፡ ውስጡ ያሉት ዜጎችም ሆኑ፡ ሌሎች ኢትዮጵያውንም የሚሰጉለት ድርጅት እየሆነ ነው።
ይህ ማለት ግን በእነዚህ ሁለት አሥርተ ዓመታት አየር መንገዱ አልተስፋፋም ማለት አይደለም – ብዙ ዕዳ ቢኖርበትም። ብዙ አውሮፕላኖች ተገዝተዋል፡ ብዙ የበረራ መስመሮች ተክፍተዋል። ነገር ግን የትኛውም ትክክለአኛ የማኔጅመንት ምሁር ሊያስረዳ እንደሚችለው፡ የአንድ ኢንተርፕራይዝ ጤንነትና አስተማማኝነት የሚለካው በዚህ ብቻ ቢሆንማ፡ ነገሮት ሁሉ ቀላል በሆኑ ነበር በዚህ በፉክክር በተወጠረ ኢንዱችትሪ ውስጥ።
CEO Tewolde Gebremariam during the Boeing award (Credit ENA)
CEO Tewolde Gebremariam during the Boeing award (Credit ENA)
አሁን ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት የዘነጋው ዋናው ካፒታሉና ኢንቬስትመንቶቹ ሠራተኞቹ መሆናቸውን ነው – espirit de corps መጥፋት – እንደሌሎቹ የአገራችን ድርጅቶችና ተቋሞች ሁሉ! ድርጅቱ በዘር ፓለቲካ በመወጠሩ፡ ሕወሃት የሚመለከተው የራሱ ሰዎች በአመራር ላይ መቀመጣቸውንና የዘር ፓለቲካቸውን ማራመዳቸውንና ድርጅቱን ጠቅመው እርስ በእርስ መጠቃቀማቸውን ነው። ይህ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የወደፊት ተስፋውን ሰባሪ ሸውራራ አስተሳስብ እንጂ ቅንጣት ለሀገር ታስቦ የሚደረግ አይደለም።
እንደዚያ ካልሆነማ ለምንድነው ነባርና አዲስ የኛ ፓይለቶች የሚወዱትንና የሚኮሩበትን ኩባንያ እየተዉ፡ በአፍሪቃ፡ በመካከለኛው ምሥራቅና እስያ ውስጥ ለመሥራት የሚገደዱት? ይህ በመሆኑ አይደል እንዴ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባጋጠመው የማኔጅመንት ችግሮች የኢትዮጵያዊ ፓይለቶቻችን ቁጥር መመናመን (መሠረቱ በሁሉም መስክ በታጠቀ በስለላ ድርጅት የተጠናከረ ዘረኝነት ነው)። ለዚህ አይደል እንዴ: በዚህ ረገድ ራሷን ችላ የኖረች አገርና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለሌችም ፓይለቶችና መካኒኮች ለማሠልጠን የበቃች አገር፡ አሁን የውጭ ፓይለቶች ለመቅጥር የተገደደችው?
ዘወትር አጥሩ ዝቅተኛ በሆነበት በኩል መዝለልን ልምዳቸውና ፓለቲካቸው ያደረጉት የሕወሃት ስዎች፡ አፋቸውን አሹለው የብቃት ማንስን አንድ ጉዳይ አድርገው እንዳያነሱ፡ ደግነንቱ ዛሬም ቢሆን፡ ረዳት ካፕቴን ኃየለመድህን ስኞ ዕለት በብቃት እንዳሳየው ሁሉ፡ hኢትዮጵያውያን ፓይለቶች በሄዱበት ሁል ስመጥርና ታዋቂዎች የመሆናቸው ጉዳይ ከሕወሃትም ልደት በፊት የታሪክ ምሥክርነት አለው።
On the grass at Dar airport (Credit: Richard Bodin, via Wolfgang Thome’s Blong)
On the grass at Dar airport (Credit: Richard Bodin, via Wolfgang Thome’s Blong)
እስከአሁን በምንሰማው እስከአምስት የሚደርሱ የውጭ ሃገር ፓይለቶች እንዳሉ ይነገራል። የመረጃውን እርግጠኝነት ባላጣራም፡ ቲውተር ላይ እንዳየሁት ከሆ፡ ታህሳስ 18፣ 2013 የበረራ ቁጥር ET 815 ማረፊያውን ናይሮቢን ስቶ ዳሬስላም ሣር ውስጥር ሜዳ ቆፍሮ እግሩን የቆለፈው የኢትዮጵያ አውሮፕላን አብራሪም የውጭ ስው እንደነበረ ይነገራል።
ሌላው ችግርም እንዲሁ መካኒኮቻችንን ይመለከታል። እነርሱም አገር እየጣሉ እየሄዱ ነው። ባለፈው ዓመት ተኩል አገሩንና ሥራውን ጥሎ ጥገኝነት ለመጠየቅ ያለሁበት አገር የመጣ ከዩኒቨርሲቲ ክአሥርታት በፊት በማኒጅመንት ተመርቆ ሲሠራ የነበረ የቀድሞ የድርጅቱ ባልደረባ አንድ የኢትዮጵያውያን ማኅበራዊ ስብስብ ላይ አግኝቼው እንዳጫወተኝ፡ ባጭሩ ሁኔታው እንደሚክተለው ነው:
በሠራተኛው እይታ፡ አየር መንገዱ የድሮ ጥላውን እንጂ የዛሬ ሪያልቲው ወንካራ ነው። ድሮ ለአየርመንገድ መሥራት ኩራት ነበር። ዛሬ ለአየር መንገዱ ለመሥራትና ታማኝ ነው ብሎ ለመታየትሙያችንን ማሸነፋችን፡ ሃላፊነታችንን መወጣታችንና ኢትዮጵያውያነታችን በቂ አይደለም። በሌላ በኩልደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ዜጎች መሆናችን እንዲታወቅ ሆን ተብሎ በሕወሃት ስዎች አያያዝና ተቀባይነት፡ታማኝነት ልዩነቱ መሠመሩ ነው
“አንተ አየር መንገዱንና አገርህን ትተህ እዚህ ስትመጣ ሌላ የገፋፋህ ነገር የለም” ወይ ብዬ ስጠይቀው፡ ትክ ብሎ ተመልክቶኝ፡ “አገሪቱ ስላምና ጤና ሆና ማየትና የራሴን የወደፊት ተስፋዬን መገፈፌ ነው በተደጋጋሚ የሚሰማኝ የነበረ” አለኝ።
በእርግጠኝነት መናገር ባልችልም፡ ምናልባትም ረዳት ካፒቴን ኃይለመድህንን ያንገፈገፈውም ይህ ሊሆን ይችላል። አልያ ጤነነቱ የተረጋገጠ፡ በቆንጆ ገቢ ደህና ኑሮ ይኖር የነበረ ኢትዮጵያዊ ይህንን ትቶ ራሱን መሥዋዕት ለማድረግ ምን ያስገድደው ነበር?
ይህ ሁኔታ እንዴት ይታረማል?
እስከዛሬ ያለውን የሕወሃትን አሠራር ስመለከት፡ ጠባቡና ጎጠኛው ቡድን ትምህርት በማግኘት የሀገራችን ሁኔታ በቀላሉ መለወጡን የሚጠራጠር ስሜት በየቀኑ ይዳስሰኛል። ስዎቹ ሥልጣን በእጃችን ወይንም ማንም አይኖርም ብለው የቆረጡ ይመስላል።
ለዚህ ነው ሁሉም ሃገራችን በስላምና በብልጽግና ለልጆቻችን የምትተላፍበትን መንገድ መቀይስ የሚያስፈልገው። 95 ከመቶ የሚሆነው ሕዝባችን በሁለተኛ ድረጃ ዜግነት፡ እንዲሁም በድምሩ አምስት በመቶ የሚሆኑት የሕወሃት ደጋፊዎችና አጫፋሪዎቻቸው ከሌሎቹ ብሄረስቦች የተውጣጡትን ጭምሮ በሃገራችን ላይ የጫኑት የአፈና ቀነበር አሽቀንጥሮ መጣል አለበት።
ረዳት ካፒቴን ኃይለመድህን በወሰደው እርምጃ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ለሶስት ተከፍለዋል። አንዱ ወገን የሕወሃት ሲሆን፡ እነርሱም እንደጠላት በመፈረጅ፡ “ከሃዲ” በማለት ረዳት ካፒቴኑን በሃገር ጠላትነንት ሲፈርጁት ይሰማሉ። ቤተስቦቹንም እያስቸገሯቸው መሆናቸው ይስማል።
ሁለተኛው ወገን፡ ሁኔታውን ሀገሪቱ ካለችበት የሥልጣን ብልግናና ከላይ እንደተገለእጽው የዘረኝነት ችግር ላይ መሆኗን ተናግረው ለፓይለቱ በጎ ይመኙለታል። ለኢትዮጵያ የነፃነት ሻማ አድርገው ይመስክሩለታል።
ሶስተኛው ወገን የሚጨነቀው፡ ለፓይለቱ ወይንም ሀገሪቱ ስላለችበት ሁኔታ ሳይሆን፡ አየር መንገዳችን ምን ዐይነት የወደፊት ሕልውና ያጋጥመው ይሆን የሚለው ሥጋት የሚያበስለስላቸው ናቸው።
ለማንኛውም፡ ለሕውሃትም ሲሉ ሳይሆን፡ የስዊስ መንግሥት ረዳት ካፒቴን ኃይለመድህን ላይ የረዥም ጊዜ እሥራት እንደሚፈርድበት አልጠራጠርም። አንዳንድ ስዎች ስለኤክስትራዲሽን ሲያወሩ ይስማሉ። በኔ እምነት፡ የሞት ቅጣትን በሃገሯ የሻረች ስዊትዘርላንድ፡ የሞት ቅጣትን የሕግ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የፓለቲካ መሣሪያ አድርጋ ለምትጠቀምበት ኢትዮጵያ ግለስቡን ለሞት አሳልፋ ትሰጠዋለች የሚል ቅንጣት ጥርጥር የለኝም።
ዋናው ጉዳይ ግን፡ ለረዥም ዓመታት ስዊትዘርላንድ ውስጥ እንዲታሰር መደረጉ ለኢትዮጵያውያን የታሪኩ ፋጻሜ ሊሆን አይገባም። በተለይም ይህንን እርምጃ አሁን እንደሚገመተው ፖለቲካ ከሆነ፡ እርሱን ያነሳሳው፡ ኢትዮጵያውያን የእርሱን የትግል አርማ ከፍ አድርገው ሕወሃትን ሊፋለሙትና የሃገር ጥፋት ፓለቲካውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊገድቡት ይገባል። አለዚያማ እርሱን በቃላት ብቻ ማሞካሸቱ ከሌላው ወገን እንደሚመነጨው የጥላቻና ቂም በቀል የተለየ አያደርገውም። የእነርሱ ከሳሾች የሚሉት እኮ፡ ስዎችን አደጋ ላይ ጣልክ አይደለም – ማንም አልተጎዳምና። የእነርሱ ብሽቀት አገዛዛችንን አጋለጠ፤ ሥልጣናችንን ለአደጋ አጋለጠ ነው። የቡድን ጥቅም ቧንቧችንን ሊደፍንብን ሞከረ ነው። ይህ ደግሞ እውነትና ትክክል ነው።
የስሞኑን ጫና ለመቋቋም፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት የመረጠው የአየር መንገዱን የወደፊት ማስብ ሳይሆን፡ የዛሬዋን እሳት ማዳፈን ላይ ነው። ለምሳሌም ያህል ለመጥቀስ፡ አየር መንገዱ ከአውሮፕላን ሻጭ ኩባንያና ከሚዲያ ጋር በመተባበር፡ ለራሱ የአይዞህ መልዕክትና ምሥጋና በማስባሰብ ላይ መሠማራቱ: ከላይ እንዳመለከቱት፡ እነዚህ ስዎች እሳቱ እስኪበላቸውና ሀገራችንንም እስኪጎዳ ድረስ እንደማይቀየሩ የሚያመላክት ነው።
ስሞኑን አየር መንገዱ ብዙ ለቅሶ ደራሽች ነበሩት
ከስሞኑ ለቅሶ ፈጥኖ ደራሽች መካከል ቦይንግ ግንባር ቀደም ነበር። ይዞ የመጣውም ፋና እንደዘገበው the 2013 “GOLD Level Boeing Performance Excellence Award” ነው።
ሌላው ለቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ታቦ ምቤኪ ነፃ ቲኬት: የፕሮቶኮል ወንበር ስጥቶና በግብዣ አምነሽንሾ የኢትዮጵያ አየር መንገድን እንዲጎበኙ ማድረግ ነበር – ጥቅሙና ግንኙነቱ ገሃድ ባይሆንም። ለማንኝውም አድረጉት። ታቦ ምቤኪም የድርጅቱን ከአቪዬሽን ማሰልጠኛ አካዳሚ እና የአለም አቀፍ አየር መንገዶች አውሮፕላን የመገጣጠሚያ ክፍሎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፡ ፕሬዝዳንት ምቤኪ ከጉብኝታቸው በኋላ በሰጡት አስተያዬት የአየር መንገዱ የማሰልጠኛ አካዳሚ አለም አቀፍ የአቪዮሽን ጥራትን ያሟላና በአህጉሪቱ ቀዳሚ የሆነ ተቋም ስለመሆኑ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
Welcoming at Ethiopian for Tabo Embeki (credit: ENA)
Welcoming at Ethiopian for Tabo Embeki (credit: ENA)
ስሞኑን ይህንን ጋጋታ በጽሞና ላዳመጠ ሰው፡ የአየር መንገዱ ዝና እንዳይጎዳ የሚወስድ እርምጃ መሆኑን መገመት ይቻላል።
አየር መንገዱ ባይጎዳ ደስ ይለኛል። ሕይወቱና ነፍሱ ተጠብቆ ከድል ወደ ድል እንዲሄድ በኢትዮጵያዊነቴ እመኛለሁ። ይህ ምኞት ግን ፋይዳ የለውም – የሕወሃት ስዎች ነገ ተመልስው የከአፕርታይድ ሊቀመኳስ Hendrik Frensch Verwoerd Verwoerd ካደረገው ባላነሰ በዘርና ጎጥ ላይ የተመሠረተ ኋላቀር ፖለቲካቸው ነገ ተመልስው የጥቅም ገበያቸውና ሌላውን ማተራመሻቸው ያደርጉታል! የዜጎችን ስሜት ሲጎዱና የሃገርን ስላምና ደህንነት መሠሪ በሆነው ፖለቲካቸው ሲመርዙት: በእነዚህ ድርጊቶቻችው፡ የሕዝቡን ምሬትም እያከረሩ፡ የታሪክ መንገድ አይታውቅምና በጥቂት የታሪክ ተጋባዦች አማካይነት በድንገት የሚቀሰቀሰው እሳት እንዲገላገለን ሁኔታውን እራሳቸው እያመቻቹት ነው!
ሃገራችን ወደፊት እንድትራመድ ከተፈለገ: በኢትዮጵያውያን እኩለነት ላይ የተመሠረተ የሁሉም ኢትዮጵያውያን አሰተዳደር መፈጠር የጊዜው ጥያቄ ነው። ይህ እስካልተቻለ ድረስ፡ በውንብድና በሃገርና ወገን ከሃዲዎች የውሸትና የተንኮል አመራር ላይ የተመሠረተ የሕወሃት አስተዳደርን ዕድሜ ለማሳጠር ብዙ ነገሮች ነገ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ሊፈጸሙ ይችላሉ!
ይህ ደግሞ በሚገባ ተቀነባብሮ ካልተካሄደ፡ ብሽቀቱን በቀላሉ መገላገል ካለመቻሉም በላይ፡ በየቦታው በተበታተነ መንገድ የሚደረገው የአልገዛም ባይነትም በአገር ደኅንነትና ዕድገትም ላይ ጉዳት ይኖረዋል።
ነገር ግን ክትርፍ አሳድጅ የውጭ ኩብንያዎችና የውስጥ አላዛኞች ባለፍ፡ ሌላው ዓለምም አሁን የኢትዮጵያን አፓርታይድ አገዛዝ የሃገሪቱና የቀጠናው የወደፊቱ የችግር ምንጭ መሆኑን በሚገባ የተገነዘቡት ይመስላል!
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11198/

No comments:

Post a Comment