FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Monday, April 28, 2014

በተቃውሞ ድምጾች ላይ ያረፈው ብትር ዕንደምታ

አገዛዙ ሰሞኑን በቅርብ ጊዜ ታሪኩ የከፋ የተለዩ ድምጾችን ያለመታገስ ባህርይ አሳይቷል፡፡ ስድስት የዞን ናይን ብሎገሮችን እና ጋዜጠኛ ተስፋለም ታምራትን በአንድ ወገን፣ የሠማያዊ ፓርቲ አመራሮችና ቀስቃሾችን በሌላ ወገን ሰብስቦ ከማይሞላው ማጎሪያው ከቷቸዋል፡፡ በፕሬስ ላይ የሚደረግ አፈና እና በተቃዋሚዎች ላይ የሚደርስ ውክቢያ ከስርዓቱ የሚጠበቁ ባህርያትነት አልፈው የማንነቱ መገለጫ በመሆናቸው እርምጃው ብዙም ግርምትን አልፈጠረም፡፡

Repression in Ethiopia
ይሁን እንጂ ከ1997ቱ ምርጫ ወዲህ በነፃ ሐሳብ አቀንቃኞችና በተቃዋሚዎች ላይ ይህን መሠል መጠነ-ሰፊ የእስር እርምጃ ሲወሰድ ይህ በከፍተኝነቱ ተጠቃሽ ነው፡፡ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የአገዛዝ ዘመን ይህን መሳይ እርምጃዎች የተለመዱ የነበሩ ቢሆንም የአፈጻጸም ስልታቸው የተለየ መሆኑ ስለገዢው ፓርቲ ወቅታዊ ውስጣዊ የፓወር ዳይናሚክስ ጥቂት የሚያስገነዝበን ነገሮች አሉት፡፡
በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የአገዛዝ ዘመን ይህን መሠል የማወከብ ዘመቻ ለማድረግ ሲወሰን አስቀድሞ ዋነኛው ሰውዬ ወደ ምክር ቤታቸው ሪፖርት በማቅረብ ሰበብ ቀርበው አሊያም ወደ ሚዲያ አውታሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በመስጠት ሰበብ ብቅ ብለው አሰልቺውን “የህገ-መንግስታዊና ኢ-ህገመስታዊነት” ማብራሪያ ካቀረቡ በኋላ መንግስታቸው ስለአንዳንድ ተቃዋሚዎችና የነጻ ሚዲያ አባላት ኢ-ህገመስታዊ እንቅስቃሴ “አንድ ቶን መረጃ” እንዳለውና መንግስት ወደ እርምጃ ከመግባቱ በፊት “የጥፋት ዕጆቻቸውን እንዲሰበስቡ” በሃይለ ቃል የታጀበ ማስጠንቀቂያ ያሰማሉ፡፡ የዚህ ስልት ዋነኛ ዓላማ ህዝቡንና ዓለማቀፍ ማኅበረሰቡን ለቀጣዩ እርምጃ ማዘጋጀት ነው፡፡ በሌላ በኩልም በማስጠንቀቂያው ተደናግጦ ስደትን ወይም አፉን ለጉሞ መቀመጥን ምርጫው የሚያደርግ ተቃዋሚ ወይም የነፃ ፕሬስ አባል ካለ ከጨዋታው ሜዳ ገልል እንዲል ማድረግም በሁለተኛ ደረጃ ዓላማነት ይቀመጣል፡፡
የሰሞኑ ፀረ-ተቃዋሚ እና ነፃ ሐሳብ ዘመቻ ግን በአፈፀፀም ስልቱ ለየት ይላል፡፡ ከእርምጃው ሁለት ቀናት በፊት በምክር ቤታቸው የተገኙት ጠ/ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በወቅቱ ያቀረቡት ሪፖርት “ከወትሮው የተቃዋሚዎች ውንጀላ ነፃ ስለመሆኑ” ከብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ ከተከበሩ አቶ ግርማ ሠይፉ ሙገሳ የተቸረው ነበር፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ አንዳችም አሁን የተወሰደውን እርምጃ መምጣት የሚያመላክት ስሜታዊም ሆነ ቃላዊ ምልክት አላሳዩም፡፡
ከጠ/ሚኒስትሩ ሪፖርት ሁለት ቀናት በኋላ ግን የሆነው ሁሉ ሆነ፡፡ ስርዓቱ እጅግ የጠበበውን የፖለቲካም ሆነ የሚዲያ ምህዳር የማስፋት አንዳችም ፍላጎትም ሆነ ተነሳሽነት እንደሌለው በአደባባይ አሳየ፡፡
እዚህ ላይ የሚነሳው ዋነኛ ጥያቄ ግን ከወትሮው በተለየ ጠ/ሚኒስትሩ በንግግራቸው መጪውን እርምጃ አመላካች አንዳችም ፍንጭ እንዴት ሳያሳዩ ቀሩ? የሚለው ነው፡፡ አንደኛው ምክንያት ሊሆን የሚችለው የስልት ለውጥ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ ወቅት ይህን መሳይ የስልት ለውጥ ለማድረግ የሚያስፈልግበት አንዳችም ምክንያት መመልከት አይቻልም፡፡
ይልቁንም ሚዛን የሚደፋው፣ ጠ/ሚኒስትሩ ይህን መሳይ ዋነኛ ውሳኔ ከሚያሳልፈው እውነተኛው (De facto) የአገዛዙ የአመራር ክበብ (leadership circle) ውጪ መሆናቸውን ነው፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ከቀዳሚያቸው በተለየ ከመጋረጃ ጀርባ ዋነኛ ውሳኔ ለሚያስተላልፈው የአመራር ክበብ ውሳኔዎች ቅቡልነት ከማስገኘትና ውጫዊ የስልጣን ስርጭት ምስል ከመፍጠር ባሻገር ሁነኛ ውሳኔዎችን በግላቸው፣ አሊያም ከሌሎች ጋር ለማሳለፍ የማይችሉ ከመሆናቸውም ባሻገር በአገዛዙ ጠረጴዛ ላይ ያሉትን አጀንዳዎች ምንነት በተመለከተም ያላቸው ግንዛቤ አናሳ መሆኑን ክስተቱ አስገንዝቦን አልፏል፡፡
http://ecadforum.com/Amharic/archives/12013/

ከኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ(ኢጋመ) የተሰጠ መግለጫ፣ የጋዜጠኞቹና የአክቲቪስቶቹ እስር አሳሳቢ ነው፡

ትላንት ሚያዝያ 17 2006 አመሻሽ ላይ ዞን 9 በተሰኘ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ በሳል ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትችቶችን በማቅረብ ከሚታወቁት ፀኀፍት መሀከል 7 ቱ (ማህሌት ፋንታሁን በፍቃዱ ሀይሉ 

Ethiopians journalists forumናትናኤል ፈለቀ ዘላለም ክብረት አጥናፍ ብርሀነ አቤል ዋበላ ኤዶም ካሳዬ) እና የአዲስ ነገር ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ይታወቃል፡፡ ግለሰቦቹ በተለያየ ቦታ በየስራ ገበታቸዉ ላይ እያሉ ሁሉም በተመሳሳይ ሰዓት በፀጥታ ሀይሎች ተይዘዉ ማዕከላዊ ምርመራ ማዕከል ታስረዉ የሚገኙ ሲሆን፤ የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት እስሩ በደንብ የታሰበበት ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ታሳሪዎቹ ታሰሩ ከተባለበት ሰዓትና ደቂቃ ጀምሮ የሚገኙበትን አጠቃላይ ሁኔታ ለማጣራት አየሰራ ሲሆን ፤ እስካሁን በሰበሰበዉ መረጃ መሰረት ልጆቹን ለእስር የሚያበቃ ምን አይነት ማስረጃ እንደተገኘባቸው ለማወቅ አልቻለም፡፡
ሆኖም ግን ለእስር ከመዳረጋቸው በፊት ከመንግስት ሲርስባቸዉ በነበረዉ ህገወጥ ድርጊቶች ምክንያት ለረጅም ጊዜ ስራቸዉን ካቋረጡ በኋላ በቅርቡ ወደ ስራ መመለሳቸዉን ይፋ አድርገው እንደነበር ከድረገጻቸው ላይ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ ጉዳይ እስሩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎብናል፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ መንግስት ታሳሪዎቹን ለማሰር ያበቃዉ ተጨባጭ ማስረጃ ካለ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ፤ ያ ካልሆነ ግን እስረኞቹን በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ እናሳስባለን፡፡
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
http://ecadforum.com/Amharic/archives/12016/

ሠማያዊ ፓርቲ የነፃነት ትግልና የሃበሻ ጀብዱ

ዳኛቸው ቢያድግልኝ

በቅርቡ የሴቶችን ቀን አስመልክቶ በተደረገ የሩጫ ዝግጅት ወቅት የሚኒሊክና የጣይቱ ልጆች ነን ያሉ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች “አትለያዩን! አትከፋፍሉን! ነፃነት እንሻለን! ለድሃው ይታሰብለት! ኑሮ ከበደን! ውሃ ጠማን! መብራት ናፈቀን!” በማለት በጣም ሰብዓዊና እናታዊ ጥሪ ጮክ ብለው አሰምተው ነበር። ይህም መልካም ድርጊታቸው ለፍትህና ለአንድነት የሚደረግ ህዝባዊ ጥሪ በሚያስበርግጋቸው የወያኔ ባለስልጣናት ሁከት ፈጠራ ተብሎ ተወነጀሉ። ፕሮፌሰር አልማርያም በተቆጣው ብዕራቸው

… ያገሬ ወይዛዝርቶች በምህረት አልባ ጨካኞች ሲንገላቱና ሲወገሩ ከዳር ቆሜ ማየትን ህሊናዬ ፈጽሞ አይፈቅድልኝም። ይልቁንም የእንግልታቸው ምክንያት ሰብዓዊ በሆነው መብታቸው ድምፃቸውን ስላሰሙ በመሆኑ የነሱና የመሰሎቻቸውን ጥሪ በዚህም ሳቢያ የሚደርስባቸውን አበሳ ሁሉ ለአለም አሳውቅ ዘንድ ድምጼን ከፍ አድርጌ እጮሃለሁ…

ብለው ነበር። ከርሳቸው ድምጽ ጋር በማበር የሚያስተጋቡ ድምጾች ይኖሩ ዘንድ እውነት ነውና የኔንም ድርሻ እነሆ እጮሃለሁ። ጩሀቴም ቀደም ሲል በግፍ ለታጎሩ የህሊና እስረኞችና ሰሞኑን ለታፈሱት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና ደጋፊዎች አንዲሁም ለጎበዞቹ የዞን ዘጠኝ የሕዝብ አፈቀላጤዎችም (ብሎገሮችም) ነጻነት ያለኝ ጽኑ ፍላጎት መገለጫ ነው።
ሁከት ማለት የሌሎችን ሰላም ማደፍረስ፥ አምባጓሮና ጸብ ማንሳትና ማነሳሳት፥ የንብረት ጥፋትና በሰዎች ላይ አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳትን ማስከተል ነው። እኒህ ወጣት ሴቶች ግን ከዚህ በተቃራኒው የተንገላቱት ሰላም አንዳይደፈርስና ህዝብ እንዳይጎዳ በስልጣን ላይ ያሉት መንግስታዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ ሰላማዊ ጥሪ ነበር ያቀረቡት። የሀሰት ፕሮፖጋንዳው ሰለባ ያልሆነ በሙሉ ወጣቶቹ በአንድነትና በፍትህ የጸናች ሀገር ለመረከብ ከዚህ የበለጠ ቢያደርጉም ተገቢ ነው የሚል ይመስለኛል። የነርሱ አሳሪዎች በነርሱ እድሜ ጠመንጃ አንስተው መጥፎ ነው ብለው የፈረጁትን መንግስት ለመዋጋት ጫካ መግባታቸውን አለመርሳት ብቻ ሳይሆን እንደትልቅ ገድል በየመድረኩና በየመጽሀፉ ሲናገሩና ሲያስነግሩ እንሰማለን። ታዲያ የዛሬው ትውልድ ያውም እንደነሱ ሰው ለመግደል ጠብመንጃ ሳያነሱ ፍትህ አይጉዋደል ብለው በሰላም መጠየቃቸው እንዴት መጥፎ ሁኖ ነው ለእስርና እንግልት የሚዳርጋቸው? ማሰርንና አፈናን እንደ የስልጣን ዘመን ማራዘሚያ አማራጭ አድርጎ መውሰድ ከሚያስብ አእምሮ ሳይሆን በፍርሃት ከተዋጠና ለውጥ አይቀሬ መሆኑን መቀበል ካቃተው ደካማ ጭንቅላት የሚመጣ ነው። በአንጻሩም ነገ የነርሱ የሆነው ወጣቶች በፍርሀት ተገንዘው አረመኔዎች ሀገራቸውንና ተስፋቸውን ሲያጠፉባቸው በዝምታ ሊያዩ አይቻላቸውም።
ለዚህም ነው በወጣቶቹ የሠማያዊ ፓርቲ መሪዎችና ደጋፊዎች ላይ ያለኝን ጽኑ እምነት መግለጽ የምሻው። የወጣቶች መነሳሳት ለሁሉም ወገን ብርታትን የሚሰጥ ነው። የለገመ፣ የሰነፈና ተስፋ የቆረጠ ወጣት የሞላበት ሃገር ሕዝብ መቃብር አፋፍ እንደቆመ ለቀስተኛ ነው። ለቀስተኛ መቼም ቢሆን ስለሚቀብረው ሰው ከሚሰማው ሀዘን ባሻገር እርሱም ነገ ሙዋች መሆኑን እያሰበ ሙዋቹን አፈር እራሱን ትካዜ አልብሶ ተስፋን ሳይሆን ፍርሀትን ሰንቆ ይመለሳል። ሀገር ተስፋ በቆረጠና ሽንፈትን በጸጋ በተቀበለ ወጣት ከተሞላች ቀብርዋ ተቃረበ ማለት ነው። ስለዚህ የሀገራችን ወጣቶች ተስፋ የሰነቁ፣ የበረቱና በእውቀትና ስነምግባር የታነጹ እንዲሆኑ ሁላችንም የየአቅማችንን ማድረግ ይኖርብናል። የሀገራችን ሰዎች “እናት የሞተች ቀን በሀገር ይለቀሳል… ወንድም የሞተ እንደሁ በሀገር ይለቀሳል…. ሀገር የሞተ እንደሁ ወዴት ይደረሳል?” ይሉ የነበረው ያለምክንያት አልነበረም። እናም የዛሬን ወጣቶች ድርጊት ከቀድሞው የሃበሻ ጀብዱ (የሀበሻ ጀብዱ ከሚለው መጽሀፍ) ጋር ጣምራ ቅኝት ላደርግበትና ወጣቶችን ላደንቅበት መርጫለሁ።
ስለምን የሃበሻ ጀብዱን እንደመረጥኩ ግን እመለስበታለሁ። የጣልያኑም ወረራ ሆነ የባንዳ መራሹ ወያኔ አገዛዝ ለኢትዮጵያ የሚበጅ አይደለምና ሀገሪቱን ወደተሻለ መንገድ ለመውሰድ የሚደርገው ጥረት ኢትዮጵያውያን ነን ለሚሉ ሁሉ የህልውናና የነፃነት ፍልሚያ መሆኑ ግልጽ ሊሆን ይገባል። የሠማያዊ ፓርቲና የትግራይ ተገንጣይ ነን የሚሉትን አቅም በመፈተሽ መንደርደርያውን ማጎልበት ያስፈልግ ይሆናል። ይህም መድፍ ተኳሽና በአውሮፕላን መርዝ የሚርጭን የግራዚያኒን ጦርና ነጠላ ለባሽ ባለጎራዴ እግረኛን እነደማወዳደር ማለት ነው። ምንና ምን ታወዳድራለህ የሚሉ እንዲህ ብለው ሊሞግቱኝ ይችላሉ።
ሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች፣ ተገንጣዮቹ እድሜ ጠገቦች ፤ ሰማያዊ ፓርቲ ባዶ ኪስ፣ መንግስት ነን የሚሉት ደግሞ የሀገሪቱን ሃብት የግላቸው ያደርጉ ዲታዎች አዎ ምንና ምን? ሰማያዊ ፓርቲ ብእርና ወረቀት ፣ ወያኔዎች ባለታንክ፣ አውሮፕላን መድፍና መትረየስ ታጣቂዎች። እናም የማይቻል የሚመስለውን ይቻላል የሚሉ ወጣቶችና ሰው እንደዘበት መፍጨት የማይገዳቸው ‘ተራራ አንቀጥቃጮች’ እንደምን አድርገው መጋጠም ይችላሉ? በዚህ አይነት ንፅፅር ተስፋ የቆረጡት ወገኖች “ይቻላል!” ብለው የተነሳሱትን ወጣቶች “እንዲያው አርፈው ቢቀመጡ ነው የሚሻለው። በአጉል ወኔ ተነሳስተው ማለቅ ብቻ ሳይሆን እኛንም ያስጨርሳሉ። ጊዜው አሁን አይደለም” የሚል ምክር ቢጤ ሲሰጡ ይሰማሉ። የፖለቲካ መሪና ጠቢብ ነን የሚሉም “ለአሁኑ ወያኔ ስልጣን ላይ ቢቆይ ይሻላል” ሲሉ ተደምጠዋል አሉ።
እውነትም ብቸኛ ሃይል መመዘኛ ሁኖ የሚታየው የጠብመንጃው ቁጥርና የመግደል አቅም ከሆነ ያስፈራል። እውነታው ግን የሀይል ምንጭ የጠብመንጃና የጦር ጋጋታ ብቻ አይደለም። ከጠብመንጃ በላይ የዘላቂ ሀይል መሰረቱና የመጨረሻ ድል አጎናጻፊው እውነትና ፍትሀዊ ምክንያት ነውና።
ጊዜው ዛሬ አይደለም የሚሉትም መካሪዎች ጊዜው መቼ እንደሚመጣ ቢያሳውቁንም ደግ ነበር። ኬይንስ የሚባለው የምጣኔ ሀብት ምሁር እንዳለው “ከረጅም ጊዜ በሁዋላ ሁላችንም ሙዋች ነን።” ስለዚህም የዛሬውን ነጻነታችንን ተነፍገን በነገ ተስፋ ብቻ ተሸንግለን ግፍን በፀጋ እንድንቀበል መመከራችን ደግም አይደለም። ነፃነት ተነፍጎ፣ ፍትህን አጥቶ፣ በደልን ተሸክሞ ተስፋ ቢስም ሆኖ መኖር አይቻልም። በደል ሲበዛ በቃኝ ማለት የሰው ልጅ ትክክለኛ ባህርይ ነው። ቢሆንም በርካቶች “እግዜር ያመጣውን እግዜር እስኪመልሰው” ሲሉ ይደመጣል። እግዜር የሌለውን አመል አውጥቶ ጥላቻ ቢለማመድ እንኳን እነዚህ አረመኔ ወንበዴዎች ለዚህን ያክል ጊዜ አናታችን ላይ ሁነው እንዲጨፈጭፉን አያዝብንም።
ፍትህና ነጻነት የሚገኘው በፀሎትና ልመና ብቻ ቢሆንማ ኖሮ አውሮፓውያን ሰሜን አሜሪካ ዘልቀው ሀገሬውን በበሽታና ረሀብ ሲጨፈጭፉት፣ እግዜሩ ዝም አይልም ነበር። አዎን እሱ መሬት ወርዶ ፍርድ የሚሰጥ ቢሆን አውሮፓውያን ጥቁር አፍሪካን ባርያ አድርገው በገዛ ምድሩ ላይ የግፍ ግፍ እየፈጸሙበት የእግዜርን ስም እየጠሩ መስቀልና መጽሀፍ ቅዱስ ይዘው ሲያስገበሩት ዝም ባላለ ነበር። ስለዚህም ነው ለነጻነት ሲባል ታንኩንም መትረየሱንም እንደነ አቡነ ጴጥሮስ መጋፈጥ የግድ የሚሆነው። ጸሎት ለብርታት ጥሩ ነውና ባይሆን እመብርሃን ለልጅሽ በደሌን እንደኔ ሆነሽ ንገሪልኝ ማለት፣ አላህንም ልጆችህ መከራችንን ከትከሻችን አሽቀንጥረን እንጥል ዘንድ ጉልበትና ብልሃት ጀባ በለን እያሉ መለማመን ጥሩ የሚሆነው። ግን ለብቻው በቂ አይደለምና ወጣቶች እንደ የግል ሀይማኖታቸው እያመለኩ እንደ እምነታቸው በጋራ ለነፃነት መታገላቸው የሚያበረታታንም ለዚህ ነው።
አሁን የሃበሻ ጀብዱን ለምን እንደጻፍኩ ላስረዳ አዎን የጣልያን ጀነራሎችን ሹምባሾችና አስካሪዎችን አስታውሼ መሆን አለበት። ታንኩንም፣ አውሮፕላኑንም መድፉንም መትረየሱንም ጭምር። የባንዳ ውርንጭሎችን፣ ልጆችና የልጅ ልጆችንም እንዲሁ አስቤያቸው ነው።
እነዚህ ነጠላ ላባሽ ባዶ እግር ተጓዥ ኢትዮጵያውያን በጣም የሚገርሙ ነበሩ። ኩራታቸውና በራሳቸው የመተማመን አቅማቸው ለውድድር አይመችም። እንደ ሀይል አሰላለፍ ቢሆን ከጣልያን ጋር ደፍሮ መጋጠም ከሞኝነት አይቆጠርም ትላላችሁ? ካላቸው የመሳርያና የወታደር ብዛት፣ ሰልጥኛለሁ የሚለው የነጩ ዓለም ያለው ጉልበትና ስልጣኔን የሚያውቅ ሰው በባዶ እግሩ ታንክ መግጠም ሞኝነት ነው ቢባል ማመን ብዙም ላይከብድ ይችላል። ለነርሱ ማን አልተንበረከከምና? ማንስ ቅኝ ግዛት አልሆነምና! ግን ኢትዮጵያ ምድር ላይ ታንክ በጎራዴ ድል ሆነ። አንዴ ቢሆን እድል እንለዋለን ሁለቴ ሶስቴም ሆነ። ሁለቴም ሶስቴም ነጠላ ለባሽ በባዶ እግር የሚጓዝ እግረኛና ቆመህ ጠብቀኝ ምንሽር ባለአውሮፕላንና ባለታንኩን ድል ነሱት። ግን ይህ አሸናፊነት እውን የሆነው ትክክለኛ ስነልቦና፣ አልገዛም አልንበረከክም የሚል እምቢ ባይነት ስለነበረ ነው። ለነፃነቱ ቀናዒ መሆን ከዚያም በላይ ወንድም የወንድሙ ተበቃይ መሆኑን ነበር። አይዞህ ባይና አጋር አብራ በረሃ ለበረሃ የምትጓዝ ጓድም ነበረችው። እሷን ማሳፈር ለባርነትም አሳልፎ ከመስጠት ሞቱን ይመኝ ስለነበር ነው። ሴቲቱም ብትሆን እርሱ ለነጻነቱ ሞቶ ግን የርሱን የጀግናውን ስም ይዘው ትውልድ የሚቀጥሉት ልጆቻቸው በነፃነት ቢኖሩ ምርጫዋ ስለነበረ ነው። የሴቶቹ ጀግንነትና ድፍረት ለወንዶቹም መነሳሳትና መበረታት ምክንያት ይሆናቸው ስለነበረ ነው የሚል ሃሳብን ነበር የሃበሻ ጀብዱን የጻፈው ፈረንጅ አዶልፍ ፓርለሳክ የዘገበው። “እነዚህ ነጠላ ለባሽ እግረኞች ይላል አዶልፍ ፓርለሳክ በጠላት መትረየስ አስሩ ሲወድቁ ሃያው ወደፊት ይገፋሉ ሃያው ሲወድቁ ሃምሳው ወደፊት ይገፋሉ ለሞት እየተጋፉ ወደፊት ይገሰግሳሉ እናም ያሸንፋሉ” ብሎ ሺህ ጊዜ አድናቆቱን መሰከረላቸው። እርግጥም ፍርሃቱን ያሸነፈ ጀግና ነው! እንዲያውም ነገስታቱ ወይም መሪዎቹ እየገቷቸው እንጂ ጣልያንን ድባቅ እየመጡ ቀይ ባህር ሊከቱ የሚችሉ ጎበዞች እንደሆኑ ሲጽፍ ገድላቸው በዐይነህሊናው የሚታየው ይመስላል። ታድያ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ምን አገናኘው ሰማያዊ ሰላማዊ ትግል ነው ታንክና ጎራዴን ምን አገናኘው? ለሚሉ በሚከተለው አስተያየት የተነሳሁበትን ለመደምደም እሞክራለሁ።
ልክ ይህንን ታሪክ አስቀምጠው የነገሯቸው አዛውንቶች ያሉ ይመስል ባዶ እጃቸውን ነፃነት ወይም ሞት ያሉ ቆራጦች የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ጀግነው ተነስተዋል። ይህንን መነሳሳት ደግሞ በሚገባ አሳይተዋል። አምስት ሲታገትባቸው አስራ አምስት ሆነው ይተማሉ፣ አስራ አምስት ቢታገት አምሳ አምስት ይሆናሉ። ስለዚህ የነጻነት ፍላጎታቸው ካልሞተ ለነፃነት የሚያደርጉት ትግል እንደማይቆም ግልጽ ነው። አዎ በጎበዝ አለቃ ተደራጅቶ በባላባት በባላባት ተጠራርቶ የወጣው ጀግና እንደዚያ ነበር ነፃነትን የተቀዳጀው። ሰማያዊ ፓርቲም መሪው ሲታሰር ሽባ የሚሆን ጥቂት አባላት ቢታገቱ የሚሽመደመድ እንዳይሆን ሆኖ የተደራጀ ይመስላል። እንደዚያ ሆኖ ሊጠናከርም ይገባዋል። ወጣት ወጣት የሚሸት እንቅስቃሴ ተስፋ ይሰጣል። ነቅተው ሌሎችንም የሚያነቁ፣ ጎብዘው ሌሎቸንም የሚያበረታቱ በዘርፈ ብዙው ትግል ውስጥ ብዙሃኑ እንዲሳተፉ ያበረታታሉ። ለዚህም ነው ታስረው ታስረው የማያልቁ… ከጎንደር መልስ አዲሳ አበባ፣ ከአዲስ አዋሳ እያሉ ሺህ ሚሊየን ወጣቶች ለነፃነትና ለክብር ሲቆሙ የምናየው። ያኔ በጠላት ወረራ ጊዜ አቢቹ የሚባል ለጋ ወጣት ነበር በወንድሞቹ ሞት ማግስት ጨርቄን ማቄን የማይሉ 200 ጎበዞች ብቻ ስጡኝ በማለት የራሱን ጦር ሊመራ ወሰነ። የርሱ የነበሩ በሬዎችን አሳርዶ የወንድሞቹን ተዝካር አወጣና ወደ ደፈጣ ውጊያም ገባ። ያ ወጣት ለጣልያን ያደሩ የትግራይ ሽፍቶችን ጨምሮ ጣልያኖችን አርበደበዳቸው። የ16 አመት ወጣት ምንም የጦር ስልጠና ያልነበረው ጀግና ሰልጥነናል ያሉትን መግቢያ መውጫ አሳጣቸው። ምንም እንኳ ከጀግኖቹ ተርታ ስሙን ሊናገሩ ያልፈለጉ ቢኖርም እንኳ ዛሬ ታሪኩ ታውቆ ወደፊትም ሲነገርለት ይኖራል። የዛሬዎቹ ወጣቶች በውል የሚያውቁት ወያኔን ብቻ ነው። ወያኔ ጸረ ኢትዮጵያ ፕሮፓጋንዳውን በሚነዛበት ሀገር ነው ያደጉት። ይሁን እንጂ የማይሞተው ኢትዮጵያዊነትና የነጻነት ጥያቄ አነሳስቷቸዋል። ዛሬም ብዙ አቢቹዎች ይኖሩናልና የወጣቶች መነሳሳት የነፃነት ብስራት ነው ስንል ከጎናችሁ አለን እያልናቸውም ነው። ሞት እስርና እንግልት ሌሎችን ወደፊት ያመጣል። ትግሉ ስልጣን መያዝ አይደለም ስልጣን በሰላማዊ መንገድ የሚያዝበትን የእኩልነት የነፃነት ብስራት የሚሰበክበትንና በተግባርም የሚረጋገጥበትን ጎዳና መቀየስ ነውና ለዚህ ቅዱስ ዓላማ አሁን ተመሳሳይ ዓላማ አለን የሚሉ በተለያየ የትግል ስልት ግን ለነፃነት ለሚታገሉ ሁሉ ብርታትና መነሳሳትን ይፈጥራሉ። ኢትዮጵያ ከጎጠኛ ወራሪዎችና አገር አፍራሾች ነፃ እስክትሆን ድረስ ትግሉ ይቀጥላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ።
biyadegelegne@hotmail.com
http://ecadforum.com/Amharic/archives/12046/

Thursday, April 24, 2014

ከሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለንግዱ ማህበረሰብ የተላለፈ ጥሪ!

በንግዱ ዓለም ለተሰማራችሁት ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤

በአሁኑ ወቅት ስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ ሁሉንም የኢኮኖሚ መስክ ጠቅልሎ በመያዙ በአገሪቱ ኢኮኖሚ የሚገባችሁን አስተዋጽኦ እያደረጋችሁ እንዳልሆነ እንረዳለን፡፡ ለይስሙላ ብቻ ነጻ ገበያን ‹‹ፈቅጃለሁ!›› የሚለው ገዥው ፓርቲ ኢኮኖሚውን በራሱ ድርጅቶች ተቆጣጥሮ ለስልጣን መቆያ መሳሪያ አድርጎታል፡፡ የመንግስት ድርጅት የሚባሉትም ቢሆኑ ኢኮኖሚው ጠቅልለው ለተመሳሳይ አላማ መሳሪያ በመሆን ላይ ናቸው፡፡ ይህን ተከትሎም አገራችን ነጻ ገበያና የግል ባለሃብቶች የተዳከሙባት ግንባር ቀደም አገር ሆናለች፡፡A call from Semayawi party April 2014
ይህ በአንድ ኃይል የተጠቀለለ የኢኮኖሚ ስርዓት እናንተ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በነጻነት እንዳትሰሩ ከማድረጉም ባሻገር ህዝባችን በኑሮ ውድነት እንዲታመስ አንድ ምክንያት ሆኗል፡፡ በተለይ በቅርብ አመታት ከስርዓቱ ጋር አብሮ መሄድ ያልቻለውን የንግዱን ማህበረሰብ ለስርዓቱ እጁን እንዲሰጥ ለማድረግ እንዲመች ከሚሰራው ስራ ጋር የማይመጣጠን ግብር በመጫን ላይ መሆኑን ለመረዳት ችለናል፡፡ ሱቅ በደረቴ የሚሰሩ፤ እንጀራ ጋግረው የሚሸጡ እናቶች፤ የጀበና ቡናና ሌሎቹንም አነስተኛ ስራዎች የሚሰሩ ወጣት ኢትዮጵያውያን ሳይቀሩ የማይችሉት ግብር ተጭኖባቸዋል፡፡ የንግድ ፈቃድ እድሳት፤ የመስሪያ ቦታና ሌሎችም ነጋዴው በኢትዮጵያዊነቱና ለህዝብ በሚሰጠው ጥቅም ሊያገኛቸው የሚገባቸው መብቶች በሙስና ለፓርቲ ባለው ቅርበትና በሌሎች በዚህ ስርዓት በተሳሳቱ አሰራሮች የንግዱን ማህበረሰብ አስረው ይዘውታል፡፡
ነጋዴውን የሚፈራው ህወሓት/ኢህአዴግ የራሱን ነጋዴዎች ደጋፊ ማህበር አቋቁሟል፡፡ ይህም ነጋዴውን በነጻነት ከመስራት ይልቅ የኢሕአዲግ ተለጣፊ እንዲሆን ካለው ፍላጎት መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ በአንጻሩ ሌሎች የንግዱ ማህበረሰብ አካላት የራሳቸውን ነጻ የነጋዴ ማህበር ሲያቋቁሙ አይታዩም፡፡ የመስሪያ ቦታ፤ ግብር እና ሌሎችም ነጋዴው የሚጣልበት ግዴታና የሚገባው መብት ላይ ያለውን ኢፍትሃዊነት ለማስተካከል ጥረት የሚያደርግ የንግዱ ማህበረሰብ አካል አይታይም፡፡
ህወሓት/ኢህአዴግ በሁሉም የኢኮኖሚ መስኮች ሊሳካለት ባለመቻሉ እንዲሁም ነጻ ገበያ ተግባራዊ እንዲሆን አለመፍቀዱ የአገራችን ኢኮኖሚ ከመቸውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ ተባብሷል፡፡ በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያውያን በሰፊው የሚያመርቷቸው ምርቶችም ጭምር ለህዝብ የሚደፈሩ አልሆኑም፡፡ የእነዚህ ምርቶች እጥረት ሲከሰት ጥያቄውን ከእሱ ትከሻ ለማውረድ የሚከሰው የንግዱን ማህበረሰብ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ ‹‹ዘይት የደበቀ፣ ስኳር ያልሸጠ፣…›› እየተባለ በሰበብ አስባቡ የስርዓቱ ግፍ ገፈት ቀማሾች ሆናችኋል፡፡
አገራችን ኢትዮጵያ ድሃ ከሚባሉት አገራት ቀዳሚውን ተርታ መያዟን ለንግዱ ማህበረሰብ ማስረዳት ለቀባሪው አረዱት ይሆናል፡፡ የንግዱ ማህበረሰብ ይህን መሰረታዊ ችግር ከስር ከመሰረቱ ለመፍታት በሚደረገው ትግል የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ ባለመሆኑ አገሪቱን ከገባችበት አረንቋ ለማውጣት የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት መጠቆም ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ይህን ለማድረግም መጀመሪያ የራሱን ነጻነት በማስከበር፣ በመደራጀት የንግዱን ማህበረሰብና ኢትዮጵያውያን አቅርቦቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያገኙበትን አጋጣሚ መፍጠር አስፈላጊ ነው፡፡ በተለይ በተለይ የራሱን የፖሊሲ ችግር ተለጣፊ ባልሆኑት የንግዱ ማህበረሰብ አካላት ላይ ለማላከክ የማይታክተውን የገዥውን ፓርቲ ተግባር በማጋለጥ እና ከህዝብ ጎን በመቆም ግዴታችሁን መወጣት ይገባችኋል እንላለን፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19/2006 ዓ.ም ጃን ሜዳ ‹‹የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልሳለን!›› በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡ መብታችሁን የተነጠቃችሁት የንግዱ ማህበረሰብ አካላትም የራሳችሁንና የቀሪ ኢትዮጵያውያንን መብት ለማስመለስ በሰልፉ ቀዳሚ ተሳታፊ እንድትሆኑ ፓርቲያችን ጥሪውን አቅርቦላችኋል፡፡
ኑ ራሳችንን ነጻ በማውጣት የአገራችንን እጣ ፈንታ እንወስን!
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11933/

አስፈላጊው ለውጥ ፣ መጭው ምርጫና የተቃዋሚዎች “መሳተፍ” ጉዳይ

(ናትናኤል ካብትይመር ኖርዌይ)




ethiopian_election_ballot_boxየሰው ልጅ ግላዊና ማህበራዊ ህይወቱን ለማሻሻል እንዲሁም የለት ተለት ህይወቱን የተሻለ ለማድረግ በአካባቢው ወይም በሚኖርበት ሃገር ያለውን አካባቢያዊና መንግስታዊ ስርዓት ጤናማ መሆኑ ግድ ነው። የማህበረሰቡም የለት ተለት ህይወት ከግዜ ወደ ግዜ አስቸጋሪ እየሆነ ሲሄድ የዛ ማህበረሰብ መንግስት ወይም አገዛዝ መቀየሩ አንደኛው መፍትሄ ነው። እንደሁለተኛ አማራጭ መፍትሄ  የሚወሰደው ደግሞ የነበረውን አገዛዝ ለአነስተኛና ከፍተኛ ለውጦች ካለው ምቹነት አንፃር ተመዝኖ አስፈላጊ የሚባሉ የፖሊሲና የመንግስታዊ አወቃቀር ለውጦችን መተግበር ሲሆን ይህም በሌሎች ሃገራት ተሞክሮ ጥሩ ሊባል የሚችል ለውጥ ሲያስገኝ ተስተውሏል።
ነገር ግን ወደ ሃገራችን መንግስት ስንመጣ ከበድ ያሉ የማስተካከያ መፍትሄዎችን ቀርቶ እጅግ አነስተኛ የሚባሉ የማህበረሰብ የመብት ጥያቄዎችን እንኳን በሃይል በመጨፍለቅ ሃገራዊና ማህበረሰባዊ ችግሮችን ይበልጡን እያወሳሰበ ይገኛል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ የአለማችን ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ አቅጣጫ ዝንባሌው ከታችኛ ረድፍ ላይ ያሉትን ሃገራት የወደፊት እጣ ፈንታ እጅግ የከፋ ሊሆን እንደሚችል የሚያሳይ እንድምታ እየተስተዋለበት ነው። ባለፉት ግዜያት በመጨረሻው ረድፍ ላይ ያሉ ሃገራት “ከድህነት ወለል በታች ያሉ ሃገራት” ተብለውም ቢሆን እንደሃገር ይመደቡ ነበር። ነገር ግን ከግዜ ወደ ግዜ ይህ እየተቀየረ እየሄደ ይገኛል። “ከድህነት ወለል በታች ያሉ ሃገራት” ከሚባሉት ውስጥ የተወሰኑ ሃገራት (Failed States) የሚባለው ምድብ ውስጥ እየገቡ ነው። ይህ ማለት በቀላል ማጠቃለያ በሚመጡት ግዜያት እንደ ከዚህ ቀደሙ ደሃ ሃገር ሆኖ መኖር ወደ የማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ገብቷል ማለት ነው። ይህ ደግሞ ከመቼውም ግዜ በላይ የለውጥን አፋጣኝ አስፈላጊነት የሚያመላክት ነው።
ከዚህ ቀደም በአለማችን ታሪክ ለውጥ በተለያዩ መንገዶች ሲካሄድ አስተውለናል ፡ ለአብነት ለመጥቀስም ያህል የነበሩትን ስርዓቶች ጭርሱን በማጥፋት ሌላ ስርዓት መገንባት አንዱ ሲሆን ሌላው ደግሞ በነበረው ስርዓት ላይ ግጭቶችንና የፖለቲካ አመለካከት ልዩነቶችን አቻችሎ ህዝብ በምርጫ መሪዎቹን የሚመርጥበትን መንገድ ማመቻቸት ነው። በወያኔ ኢህአዴግ  ስርዓት ህዝባችን በትዕግስትና በጨዋነት የለውጥን አስፈላጊነት አምኖ ፣ የምርጫን ምንነት ተረድቶ ፣ ይሆኑኛል ያላቸውን መሪዎቹን በተስፋ ሲመርጥ በምርጫ 97 አይተናል። ነገር ግን አሁንም ባባሰ መልኩ የህዝብ መብትና ፍላጎት ታፍኖ ህዝብና ሃገር በጉልበተኞች አምባገነናዊ ጭቆና ስር እየማቀቁ ይገኛሉ።
የወያኔ መንግስት ምርጫውን ብቻውን ሊያረገው አይፈልግም የተወሰኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለይስሙላና ለውጭ ታዛቢዎች ማታለያ እንደሚጠቀመው የሚጠበቅ የተለመደ አካሄዱ ነው። የወያኔ መንግስት ለሃገር እድገትና ለህዝብ መብት መከበር ለሚጥሩ አማራጭ ሃይሎች ህዝብ የሰጣቸውንና የሚገባቸውን የህዝብ ውክልና መቀመጫ በጉልበት እንደነጠቃቸውም የከዚህ ቀደም ተሞክሮን ማስታወስ በቂ ነው። ታዲያ በዚህ መሰል የይስሙላ ምርጫ መሳተፍ ፋይዳው ምንድነው።
መጭው ምርጫን መሳተፍ ማለት ለወያኔ የኢትዮጲያን ህዝብ በረሀብ ፣ በጥማት ፣ በእርዛትና በዲሞክራሲ እጦት አሰቃይ ብሎ ፍቃድ እንደመስጠት ነው፡፡ ምርጫ እኮ የህዝብን ፍላጎት መጠየቂያ ነፃ የሆነ የዲሞክራሲ መንገድ ነው እንጂ የመርሀግበር ማሟያ አይደለም፡፡ እዚህ ላይ ካለፉት ምርጫዎች የተወሰኑ ኩነቶች ማንሳት ይቻላል።
ምርጫ 97፡ በተነጻጻሪ የተሻለ ዲሞክራሲ የታየበት ነው ሲባል ይደመጣል ፡ በእርግጥ ወያኔ ለዲሞክራሲ እና ነፃ ምርጫ ዝግጁ ስለነበር ነው ወይስ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አካሄድኩ ብሎ ደጅ የሚጠናቸውን ምዕራብያዊያንን ልብ ለማለስለስ?  ለዚህ ጥያቄ አዘል እይታ እንደ  ዋና ማሳያ ሊሆነን የሚችለው ከምርጫው በኋላ ወያኔ የተከተለው የጭካኔ ግድያ ነው፡፡ ስለዚህም ወያኔ ምርጫን መሰረት አድርጎ ለሚመጣ ማንኛውም የስልጣን ሽግግር ያልተዘጋጀና ተቃዋሚዎችም ህዝቡ በሰጣቸው ድምጽ ሳይሆን ወያኔ ተምኖ በሰጣቸው ወንበር ፓርላማ ተቀምጠው ምንም ፋይዳ የሌለው የተቃውሞ እና የድምጸ ተዓቅቦ እጅ የማስቆጠር ስራ ብቻ እንዲሰሩ ስለሚፈልግ ነው፡፡
ምርጫ 2002፡ ወያኔ ከምርጫ 97 ትምህርት በመውሰድ ከምርጫ በኋላ የሚመጣን ስልጣን የማጣት ስጋት ለማስወገድ በከፍተኛ ሁኔታ የተዘጋጀበት ነው፡፡ ይህ ምርጫ ወያኔ ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያልተዘጋጀ መሆኑ በተጨባጭ የታየበት እና ምርጫ 97 ካጋለጠበት ትክክለኛው ፀረ-ደሞክራሲያዊነት ባህሪው በባሰ መልኩ ምርጫውን ከጅምሩ በቁጥጥር ስር በማዋል ጭቆና እና የመብት ረገጣ እለታዊ የኑሮ አካል በሆነባት ኢትዮጲያ  በምርጫ ታሪክ ያልታየ የምርጫ ውጤት ሲመዘገብ አይተናል፡፡
መጭው ምርጫ 2007፡ ምርጫ 2002 በአጠቃላይ ሲታይ ለወያኔው ጨቋኝ መንግስት ከጠበቀው በላይ ቢሆንም ውጤቱ ፀረ-ዲሞክራሲያዊነቱን ፍንትው አድርጎ ያሳየበት መሆኑ ለመጭው ምርጫ 2007 እንዳንድ ማስተካከያ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡ ለመገመት ያህልም በመጭው ምርጫ ወያኔ የተወሰኑ ወንበሮችን “ታማኝ” ለሚላቸው ተቃዋሚዎች ለመስጠት የሚያስብ ይመስለኛል፡፡ በዚህ መሰረተ የስልጣን እድሜውን እያራዘመ እና የውሸት ፕሮፓጋንዳውን እየነዛ በኢትዮጵያውያን ላይ ገደብ አልባ ገዥነቱን የሚያውጅ መሆኑ ማንም ሊገነዘበው የሚችል ሀቅ ነው፡፡
ናትናኤል ካብቲመር
ናትናኤል ካብቲመር
ተቃዋሚዎች ለመጭው ምርጫ መዘጋጀት ያለባቸው እንደቀድሞው “ተሳትፎ ለመሸነፍ” ከሆነ የወያኔ የጭቆና አጋፋሪ ከመሆን የዘለለ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈይዱለት አንዳች ነገር የለም፡፡ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የህዝቡን ሮሮ፣ ችግር፣ የመብት ረገጣ እና ጭቆና ማዳመጥ እና ታግሎ ህዝብን በማታገል መፍትሄ የማምጣት ታሪካዊ ግዴታ አለባቸው፡፡ ስለዚህም መጭውን ምርጫ አለመሳተፍ ብቻ ሳይሆን ምርጫው እንደቀደሙት ምርጫዎች የህዝብ መብትን ማፈኛ እንዳይሆን መታገል አለባቸው፡፡ ከወያኔ በስተቀር ለማንኛውም የኢትዮጲያን ህዝብ እወክላለው ለሚል ተቃዋሚ ፓርቲ የጋራ አጀንዳ መሆን ያለበት በህዝብ እየተቀለደ የሚደረግ የይስሙላ ምርጫ እንዳይካሄድ ማድረግ ነው፡፡ ሥለዚህም መጭው ምርጫ ከመካሄዱ በፊት የታሰሩ የፖለቲካ መሪዎችና ለህዝብ የቆሙ ሀቀኛ ጋዜጠኞች ሳይፈቱ ፣ ለወያኔ በግልጽ የሚያዳሉና አሳሪ የሆኑትን “የምርጫ ህጎች” ሳይሻሻሉ እንዲሁም ሌሎች  መሻሻል ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ አለመሳተፍ ብቻ ሳይሆን የምርጫው ባለቤት የኢትዮጵያ ህዝብ በመሆኑ ምርጫው እንዳይካሔድ ህዝቡን በነቂስ በመቀስቀስ የታሰበውን የይስሙላ ምርጫ ማስቆም አለባቸው፡፡ አዎ ይህ ምርጫ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ከዚህ ቀደሙ የሚቀለድበት እንዲሆን ማናችንም መፍቀድ የለብንም፡፡ ይህ ምርጫ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ምርጫዎች ከሚካሄድ ይልቅ ምርጫው ቀርቶ ለአለም የኢትዮጵያዊያንን ችግርና የጨቋኙን የወያኔን ትክክለኛ ማንነት ማሳወቅ እንዲሁም የአትዮጵያ ህዝብ ትክክለኛ የስልጣን ባለቤትነቱን ወያኔ ባዘጋጀው የይስሙላ ምርጫ ሳይሆን ነፃ የሆነ በሁሉም ተወዳዳሪዎች ይሁንታ ያገኘ አካል በሚያካሂደው እውነተኛ ምርጫ እንዲሆን ማድረግ የሁላችንም ግዴታ ነው፡፡ ምክንያቱም ወያኔ ነጻ ምርጫ ለማካሄድ ጭርሱንም ፍላጎት ስለሌለው።
ውድቀት ለአምባገነኖች !!
http://www.goolgule.com/the-upcoming-election-in-ethiopia/

ከሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተላለፈ ጥሪ!

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን መፍለቂያ ለመሆኗ አለም ይመሰክርላታል፡፡ አንቱ የተባሉ ምሁራንን በማፍራት ለዓለም አበርክታለች፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በአለም ካሉ ታላላቅ ዩንቨርስቲዎች እና የምርምር ተቋማት እስከ አመራነት ድረስ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች መገኘታቸው ነው፡፡ እነዚህ ምሁራን በተሰማሩበት ስራ መስክ የሚያስመዘግቡት ውጤት እና በስራቸው ተሸላሚ መሆን ላነሳነው ሀሳብ ማጠናከሪያነት ያገለግለናል፡፡ እጅግ የሚያሳዝነውና ልብ የሚሰብረው ግን ሀገራችን ከእነዚህ ውድ ልጆቿ ተገቢውን ዋጋ አለማግኘቷ ነው፡፡ ሀገራችን የወላድ መካን እየሆነች ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሆነ ተብሎ የሚቀነባበር ሴራ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን መፍለቂያ ብትሆንም ቅሉ በተከታታይ ስልጣኑን የጨበጡት ጭፍን አንባገነኖች በሚያራምዱት አግላይ ምሁር ፖሊሲ ምክንያት እውቀታችሁን እና ገንዘባችሁን በምትወዷት ሀገራችሁ ኢንቨስት አድታደርጉ ሁኔታዎች ባለመመቻቸታቸው የስደትን መራራ ጽዋ እንድትጨልጡ ተገዳችኋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለይ ባለፉት 10 አመታት በተቃዋሚዎች መዳከም የሚያታግል ኃይል አጥታችሁ እንደቆያችሁም እናምናለን፡፡
ፓርቲያችን ሰማያዊ እያንዳንዱ ዲያስፖራ ሀገር ቤት ያለውን ዜጋ ያክል የኢትዮጵያዊነት መብት አለው ብሎ ያምናል፡፡ ይህ ይረጋገጥ ዘንድም አጥብቆ ይታገላል፡፡ በተለያየ ሁኔታና ወቅት አንባገነኖችን በሀገር ውስጥ እንደታገላችሁ እናምናለን፡፡ ለዚህ ትግላችሁና ለከፈላችሁት ዋጋም እውቅና እንሰጣለን፡፡ በስርዓቶቹ ጨካኝ ዱላ እና ሰቆቃ ብዛት ውድ ሀገራችሁን ትታችሁ የሥደትን ኑሮ ትገፉ ዘንድ ቢበየንባችሁም ስለ ኢትዮጵያ ከመብሰልሰል እንዳልዳናችሁና ሀሳባችሁ ሀገር ቤት ስለ መሆኑ መስካሪ አያሻም፡፡
ውድ የሀገራችን ልጆች እናንተ የሰው ሀገር በምታለሙበት በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ኢትዮጵያ የጉልበት ሰራተኛ ሳይቀር ከቻይናና ከህንድ በከፍተኛ ክፍያ እያስመጣች ትገኛለች፡፡ ይህ ደግሞ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ስለ መሆኑ ለእናንተ መንገር ለቀባሪ እንደ ማርዳት ያለ ነው፡፡ ይህ በእውነት ለአንድ ሀገር ወዳድ ዜጋ እንደ እግር እሳት ያንገበግባል፡፡ ልማታዊ መንግስት ነኝ በሚል የቃላት ጋጋታ ብቻ ከድሃው ወገናችሁ በሚሰበስበው ገንዘብ የሰከረው ጉልበታም መንግስት ዴሞክራሲና ልማት አንድ ላይ አብረው አይሄዱም በሚል ማሳሳቻ በየጊዜው ጉልበቱን እያፈረጠመ የሄደው በአብዛኛው እናንተ ከምትኖሩበት ከምዕራባውያን ሀገራት በሚቀበለው እርዳታ መሆኑ ሀቅ ነው፡፡
ዳያስፖራው በነጻነት መኖር ምን ማለት እንደሆነ በተግባር ያውቀዋል፡፡ ነጻ ሆኖ መስራት ለሀገር ልማት ግንባታ ያለውን ጠቀሜታም ሀገር ቤት ካለው ህዝብ በተሻለ ሁኔታ ይገነዘባል፡፡ ድህነትና አንባገነንነት ባመጣው ጦስ ኢትዮጵያዊ ክብራችን ተገፎ በየ በረሃው ዜጎቻችን እንደ እንስሳት ሲታረዱ፣ እህቶቻንን በቡድን ሲደፈሩ፣ ወገኖቻችን ልብና ኩላሊታቸው ወጥቶ ለገበያ ሲውል እንደማየት ያለ ዘግናኝ ተግባር ምን አለ?!! ይህ ህገ ወጥ ተግባር ሊፈጸምባቸው አይገባም ብላችሁ ያሳያችሁት ለወገን መቆርቆር ይበል የሚያስብልና ሊበረታታ የሚገባው ነው ብለን እናምናለን፡፡
በተለይ የሳውዲ መንግስት በዜጎቻችን ላይ የወሰደባቸውን ህገ ወጥ ተግባር ለማውገዝ ያደረጋችሁትን ርብርብና ለሀገራችን በአንድ ሆ ብላችሁ መቆማችንሁን በድጋሚ እያመሰገንን አንባገነኑን ኢህአዴግ ለመታገል በሚደረገው ትግል አጋራነታችሁን ስለምንገነዘብ ከጎናችን በመሆን ለምታሳዩት ውጣ ውረድ እውቅና እንሰጣለን፡፡ ከዚህ በፊት ያሳያችሁትን የትግል ቁርጠኝነት እንደምትደግሙት በማመን ያላችሁን የገንዘብ አቅም፣ የእውቀትና የተሰሚነት ሚና በመጠቀም የአንባገነኑን ስርዓት አፈና በማጋለጥ ከጎናችን እንድትሰለፉ ስንል እንጠይቃለን፡፡ ዳያስፖራው ያለውን የኢኮኖሚ ነጻነት፣ የሚዲያ ነጻነትና፣ ሀገር ቤት ካለው ጋር ሲነጻጸር ያለው የለሻለ የትምህርት ደረጃና ልምድ፣ እንዲሁም በእርዳታ ሰጭ ሀገራት ያለው የተሰሚነት አቅም ተጠቅሞ ሀገር ቤት ያለውን ትግል በማገዝ ነጻ የምንወጣበትን ቀን ሊያፋጥን እንደሚገባ ፓርቲያችን ያምናል፡፡
ፓርቲያችን የህግ የበላይነትን ለማስፈን ሁሉንም የሀገሪቱን ዜጋ ያሳተፈ ትግል በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ዘርፈ ብዙ ትግል ውስጥ ደግሞ ሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ‹‹የተነጠቁ መብቶቻችን እናስመልስ›› በሚል መሪ ቃል ታላቅና ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ያካሂዳል፡፡ በመሆኑም ይህን ሁሉን አቀፍ የሆነ ሰላማዊ ትግል በሞራል፣ በእውቀትና በምክር፣ እንዲሁም በገንዘብ በማገዝ የትግሉ አጋር ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡
ከአገራችሁ እርቃችሁ የምትኖሩ በመሆናችሁ አዲስ አበባ ውስጥ አብራችሁን ባትቀሰቅሱ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ባትወጡና ባትታሰሩም መረጃውን ለዓለም ህዝብ በማድረስ ከፍተኛ ሚና እየተጫወታችሁ ቆይታችኋል፡፡ በዚህ ሰልፍም አገር ቤት ለሚኖሩ ቤተሰብ፣ ጓደኛ እንዲሁም ሌላው ህዝብ በስልክ፣ በማህበራዊ ድህረ ገጽና የተለያዩ መልዕክት ማስተላለፊያዎች በመጠቀም ህዝቡን የማነቃቃት አቅምና አጋጣሚ ተጠቅማችሁ በትግል ጉዟችን ተሳታፊ እንድትሆኑ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ኑ ራሳችንን ነጻ በማውጣት የአገራችንን እጣ ፈንታ እንወስን!
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11945/

ቴሌፎኑ ‘ለግዜው’ ጥሪ አይቀበልም

(ክንፉ አሰፋ)

telecom


“የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።…” የምትለዋ አሰልቺ የቴሌ መልእክት ያላጋጠመው ቢኖር  ወደ ኢትዮጵያ ስልክ ደውሎ የማያውቅ ሰው ብቻ መሆን አለበት። ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ወደ ቀድሞ ወዳጆቻቸው መደዋወል ጀመሩና በመሃል ተስፋ ቆረጡ አሉ። አስር ለሚያህሉ አርሶአደሮች እና የሰራዊቱ አባላት ዘንድ ደውለው አልተሳካለቸውም። ለሁሉም ጥሪ ያገኙት ምላሽ “የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።” የሚል ሲሆንባቸው ራሳቸውን ነቀነቁ። ሰው ሁሉ የጨከነባቸው መሰላቸው። እንዲህም አሉ። “የሃገሬ ሰው እንኳን የስልክ ጥሪ፤ የእናት ሃገር ጥሪስ መች ተቀበለ።”
ለአመታት በተከታታይ በሁለት ድጅት እያደገች ያለች ሃገር የስልክ መስመር ችግር ይገጥማታል ብሎ ማሰብ ይከብዳል። ችግሩን በደንብ ላልተረዳው፣ ሰው የሞባይል ስልክ የሚገዛው እንዲሁ ይዞ ለመታየት ነው ያስብል ይሆናል። ይህ አባባል በከፊል ትክክል ነው። ዘመናዊ ስልክ በመያዝ ለላንቲካነት ብቻ የሚጠቀሙበት ሰዎች አይጠፉም። የቻይናው ቀፎ ከሞዴል አርሶ አደሮች አልፎ ተራው አርሶ-አደር እጅ ላይም ገብቷል። አብዛኞቹ ግን ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን አይጠቀሙበትም።  ለዚህም ይመስላል በርካታ ተንቀሳቃሽ ስልክ የሚይዙ ሰዎች እንዲሁ ለእይታ እና ለላንቲካ ብቻ የሚመስላቸው። አገልግሎቱን በተመለከተ ግን 99 በመቶ የሚሆነው ችግር የመዋቅር ችግር ነው።
ለዓውዳመቱ ወደ ኢትዮጵያ ስልክ የደወላችሁ ካላችሁ፤ ይህ ነገር እንደገጠማችሁ እርግጥ ነው። ዘንድሮ ደግሞ ቴሌ ከፍቷል። የሞባይሉ መስመርማ እንደ አይን እልም ብሎ ነው የጠፋው።  ከበርካታ ሙከራ በኋላ መስመር ያገኘ ሰው ካለ በደስታ ይዘልላል።  የተቀባዩም ስልክ ካቃጨለ ተዓምር ነው የሚባለው። ከርማ ብቅ እንደምትለው የአዲስ አበባ መብራት … ልክ እንደ ቧንቧ ውሃ፤ ስልኳም “መጣች – መጣች!” ብሎ መጨፈሩ አይቀርም።
(በመከራ መስመር ሲገኝ እንዲህ ያስደስታል)
(በመከራ መስመር ሲገኝ እንዲህ ያስደስታል)
“እንኳን አደረሳችሁ!” ለማለት እኔም ወደ ሃገር ቤት ስልክ መታሁ።
“የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።” የሚል መልስ ነበር ያገኘሁት። ለሁለተኛ ግዜ ስሞክር ደግሞ “የደወሉት ስልክ ለግዜው ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ነው።”  የሚል ምላሽ አገኘሁ።  ደቂቃ ባልሞላ ግዜ ውስጥ ጥሪ ያማይቀበለው ስልክ ከአገልግሎት መስጫ ክልል መውጣቱ አስገረመኝ። ተስፋ ሳልቆርጥ ደገግሜ ሞከርኩ።  ቢያንስ ከአስር ግዜ ሙከራ በኋላ፤ መስመር አገኘሁና ሎተሪ የወጣልኝ ያህል ተሰማኝ።
ደስታዬ ግን ብዙም አልዘለቀም። በመሃል እንግዳ ነገር ተፈጠረ። ስልኩን የተቀበለኝ የደወልኩለት ሰው አልነበረም። የተፈጠረው ክስተት – ባለንበት የመረጃ ዘመን እንደ 17ኛው ክፍለዘመን “ቴሌ በኦፐሬተር መስራት ጀመረ እንዴ?” ያሰኛል። ነገሩ ግን ሌላ ነው። ስልኩን ያነሳው የተለመደው የስልክ ጠላፊ ስለመሆኑ አንዳች ጥርጥር አልነበረኝም። ሶማሌያውያን መርከብ ሲጠልፉ ጸሃዩ መንግስታችን ደግሞ የስልክ ፓይረት መሆኑን ሂዩማን ራይትስ ዎች በዚያን ሰሞን ነግሮን ነበርና።
ውጭ ሃገር ያለ ኢትዮጵያዊ ዘመድ ለመጠየቅ መደወሉ አይቀርም። ተስፋ የማይቆርጥ፤ ደጋግሞ ይሞክራል። እንደ እድል የስልኩን መስመር ካገኘ ደግሞ ሌላ ችግር ይገጥመዋል። ዘው ብለው የሚገቡ የስልክ ጠላፊዎች መስመሩን ያውኩታል። ሌላው አማራጭ ደግሞ አጭር የጽሁፍ መልእክት ነው። በኢትዮጵያ ቴሌኮም አጭር መልእክት ከመላክ ይልቅ ደብዳቤ ጽፎ በፖስታ መላኩ እየፈጠነ መጥቷል። አጭር መልእክት የሚደርሰው ከቀናት ብኋላ ነው። ከላኪው ዘንድ መልዕክቱ መድረሱ ቢረጋገጥም ተቀባዩ ጋ ጨርሶ ላይደርስም ይችላል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ በሰጡት ጋዤጣዊ መግለጫ “የኢትዮጵያ ቴሌኮም ቴክኖሎጂ ከዴንማርክ፣ ከኖርዌይ እና በከፊል ከእንግሊዝ ቴክኖሎጂ ጋር አንድ ነው” ብለው ነበር። በዚህ መግለጫቸው አቶ ሃይለማርያም የኢትዮጵያን የኢንተርኔት አገልግሎት፣ እንዲሁም የስልክ መስመሩ ጥራት እና አስተማማኝነት በደንብ አድርገው ነበር “ለጋዜጠኞቹ” የገለጹላቸው። ይህን ተናግረው እንዳበቁ ግን የራሳቸውም ስልክ መጠለፉን ሰማን። ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንዲሉ አልሰሙት ይሆናል እንጂ፤ “እኛ ሲም ካርድ፤ አንተ ደግሞ ቀፎ ነህ!” ይሏቸዋል – ከላይና ከታች ያሉ አለቆቻቸው።
የኢትዮጵያን ስልክ አገልግሎት ከዴንማርክ፣ ኖርዌይ እና እንግሊዝ ጋር አወዳድረው ማወደሳቸው ግን ራሳቸው ካዴሬዎቹንም ሳይቀር ሳያሰፍራቸው አልቀረም።  ሰውየው የኢትዮጵያን ቴሌኮም እያወዳደሩ ያሉት 99.9 በመቶ ሳያቋርጥ አገልግሎት ከሚሰጠው አራተኛው ጀንሬሽን የምእራቡ ቴክኖሎጂ ጋር ነው። መቼም ሁሉም ይዋሻሉ። ነብሳቸውን ይመርና አቶ መለስ ዜናዊም ይዋሹ ነበር። ለዛ ያለው ውሸት አለ። እጅ፣  እግርና አይን የሌለው ውሸትም አለ። እንዲህ አይነት ያፈጠጠ ውሸት ግን እመራዋለሁ የሚሉትንም ሕዝብ እንደመናቅ ይቆጠራል። እኚህ ሰው የሞራል እሴታቸውን ሁሉ አሽቀንጥረው ሊጥሉት ይችሉ ይሆናል። ምሁራዊ ግብአታቸውንም ለተራ ፖለቲካ ጥቅም ሊያስወግዱት ይችላሉ።  እምነታቸውስ እንዲህ አይነቱን ቅጥፈት ይፈቅድላቸው ይሆን?
የቴሌ የኢንተርኔት አገልግሎት የመንግስት አልባዋ ሶማልያን አንድ መቶኛም። ኮሜዲያን ክበበው ገዳ እንደቀልድ የነገረኝ ቁም-ነገር የኢትዮጵያን ኢንተርኔት ፍጥነት በደንብ ይገልጸዋል።  ክበበው ሰሜን አሜሪካ የስራ ጉብኝቱ ወቅት ፎቶ ተነስቶ ለቤተሰቡ በኢሜይል ይልካል። የላከው ፎቶ መድረሱን ለማረጋገጥ በነጋታው ወደ አዲስ አበባ ደወለ።
“ፎቶ ደረሰ?”
“አልደረሰም!”
ሌላ ቀን እንደገና ደውሎ የላከው ፎቶ እንዳልደረሰ ተነገረው። ለሶስተኛ ግዜ ደውሎ ኢሜይሉ እንደደረሰ ጠየቀ። አሁንም አልደረሰም ተባለ። እንዲህ እያለ ሳምንት ሞላው።
“በሳምንቱ እኔ ቀድሜ ደረስኩ።” ነበር ያለው ክበበው።
telecom tየኢሜይል መልእክቱ መድረሱ ከተረጋገጠ በኋላ – ሌላ ችግር ገጠመው። ኢሜይሉ ሲከፈት ግማሽ አካሉን ነበር የሚያሳየው። ፎቶው እስኪያወርድ (ዳውንሎድ እስኪያደርግ) ደግሞ ግማሽ ቀን መፍጀቱ ግድ ነበር።
ይህንን አገልግሎት ነው አቶ ሃይለማርያም ከምእራቡ አለም አገልግሎት ጥራትና ፍጥነት ጋር እያወዳደሩ የሚነገሩን።  በአስር ሜትር ርቀት ላይ ሆኖ በስልክ መገኛኘት ህልም በሆነበት ሃገር፤ ስለ ስልክ ጥራት መናገር ቅጥፈት ብቻ ሳይሆን የሰውየውንም የሞራል ውድቀት ያመላክታል።
የኢትዮጵያ ቴሌኮም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀጥሎ ትልቅና ግዙፍ የሃገሪቱ ተቋም ነው። እድገቱ ግን ያሳዝናል።  በአስር አመት ግዜ ውስጥ ብቻ  እንኳን እድገቱ በ75 በመቶ ቁልቁል ወርዷል። ለዚህ ዋናው ምክንያት ተቋሙ አገልግሎት መስጠቱን አቁሞ ወደ ስለላ ተቋም መቀየሩ ነው። ባለፈው ወር ይፋ የሆነው ባለ 100 ገጹ የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ ይህንን መንግስታዊ የስልክ እና የኢንተርኔት ጠለፋ አረጋግጧል።
“የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የነበረን አንድ ዜጋ አፍነው ካሰሩት በኋላ ውጭ የተደዋወለበትን የስልክ ቁጥር ዝርዝር አሳዩት።” ይላል ጠቀማጭነቱ ዩናይትድ ስቴትስ የሆነው አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋም። ሰውየው የታሰረው ያልተከፈለ የስልክ ሂሳብ ኖሮበት አልነበረም። ባለስልጣናቱንም አላማም፣ ወይንም መንግስትን በሃይል ለመገልበጥ አላሴረም። ወንጀሉ፤ ከውጭ ሃገር ስልክ ስለተደወለለትና ከወዳጅ ዘመዶቹ ስለተወያየ ብቻ ነበር። ይህ ደግሞ ፍጹም እንግዳ ነገር ነው። ከተለምዶ ልማታዊ መንግስት አስተሳሰብም እጅግ የከፋ!
የዜጎች ሁሉ ስልክ በቴሌ በኩል ይጠለፋል። እንደ ስካይፕ እና ቫይበር ያሉ የቮይስ ኦቨር ስልኮች ደግሞ ፊን ፊሸር በተባለ የኮምፒዩተር ቫይረስ አማካኝነት ይጠለፋሉ። በዚህ አይነት በዜጎች የግል ህይወት ሳይቀር እየገቡ ቴሌን ሙሉ በሙሉ የስለላ ተቋም አደረጉት።
ሞባይል ስልክ እና ኢንተርኔት በአፍሪካ አህጉር በእጅጉ እየተስፋፋ ይገኛል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ 30 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ ህዝብ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጠጠቃሚ እየሆነ መጥቷል። በኢትዮጵያ ግን የስልክ እና የኢንተርኔት ተጠቃሚው  ከ2.5 በመቶ አልዘለቀም።  ጎረቤት የሆነችው የኬንያ ህዝብ 40 በመቶ  የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ ነው። መንግስት አልባዋ ሶማልያ እንኳን፣  ስድስት የቴሌፎንና ስልክ አቅራቢ ኩባንያዎች አሏት።  የሶማልያ ህዝብ ጥራት ያለው የስልክ መስመር እና ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆነ ሰንበትበት ብሏል። በኡጋንዳም የዚህ አገልግሎት ሰጪ በመንግስት ሞኖፖሊ ስር አይደለም።  ከሰባት በላይ የግል ኩባንያዎች እየተፎካከሩ ፈጣን አገልግሎት እየሰጡ ጠተቃሚውን ህዝብ ወደ 50 በመቶ አድርሰውታል።
ያለነው በመረጃ ዘመን ነውና ያለመረጃ እና ያለ መረጃ ቴክኖሎጂ እድገት አመጣለሁ ማለት ዘበት ነው የሚሆነው። የኢትዮጵያ ሁኔታ ግን ሃገሪቱን  ወደ መረጃ ሳይሆን ወደ ጨለማ ዘመን ነው እየመራት ያለው።  እንድምናነበው ከሆነ የኢትዮጵያን ቴሌኮም ለማስፋፋት  ከሶስት ቢሊየን ዶላር በላይ ወጪ ሆኗል። ይህ ገንዘብ በትክክል ስራ ላይ ቢውል አባይንም ይገድባል። ለዚህ የእድገት ሳይሆን ይልቁንም የጥፋት ጎዳና ተባባሪ የሆነቸው ቻይናም በውጭ ምንዛሪ እየተከፈላት ቴሌን ብቁ የስለላ ተቋም አድርጋዋለች። የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስትሩም ከተለያዩ የኢንዱስትሪ ሃሮች ጋር በመተባበር የቴሌ ጥራት ላይ ሳይሆን የሚሰራው የስለላ ሃርድዌር እና ሶፍትዌር ማስገባቱ ላይ ነው።
የሃገሪቱ ግብር ከፋዮች ገንዘብ መልሶ ራሳቸውን እንዲያፍን መደረጉ እጅግ ያሳዝናል።
የቴሌ መልስ መስጫ ላይ ያለው መልዕክት ግን መሻሻል አለበት። “ለግዜው” የሚለው ቢቀየር ድርጅቱን ከሃሜት ያድነዋል። እናም መልእክቱ እንዲህ ነው መሆን ያለበት፣
“የደወሉላቸው ደምበኛ  ‘ለሁልግዜ‘  ጥሪ አይቀበሉም። …”
ከዚያ በኋላ ደዋዩም ተስፋ ቆርጦ መደወል ያቆማል።
http://www.goolgule.com/the-telephone-is-not-accepting-calls/

Saturday, April 19, 2014

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ‘ሮሮና ስጋት

“ምላሽ ካልተሰጠን የትምህርት ማቆምና ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን!”

addis ababa university


የትምህርት ሚኒስትር በ2006 ዓ.ም በአገሪቱ በተፈጠረው የመምህራን እጥረት ምክንያት በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ኢትዮጵያውያንን ለአንድ አመት ሙሉ ወጫቸውን ችሎ የማስተማር ስነ ዘዴ (ፔዳጎጅ) በማስተማር ወደ መምህርነት እንዲገቡ ማስታወቂያ ያወጣል፡፡ በወጣው ማስታወቂያ መሰረትም ለማጣሪያነት የቀረበውን ፈተና በመፈተን መልምሎ ለስልጠና እንዲገቡ ይደረጋል፡፡ በዚህ መሰረት በ10 ዩኒቨርሲቲዎች (መቀሌ፣ ባህር ዳር፣ ወሎ፣ ወለጋ፣ ጅማ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ዲላ፣ ሀሮማያ፣ ሀዋሳና አዲስ አበባ) እንዲሰለጥኑ ይደረጋል፡፡
ይህ ስልጠና እየተካሄደ ባለበት ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡት ሙሉ ወጫቸውን መንግስት እንደሚችል ተነግሯቸው ነበር የመጡት፡፡ በዩኒቨርሲቲው መጀመሪያ የተደለደሉት 330 ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን ተማሪዎቹ ቃል በተገባላቸው መሰረት መቀጠል አለመቻላቸውን ነው በቅሬታ የሚናገሩት፡፡ ወደ ዝግጅት ክፍላችን በአካል መጥተው ስለሁኔታው ያስረዱት ተማሪዎች ሁኔታውን እንደሚከተለው ያስረዳሉ፡፡ ‹‹ማስታወቂያውን አይተን ስራችን ለቀን ነው የመጣነው፡፡ ሆኖም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሚኒስትር ቃል በገባው መሰረት ከህዳር 23 ጀምሮ የምግብም ሆነ የቤት አገልግሎት ሊሰጠን አልቻለም፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመኝታ አገልግሎት የለም በመባሉ ደብረዘይት በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ቅርንጫፍ የእንሰሳት ህክምና እና የግብርና ኮሌጅ ለሁለት ሳምንት እንድንቆይ ተደረገ፡፡ ሆኖም ደብረ ዘይት በሚገኘው ኮሌጅ ጥቁር ሰሌዳን ጨምሮ ለመማር ማስተማር የሚያገለግሉ አቅርቦቶች ልናገኝ አልቻልንም፡፡››
ከዚህም ባሻገር በዚህ ወቅት ተማሪዎቹ የመብት ጥያቄ እንዲያነሱ ያደረጋቸው ሌላ ምክንያትም ተፈጠረ፡፡ ‹‹ትምህርቱ በተባለው መልኩ ሊሰጠን አልቻለም፡፡ አንድ መምህር ወደ ደብረዘይት ሄዶ የሳምንቱን የትምህርት ፕሮግራም ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት እንዲሁም ከ7 ሰዓት ተኩል እስከ 11 ሰዓት ተኩል አስተምሮ ይሄዳል፡፡ ይህን ተከትሎም አንዳንድ የመብት ጥያቄዎችን ማንሳት ጀመርን፡፡›› ይላል አስተባባሪውና የጅኦግራፊ ተማሪው ጋሻነህ ላቀ፡፡
ተማሪዎቹ ሌላ ስራ ስለሌላቸውና ከቤተሰብ ውጭ ስለሚኖሩ አንዳንድ መሰረታዊ አቅርቦቶች እንዲሰጧቸው ለትምህርት ሚኒስትር ያሳውቃሉ፡ ፡ አያይዘውም የትምህርት እድል እንዲያገኙና በደሞዝ ጉዳይም ድምጽ አሰባስበው ያስገባሉ፡፡ ትምህርት ሚኒስትርም ‹‹እናንተ የወጭ መጋራት ስላልሞላችሁ የጠየቃችሁት አቅርቦት አይሰጣችሁም፡፡›› ይላቸዋል፡፡
በዚህ ሁኔታ በሁለት ሳምንት ውስጥ ወደ አዲስ አበባ ይመለሳሉ የተባሉት ተማሪዎች ለሁለት ወር ከሁለት ሳምንት በላይ (ከህዳር 24- የካቲት 8) በደብረዘይት እንዲቆዩ ይደረጋል፡፡ ከደብረ ዘይት ሲመለሱ ይዘጋጃል ተብሎ የነበረው አልጋም ሆነ ሌላ አቅርቦት አልተዘጋጀም፡፡ ይልቁንም ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ውስጥ ከሚገኝ ባዶ ክፍል ውስጥ መሬት ላይ አራት አራት ፍራሽ እያነጠፉ እንዲተኙ ይደረጋሉ፡፡ ትምህርቱን ጥለው እንዳይሄዱ እስካሁን ያሳለፉትን ችግር ትተው መሄድ አልፈለጉም፡፡ ከዚህ ይልቅ ትምህርት ሚኒ ስትርንና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ችግሩን እንዲፈታ በተደጋጋሚ ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡ ይህ ጥያቄያቸው ንም እስከ ፓርላማና ሌሎች ተቋማት ድረስ አድ ርሰዋል፡፡ ሆኖም ተገቢውን ምላሽ ሊያገኙ እንዳ ልቻሉ ይገልጻሉ፡፡
በዚህ ምክንያት የተማሪዎች ችግር እንዲፈታ ጥረት የሚያደርጉ አስተባባሪዎች ጉዳዩን ወደ ሚዲያ ለማውጣት ይቆርጣሉ፡፡ የሸገር ሬድዮ ጋዜጠኞችም ጉዳዩን ተማሪዎቹ ያሉበት አካባቢ ድረስ ሄደው ይዘግቡታል፡፡ እነዚህ ተማሪዎች ከሌሎች በተለይም አስተባባሪዎቹ በሌሎች ዩኒቨ ርሲቲዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ከሚማሩት ጋርም ግንኙነት ይመሰርታሉ፡፡ እነዚህ ተማሪዎች የሚ ያደርጉትን የመብት ጥያቄና እንቅስቃሴ አብረዋ ቸው የሚማሩ ካድሬዎች (እነሱ ሰርጎ ገቦች ይሏ ቸዋል) ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መሆኑን ለሶስተኛ አካል (ለመንግስት) መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ከተቃዋሚ ዎች ጋርም ግንኙነት እንዳላቸው ይናገራሉ፡፡ ይህ መረጃ ለመንግስት አካላት መድረሱንም መረጃው ከደረሳቸው መካከል ውስጥ አዋቂዎች መልሰው ለአስተባባሪዎቹ ይነግሯቸዋል፡፡ አስተባባሪዎቹ የሚያነሷቸው የመብት ጥያቄዎችም ወደ አመጽ ሊቀይሩት እንደሆነ በመግለጽ መታሰር እንዳለባ ቸው መወሰኑን ይገልጻሉ፡፡ ይህንን ተከትሎም እስ ራትና አፈና ሊደርስባቸው እንደሚችል ስጋታቸውን ይገልጻሉ፡፡
አስተባባሪዎቹ ‹‹ፖለቲካዊ ጥያቄ መጠየቅ መብታችን መሆኑን አላጣነውም፤ ነገር ግን የአሁኑ ጥያቄያችን የመብት እንጂ ፖለቲካዊ ጥያቄ አይደለም›› ይላሉ፤ አክለውም ሊታሰሩ እንደሚችሉ የውስጥ ምንጫቸው በእርግጠኝነት እንደነገራቸው ይገልጻሉ፡፡
ወጭ መጋራት በስምምነታቸው ላይ ያልነበረ ቢሆንም አሁን ግን እንደገና መጥቷል፡፡ መምህር ከሆናችሁ በአገልግሎት ዘመን፣ ሌላ ስራ ከሰራ ችሁ በገንዘብ ትከፍላላችሁ ተብለዋል፡፡ ይህ ግን ስምምነቱ ላይ አልነበረም እንደተማሪዎቹ ገለጻ፡፡ ‹‹እንዲያው ይህን ስምምነት እንሙላ ከተባለ እንኳን የሚሰጡን አገልግሎቶች ሊሟሉልን ይገባ ነበር፡፡ አሁንም ያቀረብነው አገልግሎቶች እንዲሟ ሉልን የሚል ነው፡፡ ያቀረብናቸው ቅድመ ሁኔታ ዎች ከተሟሉ ወጭ መጋራቱን ልንፈርም እንችላ ለን፡፡ እነሱ ግን በሚገባ ጥያቄያችን ሊመልሱልን አልቻሉም፡፡ እንዲያውም ምግብና ሌሎች አቅርቦቶች እንደማይሰጠን፣ ትዕዛዙ ከትምህርት ሚኒስትር የመጣ በመሆኑ ካልፈረሙ ዩኒቨርሲቲውን ለቀን ልንሄድ እንደሚገባ ሁሉ አስፈራርተውናል፡፡›› የሚለው ደግሞ የስፖርት ሳይንስ ተማሪና እንቅስቃሴውን ሲመራ የቆየው ሚሊዮን ታደሰ ነው፡፡
በተመሳሳይ ጅማ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙት ተማሪዎች መብታቸውን ስለጠየቁ ሁለት ቀን ምግብ ከልክለው ጾም እንዳዋሉዋቸው ይገልጻሉ፡፡ በፖሊስ እያስደበደቡም ከግቢ አስወጥተዋቸዋል፡ ፡ ‹‹ባልተዘጋጀንበት ሁኔታ ትምህርቱን ጥለን አንሄ ድም!› ብለው መኖሪያቸው ቁጭ ቢሉም በፖሊስ ተከበው በመደብደባቸው በግድ የወጭ መጋራቱን ለመሙላት ተገደዋል፡፡ ከጅማ ውጭ በሌሎች ዩኒ ቨርሲቲዎች የሚገኙት ተማሪዎች የወጭ መጋራት አልሞሉም፡፡ በሶስቱ ዪኒቨርሲቲዎች (መቀሌ፣ ባህር ዳርና ወላይታ ሶዶ) የወጭ መጋራት አልተጠ የቀም፡፡ እነሱም ግን መጠየቃቸው የማይቀር ነው፡፡ ጅማ በግድ ሞልተዋል፡፡ ሌሎቹ ጋር በግዳጅ እንዲሞላ ጫና እየተደረገ በመሆኑ ያልተጠየቁትንም እንዲሞሉ ያስገድዷቸዋል፡፡››
ለተማሪዎቹ የተሰጠው ምላሽ በዚህ አያበቃም፡ ፡ ‹‹መብት ብላችሁ መጠየቅ የለባችሁም፡፡ አርፋችሁ ተማሩ›› ተብለናል፡፡ የወጭ መጋራቱን እንድንሞላ ለማስገደድ ከትምህርት ሚኒስትር ሳይቀር ሰዎች እንደተላከባቸውን ይገልጻሉ፡፡
አስተባባሪዎቹ ተማሪዎችን በማስተባበር የምንመደበው መሰረታዊ ወጭዎችን አሟልተን የማንኖርበት መምህር ነት፤ መንግስት እያዋረደው፣ ህዝብም እየናቀው ባለ ሙያ ውስጥ ልንገባ ተጨማሪ እዳ አንገባም ይላሉ፡፡ ተማሪዎቹ እንደሚሉት መንግስት አስተባባሪዎቹን በማሰር ጉዳዩን አድበስብሶ ለማለፍ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ‹‹በእኛ በኩል ምላሽ ካልተሰጠን ትምህርት ማቆምና ሰላማዊ ሰልፍ የማ ድረግ እርምጃዎችን እንወስዳለን፡፡ ምግብ ሊከለክሉን አይችሉም፤ ይህ በእኛ እና በአባቶቻችን ስም ተለምኖ የመጣ ነው›› በማለት መብታቸውን አሳልፈው እንደማይ ሰጡም ይናገራሉ፡፡ የዝግጅት ክፍላችን ድረስ መጥተው ስለጉዳዩ መረጃ የሰጡት የእንቅስቃሴው መሪዎች የሚከ ፈለውን መስዕዋትነት ከፍለው መብታቸውን እንደሚያስ ከብሩ ገልጸውልናል፡፡ (ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ)
http://www.goolgule.com/students-of-aau-are-demanding-their-right-to-be-respected/

አይ አዜብ!

(ዘመናይ ዘ አራት ኪሎ)

azeb a


አዜብ ሲባል ማን በአዕምሮህ ሊመጣ እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ በውስጥህ ያሰብከው ‹የባለራዕዩን መሪ› ባለቤት አዜብ መስፍንን ከሆነ ለጊዜው ግምትህ አልሰራም፡፡ አሁን አዜብ የምልህ ሌላ ሴት ናቸው፡፡ አዜብ አስናቀን ነው፡፡ (አስናቀ ስልህም እንዳትደነግጥ…የሰው ለሰው ድራማው አስናቀ አይደለም፡፡) ለማነኛውም አዜብ አስናቀ የግልገል ጊቤ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩትን ሴት ነው እየጠቀስኩልህ ያለሁት፡፡
እና አዜብን እንዴት አነሳኋቸው ካልክ ጉዳዩ ወዲህ ነው፡፡ ሴትዮዋ ከግቤ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅነታቸው ተነስተው ወደ ሌላ ‹ከፍ› ወዳለ ሹመት መጥተዋል፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚነት አድገዋል፡ ፡ ሹመታቸው በቀድሞው ስራ አስፈጻሚ አቶ ምህረት ደበበ ቦታ መሆኑ ነው፡፡ እኒህ ሴት ታዲያ ‹አይ› የሚያስብል ነገር ገጥሟቸዋል፤ ወይም እንዲያ እንድንል አድርገውናል፡፡
ሴትዮዋ ይህን ሹመት ካገኙ ወዲህ የት እንዳሉ ጠፍተዋል፤ ማለቴ ከበፊቱ የበለጠ ስልጣን ይዘው ከበፊቱ ያነሰ ነው ወደ ህዝብ በሚዲያ እየወጡ ያሉት፡፡ ታዲያ በእኒህ አዜብ በተባሉ መሐንዲስ ሴት ምክንያት አንዳንድ ‹ጉድ-ዳዮች› እየተሰሙ ነው እልሃለሁ፡፡ ይህ ኢህአዴግ የሚባል ድርጅት ጉዱ ብዙ ነው መቼም! ድርጅቱ የአራት ውላጆች ጥርቅምም አይደል! እና አልኩህ የእኒህ ሴትዮ አባልነት ወይም ወገንተኝነት ከወዴት እንደሆነ ግራ ያጋባል፡፡
አብረን እንጠይቅ እስኪ…እውነት ሴትዮዋ ለማን ይወግናሉ? ለህወሓት ነው? ለኦህዴድ ነው? ለደኢህዴን ነው? ወይስ ኢህአዴግ የሚባለው ራሱን ችሎ ያለ መስሏቸው ተታለው ነው?! በነገርህ ላይ ብአዴን ብዬ ያለጠየኩት በምክንያት ነው፡፡ ምክንያቱ ምን መሰለህ…ሴትዮዋ ብአዴንን እንደማይወግኑ የታወቀ ጥርጣሬ ነው፤ (የታወቀ ጥርጣሬ ምን ማለት ነው አልክ?)
እውነትም ሴትዮዋ ተታልለዋል! እኔን ካልወገንሽ የሚል አተያይ ይገጥመኛል ብለው የሚገመቱ አልመሰሉም ነበር ማለት ነው! ለዚህ ነው ‹መደበቅ› ያበዙት፡፡ ታዲያ አልኩህ ብአዴን ሆዬ ቦታው ለእኔ ይገባኝ ነበር ብሎ ዘራፍ ለማለት ቃጣው አሉ፡፡ በዚህ ምክንያት አለመግባባቱ አይሏልም እየተባለ ነው፡፡ ምክንያት ህወሓት ማንም ዘራፍ እንዲል አለመፈለጉ ነው! በዚህ ምክንያት እኮ ነው አሉ የመብራት መቆራረጡ የባሰበት፡፡ እንዴ ማን ማንን ይምራ!? ፍትጊያቸውን እንጂ ህዝቡን ማን ልብ ብሎት!
አይ አዜብ! ባላሰቡት መልኩ ፍትጊያውን ተቀላቅለው ቁጭ አሉት፡፡ (ከፍትጊያው ከሌሉበት እንኳ በፍትጊያው ምክንያት ስራቸውን እንዳይሰሩ ተደርገዋል!) አንተዬ እነዚህ ኢህአዴጎች ሊበላሉ እኮ ነው፡፡ (ለነገሩ ህዝብን ብቻ እያኘኩ ከሚኖሩ እርስ በእርሳቸውም ቢናከሱ ይሻላቸዋል፡፡ ድሮስ ጅብና ጅብ መቼ ተስማምቶ በልቶ ያወቃልና!)፡፡ የህዝብ አምላክ መልካሙን ቢያመጣ ያምጣ ብሎ ዝም ያለው ህዝብም አንድ ቀን መነሳቱ አይቀርም፡፡ ያኔ ምን ይውጣቸዋል? ካሁኑ እርስ በእርስ ቢበላሉ ከአደባባዩ ገመና ይሻላቸዋል! ለማነኛውም መሐል ሜዳ ላይ የሚዋልሉት አዜብ ጥግ ቢይዙ ሳይሻላቸው አይቀርም፡፡ ምስኪን አዜብ!
http://www.goolgule.com/oh-azeb/

Thursday, April 17, 2014

ሰማያዊ ፓርቲ በፌደራል መንግስቱና በቡለን ወረዳ የመሰረተው ክስ ሀሙስ ፍርድ ቤት ይቀርባል!

ሰማያዊ ፓርቲ በቤንሻንጉል ጉምዝ በህገ ወጥ መንገድ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ወደ ቦታቸው በአስቸኳይ እንዲመለሱና ተገቢው ካሳ እንዲከፈላቸው በተደጋጋሚ ባካሄዳቸው ሰላማዊ ሰልፎችና ባወጣቸው መግለጫዎች የጠየቀ ሲሆን መንግስት ለጥያቄው ምላሽ ባለመስጠቱ ዜጎቹ የተፈናቀሉበትን ቡለን ወረዳና የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እንዲሁም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ላይ ክስ መስርቶ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ክሱን ታዋቂው የዓለም አቀፍ የህግ ባለሙያ ዶክተር ያእቆብ ኃይለ ማሪያም ይዘውት የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ቢሮክራሲያዊ ምክንያቶች መዝገብ ሳይከፈትለት እንደቆየ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል፡፡

Amhara Ethnic group members Ethiopia
ይሁን እንጂ ሰማያዊ ፓርቲ ባደረገው ተደጋጋሚ ግፊት ክሱ በአሁኑ ወቅት መዝገብ ተከፍቶለት፣ የዳኝነት ክፍያ ተከፍሎ በቀጣይ ሀሙስ ሚያዝያ 9/2006ዓ/ም ክሱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስምንተኛ ፍትሃብሄር ችሎት ላይ መታየት እንደሚጀምር ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
‹‹ሰማያዊ ፓርቲ በጉዳዩ ላይ አቋም ወስዶበት ከሰላማዊ ሰልፉም ባሻገር ዜጎቹ ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱና ካሳ እንዲሰጣቸው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ እስካሁንም ድረስ በዜጎች ላይ በሚደርሰው ችግር ከጎናቸው ሆኖ የሞራልና የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡›› ያሉት አቶ ብርሃኑ ፓርቲው ኢትዮጵያውያኑ በመፈናቀሉ ሂደት በደረሰባቸው ችግር ልጆቻቸው የታመሙባቸውን ለህክምና እንዲሁም ለመጓጓዣም ፓርቲው እገዛ ሲያደርግ መቆየቱንና አሁንም ዜጎቹ ፍትህ እስኪያገኙ ድረስ ከጎናቸው እንደሚሆኑ አሳውቀዋል፡፡
በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታቸው ትክክል ነው ወይ ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄ ‹‹አሁንም ማፈናቀሉ ቀጥሏል፡፡ አሁንም ዜጎች እየተፈናቀሉ ስለመሆኑ በተለያዩ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡ አሁንም ሰልፉን የጠራንበት ምክንያት ይህ የማፈናቀል ህገወጥ ድርጊት ባለመቆሙ ነው፡፡ እኛ እየከሰስን ያለነው ባለፈው የመፈናቀል ህገወጥ ተግባር በተፈጸመባቸው ላይ ነው፡፡ የቡለን ወረዳ ቀኑን ጠቅሶ ‹‹ስለምትፈናቀሉ ልቀቁ!›› ያለበትን ማስታወቂያና ማስጠንቀቂያዎች በመረጃነት ይዘናል፡፡ ይህ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ነው፡፡ ይህን ጥያቄ ማንሳት ደግሞ ዋነኛው ስራችን ነው፡፡›› ብለዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም ‹‹አሁን ይህ ድርጊት ከወረዳና ከክልሎች አልፎ የመንግስት ፖሊሲ ወደመሆን በመሸጋገሩ በተደራጀና ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ መታገል አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡›› ብለዋል፡፡ የሰልፉ አላማም በኢህአዴግ የፖሊሲ ችግር ላይ መሆኑን የገለጹት የህዝብ ግንኙነቱ ‹‹ኢህአዴግ መሬት የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ንብረት ነው፡፡›› በሚል ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ተዘዋውረው የመስራትና የመኖር መብታቸውን ስለገደበና በዚህ የተሳሳተ ፖሊሲ ኢትዮጵያ እንደ አገር ትልቅ ችግር እየገጠማት በመሆኑ ችግሩ ከሚደርስባቸው ዜጎች ጎን በመሆንና ሌላውን ህዝብ በማንቀሳቀስ ኢህአዴግ ሃገር የማስተዳደር አቅምም ሆነ ችሎታ እንደሌለው በማጋለጥ ስልጣኑን እንዲለቅ ግፊት ለማድረግ እንደሆነ አቶ ብርሃኑ ለነገረ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል፡፡ የክሱን ሂደትም ሚዲያውያና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲከታተሉት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Source: Negere Ethiopia
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11866/

ነገረ-ኢትዮጵያ ቅፅ 1 ቁጥር 8 (PDF)

ነገረ ኢትዮጵያ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮችን ይዛ ቀርባለች፡፡ በተለያየ ምክንያትጋዜጣዋን ኮፒ በዕለቱ ያላገኛችሁ ይኸው መረጃ ይደርሳችሁ ዘንድ በፒዲኤፍ (PDF) ለቀናታል፡፡

- ፕሮፈሰር አለማየሁ፣ ታምራት ታረቀኝ፣ ግርማ ሞገስና ታዲዮስ ታንቱ ጥልቅ ትንታኔዎችን ሰጥተውባታል፡፡
- የተማሪዎች የሰላማዊ ሰልፍ ማቆም አድማ፣ የአርሶ አደሮች ሰቆቃና ሌሎችም አዲስ ወሬዎች ተካተውባታል፡፡
- በላይ ማናዬ የብሄርፌደራሊዝሙን ቅዝምዝሞሽ ይተነትንልናል፡፡
- ዮናታን ተስፋየ ለምን ፈራን ይለናል፡፡
- እያስፔድ ተስፋዬ የስርዓቱን ሰለባዎች (ከማሞ መዘምር እስከበቀለ ገርባ ዳስሷል፼፡፡ -
- ጌታቸው ሺፈራው ኢህአዴግ ምንም እንደማያሟላ ይሞግታል፡፡
- ብርሃኑ ተክለ ያሬድ የእስር ቤት ትዝታውን አቅርቦባታል፡፡ ወጣቱ አቃቤ ህግ የፍትህ ስርዓቱ ፍትህ ያስፈልገዋል ብሏል፡፡
- የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ስራ አስኪሃጅ በደሎች ተዘርዝረውበታል፡፡
Negere Ethiopia Semayawi party newspaper issue8
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11862/

“ዘላለማዊነት ለገንዳዎች!! ዘላለማዊ ክብር ለገንዳዎች”

የድህነት ራዳር እንደ ድህነት "ክፉ" ነው

hailemariam qurt


የገንዳዎች የደራጃ መዳቢ ድርጅት ሊቋቋም ይገባል። ገንዳዎች የኑሮ መሰረት የሆኑላቸው እየበረከቱ ስለሆነ በደረጃ መከፋፈል አለባቸው። የአጠቃቀማቸውም መመሪያም በግልጽ ሊቀመጥ ይገባል። የደረጃዎች መዳቢ ድርጅት ቢያንስ በገንዳዎች ውስጥ ስለሚጣሉ ቆሻሻዎች መመሪያ በማውጣት የሚበሉ ነገሮች ከሌሎች አይነት ቆሻሻዎች ተለይተው እንዲጣሉ ማዘዝ አለበት። ከሸራተንና ከቤተ መንግስት የሚወጡ የምግብ ትራፊዎች ተጠቃሚ ጋር ሳይደርሱ ፓስተር እንዲመረመሩ የሚያዝ መመሪያ ቢወጣም መልካም ነው። ቀጭኑ ዘ-ቄራ ማሳሰቢያ አለው።
ገንዳዎች የኢህአዴግን ስራና ሃላፊነት በመወጣት ለድህነት ሰለባዎች “የላቀ” አስተዋጽኦ እያበረከቱ ስለሆነ የሽልማት ኮሚቴ ይቋቋምላቸው። ገንዳዎች በሚወጣላቸው ደረጃ መሰረት ተለይተው ይሸለሙ። የጥሬ ስጋ ተጠቃሚዎችና አንዳንድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሽልማቱን ለግል ውዳሴ እንዳይጠቀሙበት አቶ ደመቀ መኮንን የሚመሩት ተቆጣጣሪ ይመደብ። ይህ የእለቱ ጥቆማዬ ነው። ገንዳዎች ባይኖሩ ኖሮ ምን ይኮን ነበር? “ዘላለማዊነት ለገንዳዎች!! ዘላለማዊ ክብር ለገንዳዎች!!”
gendaድህነት ክፉ ነው። ድህነት ስል የሚያምረውን ድህነት አይደለም። “የሚያምር ድህነት ምንድነው?” ለምትሉ መልስ የለኝም። ስለምንግባባ!! እኔ “ክፉ” የምለው መረን የወጣውን ድህነት ነው። ገደብ የለቀቀውን ማለቴ ነው። እረፍት ነስቶ ሞራል የሚያንኮታኩተውን ነው። ሞራል አድቅቆና ሰውነትን አዝሎ አንገት የሚሰብረውን ነው። መጥፎ ጠረንን በመጠየፍ አፍንጫን ጠቅጥቆ ገንዳ ውስጥ ለጉርስ የሚያስዋኘውን አይነት ድህነት ነው። እናት ልጇን ለወሲብ ገበያ አበረታታ እንደትልክ የሚያስገድዳትን ድህነት ነው። የወለዱ የከበዱ አባትና እናትን በስተርጅና ጎዳና ላይ የሚጥለውን ድሀነት ነው …
ብዙ ጉድ፣ ብዙ ዓይነት ጓዳ አለ። መልከ ብዙ ችግር፣ መልከ ብዙ ችጋር አለ። የመከረኛዋ አገር ኢትዮጵያ ጎጆዎች ይቁጠሩት። የሚቦካ አጥታችሁ ቦሃቃ ለሰቀላችሁ፣ ሌማት ለደረቀባችሁ፣ አቁላልቶ መብላት ቅዠት ለሆነባችሁ፣ የእናት ጓዳ ለተዘጋባችሁ፣ መማሪያ ክፍል ውስጥ ርሃብ ለሚፈነግላችሁ ህጻናት፣ ጧሪ ለሌላችሁ የወግ እናትና አባቶች … ጠኔ በየጓዳው ለከነቸራችሁ … ለናንተ ሁሉ መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ። ፋሲካ … አሁን ለናንተም ፋሲካ ሊሆን ነው። ያስለቅሳል።
ቀጭኑ ዘ- ቄራ ነኝ። ዛሬ እጅግ ስሜቴ ተነክቷል። አንድ ነርስ ወዳጄ ያጫወተችኝ ትዝ አለኝና አልቅስ አልቅስ አለኝ። እሷ በምትሰራበት የግል የርዳታ ድርጅት ውስጥ የኤችአይቪ/ኤድስ ተጠቂዎች ለሆኑ በወር በወር የሚሰጥ ገንዘብ አለ /በነገራችን ላይ የርዳታ ድርጅት ራሱ ሌላ ቫይረስ አለበት/ ርዳታው የሚሰጠው ምርመራ እየተደረገ ነው። በምርመራው ቫይረሱ የሌለበት ሰው ርዳታ አይሰጠውም። “ቫይረሱ ስለሌለብዎ እንኳን ደስ አለዎ” ተብሎ ሲነገራቸው የሚከፋቸው ብዙ ናቸው። አንዳንዶቹ “በዚህም ትለዩኛላችሁ፤ ርዳታ እንዳላገኝ ነው?” በማለት ይከራከሩ እንደነበር በተረበሸ የሃዘን ስሜት ታወጋኝ ነበር። መጨረሻ ላይ በዚህ ሁኔታ መቀጠል አቅቷት ስራ ቀየረች።
በወር 200 ብር ለመቀበል ድህነት የሚያስመኘውን አስቡት፤ የት እንደደረስን ገምቱ። ድህነት “ዛሬን ብቻ ይለፈኝ” የሚባልበት ደረጃ ደርሰናል። ይህ ደረጃ አደገኛ ነው። ዛሬን ብቻ ስለማለፍ የሚያስቡ በፍጥነት እየበረከቱ ነው። ዛሬን ማለፍ ብቻ አላማቸው ያደረጉ ሲበዙ ሁሉም ነገር “በዛሬ ይባዛል” ሁሉም ለራሱ የ”ጎበዝ አለቃ” ይሆናል። የጎበዝ አለቆች … የዚያኑ ያህል ለልጅ ልጅ የሚያካብቱ ጥቂቶች አሉ። እነዚህ ሃብታቸው ሞልቶ የገነፈለባቸውና ጥጋብ ልብ የነሳቸው የሚያደርጋቸውን አሳጥቷቸዋል። እነሱ ምድሪቱ ላይ፣ ጥጋብ ደግሞ እነሱ ላይ ህንጻ ገንብተዋል። የሰበሰቡት ሃብት፣ የገነቡትና የተገነባባቸው ህንጻ በድህነት ራዳር ውስጥ ናቸው። የድህነት ራዳር እንደ ራሱ እንደ ድህነት “ክፉ” ነው። አይምሬ ነው … ድህነት ሲያመር አመረረ ነው። አገርን ሁሉ “በዛሬን ልደር” ያጣፋል።
የማጣፋት ጨዋታ አደገኛ ነው። የጎበዝ አለቆች ሲያብቡ ጨዋታ ይፈርሳል። አዲስ ጨዋታ ይጀመራል። ህግ አልባ ጨዋታዎች ይጀመራሉ። በነገራችን ላይ አሁንም ህግ አልባ ጨዋታ የሚጫወቱ አሉ። ከቻሉ ኢትዮጵያን ከህዝቧ ነጥለው በፓራሹት ወደ ሌላ ስፍራ እንዲያዘዋውሯት የተፈቀደላቸው አሉ። እነዚህ የጎበዝ አለቆች የተበደሩትን ብር እየረጩ ይዘፈንላቸዋል። ይሞካሻሉ። የፈለጉትን አጥር ዘለው የተከበረ አንሶላና ብርድ ልብስ አስገድደው ይከፍታሉ። የህሊናቸው ጠረን በሰሩት ግፍ መጠን ሸቷል። ስብእናቸው ቀርንቷል። የሰውነት ማዕረግ የላቸውም። በእርም ሃብት ህሊናቸው ተጋርዶ “ሰው እኩል ይሆናል ብር” በሚል የወደቀ የሂሳብ ቀመር ውስጥ ተነክረዋል። የድህነት ራዳር እነዚህንም ይከታተላቸዋል።Circus therapy for young homeless
“የራበው ሰው የአፍ ጠረኑ ይቀይራል” የሚል ጓደኛ ነበረኝ። ሰው የአፉ ጠረን የሚቀየረው ጨጓራው የሚፈጨው አጥቶ ሲጨስ እንደሆነ ሁሌ ይናገራል። ለጋስ ነበር። ሰው መርዳት ያስደስተዋል። ሆን ብሎ የሚጎበኛቸው ድሃ እናትና አባቶች ነበሩት። ይኸው ባልደረባዬ “ከራበው ላይ የሚዘርፉ ደግሞ ህሊናቸው ይገማል” በማለት ይጠየፋቸዋል። ዛሬ እሱም ትዝ አለኝ። ነብሱን ይማረው!!
አዎ!! በቀን ሶስቴ እንደሚበላ የተወተወተ ህዝብ በወጉ አንዴም መጉረስ ተስኖታል። ከ22 ዓመት በኋላም ስለ ጉርስ ሳይሆን ስለ “ውርስ” ነው የምንሰማው። በቂም በቀል ዜጎች ከስራ እንዲባረሩ የወሰነ “ውርስ” ለማስተዋወቅ፣ ለመዘከር፣ መታሰቢያውን ለመትከል በጀት ከድሃ ጉሮሮ እየተነጠቀ ይፈስለታል። በቁም ድህነት ነቃቅሎ ያፈረሳቸው እያሉ ለሞተው ቂመኛ መንፈስ ግብር ይገባል። አዶ ከርቤ ይባላል። የኢትዮጵያን ታሪካዊ ፋይዳና ሚስጥራዊ የባህር በር ላዘጋ መንፈስ ስግደት … ቀጭኑ ጥያቄ አለው። ጥያቄው አንድ ነው። ከሙት መንፈስና ከነዋሪ የቱ ይብሳል። ለየቱ መገበር ይቀላል። የቱ ተግባር ህሊናን ያሸታል ወይም ያለመልማል?
አንድ ሳሪስ አዲስ ጎማ ሀዲዱ አካባቢ ያገኘሁት እብድ ትዝ አለኝ። ስለመቆም ይለፈልፋል። “የቆሙ የሚመስላቸው ብዙ ናቸው፣ ግን አልቆሙም። ያልቆሙት መቆም ስለማይፈልጉ አይደለም …” በፍጥነት ይናገራል። ይደጋግማል። “… መቆም እንዴት እንደሆነ ስላላወቁ ነው። መቆም የራሱ ምስጢር አለው። አንተ ግን ተደገፍ፣ ተደጋገፍ፣ ብቻህን አትቁም፣ እንኳን ሰው እንጨት ይደግፋል። ክራንች ይደግፋል። ብቻህን ከምትቆም …” ይናገራል። የስብከት አይነት ነው። ይሰብካል። “አንተ ግለኛ ሁሉ። ሆዳም ሁሉ። ስማ” እያለ ይጮሃል። ስለመብላት ሲናገር “የሞተ ነገር የምትበሉ ሁሉ” ይላል። ለምን እንደዚህ እንደሚል በወቅቱ አልገባኝም። ግን ታላቅ ነገር እንደተናገረ ሁሌም አስባለሁ። አዎ!! መደገፍ። እንኳን ህዝብ እንጨትም ምርኩዝ ይሆናል። ኢህአዴግ ድጋፉ ጠብ መንጃ ነው። ታንክና አጋዚ ነው። ፌደራል ሰራዊትና ስለላው ነው። ለዚህ ሁሉ ብር ይፈሳል። በህዝብ ተደግፎ ገንዘብ በመቆጠብ ጠኔ ለሚደፋቸው ማዋሉ አይቀልም? የህሊና መሽተትና መዋብ እዚህ ጋር ይነሳሉ። ድህነትም የሚያቅራራው እዚህ ወሳኝ ነጥብ ላይ ነው። ክፉ ነዋ!! ሲነሳበት ራዳሩን ሲያበራው … ዋ! ያኔ!! ሳይቃጠል በቅጠል አሉ!!
ስለ ጡረተኞች አስባችሁ ታውቃላችሁ። እንደው ለብቻቸው ገበያ የሚገበዩበት ስፍራ አላቸው? የነሱና የቤተሰቦቻቸው ፍላጎት በቀዶ ጥገና ተኮላሽቷል? አንዴ አንዲት አሮጊት እናት እንዲህ አጫውተውኝ ነበር። በደርግ ስርዓት አንድ ያከራዩት የጭቃ ቤት “ትርፍ ሃብት” ተብሎ ተወሰደባቸው። አበል 7 ብር ከሃምሳ አላቸው። ኢህአዴግ ገብቶ 18 ዓመት እስኪሞላው ገቢያቸው ያቺው 7 ብር ከሃምሳ ነበረች። በየወሩ ደሞዝ ለመቀበል ቀበሌ ሄደው ይሰለፋሉ። ደሞዝ!! እኚህ እናት ብዙ ብለውኛል። መፈጠርን የሚያስጠላ የድህትን ወለል አሳይተውኛል። ለነብስ ያሉ እየረጠቧቸው እንጂ እሳቸው የአንድ ጎልማሳ ዘመን ሸምተው አያውቁም። መለስ እኚህን አዛውንት ጨምሮ ነበር “በቀን ሶስቴ አስበላችኋላሁ /ይቅርታ አበላችኋለሁ/” ሲል የዋሹት። የቂም ፖለቲካ ምህንድስናው ወጥሮ ይዟቸው እንደሁ አላውቅም። እንደወጋችን እዚህ ላይ ነብስ ይማር ማለት አይቻለኝም። መለስን ነብስ ይማር ካልኩ፣ ኑሮ አድቅቆ ለሞት ያስረከባቸውን እናት ምን ልላቸው ነው? ከፈለጋችሁ ታዘቡኝ!!
ጅቡቲ እጇን አጣጥፋ ትበላለች። ቀን የጅቡቲ ጭሰኛ አደረገን። ቂምና የበታችነት መንፈስ ለጅቡቲ አምበረከከን። ጅቡቲ የለፋንበትን እየሰበሰበች ትገምጣለች። “እያንጓለለ” ይላል ይህ ነው። የተንኮል ፖለቲካ!! ጅቡቲን የሚያስፈስክ ሲስተም … አሁን ፋሲካ ነው። ለክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ሁሉ ፋሲካ ታላቅ በዓል ነው። ከላይ በመግቢያዬ ለጠቀስኳችሁ ሁሉ ምን እንደምመኝ አላውቅም። የፋሲካው ጌታ መላ ይበላችሁ። ከፋሲካው ጌታ በላይ ጌቶች ፈጥራችሁ በውርስ አምልኮ ለታሰራችሁ፣ ህሊናችሁ ለሸተተ፣ ልቡናችሁ በትዕቢትና በጥጋብ ለተወጠረ የፋሲካው አምላክ ይርዳችሁ!! የሞተ/አርዶ ለመብላት ካሁኑ መደራጀት የጀመራችሁ ግራና ቀኙን እዩ። የድሆች ራዳር በስራ ላይ ነውና!! እስከዛው ግን “ዘላለማዊ ክብር ለገንዳዎች”… እስኪ እንረፍ። መልካም እረፍት!! ቀጭኑ ዘ – ቄራ!
http://www.goolgule.com/eternal-adoration-to-dumpsters/

Tuesday, April 15, 2014

በስደትም መሰለል – በኖርዌይ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሰሙ

“እነሱ ሁለት አገር አላቸው፤ እኛ አገር አልባ ሆነናል”

1


የኢህአዴግን የስለላ መዋቅርና አካሄድ አስመልክቶ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ተበራክተዋል። ኢህአዴግ ራሱን እንደሚስለው ዓይነት ድርጅት ሳይሆን በሰብዓዊ መብት አያያዝ ጉድለት ያለበት፣ በሚዲያ ነጻነት ኋላ ቀር፣ የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን በማሳደድ ግንባር ቀደም፣ አፋኝ ህግ በማውጣትና በማሸማቀቅ ወደር የማይገኝለት፣ ለሚያወጣው ህግና ደንብ የማይገዛ፣ የውስጥ ችግሩ ታይቶ በማይታወቅ መጠን ዜጎችን ለስደት እየዳረገ እንደሆነ እየተመሰከረበት ነው።
ኦባንግ ሜቶ
ኦባንግ ሜቶ
ኢህአዴግን ሸሽተው አገር ለቀው የተሰደዱ በስደት ምድርም ኢህአዴግ እየተፈታተናቸው እንደሆነ መግለጽ ከሰነበቱ ቆይቷል። በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በጀርመን፣ በስዊድንና በእንግሊዝ አገር ስደተኞችን በመሰለል ተግባር ላይ የተሰማሩ “የስደተኛ ሰላዮች” በስፋት ስለመኖራቸው መረጃ ማቅረብ እንደሚችሉ የሚገልጹ ጥቂት አይደሉም። የተለያዩ ድርጅቶች በዚህ ጉዳይ ምን ያህል እንደገፉበት መረጃ ባይወጣም አቶ ኦባንግ ሜቶ የሚመሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ስራውን ያገባቸዋል ከሚላቸው ክፍሎች ጋር እየሰራ እንደሆነ በዚሁ መድረክ መገለጹ ይታወሳል። በወቅቱ አቶ ኦባንግ “ስደተኛ ሆኖ ስደተኛን መሰለል በህግ የተከለከለ ወንጀል ነውና በዚህ ጉዳይ ርህራሄ ሊኖር አይችልም” ነበር ያሉት።
ማርች 11 ቀን በኖርዌይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር አስተባባሪነት ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዶ ነበር። በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የፓርላማ ተወካይ፣ የኖአስና/NOASና ዘረኝነትን የሚቃወመው ድርጅት መሪ ተገኝተው ነበር። በሰላማዊ ሰልፉ ተገኝተው ንግግር ካደረጉት መካከል ወ/ት የሺሃረግ በቀለ ይጠቀሳሉ። በኖርዌይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር ጸሐፊ ወ/ት የሺሃረግ በቀለ “እነሱ አገር ቤትም አገር አላቸው፤ በስደትም አገር አላቸው” በማለት ነበር ለጎልጉል አስተያየታቸውን መስጠት የጀመሩት።
yeshihareg
የሺሃረግ በቀለ
በሰልፉ ላይ ካቀረቡት ንግግር በተጨማሪ ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡት ጸሐፊዋ፣ ስደተኞች ሁሉ አንድ አይደሉም። “ሆን ተብሎ የስደት መረጃና ማስረጃ ማመልከቻው ተመቻችቶላቸው የሚላኩ የወያኔ ቅጥረኛ ሰላዮች አሉ። እነሱ ባለሁለት አገር ናቸው። እኛ አንድም አገር የለንም” ብለዋል። ይህንን ጉዳይ አቅም በፈቀደ ሁሉ ማህበሩ ከአባላቱና ድጋፍ ከሚሰጡት ሁሉ ጋር በመሆን ከዳር እንደሚያደርሰው ገልጸዋል።
“ልብ እንበል” በማለት አስረግጠው የገለጹት ስለ ሁለተኞቹ ስደተኞች ነው። ስርዓቱ ባለው የግፈኛነት፣ የዘረኛነት፣ የከፋፋይነት፣ የዴሞክራሲና የነጻነት እጦት የገፋቸው እውነተኛ ስደተኞች ባግባቡ መልስ ያለማግኘታቸው ጉዳይ ነው። “እነዚህ እውነተኛ ስደተኞች እኔን ጨምሮ አገር የለንም” ሲሉ አገር አልባ የመሆንን ስሜት ይገልጻሉ። ወ/ት የሺሃረግ የኖርዌይ ሚዲያዎችና በስለላ ተግባር የተሰማሩ “ስደተኞች” እንዳሉ በይፋ ቢናገሩም መንግሥት መልስ አለመስጠቱ ቢያሳዝናቸውም ማህበራቸው ትግሉን ይበልጥ እንዲገፋበት እንዳደረገው ነው የሚናገሩት።
የዲሞክራሲ ለውጥ ድጋፍ ሰጪ በኖርዌይ ተወካይ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ያረጋገጡትን በመጥቀስ ወ/ት የሺሃረግ የትግሉን መደጋገፍ አመላክተዋል። ድጋፍ ሰጪው መረጃ የማሰባሰብ ስራውን ማጠናቀቁን ማረጋገጡ፣ የስደት ከለላ ካገኙ በኋላ በስለላ የተሰማሩትን ክፍሎች አደባባይ ለማውጣት የሚደረገውን ትግል እንደሚያፋጥነው ከምስጋና ጋር እምነታቸውን ገልጸዋል።
3ማህበራቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ባሉበት ሁሉ ወኪሎችን በመሰየም የግንኙነት መረብ መፍጠሩን ያመለከቱት ጸሐፊዋ፣ የግንኙነት ሰንሰለቱ መረጃዎችን በቅርብ ለመሰብሰብ እንደሚረዳ አስታውቀዋል። ላለፉት ሰባት ዓመታት የስደት ማመልከቻቸው አዎንታዊ መልስ እንዳላስገኘላቸው የጠቆሙት ወ/ት የሺሃረግ፣ “እንደ እኔ አይነቶች ብዙ ነን። ከኔም የሚብሱ አሉ። ከሚደርስብን የማህበራዊ ችግር በተደራቢ ካገራችን እንድንባረር ያደረጉን ሰዎች እዚህም እረፍት ሊነሱን አይገባም። አገር አልባ መሆን ያሳዝናል። እዚህ ኖርዌይ የተወለዳችሁ ወገኖችም ብትሆኑ ስደተኞች ናችሁና በመረጃ ማሰባሰቡ ስራ ተባበሩን” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል። ቀደም ሲል ለተባበሩትም ምስጋና አቅርበዋል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሙያዊ ምክርም ሆነ አግባብነት ያለው አስተዋጽዖ ለማበርከት ለሚፈልጉ ሁሉ ማህበራቸው በሩ ክፍት እንደሆነም ተናግረዋል።
በኖርዌይ የኢትዮጵያዊ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር አቶ ፋሲል አለባቸው በበኩላቸው በተጠቀሰው ቀን ለተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጡ ገልጸዋል። “ሆን ተብሎ የስደት መረጃና ማስረጃ ተመቻችቶላቸው የሚመጡት ሰላዮች የስደት ሂደቱን በማበላሸት እውነተኛ ስደተኞች የከለላ ምላሽ እንዳይሰጣቸው ያደርጋሉ። በዚህ ዜጎች ተጎድተዋል” ሲሉ ለጎልጉል ገልጸዋል።
“እነዚሁ የተመቻቸላቸው ስደተኞች መልስ ካገኙ በኋላ ሆን ብለው ወደ አገራችን መመለስ እንፈልጋለን በማለት የስደተኛ ጉዳይ ለሚያስተናግዱት ክፍሎች የተሳሳተ መረጃ በመስጠት የሌሎች ስደተኞችን ጉዳይ በማበላሸት ስራ ይሳተፋሉ” የሚሉት አቶ ፋሲል አንዳንዴም የተሳሳተ መረጃና የተሳሳተ ምክንያት እንዳቀረቡ በመግለጽ እውነተኛ ስደተኞች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፍ የሚችል ተግባር እንደሚፈጽሙ አመልክተዋል።2
ከዚህ በተለየ መልኩ ገንዘብ በመላክ /በሃዋላ/ ስራ የተሰማሩ ሰዎች እንዳሏቸው የሚገልጹት አቶ ፋሲል፣ “ወያኔዎቹ ገንዘብ በመላክ ስራ ባሰማሯቸው ሰዎች አማካይነት አገር ቤት ያሉትን ቤተሰቦች በመለየት እንደሚያስፈራሩ ይታወቃል” ሲሉ የትግሉን አስፈላጊነትና ከስደተኞች ማህበር ጥሪ ጎን ስለመቆም ይናገራሉ።
ኮሚኒቲው ለወገኖቹ ጉዳይ ዘወትር እንደሚያደርገው ሁሉ አሁን ለሚደረገው ትግል ከድጋፍ መስጠት ባለፈ አብሮ ለመስራት ዝግጁ እንደሆነ ያሳሰቡት አቶ ፋሲል፣ ማንም ቢሆን ለህግ ሊገዛ እንደሚገባ በሚያስገድድ ስራ ላይ መሰማራት እንደሚኖርበት አመላክተዋል። በማያያዝም አሁን ወደ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ወደ ማህበረሰቡ፣ ወደ አክቲቪስቶችና አቅም ያላቸውን ክፍሎች ግንዛቤ የማስጨበትና ጉዳዩን አጀንዳ አድርጎ የመትከል ስራ ላይ ትኩረት ተደርጎ ስራው እንደሚሰራ አስረድተዋል።
ወ/ት የሺሃረግ የመረጃ ማሰባሰቡ ስራ ሲጠናቀቅ ጉዳዩን ከኖርዌይ የፍትህ ተሟጋች አካላት ጋር በመሆን አስቀድሞ ለፍትህ ሚኒስትር፣ በመቀጠልም በየደረጃው ለሚመለከታቸው ክፍሎችና ለዓለም አቀፍ ተቋማት የማሳወቁ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለጎልጉል ተናግረዋል።
4በሰላማዊ ሰልፉ የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ሃሳቡን የደገፉ ተገኝተዋል። አቶ መለስ ለመጨረሻ ጊዜ ኖርዌይ በመጡ ጊዜ የተፈጠረውን ጉዳይ በማስታወስ የስደተኞች ማህበር ቢዘገይም አሁን የደረሰበት ደረጃ ሊበረታታ እንደሚገባ የጠቆሙ አሉ። ስቴንሻዬር የስደተኞች ካምፕ “ስደተኛ” ተብሎ ተመዝግቦ የነበረ እብድ ወጣት አብረውት ካምፕ የሚኖሩ አገር ቤት ያለውን ስርዓት በመቃወም ለህዝብ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ሲሰሩ አብሯቸው ይሳተፍ ነበር። ሲሰለፉና ህወሃትን ሲያወግዙ፣ ኢህአዴግን ሲቃወሙ፣ አብሮ በመሆን እየተቃወመ ቪዲዮ ይቀርጽ ነበር። በመጨረሻ በድንገት ተነስቶ አገር ቤት ተመለሰ።
የልጁ በድንገት መሰወር ያሳባቸው የካምፑ ነዋሪዎች ሲያጣሩ በስም የጠቀሱት ሰው አዲስ አበባ መመለሱ ተረጋገጠ። ከወራት በኋላ አቶ መለስ ኦስሎ ሲመጡ ይኸው ሰው ኦስሎ ተገኘ። በማለት የጠቆሙት ክፍሎች ይህንን ጉዳይ ፖሊስ እንደሚያወቀው፣ ማመልከቻ እንደገባለት አብረውት የነበሩት አሁን ድረስ በስጋት ላይ እንዳሉ ይገልጻሉ።
http://www.goolgule.com/eprdf-tplf-spying-ethiopians-in-norway/

Monday, April 14, 2014

በወላይታ ዞን አፈናና ወከባው ቀጥሏል


wolayta


መጋቢት 20/ 2006 ዓ.ም ሶዶ ውስጥ ስብሰባ ለማድረግ ዝግጅት እያደረጉ በነበረበት ወቅት ለእስር የተዳረጉት የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ድብደባና ወከባ እንደተፈጸመባቸው የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ጌታነህ ባልቻ ገለጹ፡፡
በወቅቱ ታስረው ከነበሩት መካከል ወጨፎ ሳዳሞ የወላይታ ዞን ምክትል ሰብሳቢ፣ ታደመ ፍቃዱ የወላይታ ዞን አደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ፣ አቶ ጻድቁ ወ/ስላሴ የወላይታ ዞን የፋይናንስ ኃላፊ፣ አቶ ቴዎድሮስ ጌታ የዞኑ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ እና አቶ ቦጋለ የፓርቲው አባል ይገኙበታል፡፡ ጠዋት 4 ሰዓት ላይ የታሰሩት የዞኑ አመራሮች ምግብ፣ ውሃና ልብስ እንዳይገባላቸው ተከልክሎ እንደነበርም የአካባቢው አመራሮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
“ከዚህ በፊት ሁለት የፓርቲው አመራሮች በአራዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ለፓርቲው ስራ የሚገለገሉባቸውን ሰነዶች ተወስዶባቸዋል፡፡ የዞኑን መዋቅር ለመጎብኘት ከአዲስ አበባ ወደ አካባቢው የተጓዙ ሶስት የፓርቲው አመራሮችና የአካባቢው ተወካዮች ታስረው ስራቸው ከመስተጓጎሉም ባለፈ መገልገያ እቃዎቻቸውን ተቀምተዋል፡፡” ያሉት አቶ ጌታነህ በአሁኑ ወቅት የሚደረገው እስርና ወከባ ከቀደመው የቀጠለ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ቅዳሜ መጋቢት 20 የታሰሩት የወላይታ ዞን የፓርቲው አመራሮች ከምሽቱ 4፡00 አካባቢ ከእስር ቢለቀቁም ሲም ካርዳቸውን በመስበር ከጥቅም ውጭ እንዳደረጉባቸው እና በራሪ ወረቀቶችን፣ ሰነዶችንና ሌሎች የመገልገያ መሳሪያዎችንም እንደቀሟቸው ታውቋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በምሽት የተፈቱት ታሳሪዎች ወደ ቤታቸው በሚያቀኑበት ወቅት የአራዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ታጠቅ፣ በሶዶ ከተማ የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር አቶ ጌታቸው መኮንን፣ የአራዳ ክ/ከተማ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ዝናቡ ተክሌ፣ የአራዳ ክ/ከተማ ደንብ አስተባባሪ አቶ መስከረም፣ እንዲሁም አቶ ተሾመ፣ አቶ ደጉና ሌሎች ማንነታቸው ያልታወቀ ሰዎች የሰማያዊ ፓርቲ ወላይታ ዞን አደረጃጀት ኃላፊ የሆነውን አቶ ታደመ ፍቃዱ እና የዞኑ ም/ሰብሳቢ የሆነውን አቶ ወጨፎ ሳዳሞ በመደብደብ ጉዳት እንዳደረሱባቸው ከአካባቢው መዋቅር የተገኘውን መረጃ በመጥቀስ አቶ ጌታነህ ባልቻ ለዝግጅት ክፍላችን አስረድተዋል፡፡ (ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ)
http://www.goolgule.com/intimidation-and-harassement-continues-in-wolayitta/

የመምህራን ፍዳ

(በላይ ማናዬ)

teacher1


‹‹እኔ ጆርጅ ቡሽን (ፕሬዚዳንት) አላደንቅም፤ ጠፈር ላይ የወጡትንም አላደንቅም፡፡ የማደንቀው እነዚህን ሰዎች ለትልቅ ደረጃ ያደረሷቸው መምህራንን ነው፡፡››
መምህራን የሀገር ምሰሶዎች… መምህርነት የሙያዎች አባት… መምህር የእውቀት ብርሃን…ይህ እውነት ነው፡፡ እውነቱ ግን ዛሬ ላይ ተጋርዷል፡፡ መምህርነትም ሆነ መምህራን የነበራቸው ክብር ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ መሬት በአስደንጋጭ ፍጥነት እየወረደ ይገኛል፡፡ መምህራን በሙያቸው እያፈሩ ነው፡፡ እውቀታቸውን እየሰሰቱ ነው፡፡ አዎ፣ መምህራን ጫንቃቸው ጎብጦ ነገን በደበዘዘ ተስፋ የሚጠባበቁ ‹ምስኪኖች› እየሆኑ ነው፡፡ ግን እንዴት?
ካድሬነት Vs መምህርነት
ወጣት ነው፤ ገና ለስራው ዓለም ብዙ አበርክቶት የሚጠበቅበት፡፡ ወጣቱ በአዲስ አበባ አብዮት ቅርስ መሰናዶ ት/ቤ የኬሚስትሪ መምህር ነው፡፡ በስራው ዓለም ለአራት ዓመታት ያህል ቆይቷል፡፡ በእነዚህ ዓመታት ግን የሚሽተው ሙያዊ ተግባሩን ለመወጣት ከብዶታል፡ ፡ መምህርነቱን የሚፈታተኑ በርካታ ጉዳዮች እየተፈራረቁበት ተቸግሯል፡ ፡ ወጣቱ ትዳር መሥርቶ፣ ወልዶና ከብዶ መኖር ቀርቶ ጥሩ ጫማና ልብስ ገዝቶና ጥሩ ምግብ ተመግቦ ለመኖር እንኳ እንዳቃተው ይናገራል፡ ፡ ከተማሪዎቹ በታች እየሆነ የሚታይበትን የኑሮ ጫና መቋቋም እንደተሳነውም ይገልጻል፡፡ በዚህ ሁኔታም ሆኖ ማስተማር ይፈልግ ነበር፡፡ ዳሩ ግን መምህርነቱ ከዚህም በላይ ፈተና አሳይቶታል፡፡ ነጻነቱን ነፍጎታል፡፡
የፖለቲካ ሰዎች (ካድሬዎች) የሚያስተምርበት ድረስ እየሄዱ ተጽዕኖ ያደርጉበታል፡፡ ት/ቤቶች የእውቀት ማበልፀጊያና መጋሪያ ደጆች ቢሆኑም አሁን አሁን ስልጣን ፈላጊዎች መናሃሪያ አድርገዋቸዋል፤ የፖለቲካ ማዕከላት ሆነዋል፡፡
ወጣቱ መምህር ይናገራል፤ ‹‹… የኢህአዴግ ካድሬ ካልሆንክ ችግር ነው፡፡ ካድሬነት ወደህ የምትገባበት ሳይሆን ካድሬ ባለመሆንህ ከሚደርስብህ አድሎአዊ አሰራር ለማምለጥ ብለህ የምትገባበት ሲኦል ሆኗል፡፡ መምህርነት መሰረቱ እውቀት ነው፡፡ አሁን ግን ያ አይደለም መሰረቱ፤ ካድሬነት ነው፡፡ በእውቀት ላይ ብቻ ተመስርቼ አስተምራለሁ ካልክ በድህነት እያከክ ትኖራታለህ፡፡ አንድ ተራ ካድሬ ከአንተ በላይ ገንዘብ ይከፈለዋል፡፡ እናም ብታምንበትም ባታምንበትም ካድሬ ሆነህ ወደ ቀበሌ ከተሾምክ ደመወዝህ 4000 ብር ይደርሳል፡፡ መምህርነት ላይ ከቆየህ ግን ይህን ደመወዝ በ20 ዓመት እንኳ አትደርስበትም፡፡››
እንደ ወጣቱ ገለጻ መምህራን ሙያቸውን አሻሽለው ነገን በተስፋ ለማለም አልታደሉም፡፡ በሙያቸው ክብርን አያገኙም፡፡ ወርን ጠብቃ ከምትመጣ መናኛ ደመወዝ በቀር ሌላ ማበረታቻ ጥቅማጥቅሞች የላቸውም፡ ፡ በእርንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ደግሞ መምህራን ከተማሪዎቻቸው ሳይቀር የሚደርስባቸው ንቀትና ማንጓጠጥ እየጨመረ ይገኛል፡ ፡ ‹‹የሚገርምህ አንዳንድ ተማሪዎች ከመምህራን በላይ ስልጣን አላቸው፡፡ ያዝዙሃል ማለት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም ካድሬ ተማሪዎች በዝተዋል፤ የተማሪ ደህንነቶችም አሉ፡፡ ስለምታስተምረው ነገር ነጻነት የለህም፡፡ ይህ መምህራንና ተማሪዎች እርስ በእርስ እንዳይግባቡ እየተገነባ ያለ የበርሊን ግንብ ነው፡፡
‹‹ተማሪ መምህሩን እየደበደበ እንዴት ማስተማር ትችላለህ…ለምሳሌ በቅርብ ጊዜ በተማሪ ድብደባ የደረሰበት አንድ መምህር ኮማ ውስጥ ይገኛል፡ ፡ የተማሪ ወላጆችም እኛ መምህራንን እንደ ተላላኪ ነው የሚያዩን፡፡ ምን ታደርጋለህ…አንዱ ልጅ አንዱ የእንጀራ ልጅ የሆነበት ስርዓት ለዚህ አበቃን፡፡ እንደ ባለሙያ ሳይሆን እንደ ሎሌ ነው እየታየን ያለነው፡፡››
ሌላው ያነጋገርኩት መምህር በእንጦጦ አንባ ት/ቤት ታሪክ ያስተምራል፡፡ መምህሩ ቀደም ብሎ የተጠቀሰውን የባልደረባውን አባባል ይጋራል፡፡ ት/ቤቶች የፖለቲካ ማዕከላት እየሆኑ መምጣታቸውንም ይጠቅሳል፡፡ ‹‹…የኢህአዴግ መሰረታዊ ድርጅት የሚባሉ የአደረጃጀት አባላት ት/ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ስብሰባ የሚያደርጉት ት/ቤት ውስጥ ነው፡፡ ለድርጅት ስብሰባ ተብሎ የትምህርት ጊዜ ይባክናል፤ የት/ቤት ንብረት ለፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ይውላል፡ ፡ የተማሪ አደረጃጀት የሚባል ነገርም አለ፡፡ በትምህርት ሽፋን የፖለቲካ ስራ የሚሰሩባቸው ናቸው፡፡››
እንደ መምህሩ አባባል፣ መምህራን ሁለት ሚዛን ላይ ሆነው ነው የሚመዘኑት፡፡ የኢህአዴግ አባል የሆኑት በአንድ ወገን፣ አባል ያልሆኑት በሌላ ወገን፡፡ በዚህም አባል ያልሆኑ መምህራን ከሌላው የበለጠ አስተዳደራዊ በደል ይደርስባቸዋል፡ ፡ በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ እየተለኩ ጫና ይደረግባቸዋል፡፡ ‹‹አንድ ለአምስት የሚባል አደረጃጀት አለ፡፡ መምህራንን በአመለካከታቸው ልዩነት ‹ታርጌት› ይደረጉበታል፡፡ ይህ አንድ ለአምስት የሚባለው አደረጃጀት የፖለቲካ ስራውን ለመከወን የተዘየደ መረብ ነው፡፡ አንዱ አንዱን እየሰለለ እርስ በእርሱ መተማመንን እንዳያጎለብት ነው እንዲህ የተደረገው፡ ፡ በእውነት ት/ቤቶች ዋና የፖለቲካ ማዕከላት እንደሆኑ ደግሜ ደጋግሜ ልነግርህ እችላለሁ፡፡››
የደመወዝ ማነስ፣ መገለልና ንቀት
ደመወዝና መምህራን አልተገናኙም፡፡ ጭማሪ ተደረገላቸው ሲባልም የይስሙላህ ይሆናል፡፡ ለአብነትም 2004 ዓ.ም ላይ መንግስት ለመምህራን የደመወዝ ጭማሪ አደረኩ ብሎ የጨመረውን መጠን ማስታወስ ይቻላል፡፡ የዛኔው የደመወዝ ጭማሪ የመምህራንን ሕይወት የሚለውጥና የሚያሻሽል ሳይሆን ክብረ ነክ እንደነበር ይታወሳል፡፡ እናም የተደረገው ጭማሪ ለመምህራን የማይመጥን እንደነበር በመግለጽ ተቃውሟቸውን ያሰሙ መምህራን (በተለይ በአዲስ አበባ) እንደነበሩ የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ከመንግስት የተሰጣቸው ምላሽ ግን ህገ-ወጥ ተብለው ከስራ መሰናበት ነበር፡፡
የመምህራኑ ጥያቄ ግን ተገቢነት ነበረው፡፡ የኑሮ ውድነቱ እየጦዘ ባለበት ወቅት የሰባ ሦስት ብር ጭማሪን ከቁምነገር ቆጥሮ ‹ጭማሪ ተደረገላቸው፤ ጭማሪውም ህይወታቸውን ይለውጣል› እያሉ መልፈፍ በመምህራን ሞራል ላይ ክፉኛ መዘባበት ነበር፡፡ መምህራንም ይህን ሐቅ ይዘው የስራ ማቆም አድማ ሳይቀር አድርገው ነበር፤ ሰሚ አላገኙም፡፡
teacher1መምህራን አሁንም ዝቅተኛ ተከፋዮች እንደሆኑ ነው የሚናገሩት፡ ፡ አንድ መምህር በሶስት ዓመት አገልግሎት 1700 ብር ገደማ ይከፈለዋል፡፡ ከዚህ ወርሃዊ ገቢ ላይ በትንሹ 800 ብር የቤት ኪራይ ይከፍላል፤ ግብር አለ፤ የተለያዩ መዋጮዎችም ይቀነሱበታል፡፡ ‹‹በቸርነቱ እንጂ ገቢያችንማ ሊያኖር የሚችል አይደለም፡፡ መምህር በነጻ እየሰራ እንደሆነ ነው የማምነው፡፡›› ይላል የአብዮት ቅርስ መምህሩ፡፡
የገቢ ልክ ማነስ መምህራን በማህበረሰቡ ዘንድ ያላቸውን ቦታ ዝቅ እንዲል እንዳደረገ መምህራን ይናገራሉ፡፡ ‹‹እንደድሮው ሳይሆን አሁን ላይ መምህራን በማህበረሰቡ ዘንድ እጅግ ዝቅተኛ ተቀባይነት ነው ያለን፡፡ መምህር በምንም ሁኔታ ከተማሪው ተሽሎ መታየት አልቻለም፡፡ እስኪ አሁን ከተማሪና ከአስተማሪ የትኛው ነው ላፕቶፕ በእጁ የሚገኘው…ተማሪው ነው፡፡ መምህራን ላፕቶፕ እንኳ መግዛት ይከብዳቸዋል፤ ሳያስፈልጋቸው ቀርቶ ግን አልነበረም የማይገዙት፡፡››
እንደመምህራኑ ከሆነ ማህበረሰቡ ለመምህራን ቦታ አጥቷል፡፡ ‹‹መምህር የተናቀበት ማህበረሰብ ፈጥረናል፡፡ ወዴት እያመራን እንደሆነ አይገባኝም፡፡ ያለመምህር አንዲት ሀገር ወዴትም ልትደርስ አትችልም፡፡›› በእርግጥም መምህራን ቀደም ባለው ጊዜ የነበራቸው ክብር ከፍተኛ ነበር፡፡ እንዲያውም፡-
የእኛ ሙሽራ ኩሪ ኩሪ
አገባሽ አስተማሪ፤ ወሰደሽ አስተማሪ፤
ይባል ነበር፡፡ ‹‹…ዛሬ ላይማ ገና መምህር መሆንህ ሲታወቅ ሰው ይሸሽሃል፡፡ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ለምሳሌ ተማሪዎች ሁሌም መምህሩን እያዩ ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡ መማርን ሲያስቡ የተማረውስ የት ደረሰ ብለው ይጠይቃሉ፤ የመምህሩን ህይወት በአጠገባቸው ያያሉ፡፡ ብዙ ተማሪዎች ወደ አረብ ሀገራት ለመሄድና መንጃ ፍቃድ ለማውጣት የሚያስችላቸውን ደረጃ ነው የሚያልሙት፡፡ ተስፋ አይታይባቸውም፡፡ ለምን አትምሩም የሚል መምህር ካለም አንተ የት ደረስክ ብለው ነው የሚጠይቁት፡፡›› ይላል የእንጦጦ አምባ መምህሩ፡፡
የአብዮት ቅርስ ወጣት መምህሩ በበኩሉ፣ ‹‹መምህራን የምንኖረው በኩሽና ቤትና በሽንት ቤት ውስጥ ነው ማለት እችላለሁ፡፡ ጥራት ሳይሆን ዋጋ የሚቀንስ ቤት ነው የምንፈልገው፡ ፡ ገንዘብ የለማ! ይህን ህይወታችንን ደግሞ ተማሪዎች ያያሉ፡፡ ምክንያቱም መምህሩ የሚኖረው በተማሪ ወላጆች ቤት ተካራይቶ ነው፡፡ የወረደ የሚባል ኑሮ ሲኖር እያዩ እንዴት መምህሩን ማክበር ይቻላቸዋል?›› ሲል ይጠይቃል፡፡
ይህ ሁሉ በመምህራን ላይ ለምን?
ያነጋገርኳቸው መምህራን መንግስት ሆን ብሎ መምህራንን የማዳከም ስራ እየሰራ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ አንድ ፀሐይ ጮራ ት/ ቤት የሚያስተምር የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህር እንዲህ ሲል ይገልጻል፤ ‹‹የመንግስት ዓላማ መምህራንን ከማንኛውም ለውጥ ለማግለል ነው፡፡ በቀደመው ጊዜ መምህራን ግንባር ቀደም የለውጥ ጠንሳሾችና አንቀሳቃሾች ነበሩ፡፡ በራሳቸው መብታቸውን ያስከበሩና ለሐገርም አለኝታ ነበሩ፡፡ ይህም የሆነው መምህራን በራሳቸው የቆሙ ስለነበሩ ነው፤ በገቢም በእውቀትም ጥሩ ደረጃ ላይ ይገኙ ስለነበር ነው፡ ፡ ስለሆነም ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ማንሳት ይችሉ ነበር፡፡ አሁን ግን ስለዕለታዊ ዳቦህ ብቻ እንድታስብ ነው የተፈለገው፡፡ የመብት ጥያቄ ለማንሳት እንዳይቻለን አድርገው ነው የያዙን፡፡››
በእርግጥም አብዛኛውን ጊዜ በማንኛቸውም የለውጥ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መምህራን ይኖራሉ፡ ፡ ራሳቸው ነቅተው ማህበረሰቡን በማንቃት የመብትና የዴሞክራሲ ጥያቄዎችን በማንሳት መምህራን ግንባር ቀደሞች ናቸው፡፡ ለአብነትም በኢትዮጵያ አብዮት ወቅት መምህራን ተማሪዎችን በማስተባበርም ሆነ በራሳቸው ተደራጅተው በመንቀሳቀስ ጉልህ ድርሻ ነበራቸው፡፡
ስለዚህም መምህራን አሁንም ለስርዓቱ የማይመቹ ሊሆኑ እንደሚችሉ ኢህአዴግ የተገነዘበ ይመስላል፡፡ ‹‹…ስለዚህ መምህራንን አጥብቆ መያዝ አለበት፡፡ በገቢም በፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችም መምህራን ከእጁ እንዳይወጡ መንግስት ሆን ብሎ የሚሰራ ይመስለኛል፡፡ እንዲያውም አንድ ለአምስት ይህን ለመቆጣጠር የተዘረጋ ነው፡፡ ስለሀገርህ ለውጥ እንዳትወያይ ተራ አጀንዳ በየጊዜው እያወረደ በስራ ይጠምድሃል፡፡ በገቢ እንዳትደረጅ ከልክሎሃል፡፡ ድሮ መኪና ያለው መምህር ነበር፡፡ የራሱ ቤት ነበረው፡ ፡ ሱፍ ለባሽ ነበር፡፡ አሁንስ? አሁን ይህ ሁሉ እንዲኖርህ አይፈለግም፡፡›› ይላል የፀሐይ ጮራ ት/ቤት መምህሩ፡ ፡
የእንጦጦ አምባ መምህሩም ይህን ሐሳብ ይጋራል፡፡ ‹‹…በእርግጥም መንግስት ይህ (መምህራንን ማዳከም) ዓላማዬ ብሎ የያዘው ነገር ባይሆን ኖሮ ህይወታቸውን መቀየር ቀላል ነበር፡፡ ግን አይፈልግም፤ ጥገኛ ሆነው እንዲኖሩ ብቻ ነው የሚፈልገው፡፡ አሁን መምህራን ላይ ቀልድ የማይቀልድ ማን አለ…እንደ መምህራን ደመወዝ ቡን ያድርገኝ የሚሉ ወጣቶች ስንት ናቸው? ይህ ምን ማለት ነው? በራስ እንዳትተማመን ማድረግ አይደለም? ይህ ሆን ተብሎ የተሰራ ስራ ነው፡፡››
ተቆርቋሪ ማጣት!
የኢትዮጵያ መምህራን በ1960ዎቹ መጨረሻና 70ዎቹ ጠንካራ የሙያ ማህበር ነበራቸው፡፡ ያን የመሰለ ጠንካራ መምህራን ማህበር አሁን ላይ ማግኘት እንዳልተቻለ ነው ያነጋገርኳቸው መምህራን የሚገልጹት፡፡ ‹‹ያን ጠንካራ ማህበር አሁን አታገኘውም፤ አፈራርሰውታል፡ ፡ ለምን ያልክ እንደሆን ማሽመድመድ ስለፈለጉ ነው፡፡ ማህበር ለይስሙላ አለ፤ ዳሩ ግን የመምህሩን ጥቅምና ሙያዊ ክብር ማስጠበቅ አልቻለም፡፡ ሲመስለኝ የማህበሩ ዓላማ መንግስትን ማገልገል ነው፡፡
‹‹የሙያ ማህበሩ ተለጣፊ ነው፡ ፡ ለሙያውና ለመምህራን ጥቅም ሳይሆን እንደማፈኛ መሳሪያ የዋለ አድርጌ ነው የማየው፡፡ የሆነ ጊዜ ማህበሩ አይወክለንም ብለን ፊርማ ብናሰባስብ ‹‹የህዝብ ክንፍ ለማፍረስ ተንቀሳቅሳችኋል›› ተብለን ፍዳችን ነው ያየነው፡፡ ይህ የሚያሳይህ ማህበሩ እንደ አንድ የፖለቲካ ክንፍ ሆኖ የሚያገለግል እንጂ ለመምህራን ጥቅም አለመቆሙን ነው፡፡›› ሲል ያብራራል የእንጦጦ አምባ የታሪክ መምህሩ፡፡
እንደ መምህራኑ ገለጻ የሙያ ማህበሩ በየጊዜው መዋጮ ይሰበስባል፡ ፡ ሁሉንም መምህራን በአባልነት እንዳቀፈ አድርጎ ራሱን ይስላል፡ ፡ እውነታው ግን ሌላ ነው፡፡ ‹‹… መምህር ከሆንክ የማህበሩ አባልነት ግዴታ ነው፡፡ ወደድህም ጠላህም ከደመወዝህ ላይ የአባልነት መዋጮ ተብሎ ይቆረጣል፡፡ ከአንድ መምህር በአማካይ 4 ብር ወርሃዊ መዋጮ አለ፡፡ አሁን ባለው መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ ያለው የመምህራን ቁጥር ከ350000-400000 ይደርሳል፡ ፡ በአዲስ አበባ ብቻ ወደ 16000 መምህራን አሉ፡፡ ብዙ ገንዘብ እየገባ ግን መምህራን ምንም ሲደረግላቸው አታይም፡፡›› ሲል ይናገራል የአብዮት ቅርስ የኬሚስትሪ መምህሩ፡፡
‹‹ከመምህርነት ማምለጥ››!
እንደ መምህራኑ ገለጻ አሁን ላይ መምህርነት የሚሸሽ ሙያ እየሆነ ነው፡፡ የኬሚስትሪ መምህሩ ይናገራል፤ ‹‹በፊት በፊት መምህር ስትሆን የሞራል እርካታ ይኖርሃል፡ ፡ በማህበረሰቡ ዘንድም ተቀባይነትህ ከፍተኛ ነበር፡፡ ይህም መምህራን ሙያውን እንዲወዱት ያደረገ ነበር፡፡ አሁን ክብር ማጣት አለ፤ ትናቃለህ፡ ፡ መምህር ነኝ ካልክ እንደ አንዳች የሚዘገንን ነገር ፊቱን የሚያዞርብህ ነው የሚበዛው፡፡ እኔ መምህር ነኝ ብዬ አልናገርም፡፡ መምህር ነኝ ስል እንደ መጥፎ ሽታ ሰው የሚያርቀኝ ከሆነ ለምን መምህር ነኝ እላለሁ…? በሙያህ ማፈርን የመሰለ አሳዛኝ ነገር ምን አለ…? ግን እየሆነ ያለው ይህ ነው፡፡››
መምህሩ ከመምህርነት ሙያ መውጣት ይፈልጋለሁ፡፡ ለዚህም ሌላ ዲግሪ እየተማረ ነው፡፡ ‹‹ማምለጥ እፈልጋለሁ፡፡ መምህር ሆኜ መሞት አልፈልግም›› ሲል ተስፋ በቆረጠ ስሜት ይናገራል፡፡ እንደ መምህሩ እምነት መምህራን ሌላ አማራጭ ስራ ቢያገኙ ሁሉም በአንድ ሴኮንድ ት/ቤቶችን ትተው ሊሄዱ ይችላሉ፡ ፡ ‹‹አንዳንዶች ጡረታ ለማስከበር ነው ቀናቸውን የሚጠብቁት፡፡ በዚህ ከቀጠልን ት/ቤቶች ኦና ከመሆን አያመልጡም፡፡››
አሁን ባለው የደመወዝ ስኬል መሰረት አንድ መምህር ከ21 ዓመት በኋላ (በሚገባ እርከኖችን ካለፈ) 3060 ብር ላይ ነው መድረስ የሚችለው፡፡ ለዚያውም ታታሪ የሚባለው መምህር ነው፡፡ ‹‹ታዲያ ተስፋህ ምንድነው? …በግሌ መምህርነት ትልቅ ሙያ መሆኑን አምናለሁ፤ ነውም ደግሞ፡ ፡ ግን አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ምክንያት እጠላዋለሁ፡፡ ከማስተማር ሙያ መውጣት አለብኝ፡፡››
የእንጦጦ አምባ ት/ቤት የታሪክ መምህሩም ይህን ሀሳብ ይጋራል፡ ፡ ‹‹እኔ በመምህርነት ዲግሪ አለኝ፡፡ ነገር ግን አሁን ከሙያው መውጣት እፈልጋለሁ፡፡ ለዚህም ወደታች ወርጄ ሌላ ትምህርት በዲፕሎማ እየተማርኩ ነው፡፡ ሙያውን ጠልቸው አይደለም፤ የሚያሰራኝ ሁኔታ ግን የለም፡ ፡ መኖር እኮ አልቻልኩም፡፡ ትዳር መመስረት አልችልም፤ ምን አለኝና ትዳር እመሰርታለሁ፡፡››
belay
በላይ ማናዬ
•በመጨረሻም የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ ሁለት ነገሮችን ብቻ ማስቀመጥ ይፈልጋል፡፡ አንድ፣ የመምህራንን ጩኸት መንግስት እንዲሰማ ያሳስባል፡ ፡ ሁለት፣ መምህራን ህብረታችሁን አጠናክራችሁ በመታገል ጥቅማችሁን ማስከበር ይቻላችኋልና አድርጉት፡ ፡ ከሙያችሁ መሸሽ ዘላቂ መፍትሄ አይሆንም፤ ስርዓቱ ባይፈልጋችሁም ኢትዮጵያ ትፈልጋችኋለች! ሐገር ያለእናንተ ባዶ ነች፡፡
በመግቢያየ ላይ የጠቀስኩት አባባል የአንድ የባዮሎጅ መምህር የዘወትር ንግግር ነው፤ ታመነ ይባላሉ (ጋሽ ታመነ)፡፡ ይህን ግሩም የጋሽ ታመነ አባባል በድጋሜ ልዋስ፣ ‹‹እኔ ጆርጅ ቡሽን (ፕሬዚዳንት) አላደንቅም፤ ጠፈር ላይ የወጡትንም አላደንቅም፡፡ የማደንቀው እነዚህን ሰዎች ለትልቅ ደረጃ ያደረሷቸው መምህራንን ነው፡፡››
(በቀጣይ፣ ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሌሎች ጽሑፎችን ለማስነበብ እሞክራለሁ፡፡)
ብሩህ ጊዜ ለመምህራን ይሁን! (ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ)
http://www.goolgule.com/the-suffering-of-ethiopian-teachers/