FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, October 15, 2013

በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተለቀቅን!!! ዜጎችን በፖለቲካ አቋማቸዉ ማሰርና ማዋከብ ይቁም!

ጓዶች ተመልሰና . . . ጉድ አይተን . . . ያዉ የኛ ጉዳይ ሲለመድ እስር እና ዱላ እንደ ተራ ነገር እያየነዉ ምንም አልመሰለኝም ነበር . . . ያሁኑ ግን እኛን እያዋከቡና እየሰደቡ ወደ ዉስጥ ሲያስገቡን ከዉጪ ሆነዉ እኛም ከነሱ ጋር ነን እኛንም ዉሰዱን ባሉ ጓደኞቻችን ላይ የደረሰባቸዉ ድብደባና ስድብ አፀያፊ ብቻ ሳይሆን ምን ያህል ፖሊስ ገለልተኛ እንዳልሆነ በይበልጥ ግልፅ አድርጎታል . . . አንዳንዶቹን በጃቸዉ የነበረ መፅሃፍና መፅሄት በመንጠቅ “አሁን እናንተ ስለፖለቲካ ምን ታዉቃላችሁ” እስከማለት የደረሰ የአምባገነን ወገንተኝነት አንፀባርቀዋል፡፡ በዛም አካባቢ እንዳይቆሙ አመራሮችን ሳይቀር በቆመጥ እየመቱ አብረዋቸዋል፡፡ ዉስጥ የገባነዉም ብንሆን ሞራላችንን ለመንካትና ለማሸማቀቅ ያልተባለ ነገር የለም . . . አንዱ “አንዴት ብትደፍሩ ነዉ በኛ ክልል (ጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ) የምታልፉ” ሲል . . . አንዷ ደሞ (ለስሙ 3 ኮከብ በትከሻዋ ተደርድሯል) ቀበል አድርጋ ለምን “የማይገፋ ትገፋላችሁ አርፋችሁ ቁጭ ብትሉ ይሻላችኋል” ብትለንስ!!! በነገራችን ላይ ነሀሴ ላይ ታስረን ስንደበደብ “ለነዚህ ደርግ ነበር የሚሻላቸዉ” ብላ ከኢህአፓ ጋር ያመሳሰለችን ‘ሰዉ’ ናት (ጌታ ልብ ይስጣት). . . ብቻ ምን አለፋችሁ ብዙዉን እዚህ መነሳት የሌለበት ጉድ ትተን ለመብት መከራከር በተረጋጋ ሁኔታ ስለሁኔታዉ መነጋገር ፤ ቃል አልሰጥም ማለት ፤ ለምን ማለት እንደ ወንጀለኛ ያስቆጥር ነበር፡፡ ገና ሲይዙን ጀምሮ ሰማያዊዎች መሆናችንን ሲያዉቁ እንደሆነ ነገር ነበር ያደረጋቸዉ አጃኢብ ነዉ ሰዉ የገደለ እንኳን እንዲህ አይንገላታም በስእብናዉ ላይ መንቋሸሽ አይደርስበትም!!!
የሆነ ሆኖ በዚህ መልኩ ታስረን እስከ ሌሊቱ 8 ሰዓት መኪና የለም በሚል ብርድ ላይ አቆይተዉን ኋላም ወደ ወረዳ 9 ፖሊስ ጣቢያ ተወሰድን እዛ ነበር በይበልጥ አሳዛኙንና ሊታረም ይገባዋል የምንለዉን አሳዛኝ ሁኔታ የታዘብነዉ (ስለ እስረኛ አያያዝ በሌላ ፅሁፍ እመለስበታለሁ) . . . እናም በዚህ ማቆያ እስር ቤት ቅዳሜን እና እሁድን አሳለፍን፡፡ ሰኞ ሲደርስ እንደለመዱት ሊፈቱን ምንም እንዳልተፈጠረ ሊለቁን አማራቸዉና እንደለመዱት ዉጡ ተባልን ይህ ጨዋታ ግን በኔም ሆነ በጓደኞቼ አልታመነበትም ነበርና ለፍርድ ካልቀረብን አንወጣም አንፈታም አልን . . . በሰዓቱ በቦታዉ አንዳንድ የደህንነት አባላት የነበሩ ሲሆን ሁኔታዉን ለአለቆቻቸዉ ደዉለዉ ሲያስታዉቁም ታዝበናል . . . በአንዳንድ የፖሊስ አባላትም በሁኔታዉ የመገረምና የመናደድ ነገር ይታይባቸዋል፡፡ ግን በኛ እምነት ማንኛዉም አካል ሲታሰር በወንጀለኝነት ተጠርጥሮ ወይም እጅ ከፍንጅ ተይዞ ሲሆን ከዛም ነፃ መልቀቁም ሆነ ወንጀለኛ ማለቱ የፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ነዉ ነገር ግን በተደጋጋሚ ጊዜ የኢህአዴግን የአፈና ስራ በሚፈፅሙለት ፖሊሶች ታስረን ተደብድበን ምንም እንዳልተፈጠረ ሂዱ ከዚህ ጥፉ ከማለትም አልፈዉ አላሰርንም እስከማለት ይዋሹ ነበር ያ ግን መስዋዓትነት ተከፍሎበትም ቢሆን መቅረት ያለበት የመንግስት ሸፍጥ ነዉ . . . ወደ ነገሩ ስንመለስ ከወረዳ 9 ወደ ጃንሜዳ መልሰዉን በቀበሌ መታወቂያ ዋስ ጠርተን እንድንወጣ ማስፈራራት በሚመስል መልኩ ቢነግሩንም ሳንስማማ ቀረን በኋላም ሃሳባችን እንደማይቀየር ሲያዉቁና አንደተረዳነዉም ከአለቆቻቸዉ በደረሰባቸዉ ጫና በቀላል ወንጀል ማለትም ሁከት ለመፍጠር በሚል ክስ በፍርድ ቤት እንደሚያቀርቡብን አሳወቁን . . . ጉዞም ወደ ችሎት መድሃኒዓለም የ8 ሰዓት ምድብ ሆነ እዛም እንደደረስን ዳኛዋ ክሱን ላለመቀበል ብትፈልግም በሆነ መንገድ እድንገባ ተፈቀደ በሂደቱም የፖሊስ አቃቢ ህግ ገና ክሱን እያጣራሁ ነዉ ስላለ እንዲሁም በፍርድ ቤቱ የክሱ ሀተታ አሳማኝ ስላልነበረ ያለአግባብ እንደታሰርንና በሰንበት እንደተንገላታን አሳስባ ባስቸኳይ በመታወቂያችን ዋስ እንድንወጣ በትናንትናዉ ዕለት ወሰነችልን!!!
ዋናዉ ነገር ይህ የትግሉ በጣም ትንሹ ነገር ሲሆን ገና ብዙ እንደሚጠብቀን እያሰብን እንደእኛም ሰዉ ሆነ እንደ ሰማያዊ ከተነሳንለት ዓላማ አንዱ ከፍርሃት ተላቀን ማንኛዉም ሰዉ ከህግ በላይ እዳልሆነ እንዲረጋገጥ ከትንሹ ይህን ከመሳሰሉ አጋጣሚዎች በመጀመር ወደ ከፍተኛ ጉዳዮች መድረስ መቻል ነዉ . . . ይህም አካሄድ ከጊዜ ወደ ጊዜ ዉጤታማ እያደረገን ይገኛል፡፡
ማናችንም ብንሆን ነፃነታችንም ሆነ ዲሞክራሲያዊ መብቶቻችን በሆነ አካል በችሮታ የሚለገሱን ሳይሆን በራሳችን ትግል ለራሳችን ምናጎናፅፋቸዉ ሰብዓዊ እኛነታችን ናቸዉ ስለዚህም ከትንሹ ጀምረን መታገል ለመብታችን መቆም ያለህግ የሚደረጉ ክንዉኖችን እምቢ አልተባበርም ማለትና እነዚህንም ማጋለጥ ግዴታ አለብን! በመጨረሻም በመታሰራችን ለተጨነቃችሁና በሁሉም መልኩ ድጋፍ ላደረጋችሁልን ሁላ ዝቅ ብለን አመሰገንን!!!
Amha Teresa

No comments:

Post a Comment