FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, October 18, 2013

ሃበሻው ዶክተርና ልጁ – በአሜሪካ (አርአያ ተስፋማሪያም)

Robelዶ/ር ጳውሎስ ይባላል፤ ሃበሾችን ጨምሮ የሚያውቁት በርካታ ወገኖች ስለዶ/ር ጳውሎስ ተናግረው፣ አድናቆትና ምስጋናቸውን ሰጥተው አይጠግቡም። በዲሲ ከተዋወቅኳቸው እጅግ መልካም ሰዎች አንዱ ነው። ትብብር ለጠየቁት ሁሉ የነፃ ህክምና እርዳታ ያደርጋል። በተለይ የቁርጥማትና አጥንት ወዘተ ሕመም ለሚያሰቃያቸው በዘመናዊ መሳሪያ ፈውስ ይሰጣል። እረፍት በሆነ ቀን የህክምና መሳሪያውን እንደያዘ ነው የምታገኘው። « ገንዘብ እንክፈልህ..» የሚል ጥያቄ በጭራሽ መስማት አይፈልግም።..በአብዛኛው ከመናገር ይልቅ ማድመጥን ያዘወትራል። ለወገኖቹ አዛኝ፣ እንዲሁም አገሩን የሚወድ ሰው ነው። ንግግሩ ቁጥብ ነው፤ ከእርሱ ጋር ቁጭ ስትል ብዙ የህይወት ልምዶችን ትቀስማለህ።
ዶ/ር ጳውሎስ በመደበኛ ስራው ከአሜሪካ መንግስት ጥሩ ክፍያ ያገኛል። የተቸገሩ ወገኖችን በገንዘብ ጭምር ይረዳል። በደርግ ዘመን የኢህአፓ አባል ነበር። በትግል ተፈትኗል፣ እስርና ስቃይን ቀምሷል።…የዶ/ር ጳውሎስ ልጅ ሮቤል ይባላል፤ በትግል አብራው ከነበረች የቀድሞ ፍቅረኛው በአሜሪካ ተወልዶ ያደገው የ19 አመቱ ወጣት ሮቤል ከወላጅ እናቱ ጋር በቦስተን ይኖራል። …ከ6 ወር በፊት አፕሪል 15 ቀን 2013 በቦስተን ከተማ አስደንጋጭ ነገር ይከሰታል። በእለቱ ኢትዮጲያዊያን አትሌቶች በድል አድራጊነት ያጠናቀቁበት የማራቶን ውድድር ላይ ሁለት ወንድማማቾች ቦንብ በማጥመድ ንፁሃንን ገደሉ፣ በመቶዎች አቆሰሉ።..ድርጊቱ ከተፈፀመ ከሶስት ቀን በኋላ በርካታ የF.B.I አባላት መሳሪያ ወድረው፣በጎማ የሚንቀሳቀስ ታንክ አስከትለው የነሮቤልን መኖሪያ ይከባሉ። በር ሲቆረቆር… ወላጅ እናት ባየችው ነገር ክው ብላ ትደርቃለች።
ከተፈፀመው የሽብርተኝነት ድርጊት ጋር በተያያዘ ሮቤል ተጠርጥሮ እንደሚፈለግ ገልፀው ..ይዘውት ይሄዳሉ። አራት ቀን ለታሰረው ሮቤል ሶስት ታዋቂ ኢትዮጲያዊያን ጠበቆች ጥብቅና ሊቆሙለት ፈቃደኝነታቸውን አሳዩ። ..ከሁለቱ የድርጊቱ ፈፃሚ ወጣቶች አንዱ እነሮቤል መኖሪያ ቤት መጥቶ መፅሃፍ ሲቀበለው የሚያሳይ ቪዲዮ በምርመራው የቀረበ ቢሆንም፣ የሶስተኛ አመት ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነው ሮቤል ከዚህ ወጣት ጋር አብረው የሚማሩ የት/ቤት ጓደኛሞች መሆናቸውንና የሰጠውም መፅሐፍ የትምህርት እንደሆነ መፅሐፉን -ጭምር በማቅረብ ያስረዳል። ..የምርመራ ቢሮው ይህን ከተገነዘበ በኋላ ነበር – በ4ኛው ቀን እንዲፈታ ያደረገው።..ጉዳዩ በፍ/ቤት እየታየ በመሆኑ ሮቤል በመኖሪያ ቤቱ የቁም እስረኛ እንዲሆን ተደረገ።
በአንዱ እግር ብቻ (እንደ እጅ ሰአት የሚታሰር አይነት) “tether ankle monitor” የሚባል ኤሌክትሮኒክስ መቆጣጠሪያ ተጠልቆለታል። ይህ መሳሪያ የሚገጠምለት ሰው ከተፈቀደለት ክልል ውጭ አልፎ ከሄደ መሳሪያው ለፖሊስ ጥቆማ ይሰጣል፣ በደቂቃዎች ውስጥ ፖሊስ ይደርሳል።…ዛሬ አርብ ኦክቶበር 18 ቀን ሮቤል ፍ/ቤት ይቀርባል።….ዝርዝር ጉዳዩን ያጫወተኝ ወላጅ አባቱ ዶ/ር ጳውሎስ፣ በመከፋት ስሜት ቅዝዝ ብሎ ፥ « አልፎ…አልፎ ልጠይቀው እሄዳለሁ፤ ተሰናብቼው ስወጣ ከቤቱ በር ማለፍ ስለማይችል አይኖቹ ውስጥ ቅሬታ አነባለሁ።
እኔም ሆዴ እየተላወሰ ይከፋኛል። ትንሽ ይረብሻል። ..ሞራሉ ግን ጥሩ ነው፤ ቤት ሆኖ ትምህርቱን ያጠናል፣ ያነባል። ሮቤል ልጄ ስለሆነ ሳይሆን፣ የዚህ አይነት የሽብር ወንጀል ላለመፈፀም ኢትዮጲያዊ መሆን ብቻ በቂ ነው!! ሃበሻ አሸባሪ አይደለም!! » አለኝ።…

No comments:

Post a Comment