FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, April 16, 2013

የነ አንዱዓለም አራጌ ይግባኝ ለሌላ ጊዜ ተቀጠረ


3340_3841593393661_612083176_nበፌደራሉ አቃቤ ህግ በአሸባሪነት ክስ የተመሰረተባቸው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (እንድነት) ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አንዱዓለም አራጌ እና ታዋቂው የፖለቲካ ተንታን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ 24 ተከሳሾች ላይ በተወሰነው የጥፋተኝነት ውሳኔ ለፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ተጠይቆ አርብ ጥር 10 ቀን 2005 ዓ.ም ለውሳኔ ተቀጥሮ ነበር፡፡
የፍደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ የጠየቁት አቶ አንዱዓለም አራጌ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን፣ አቶ አንዱዓለም አያሌው እና አቶ ክንፈሚካኤል ደበበ ሲሆኑ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ለየካቲት 8 ቀን 2005 ዓ.ም ጠዋት ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ይግባኝ ሰሚው 6 ኪሎ የሚገኘው የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለውሳኔ የቀጠረውን ወደ የካቲት 8 ቀን 2005 ዓ.ም ያዛወረበትን ምክንያት ሲገልፅ በስር ፍ/ቤት በነአንዱዓለም አራጌ የክስ መዝገብ ላይ የነበሩት ተከሳሾች ሻምበል የሺዋስ ይሁንዓለም እና አቶ ዮሐንስ ተረፈ ዘግይተው ይግባኝ ስለጠየቁ ጉዳዩን አንድ ላይ አይቶ ውሳኔ ለመስጠት እንደሆነ ገልፆል፡፡
ከዚህ  በፊት በልደታው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ላይ የፈረደውን ቅጣት ይግባኝ ተጠይቆ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤቱን የ14 ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት ወደ 5 ዓመት እስር ዝቅ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡

No comments:

Post a Comment