FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, April 16, 2013

!…..ህወሓት ማስጠንቀቅያ ተሰጠው……!


ባለፈው እሁድ በተካሄደው የአካባቢና ከተሞች ‘ምርጫ’ (ይቅርታ አማራጭ የሌለው ምርጫ ምርጫ አይባልም ግን ሌላ ስም ለግዜው አላገኘሁም) የትግራይ ህዝብ ባልጠበኩት ሁኔታ (ህወሓት የትግራይ ህዝብ ድጋፍ እንደሌለው ባውቅም) ለህወሓቶች አስደንጋጭ ማስጠንቀቅያ መስጠቱ መረጃ ደርሶኛል። በብዙ አከባቢዎች ህዝቡ ለመምረጥ ፍቃደኛ አልነበረም። አንዳንድ ካድሬዎች ህዝብን እያስገደዱ ወደ ምርጫ ጣብያ እንዲሄድ ቢያድርጉም ዉጤቱ እንደጠበቁት አልነበረም።
በትግራይ ተወዳዳሪ ተቃዋሚ ፓርቲ አልነበረም (በአላማጣ ኣንድ ነበር አሉ)። በምርጫው ዋዜማ ሁሉም የመንግስት አካላት ህዝብ በምርጫው እንዲሳተፍ ቅስቀሳ ያደርጉ ነበር (‘ይሄው በህዝብ ተመርጠናል’ ለማለት ያህል)። ነገር ግን በአክሱም፣ ሸረ፣ ሸራሮ፣ ዓዲግራት፣ ዉቅሮ፣ ሓውዜን፣ አላማጣ፣ ዓብዪዓዲ፣ መቐለ ብዙ ችግሮች ነበሩ። ለምሳሌ ያህል በመቐለ ከተማ ባንዳንድ ምርጫ ጣብያዎች ያጋጠመ ነገር ላካፍላቹ።
መቐለ 05 ቀበሌ በሚገኝ አንድ ምርጫ ጣቢያ 1140 መራጮች ተመዝግበው ነበር። ከነዚህ ተመዝጋቢዎች በምርጫው የተሳተፉ 619 ብቻ ነበሩ። ከተሳተፉት 370 ደግሞ የምርጫ ምልክት ሳያስቀምጡ በስድብ የታጀቡ አስተያየቶች ብቻ የፃፉ ናቸው (ምርጫ ጣብያ ተገደው ቢሄዱም አልመረጡም)።
ማይ ሊሓም በሚገኝ አንድ ምርጫ ጣብያ ደግሞ 1201 መራጮች የተመዘገቡ ሲሆን 910 መርጠዋል (ከነዚህ መራጮች ግን 521 የስድብ አስተያየት የሰጡ ናቸው)።
አቶ አባይ ወልዱ (የህወሓት ሊቀመንበር) የተሳተፉበት በዓዲ ሹምድሑን አከባቢ በሚገኝ አንድ የምርጫ ጣቢያ 1446 የተመዘገቡ መራጮች የነበሩ ሲሆን 945 ሰዎች በምርጫው ተሳትፈዋል። ከነዚህ ተሳታፊዎች 415 ስድብ ብቻ ፅፈው ያስገቡ ሲሆን 202 ደግሞ ነፃ ወረቀት ብቻውን (ምንም ምልክት ወይ ፅሑፍ ሳያስቀምቱ) ወደ ኮረጆው ከተው ተመልሰዋል። 330 ብቻ ድምፃቸው በአግባቡ ሰጥተዋል።
ባጠቃላይ በመቐሌ (እንዲሁም በትግራይ ክልል ማለት ይቻላል) ተመሳሳይ ነው። በተለይ በመቐለ (በዓይደር፣ 06፣ ዓዲሓ፣ ሓዲ ሓቂ) ጭራሽ ሰው አልመረጠም ማለት ይቻላል። የሚገርመው ነገር የህወሓት አባላት ራሳቸው አለመምረጣቸው ነው። ብዙዎቹ የህወሓት አባላት (ከቀበሌ ሰራተኞች በቀር) በምርጫው ለመሳተፍ ዝግጁ አልነበሩም። ሙሁራንና ነጋዴዎች ወደ ምርጫ ጣብያ ላለመሄድ ተደብቀው የዋሉ ሲሆን አንዳንድ ካድሬዎች የምርጫ ካርዳቸው እየሰበሰቡ ራሳቸው ይመርጡላቸው እንደነበር ተሰምተዋል። በትክክል የመረጡ ጥቂት ሴቶች (የህወሓት አባላት) ብቻ ናቸው።
በምርጫው ቀን ብዙ ህዝብ ባለመሳተፉ የተናደዱ አንዳንድ ባለስልጣናት ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ (እስከ አስር ተኩል) ቤትለቤት እየዞሩ ሰዎች ለምርጫ እንዲወጡ ያስገድዱ ነበር። በኋላ ግን በምርጫ ወረቀቱ (ድምፁ ሲቆጠር) የተፃፉ ስድቦችና አስተያየቶች ካድሬዎቹን እጅግ አስደንግጧል። በአንድ ምርጫ ጣብያ ኣስመራጮቹ (ታዛቢዎችና ፖሊሶች) ደንግጠው ለኣለቆቻቸው ደውለው ሁኔታው አስረድተዋል። እንደዉጤቱም ሦስት ከፍተኛ ባለስልጣናት (የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት) ከምሽቱ አራት ሰዓት በምርጫ ጣብያው የተገኙ ሲሆን በሁኔታው ደንግጠው በሁሉም የምርጫ ጣብያዎች ያለ የድምፅ ቆጠራ ሂደት እንዲቆም አዘዋል። ግን ኣልተሳካም፤ ምክንያቱም ኣብዛኞቹ ቆጥረው ጨርሰው ነበር።
ባለስልጣናቱ ካስደነገጡ የህዝብ ኣስተያየቶች መካከል “ ህወሓት ሌላ፣ ምርጫ አታጭበርብሩ፣ ፍትሕ አጣን፣ ከሌሎች ህዝቦች አታጣሉን፣ በሃይማኖት ጣልቃ ኣትግቡ፣ ድምፃችን ዓፍናቹ ድምፅ እንድንሰጣቹ ትፈልጋላቹ?፣ ሙስና ይቁም፣ በእኩል ዓይን እዩን …” ወዘተ።
ከዚህ በተያያዘ የዉቅሮ ህዝብ ከሌላ አከባቢ ተሽሞ የመጣው የወረዳው ኣስተዳድሪ እንዲቀየር ከፍተኛ ተቃውሞ እያሰማ ይገኛል። የወረዳው ህዝብ የዉቅሮ ተወላጅ ኣስተዳዳሪ ይፈልጋል። ህወሓቶች ግን (በኣብዛኞቹ ሌሎች የትግራይ ወረዳዎች እንደሚያደርጉት ሁሉ) የህዝቡን የተቃውሞ ድምፅ ማዳመጥ አልፈለጉም። በኣፅቢ ወንበርታ ወረዳም ተመሳሳይ ችግር አለ።
በርግጠኝነት መናገር የምችለው ተቃዋሚዎች በምርጫ ቢሳተፉ ኑሮ በትግራይና አዲስ አበባ ያለ ጥርጥር ያሸንፉ ነበር። ግን ያሸነፉበት ድምፅ በገዢው ፓርቲ ይሰረቅ ነበር።
አዎ! ‘ድምፃችን ዓፍናቹ ድምፅ እንድንሰጣቹ አትጠብቁ’።
It is so!!!

No comments:

Post a Comment