FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, April 16, 2013

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ወደ ዝዋይ ወህኒ ቤት ተወሰደ



  • digg
  • 36
     
    Share
Woubshet-Taye-Deputy-Editor-In-Chief-Awramba-Newspaper





የአውራምባ ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ወደ ዝዋይ ወህኒ ቤት ተወሰደ፡፡
የአውራምባ ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በፌደራል  አቃቤ ህግ በሽብርተኝነት ተከሶ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ጥፋተኛ በሚል 14 ዓመት ተፈርዶበት ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግበት ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ታስሮ ይገኝ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬ ሚያዚያ 8 ቀን 2005ዓ.ም. ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከአዲስ አበባ ከ170 ኪሎ ሜትር አካባቢ በደቡብ ምስራቅ ርቀት በሚገኘው ዝዋይ ወህኒ ቤት መወሰዱ ታውቋል፡፡
የጋዜጠኛው ባለቤት እና ልጁ በሁኔታው ከፍተኛ መደናገጥ እንደፈጠረባቸው ተጠቁሟል፡፡ በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ መንግስት ጋዜጠኞችን በማሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተወገዘና ያሰራቸውን ጋዜጠኞችንም እንዲፈታ በተደጋጋሚ ጫና እየተደረገበት መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም መንግስት ግን ጋዜጠኛ  ውብሸት ታዬ፣ ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እስካሁንም ለመፍታት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡

No comments:

Post a Comment