FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, April 12, 2013

! … ምርጫ የሌለው ‘ምርጫ’ … Election without Choices …!


Abraha Desta
ኢህኣዴግ ብቻውን (‘ብቻውን’ ያልኩበት ምክንያት በምርጫው የሚሳተፉ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮች አነስተኛ ቁጥር ስለሚይዙ ነው) እየተወዳደረ (ይቅርታ እየተመረጠ …. ይቅርታ እየሾመ ….. ይቅርታ ለመወዳደር ተወዳዳሪ ያስፈልጋል፣ ለመመረጥም ተመራጮች መኖር አለባቸው) የምርጫ ካርድ ‘ወሰዳቹ ኣልወሰዳቹ’ እያለ ያዋክበናል።
ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ የምርጫ ካርድ ቁጥር ይመዘግባሉ፣ ካርድ ያላወጣ እንዲያወጣ (ትእዛዝ በሚመስል መልኩ) ይገፋፋሉ። በየመንግስት ቢሮዎቹ የምርጫ ካርድ ያላቸውና የሌላቸው ሰራተኞች ይለያሉ። ይሄን ሁሉ ለምን አስፈለገ?
ዜጎች የመምረጥ (ወይ የመመረጥ) መብት ያላቸው ያህል (ካላሰኛቸው) ያለመምረጥ (የምርጫ ካርድ ያለማውጣት) መብት ‘ኮ ኣላቸው። መምረጥ መብት እንጂ ግዴታ አይደለም። ዜጎች በምርጫ እንዲሳተፉ ቅስቀሳና እገዛ ማድረግ ተገቢና የሚደገፍ ነው። ግን ይሄን መደረግ ያለበት ምርጫ ሲኖር እንጂ ሰዎች ተሰልፈው (ቆመው) እንዲውሉ ለማድረግ መሆን የለበትም። በምርጫ ሰበብ ሰዎች ስራ ፈተው ወረፋ ይዘው ቢውሉ ምን ፋይዳ አለው? ምን ለውጥ ያመጣሉ? ያው የሚወዳደረው ኢህኣዴግ ነው፤ ‘የሚመረጠውም’ ኢህኣዴግ ነው። ለውጥ ለሌለው ነገር … ኪሳራ ነው።
ምርጫ ‘ምርጫ’ የሚሆነው አማራጮች ሲኖሩት ነው። የአሁኑ ምርጫ አማራጮች አሉት? መራጩ ህዝብ ስለነዚህ አማራጮች ሙሉ መረጃ አለው? መረጃው የተገኘው ከነፃና ገለልተኛ ሚድያ ነው? ለመሆኑ ነፃ ሚድያ ተፈቅዷል? ህዝቡ መረጃ የማግኘት ሙሉ መብት አለው? ህዝቡ የሰጠው ድምፅ እንደሚከበርለት ዋስትና አለው? የህዝብ ድምፅ የሚያከብር ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ አለ? ህዝቡ ከምርጫ በኋላ ምንም ዓይነት ዛቻና ድልዎ እንደማይደርሰው የሚተማመንባቸው ተቋማት አሉት? እነዚህ ጥያቄዎች በግባቡ መመለስ ካልቻልን በምርጫ ጣቢያ ወረፋ ይዞ መዋል ጥቅም የለውም።
ምርጫው በተመለከተ አንድ አስተያየት ሰጪ የ ሰጠኝ ሓሳብ ላካፍላቹና ላብቃ። እሱ እንዲህ ይላል፦
“ለሁሉም ሰራተኞች (የኛ መስራቤት) ካርድ የጠፋቹ ከዕለት 01/08/2005 የምዝገባ ካርድ ውሰዱ የሚል ማስጠንያ ይነት ወጣ:: የምዝገባ ቀን ከተዘጋ ግን ከንድ ወር በላይ አልፎታል:: የምርጫ ጣብያዎች ደሞ የህወሓት ሰዎች እርስ በርሳቸው ብቻ እንደሚወዳደሩት እንደሆነ ተወዳዳሪዎች ራሳቸው ነገሩን:: ከኛ ሰራተኞች ደሞ እኛ እገሌ እገሌ/3/ ሰዎቸ እጩ ተወዳዳሪ ነን ሉን:: የሚገርመው ከተወዳዳሪዎቹ ያሸንፋሉ ተብለው የሚጠበቁ ሁሉት ሲሆኑ የሚወከሉት ወረዳ ተወላጅ ሳይሁኑ የሌላ ቦታ ተወላጅ መሆናቸውና በሰራተኞችና በተማሪዎች ምርጫ ጭበርብረው የወረዳ ምክር ቤት ወንበር ለማኘት እንጅ ህዝብ ሊጣቸው ይቅር እንደማያውቃቸው ነው:: እንዲህም ሉ በምርጫ ቀን ሰት ቆጥረን ድ እንሄዳለን  እንመለሳለን:: በተጨማሪ ከህወሓት ጭ መምረጥ የሚፈግ ው የት ሂዶ ይረጥ ተብለወ ሲመሱ ህወሓት የማይመርጥ ሰው ካለ የX (ኤክስ) የሚመርጥ ደሞ – (ራይት) ምልክት ያድርግ ብለው ሉን:: ግን የኤክስ ወይ ራይት ምልክት ማስቀመጥ ማለት መምረጥ ማለት ነው እንያውም ንመርጥም’ የሚል ድምፅ ቁጥር ይገባም ብየ ስጠቃቸው ወረዱብኝ::”

No comments:

Post a Comment