በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አርሲ ዞን በመንገድ ሥራ ላይ በተሠማራው የቻይና ድርጅት ማለትም የCGCOC/ ሲጂሲኦሲ/ዴራ ማኛ መቻራ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት የሠራተኞች መሰረታዊ ማህበር ሊቀመንበር አቶ ኩራባቸው ፍቅሩ ከሌሎች አመራሮች ጋር በመሆን ለደህንነታቸው በመስጋት ከሀገር መሰደዳቸውን የፍኖተ ነፃነት የዜና ምንጮች ገለጹ፡፡
የመረጃ ምንጮቻችን እደገለፁት የሠራተኛው ማህበር አመራሮች የሠራተኛውን መብትና ጥቅም ለማስከበር ባከናወኑት እንቅስቃሴ እንዲሁም ቻይናውያን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈፅሙትን በደል በማጋላጣቸው በተደጋጋሚ የተሞከረባቸውን ግድያ መቋቋም ባለመቻላቸው ከአገር ተሰደዋል፡፡
ለሰራተኛ ማህበሩ አመራሮች ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን እንደሚያስረዱት የሲጂሲኦሲ የቻይና መንገድ ሥራ ድርጅት ኃላፊዎች በሠራተኞች ላይ ከፍተኛ ግፍ ይፈፅማሉ ፡፡
“እኛ የምንተዳደረው በኢትዮጵያ ህግ ሳይሆን በቻይና ህግ ነው” በማለት ሠራተኛው በማህበር እንዲደራጅ አይፈቅዱም፡፡ 23 ጊዜ ማህበሩን ለማደራጀት ተሞክሮ በቻይናዊያኑ እንቢተኝነት ከሽፏል፡፡ በአቶ ኩራባቸው ጠንካራ ትግል በ24ኛው ሙከራ ተሳክቶ ማህበሩ ህጋዊ እውቅና አግኝቷል፡፡ ማህበሩ ህጋዊ እውቅና ካገኘ በኋላ ቻይናዊያን በኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ላይ እየፈጸሙ ያለውን ግፍ በፍኖተ ነፃነት ጋዜጣና በተለያዩ ሚዲያዎች አጋልጧል፡፡

የሰራተኛ ማህበር አመራሩ በቻይናውያን የተፈፀመ ግድያ፣ የአካል ጉዳተኛ ሆኖ ለአልጋ ቁራኛ ስለሆኑ ሰራተኞች፣ የሰራተኞች ተገዶ መደፈር፣ ከሥራ መባረር ድብደባና ስድብ፣ ህገወጥ እስር እንዲሁም የመብት ጥሰት ደሞዝና ጥቅማጥቅምን መከልከል አጋልጧል፡፡
አቤቱታውን ከወረዳ እስከ ፌዴራል ብሎም ጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤትና ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አድርሰዋል፡፡ ለኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበር ኮንፌዴሬሽንም በቻይናውያኑ ስላደረሱት የመብት ጥሰት በቂ መረጃ አድርሰዋል፡፡ ሆኖም አንድም የተገኘ መፍትሔ የለም፡፡
እንዲያውም የመንግስት ባለሥልጣናት ለራሳቸውም መፍራት ጀምረዋል፡፡ ምንጮቹ አክለውም “በቅኝ ግዛት ህግ አንተዳደርም በማለት በመታገላቸው እነሱን ለማስገደል ተሞክሯል፡፡” ሲሉ በሰራተኛ ማህበሩ አመራሮች ላይ ስለደረሰው አደጋ ተናግረዋል፡፡
እንዲያውም የመንግስት ባለሥልጣናት ለራሳቸውም መፍራት ጀምረዋል፡፡ ምንጮቹ አክለውም “በቅኝ ግዛት ህግ አንተዳደርም በማለት በመታገላቸው እነሱን ለማስገደል ተሞክሯል፡፡” ሲሉ በሰራተኛ ማህበሩ አመራሮች ላይ ስለደረሰው አደጋ ተናግረዋል፡፡
የመረጃ ምንጮቹ በመቀጠልም “የሠራተኛ ማህበራቱ በተለይም በማህበሩ ሊቀመንበር ላይ ከአራት ጊዜ በላይ የመግደል ሙከራ ተደርጎባቸዋል፡፡ በሠራተኛውና በህዝብ ትብብር ግድያው ከሽፏል፡፡” ካሉ በኋላ “አቶ ኩራባቸው እየተሠነዘረባቸው ያለውን ጥቃት መቋቋም ባለመቻላውና ህጋዊ የጥበቃ ከለላም በማጣታቸው አቶ እሸቱ አደም፣ ቄስ ብርሃኔ መኩሪያ፣ አቶ ጉልላት ከተማና እና አቶ ደምሴ ግርማ ከሚባሉ የማህበሩ አመራር ጋር ከአገር ተሰደዋል፡፡”ብለዋል፡፡
በተለይ አቶኩራባቸው በአገር ውስጥ እያሉ እየደረሰባቸው ያለውን ጥቃትና ክትትል በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የገለጹ ሲሆን ቤተሰቦቻቸው ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት አቶ ኩራባቸው ከየካቲት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ከቤት እንደወጡ አልተመለሱም፡፡ ለተወሰነ ጊዜ ለህይወታቸው በመስጋታቸው ተሸሽገው ተቀምጠው ነበር እንደሚያውቁም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
No comments:
Post a Comment