FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Sunday, April 14, 2013

ኢዴፓ ቤት ተሃድሶ ገብቷል


ኢዴፓ ቤት ተሃድሶ ገብቷል<br />በ1997 የምርጫ ሰሞን አቶ ልደቱ አያሌው የሰሩት ድራማ በየትኛውም ኢትዩጵያዊ ልብ ተቀርጾ ስለመቅረቱ እማኝ መቁጠር አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡የቅንጅቱን ውህደት እውን ለማድረግ ይረዳ የነበረውን የኢዴፓ ስምምነት ለመግለጽ ይጠበቅ የነበረውን ማህተም ይዘው የተሰወሩት አቶ ልደቱ በመጨረሻ ብዙ የትግል አጋሮቻቸውን አጥተው ‹‹ሶስተኛ አማራጭ››ይዘው መቅረባቸውም አይዘነጋም፡፡ሶስተኛው አማራጭ ለልደቱ ተከታዮች ጭምር ግልጽ ባይሆንም በ2002 ምርጫ አማራጩ ምንም የሚታይ ለውጥ መፍጠር ሳይችል ቀርቷል፡፡ከምርጫው በኋላ ኢዴፓ እምጥ ይግባ ስምጥ ሳይታወቅ ቆይቶ በመጨረሻው መጨረሻ ፕሬዘዳንቱ አቶ ሙሼ ሸሙ በአዲስ አድማስና በተወሰኑ ጋዜጦች በሚወረውሯቸው ጽሁፎች በ2005 የአካባቢ ምርጫ መሳተፍ ወሳኝ ስለ መሆኑ በመወትወት አለን ለማለት ሞክረዋል፡፡የምርጫ ስነ ምግባር ኮዱን በመፈረም የፓርቲዎች ምክር ቤት አባል መሆን የቻሉት ኢዴፓዎች በምርጫው አንሳተፍም የሚል ውሳኔ ማሳለፋቸው ቢያንስ ውሳኔው ሙሼን እንደማያካትት እርግጠኛ አድርጎኝ ነበር፡፡አሁን ጥርጣሬዬን የሚያጠራ መረጃ እጄ ገብቷል፡፡ፓርቲውን ከታማኝ ተቃዋሚነት ለመዋጀት የተነሱ ጥቂት የማይሰኙ ወጣቶች ባደረጉት ውስጣዊ ትግል ፓርቲው ከምርጫው ራሱን እንዲያገል ሆኗል፡፡ኢዴፓ ቢያንስ በ1 ዕጩ መወከል ይገባዋል እንጂ ሙሉ ለሙሉ ከምርጫው መገለል የለበትም የሚለውን ሀሳብ ያመጣው ሙሼ መሆኑን እነዚሁ የኢዴፓን መታደስ የሚናፍቁ ታጋዮች ይናገራሉ፡፡በቀጣይ ጠንካራና ተፎካካሪ ሆኖ ለመውጣት ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር እስከ ውህደት የሚደርስ ስምምነት ለመፈጸም ተዘጋጅተናል የሚሉት እነዚሁ ታጋዮች እነ ሙሼ ይህን የማይፈቅዱ ቢሆኑ እንኳ  በኢዴፓ ውስጥ ቦታ አይኖራቸውም ይላሉ ፡፡ግን ግን ኢዴፓ ቤት ተሃድሶ ገብቶ ይሆን?በ1997 የምርጫ ሰሞን አቶ ልደቱ አያሌው የሰሩት ድራማ በየትኛውም ኢትዩጵያዊ ልብ ተቀርጾ ስለመቅረቱ እማኝ መቁጠር አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡የቅንጅቱን ውህደት እውን ለማድረግ ይረዳ የነበረውን የኢዴፓ ስምምነት ለመግለጽ ይጠበቅ የነበረውን ማህተም ይዘው የተሰወሩት አቶ ልደቱ በመጨረሻ ብዙ የትግል አጋሮቻቸውን አጥተው ‹‹ሶስተኛ አማራጭ››ይዘው መቅረባቸውም አይዘነጋም፡፡ ሶስተኛው አማራጭ ለልደቱ ተከታዮች ጭምር ግልጽ ባይሆንም በ2002 ምርጫ አማራጩ ምንም የሚታይ ለውጥ መፍጠር ሳይችል ቀርቷል፡፡ ከምርጫው በኋላ ኢዴፓ እምጥ ይግባ ስምጥ ሳይታወቅ ቆይቶ በመጨረሻው መጨረሻ ፕሬዘዳንቱ አቶ ሙሼ ሸሙ በአዲስ አድማስና በተወሰኑ ጋዜጦች በሚወረውሯቸው ጽሁፎች በ2005 የአካባቢ ምርጫ መሳተፍ ወሳኝ ስለ መሆኑ በመወትወት አለን ለማለት ሞክረዋል፡፡
የምርጫ ስነ ምግባር ኮዱን በመፈረም የፓርቲዎች ምክር ቤት አባል መሆን የቻሉት ኢዴፓዎች በምርጫው አንሳተፍም የሚል ውሳኔ ማሳለፋቸው ቢያንስ ውሳኔው ሙሼን እንደማያካትት እርግጠኛ አድርጎኝ ነበር፡፡ አሁን ጥርጣሬዬን የሚያጠራ መረጃ እጄ ገብቷል፡፡ ፓርቲውን ከታማኝ ተቃዋሚነት ለመዋጀት የተነሱ ጥቂት የማይሰኙ ወጣቶች ባደረጉት ውስጣዊ ትግል ፓርቲው ከምርጫው ራሱን እንዲያገል ሆኗል፡፡ ኢዴፓ ቢያንስ በ1 ዕጩ መወከል ይገባዋል እንጂ ሙሉ ለሙሉ ከምርጫው መገለል የለበትም የሚለውን ሀሳብ ያመጣው ሙሼ መሆኑን እነዚሁ የኢዴፓን መታደስ የሚናፍቁ ታጋዮች ይናገራሉ፡፡ በቀጣይ ጠንካራና ተፎካካሪ ሆኖ ለመውጣት ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር እስከ ውህደት የሚደርስ ስምምነት ለመፈጸም ተዘጋጅተናል የሚሉት እነዚሁ ታጋዮች እነ ሙሼ ይህን የማይፈቅዱ ቢሆኑ እንኳ በኢዴፓ ውስጥ ቦታ አይኖራቸውም ይላሉ፡፡ ግን ግን ኢዴፓ ቤት ተሃድሶ ገብቶ ይሆን? —  Dawit Solomon Yemesgen

No comments:

Post a Comment