FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Monday, April 22, 2013

የህክምና ባለሞያዎች ድራማ እየተመለከቱ የታካሚዋ ህይወት ጠፋ!!!


/ ሰፊያን እንደዋጋው የተባሉት የቤት እመቤት የህክምና ባለሙያዎች ተገቢውን ኃላፊነት ባለመወጣታቸው ህይወታቸው ማለፉን ቤተሰቦቻቸው ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል አስታወቁ፡፡

የሟች ቤተሰቦች በሠነድ አስደግፈው ለዝግጅት ክፍላችን እንዳስታወቁት የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታየዕለቱ ተረኛ ሐኪሞች በፈጠሩት ኃላፊነት የጎደለው አገልግሎት አሰጣጥ የእህታቸውን ህይወት ሊያጡ ችለዋል፡፡ የሟች ቤተሰቦች እህታችን አጣን የሚሉበት ሁኔታ ሲያስረዱእህታችን መንታ ማርገዟ ተነግሯት ተገቢውን የህክምና ክትትል እያደረገች የእርግዝና ጊዜዋን ጨርሳለች ፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 / ለሊት ምጥ ያዘኝ አለች፡፡ እያማጠችና እየተሰቃየች ነጋ በማግስቱ ጠዋት ተነስተን ሳሪስ ጤና ጣቢያ ወሰናት፤ ጤና ጣቢያው የደረነው 4 ሰዓት ነው፡፡ ለጊዜው ምንም ዕርዳታ ሳይደረግ 6 ሰዓት ሆነ፡፡ የጤና ጣቢያው ሠራተኞች ለምሳ ወጡ፡፡ 7 ሰዓት ሲመለሱ የላብራቶሪ ምርመራ አድርገው ከአቅማችን በላይ ስለሆነ ብለው ለጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስታል ሪፈር ጻፉልን፡፡

ከቀኑ 8 ሰዓት ሲሆን ጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል ደረስን፡፡በማለት ይገልጻሉ፡፡ ቤተሰቦቿም በመቀጠልም ሲያብራሩ “8 ሰዓት ሆስፒታሉ ብንደርስም 8-11 ሰዓት ድረስ ከሆስፒታሉ ምንም ዓይነት እርዳታ ማግኘት አልቻለችም፡፡ 11 ሰዓት በኃላ ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ሪፈር ጻፉልን፡፡ 12 ሰዓት ሲሆን ዘውዲቱ ሆስፒታል ደረስን፡፡ የዘውዲቱ ሆስፒታል የዕለቱ ተረኞች ምንም እርዳታ ሳያደርጉ ተኝታ መታከም አለባት፡፡ እኛ አልጋ የምንሰጠው እኛ ክትትል እያደረጉ ለቆዩ ታካሚዎች ነው፡፡ ስለዚህ ወደ መጣችሁበት ሆስፒታል ተመለሱ፤ ብለው ጻፉልንና ተመልሰን ወደ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ሄድን፡ የዕለቱ ሐኪሞች ተመልሰን ስንመጣ ተቀብው ሊያስተናግዱን አልቻልንም፡፡ የደረስነው ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ነው፡፡ ሐኪሞች በአንድ ክፍል ተሰብስበውሰው ለሰውድራማ ይመለከቱ ነበር፡፡ ቀን የተመለከተቻት ሐኪምም ቆማ ድራማውን ትመለከታለች እህታችን ህመሙ ጨምሮባት የስቃይ ድምጽ ታሰማለች፡፡ ደም ይፈሳታል፡፡ ኧረ እባካችሁ ልትሞትብን ነው! እርዳታ ስጡልን ብለን ለመንን፤ ከውጪ የጥበቃ ሠራተኞች ጠርተው ሆስፒታሉን እየረበሹ ስለሆነ አስወጧቸው ብለው አስወጡን፤ ባለሞያዎቹ እኛ ነን እንጂ እናንተ አይደላችሁም ምታውቁት መውለጃ ጊዜዋ ገና ነው ብሎን አግዳሚ ላይ አስቀምጠዋት እነሱ ወደ ድራማቸው ሄዱ፡፡ እኛም አላስችል ብሎን እየተመላለስን በቀዳዳ ስንመለከት ስትሰቃይ ተመልክተናል፡፡ሲሉ በለቅሶና በቁጭት ሁኔታውን ይገልጹታል፡፡

የሟች ቤተሰቦች በማያያዝም ሲናገሩእስከ ለሊቱ 6 ሰዓት ድረስ ምንም እርዳታ አላገኘችም፡፡ ከሌሊቱ 6 ሰዓት አልጋ ተገኝቶላታል ገንዘብ ክፈሉ ተባልን ለጊዜው ደስ ብሎን ከፍለን አልጋ ይዛ ተኛች፡፡ ከቀን ጀምሮ እንደተመለከትነው አሁንም ደም ይፈሳታል የምጥ ስሜት ተናነቃታል፡፡

መርዳት ባለመቻላችን እያየን አዝነን ጥለን ወጣን፡፡ ከዚያ በኋላ መግባት እንደማንችልም ተነገረን፡፡ እስከ ለሊቱ 915 ድረስ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለች ማወቅ አልቻልንም በትግስት ተቀምጠን ጠበቅን፡፡ ዘጠኝ ሰዓት ከሩብ ሲሆን አንድ ወንድና አንድ ሴት ልጅ በሠላም መገላገሏን ለእሷ የተመደበችውና ቆማ ድራማውን የምትከታተለዋ ሐኪም አበሰረችን፡፡ ለልጆቹ ልብስ ጠየቀችን፤ ይዘን ስለነበረ ሰጠናት፡፡ ማየት እንችል እንደሆነ ጠየቅን ቆይ አሁን ትረጋጋ ብላን ሄደች፡፡

ከንጋቱ 12 ሰዓት ሲሆን አሁንም ማየት እንድንችል ጠየቅን አሁን የሚያስፈልጋት አጥሚት ስለሆነ አምጡላት አሉን፤ ሰጠናት፡፡ እኛ ደግሞ አንድ ቀን ሙሉ ደም ሲፈሳት ስለዋለች ልባችን ሊረጋጋ ባለመቻሉ ማየት ፈለግን አልፈቀዱልንም የሰጠናትን አጥሚት ትጠጣም አትጠጣም ያወቅነው ነገር የለም፡፡

ሀኪሟ ተመልሳ መጥታ በጣም በጥሩ ሁኔታ ላይ ናት 2-7 ሰዓት ትወጣለች አለችን፡፡ ሁላችንም በጣም ደስ አለን  በየአቅጣጫው እየደወልን ለዘመድ አዝማድ ተናገርን፤ ይዘናት ለመውጣት ስንዘጋጅ ትንሽ ደም ስለፈሰሳት ደም ያስፈልጋታል አሉን፡፡ ሁላችንም የእህታችንን ህይወት ለማትረፍ ወደ ስታዲየም አካባቢ ደም ለመስጠት ቀይ መስቀል ሄድን በማለት ያስረዳሉ፡፡

አክለውምሟች እህታችን ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ በቤት ውስጥ ወልዳለች፡፡ የመጀመሪያ ልጇ 17 ዓመት ከሁለት ወሩ ሲሆን ሁለተኛዋ ልጇ 16 ዓመቷ ነው፡፡ ሁለተኛዋ ልጇ ተደብቃ ገብታ እናቷን ስትመለከት በጀርባዋ ተንጋላ ተኝታለች ኗም ተጨፍኗል፡፡ ብላ ነገረችን እኛ ደም ለመለገስ ስንሯሯጥ 17 ዓመት ከሁለት ወር የሆነውን ልጇን አስፈርመው አፕራሲዮን አደረግን አሉን፡፡ ከኦፕራሲዮን በኃላ መሞቷ ተነገረን፡ በምን ምክንያት ኦፕራስዮን ልትሆን እንደቻለች ሊያስረዱን አልቻሉም ዕድሜው 18 ዓመት ያልሞላ ልጅ ለምን ማስፈረም ፈለጉ?፡፡ አስክሬን ለማስረከብ እና ገንዘብ ለመቀበል ይህ ነው የማይባል በደል ደርሶብናል፡፡ አስክሬን ለማውጣት ገንዘብ ለመክፈል በሊፍት ውስጥ የገባውን ባለቤቷን መብራት ጠፍቶ 30 ደቂቃ በአየር እጥረት ተዳክሞ በብረት ታግለንና ሊፍቱን ፈልቅቀን ስናወጣው የሊፍት ሠራተኛው እረፍት ሄዷል መብራት ስለጠፋ ነው ብለው አላግጠዋል፡፡ አስክሬኑን ከወሰድን በኋላ ከፍተን ስንመለከተው የተከፈተው አካሏ በአግባቡ አለመሰፋቱን ማየት ችለናል፡፡ እህታችን የሞተችው በሐኪሞች ጥፋት ነው፡፡ የተፈጸመብንን በደል ህዝብና የሚመለከተው የመንግስት አካል ይወቅልን፡፡ ሲሉ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍላችን ድረስ በመምጣት አስረድተዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ የጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ኃላፊዎች አስተያየት እንዲሰጡበት ተመላልሰን ጥያቄ አቅርበን ነበር፡፡ በተሰጠን መልስምበዚህ ጉዳይ መልስ መስጠት የሚችሉት ኃላፊ የሉም፤ ጥያቄውን በደብዳቤ መጠየቅ አለባችሁ፤ ከመምጣታችሁ በፊት ስልክ ደውሉልንበሚል ምክንያቶች የሆስፒታሉን አስተያየት ማካተት አልቻልንም፡፡ በጉዳዩ ላይ አስተያየት መስጠት የሚችል አካል ቢኖር አሁንም መግለጽ ደሚችል ዝግጅት ክፍሉ ያሳውቃል፡፡

http://www.fnotenetsanet.com/wp-content/uploads/2013/04/Finote-Netsanet-News-PaperNo-73.pdf


No comments:

Post a Comment