FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, April 12, 2013

የሕዝብ ጎራ ጠንካራ ጎኖች (የተቃዋሚ)


አስቀድሞ አንድ ነጥብ ማስቀመጥ ተገቢ ነው። የተለመደ ሆነና ተቀዋሚ የሚለው አገላለጽ የከበደ ነው። ተቃወመ የሚለው ቃል ኦፖዚሽን(Opposition) ከሚለው የባእድ ቋንቓ ቀጥታ የተገለበጠ የተወረሰ ነው። መቃወምን ዘዬ ያደረገ እንጂ እውነተኛ የሕዝብን ልጆች ባህሬ አይወክልም። ተቃወመ ማለት- ከፊቱ ያለውን ሁሉ ለውግዘት ዳረገ አወገዘ፤መልካሙንም ጥፉውንም። ይህ ተዋዋሚ የሚለው አገላለጽ መልካም ገጽታ የለውም በሕዝብ ጎራ የተሰለፉትንም ባግባቡ አይገልጸም። ስለዚህ የህዝም ወግን፤የሕዝብ ጎራ የሚለው አገላለጽ ተገቢ ነው። እንደቀደመው፤አብዮተኛ መባሉ ከምስራቁ ፍልስፍና የተጣበቀ ስለሚያስመስልው የአብዮቱ ሃይል መባሉም በተመረጠ ነበረ። ስለተለመደ መጠቀማችን አልቀረም።
የሕዝቡ ልጆች – ግፊት፤ ጫና፤ ሴራ በዝቶባቸው የተመናመኑ እስኪመስለ ድረስ ብዙ መከራ ተሸክመው ዘልቀዋል። ባንድ ወገን ስርአቱ፤ቀጥሎም ባመዛኙ ጥቅም አስጠባቂነታቸውን ስለማያምኑ፤ ለአገርና ለሕዝብ የቆሙ በመሆናቸው ምእራቡ፤ ከዚያም አጎራባች አገሮችና ጥቅም ፈላጊዮች፤ አልፎም ወዳጅ መሳይ መሰሪ ስርጎ ገቦች ከግራ ቀኝ ወከባ አስገብተውት፤ድሉን አስነጥቀው፤ሐይሉን አዳክመው፤በተቀነባባረ ስልት በመከፋፍፈልና በመበተን አሁን ያለበት ደረጃ አድርሰውታል። አይጉድ! ሞቱ አበቃላቸው መስሎት ስንቱ ይሆን የምትቀጥለውን ነጥብ ጓጉቶ የሚጠብቅ? ሁሉም ከፍሬው ይታወቃል ነውና ለሕዝብ ጎራ ማንነትና ምንነት አብይ ምስክረ አገር አንደ አገር ሕዝብም እነደ ሕዝብ መቀጠል መቻሉ ነው። አገርን ከመፍረስ ማዳን። ስርአቱ አገርን ህዝብን አፈረሰ በተነ ከፋፋለ እንጂ አላቀናም። የሕዝቡ ልጆች ባይኖሩ አገር ካበቃላት ቆይታለች። ይህን አለ የሚል መደቡ ከከሃዲው ጎራ ነው።
የዚህ አጭር መልእክት አላማ፤የህዝብን ጎራ-ተቃዋሚውን ካላግባቡ ለማሞገስ፤ጥሩ ቀለም ለመቀባት፤የማይገባው ቦታ-ላይ ለመስቀል ሳይሆን፤አይነተኛ ማንነቱን፤እውነቱን፤የያዛቸውን ጠንካራ እሴቶች ለመጠቆም ብሎም እስከዛሬ ሲዘንብበት የነበረውን የሀሰት ዘመቻ አቀብ ለመስጠት ሀቁ ምን እደሆን ለመጠቆም ነው።
እራስን በቅጡ መረዳት የመልካም እርምጃ ቀዳሚ ጉዳይ ነው። ብዙ ለማስልቸት ሳይሆን፤ሃሳቦች ባጭሩ ቢቀመጡ ተንታኙ፤ገምጋሚው ቢሻው ጨምቆ ካሰኘውም አብራርቶ ሊመለከተው መብት አለው። የህዝብ ጎራ፤ከሁኔታዎች አስገዳጅንተ በስተቀር የተመሰከረለት ባለድል፤ድሉንም አስከብሮ በጥናት እንደሚሟገትና እየቀጠለ እንዳለ የሚካድ አይደለም። ድል ስልጣነ መንበርን መያዝ ብቻ ነው ተብሎ ሊወሰድ አይቻልመ አይገባምም። ባለድልነቱ እላይ እንደተጠቀሰው በምርጫም ሆነ በተግባር አገርን ማዳኑና እያዳነ መዝለቁ ነው። ብዙ ማለት ይቻላል፤የተሳሳተ፤ የማያስኬድ መንገድን ጠቁሞ ታግሎ መስመር ማስገባት ከማዳንም ማዳን-ድልም ይህ ነው -መንበረ ስልጣን ሳይጨብጡ።
የህዝብ ልጆች-የባለድሉ ጎራ ጠንካራ ጎኖችና እሴቶች ለሁላችንም ግልጽ ናቸው። በጥቁርና ነች ቢቀመጡ ወገንን ያጎለብቱ ሌላውን ያርዱ እንጂ በሕዝቡ ጎራ ጠቀሜታቸው ከፍ ያለ ነው። የምናውቀውን ማየት መስማት አንፈልግም የሚል ከዚሁ ይሰናበት ወይም ገረፈ ገረፍ አድርጎ ይለፍ።
የሕዝብ ጎራ ጠንካራ ጎኖችና እሴቶች ምን ይመስላሉ? እስኪ ይታዘቡ፦
1. አገርን መውደድ
ተጠማጅ አርበኛ ባገር መውደድ ቀንበር ብሎ ካባት አያት ቅድመ አባቶች የተላለፈለትን የታሪክ አደራ ተቀብሎ ከፊደሉ፤ ከሞፈር ቀንበሩ፤ከኑረው፤ከትዳሩ ከቤት ቢተሰቡ ተለይቶ ላገር የተሰማራ የሕዝቡ ጎራ ነው። ኢትዮጵያ ከተባለ ደሙ የሚፈላ፤ወኔው የሚኮሰትር፤በአገር ፍቅር እስከ መጨራሻው መስዋእትነት የከፈለ እየከፈለ ያለ፤የጊዜን ፈተና የጠነቀቀና ያለፈ የሕዝቡ ጎራ-ተቃዋሚው አይደለምን? ሌላውማ አገር ሲንድ፤ሲበትን፤ሲከፋፍል፡ህዝብ ከሕዝብ፤ወገን ከወገን እያናከሰ የመሰሪነት ሥራ ሲሠራ ያለ የዘለቀ አይደለምን? ይህ አገር መውደድ እንዳልሆነ ባግባቡ መቀመጥ አለበት። አገርን -ማስገንጠል ለባእድ አሳልፎ መስጠት ማውረስ ወዘተ። አገሩን የሚወድ ይጠብቃታል ይንከባከባታል እንጂ አያጠፋትም አይበትናትም። የሕዝቡ ልጆች ያደረጉት ይህንኑ ነው። አለፍ ብሎም ካለኛ አገር ስለምትጠፋ፤እኛ በልተን እናጥፋት በትነን እናዝልቃት፤ዋስትናችሁ እኛ ነን ተደናቆሩልን፤ተጨፈኑ—–የሚል ማን ነው? እኒሁ አገር በቀል የወቅቱ የጥፋት መልእክተኞች አይደሉምን?
2. ከራስ ጥቅም የራቀ ህዝባዊነት
የሕዝቡ ጎራ ሕስባዊለቱ ገና ከጥዋቱ ሶድት ስርአትን አምርሮ መታገሉ ነው። የራሱን የግል ሕይወትና ጥቅም አሳልፎ ለሕብ ላገር ብሎ ስለመቆሙ ብዙ ትንተና ኣያስፈልገውም። ሕዝባዊነቱ፤ህዝቡ ሲራብ አብሮ፤ሲታመም አብሮ፤ሲሰደድ አብሮ፤በደል ሲደርስበት አብሮ ሕዝብ የሆነውን ሆኖ፤ከዚያም ባሻገር በለስ ቀናውም አልቀናው በነፍጥ ሲሟገት ጥሎና ወድጎ በበረሃው በዱሮ በፈፋውና በየመስኩ መስዋእትነትን መክፈሉ በቂ ምስክሮች ናቸው። ካልታገሉ ድል የለምና ታግሎ ሕዝባዊነቱን አስመስክሯል። በስር የሚማቅቁ ብርቅዬ ልጆች ለራሳቸው ጥቅም ቆመው ቢሆን ከበላታኛ ካፋኝ ከነጣቂና ከቱልቱላ ጋር አብረው በተሰለፉ ነበር። እናንተም ለሕዝቡ ነጻነት መስዋእት የከፈላችሁ፤መከራ የገባችሁ አገርም ሕዝብም ታሪክም ሲዘክራችሁ አንደሚኖር፤በሕይወትም ያላችሁ የታገላችሁለት አላመ ውጤት እንዳመጣ እንደሚያማጣ አትጠራጠሩ።
3. እውነት
እውንተ የት ነው ያለችው? እውነት ያለችው በሕዝብና ከሕዝቡ ልጆች ጎራ ነው። በሕዝብ ልጆች ጎራ ምን አለ ሳይሆን በየእለቱ ስርአቱ የሚለፍፈውንና የሚያደርጋቸው ለሕዝብ ልጆችና ለሚታገሉለት እውነታ በቂ ምስክር ነው። ውሽት ውሽት ውሸት የነገሰበት ስርአት። እውነት ብትኖር ቢኖራቸው ሕዝብ አይታፈንም። ሕዝብን የሚያፍን የሚደብቀው ነገር ስላለ ነው። ሕዝብን የሚያፍነው፤የሚያስፈራራው፤የሚያሳድድው እውነቱ እንዳይወጣ ስለሚፈራ ነው። ውሸትም አይነት አለው፡ዝርፊያም አይነት አለው ተንኮል መሰሪነት አይነት አለው፤የነዚህ ግን የባሰ ለው። ነገ የለችም ወይም አትመጣም ከሆነ፤ተደባብቆ እንዘልቃለን ከሆነ ብለጠት ሳይሆን ሞኝነት፡እውቀት ሳይሆን ሚዛንን ማጣት —–ነው። ባንጻሩ ተቃዋሚው እውነቱን አንጥሮ በማውጠት በማጋለጥ፤ዓይን ጆሮ ሕዘብን ሆኖ ለሕዝብ ለመሟገቱ ምስክ አያሻውም። የእውነተኝነት ምስግሩ ስነ ምግረባሩና ተግባሩ ናቸው። እውነትን የያዘ ያሸንፋል፤ ባያሸንፍም ቢያሸንፍም አሸናፊ ነው። ታዲያ ይህን የእውነት ልጆችና ሕዝብ ጎራ ማን ምን ሊመክተው ይችላል? እውነት ነጻ ታወጣለች እነደተባለም ማንም ወደደ ጠላ፤ደገፈ አልደገፍ ገፋ ጎነተለ እውንት እስከመጨረሻው ተቀብራ አትቀርም። አገር ሕዝብ ትውልድና ታሪክ በእወነት ነጻ ይወታሉ!!!!! እውነት ያለችበት ደግሞ ሁሉም መልካም ነገር አለ። እግዚአብሔርም!!!
4. የዓላማ ጥናት
ማመስገን ቢያንስ፤ዘለፋ ግን ግፍ ነው። የሕዝብ ልጆች ያላማ ጽናት በትግሉ ያሳለፉት ጊዜ አይነታኛ ዋቢ ነው። አስር አያ ሰላሳ አርባ የበለጠም። ቅን አመለካከት ያለው በርቱ ይላል፤ድል ቅርብ ነች ይላል፤ አይዞአችሁ ይላል፤ ከሃዲው ግን ይህን ያክል ጊዜ ታግለው ምን አገኙ፤ በድክመታቸው ነው ወዘተ ሌላም አቃቂር ያወጣል። ዓይኑን በጥቅም ታውሮ በሆዱ የሚአስብ ግን የሕዝቡ ልጆች-የተቃዋሚው ጎራ ከተጀምሮ እስካሁን ድረስና ወደፊትም የድል ባለቤት መሆናቸውን፤የሞራል የበላይነት መቀዳጀታቸውን፤አንገታቸውን ቀና ደረታቸውን ገልበጥ አድርገው መዝለቃቸው አይታየውም። የአላማ ጥናት ይሏል ይህ ነው። ያን ሁሉ የመሰሪ ተንኮለና የከሀዲ እብሪተኛ የከፋፋይ የበታኝ፤የዘራፊ ወሻካች ውሸች የውስጥና የውጭ የተቀናጀን ሴራ ተቋቁሞ ድባቅ መጥቶ መዝለቁ የአላማ ጽናቱ ምስክሮች ናቸው። ጠፉ ሲሉ አለን፤ ሞቱ ሲሉ አልሞትንም በተንነው ሲሉ አገር-ሕዝብ አንድ ብለው የዘለቁ ብረቅዬ የሕዙቡ ልጆች ፈር ቀዳጅ ግንባር ቀደም ተዋዳቂዎች አይደሉምን? ከዚያ ባሻገር ያለው እውነታ ግን፤ የአላማ ጽናት ሳይሆን ላስተዋለው የአላማ ማጣት አለመኖር ነው። ቢኖርም የጥፋት።
5. መስዋእትነት
የህዝብ ልጆች በሓቅ የቆሙ በተቃዋሚነት የተሰለፉ ቆራጥ ወገኖች የጊዜ፤የእውቀት፤የገንዘብ፤ የጉልበት በስዋእትነት አየከፈሉ፤ የእስር የመንገላታት የበደልን ድዋ እየተጎነጩ፤ ባገርም በውጭም በግልጽም በህቡእም እየተዋደቁ ለመዝለቃቸው ምስክር አያሸውም። ብዙ ማለት ይቻላል። ስርአቱ ከየቦታው እይወሻከተ የሚለቅመውን እየበላ እየጠጣ በልጽጎ እያሸሸ ሲየፍንና ሲገል፤የሕዝብ ልጆች እንዲት እንደዘለቁ ማን በነገራቸው። ከዚህ የበለጠ መስዋእትነት ከየት ይምጣ? ለአገር ለሕዝብ ለትውልድ!!!
6. ጥረት
የሕዝብ ልጆች ጥረት ብዙ ያናግራል። ከላይኛው ርእስ ጋር ቢዳበል ቢያስብልም ተለየ ነው። ጥረት ለምን? አላማን ከግብ ለማድረስ በቅድሚያ መስመርን መተለም አብይ ጉዳይ ነው። የህዝቡ ልጆች-በተቃዋሚነት የተሰለፉት፤ላገር ይበጃል፤ለሕዝብ ይጠቅማል፤ለትውልድ ይተርፋል ያሉትን መመሪያ በሶስቱም ስርአቶች ጊዚውን ተከትሎና መጥኖ ሲቀርጹና ሲተገብሩ አሁንም እያሳሻሉ በፍጥነት እርምጀ መገስገሳቸው ታላቅ እውነታ የላሰለሰ ጥረታቸው ማስረጃ ነው። ባንዳሩ ስርአቱ ከኮሙኒዝም ወደ ካጂታሊዝም፤ከምስራቅ ወደምእራብ፤መልሶ ከምእራብ ወደ ምስራቁ እየዋዠቀና እየተገለባባጠ እንዳረረ ይባስ ብሉ የእድገት ምንግሥት-የኪራይ ሰብሳቢ ሆኖበት ግራ ተጋብቶ-ውሸቱን ሲዘውረው የነበረውን አጥቶ የእውር ድንብር መግባቱ ከራሱ አንደበት ሲነገር ይሰማል። እድገት የልም! መልካም አስተዳዳር የለም ዲሞክራሲ ነጻነት መብተ የለም። ምን አለ? እራሱን መምራት ያቃተው፤ጊዜ የካደው ሕዝብ የናቀው፤ የውሸት ማሕደር ባዶ የብዝበዛ ስርአት።
የሕዝብ ልጆች የትኛው አስተዳደርና መርህ፤ለምንና ማቼ እንዴት ብለው ሲዋትቱ ካለውጤት አልቀሩም። ከራሳቸው አልፈው፤የተጣመመውን ውልግድ የጥፋት ስርአሀት ከጥፋት ጉዞው አቅበው፤የሚጓዙበትን ጠንቅቀው እየተመሙ አሉ። የግመልና ውሻ ግልባጭ። ግመሎቹን ትጎትተው የነበረችው ይተ ገባች? አይ ጉድ!!!!
7. ሀሳብን መተንተን-የነጠረ ሀሳብ ማፍለቅ
ሁኑን አስተውለው ቢቃኙት ፍሬው ብዙ ነው። እስኪ ላንድ አፈታ ቆም ብለን ሃሳቦችን እንዴት ስንወቅጥ እደነከረምንና ፍሬውን እንመልከት። የፓልቶክ መድረኮች፤የሰነድሁፍ ትንተናዎች፤የሬድዮ ዝግጅቶች፤የቴሌቪዥን አውታሮች ብሎግና የዘመኑ የብዙሀን መድረኮች ጋሴጣዎች፤ የድርጅት መጽሄቶች-እርምጃ! መልካም፤ ይበል ይበል የሚባል እርምጃ ነው። እዚህ ላይ የሚወቀጠው ስርአቱ ብቻ ሳይሆን የወደፊቱም መንገድ ጭምር ነው። በዚህ በሰላ የበሰለ የዳበረ የዘመናትን ልምድ ባካበተ የሕዝብ ጎራ ፊት የሚቆም ማን ነው? በቅድሚያ ሌባ ከሃዲ መሰሪ ውሸታም እራስ ወዳድ ትቅም አባራረ አይቆምም። ቀጥሎ እራስን በማጽዳት ምህረትና ቅርታ በማይል በማያልፍ የሰላ ወገን ፊት ለመቆም መዘጋጀትን ይጠቁማል። ለስርአቱ በተዘጋጀ መድረክ መፈተንም አለ። ነገ።ተግባባን!!!!!ተፈሪ ሆኖ መዳበር ያለበት አካልም ይህ ነው።ሚዛን ጠባቂ።
እያወቅን እናደርጋለን፤መገምገምም ከሰለቸ የስርአቱ የማስፈራሪያ መሳሪያነት ባሻገር እራስን መመዘኛ ሆኖ አንደዘለቀ፤ለሕዝብ ወገንን ለሃቀኛው ጎራ ሊነገር ይገባል!! ይበል የሚያስብል የሰመረ ጉዞ። ሙገሳ አይደለም-እውነት እንጂ!
8. የጠነከረ ትችት (ሂስ)
ይህም ከላይ ከተጠቀሰው ሃሳብን ከመተንተንና ከማፍለቅ ከመውቀጥ የተነየ ነው። የላይኛው ለመስመር ይህ ግን ስህተትን ለማረም የመስመርም-ለሰውም። ብዙ ጊዜ የጠነከሩ ሂሶች ቢሰጡም እንዳመለካከት ሊለያዩ ይችላሉ- ለማትፋትም ለማልማት እንደ አያያዙ። አንድን ነገር መልካምም አጥፊም በሆነ መንገድ መሥራት እንደሚቻል ሂስም እንዲሁ። ገዳይ አውዳሚ ትችት እንዳማይበጅ ግልጽ ነው። በቂ ትምህርት አንዲቀሰምበት በማስተዋል፤አንድ የተሳሳተና አጥፊ መንገድን የያዘ ካልተተቸ መንገድህ ትክክል ነው ቀጥልበት እንደማለት ይቆጠራል። መተቸትን የሚፈራ የማይሰራ ነው። የሚሠራ ሥራው ፍጹም እንዳይደለ ስለሚያውቅ ቢተች እርማትን ተቀበለ እንጂ በግብዝነት አልተፈናጠጠም። ተማረ እንጂ ለበለጠ ጥፋት አልተሽቀዳደመም። አሰተዋለ እንጂ በጭፍን አልነጎደም።
ግምገማን ሂስን ወቀሳን ትችትን የሚያፍን ማን ነው? ስህተቱን ለመስማት የማይሻው ግብዝ፤ትእቢተኛው ጭፍንተኛውና የጭለማው ስርአት መዝባሪው አይደለምን። የሚገርመው ቀድመው ተሽቀዳድመው የሕዝብን ልጆች እውነተኛ ጩኸት በመንጠቅ እውነትን ጥላሸት መቀባት እንደራስም ማቅረብ። ጩኸቴን ቀሙኝ አይነት።
9. መቻቻል
ከግለሰብ ጦርነት ወደ ሃሳብ ፍጭት፤ጦር ከመማዘዝ ወደ ጠነከረ የጠራ ውይይት፤በመስመርህ ለመጓዝ ካዋጠህ ይባጀል ካልክ በፊናህ መቀጠል ትችላለህ ማለት-ብስለት ማስተዋል አዋቂነት ብሎም መቻቻል ነው። የሗላው ለሗላ ይቀመጥና የተቃዋሚው ሃይል ከጎኑ የለውን ወንድም እህትን፤የክፉ ቀን ወዳጅና ጇድን ከትችት ባለፈ፤ ከወቀሳ በዘለለ አልፈለጠም፤አልወገረም ብሎም አልተተናኮለም-መቻቻል ማለት ይህ ነው። ካለፈውም ትምህርት መማር። በአንደ ወቅት ጦር ተማዞ ሲሟገት የነበረ ተቻችሎ አንድ ሆኖ ተጉዞ ድልም አድረጎ አይተናል። ሁሉን በተቃዋሚው እንደ ድክመት መከመር ሳይሆን ይህ ከፋፋይ መሰሪ ስርአት የሚሰራውን ደባ ማስተዋል ለተከሰቱ እክሎች የቀና መንገድን ያመልካታል፤ ከወቀሳም ከስህተትም ያድናል። የስርአቱን ደመኝነት እንጂ የተቃዋሚውን ድክመት አያሳይምና። አይነተኛ ስልታቸው ነበርና በግልጽ-ልንከፋፍላቸው ሞክርን አልቻልንም ሲኑ የዘገቡትንም አይተናል።
10. አንድነት
ብርጭቆው ግማሽ ነው። አንዱ ግማሽ ጎደሎ፤አንዱም ግማሽ ሙሉ ይላል። የቅንና ይተጣመመ አመለካከት አይንት(+-)። በዚህ ርእስ ብዙ በጣም ብዙ ተብሏል ተፅፏል። እውነቱ ግን የቱ ነው? ከመሰረቱ እንነሳ። ባጭሩ አንድነት ሲባል የአላማ አንድንተ፤የተግባር አንድንተ ማለት እደሆነ ግልጽ ነው። የአላማ አንድነት ለአገር ሉአላዊነት፤ አንድነት፤ ዘላቂነት፤ ለሕዝብ አርነት ነጻነት፤ለፍትህ፤ለመልካም አስተዳዳር፤ ለዲሞክራሲ መቆም፤ ለሕዝብ በቅን ለእድገቱና ብልጽግናው መቆም፤ ባጠቃላይ ለአገርና ለሕዝብ ይበጃል፤ መልካም ነው የተሻለ ነው በሚለው መስምር መቀጠል ነው። እኒህ የተጠቀሱት ሁሉ የሕዝብ ልጆችን ጎራ በአላማ አንድ ያደርጋቸዋል አድርጎም የዘለቀ እውነታ ነው። በቀላሉ ብርጭቆው ግማሽ ሙሉ ነው ማለት ነው። ደርበብ እናድረገው ከተባለም ደርበብ ብሏል። አስከ ዛሬ ድረስ ለአገር ሉአላዊነትና አንድነት በሕዝቡ ልጆች ጎራ የተተገበረው የተግባርም አንድለትን ያመለክታል። የተገኙ ድሎችን ከአገር አድን ከሕዝብ አድን እስከ ምርጫ ድሎች ድረስ ያሉትን መጥቀሱ ይባቃል። የተቀናጀ -የአላማና የተግባር አንድነት በጊዜው ተተግብረዋል፤ፍሬ አፈርተዋል በድልም ቀጥለው ሰርአቱ አሁን ያለበት የተንገዳጋደ አቋም ላይና የሚፈነዳ ገሞራ ላይ ኮፍሰውታል። በከፊልም በሴራ ተቀጭተዋል ከፊሉም አፍርተዋል-እነደ ምርጫው አይነት ማለት ነው።
ድል፤ፍጽም ድል የልም። በቂ ነው? አይደለም። የጎደለው አለ? በእርግጥ አለ። መንደዱ መፍትሔው ምን ይሁን? አሁንም መሰባሰብ፤መቀናጀት፤መተባበርና የበለጠ መጠናከር። በአንድ ግዜ ሁሉን መንጠቅ ብቻም ሳይሆን አንድ ባንድ በየፈርጁ ማስተፍትፍ-መንገድ ነው።
ከግለሰብ ወደ ቡድን ከቡድን ወደተደራጀ፤ከተደራጀ ወደተሰባሰበ፤ ከተሰባሰበ ወደተቀናጀ የአንድንት ጉዞ መዳበሩ ግልጽ ነው- አማራጭ ካለም ይበል። ዋናው፤ አለማና ተግባር ለውጤት መዋላቸው ላይ ነው።
በዚህ የላሰለሰ ትግል ጉዞ፤ስርአቱ መፈረካካስ ሲጀምር፤ባዶው እራሱ ይጠራል፤ያሰባስባል ለመፍትሄ ይጋብዛል፤ አመራጭ ብቻ ሳይሆን ሁነኛ አይነተኛ አለኝታ የሕዝብ አውነተኛ ልጆች-በተቃዋሚነት የተሰለፉት ይሆናሉ፤ ናቸውም።
የተበታተኑ ናቸው፤ አንድነት የላቸውም፤አቅም የላቸውም፤ጥቂቶች ናቸው ወዘተ የሚባሉት የፐሮፐጋንዳ ቱልቱላዎች እንጂ እውነትነት የላቸውም። አንድነትም ድልም እውነትም ዘለቄታም አሉ። ሕዝብም አገርም አምላክም አብረው። ትውልድም ታሪክም አብረው።
እነዚህ ጠንካራ ጎኖችና እሴቶች ብዙ የሚያራምዱ ብቻ ሳይሆን ታሪክን በውበት የሚሞሉ የድል ምእራፍና ፋና ወጊዎች ናቸው። የደረሱበትን ቆም ብሎ ማስተዋል እርማት ማስተካከያ ወስዶ መንገድን ማቅናት ተገቢ ብቻ ሳይሆን አስፈላጊም ነው። የሕዝብም ልጆች ቢዋቀሱ ለአገር ለሕዝብ ብለው እንጂ ለጥቅም አይደለምና መዋቀሱም ምልካም በዚያው ካልቀረ።
ኢትዮጵያ በሐቀኛ ልጆችዋ፤ በታታሪ ቆራጥና ታጋሽ ሕዝቧ፤ በእግዚአብሔር ሐይል ከገባችበት ፈተና ጥሽራለች!

No comments:

Post a Comment