ወያኔ በልማት ስም ገንዘብ ለመቃረምና ደጋፊ ለመመልመል አቅዶ ከሳምንት በፊት በስታቫንገር አንዲሁም በዛሬው እለት ደግሞ በኦስሎ ስብሰባ ለመጥራት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ሳይሳካላቸው የውርደት ካባቸውን ለብሰው መሄድ እጣፋንታቸው እንዲሆን የግድ ሆኗል፡፡ እንደሚታወቀው ባለፈው ሳምንት ማለትም እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ሚያዝያ 20፣ 2013 በነበረው ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያዊያን ከየተለያዩ ቦታዎች በመሰባሰብ የወያኔ አምባሳደር በስዊድን የሆኑትንና የዲያስፖራ ተወካዩን ከስብሰባ በማባረር ከፍለውበት የነበረውን አዳራሽ ተረክቦ ኢትዮጵያዊያን የራሳቸውን አጀንዳ እና ለተፈናቀሉት ወገኖቻችን እርዳታ የሚሆን ገቢ እንዲሰበሰብና ይህን አምባገነንና ዘረኛ ቡድን መታገል የሚቻለው በ አንድነት መሆኑን ሁሉም የሚስማሙበትና እጅ ለእጅ ተያይዘን መታገል እንዳለብን አስምረው፣ ከ አንድ ሳምንት በሗላ ለሚደረገው የወያኔ ገቢ ማሰባሰቢያ ይህንኑ ድል መደገም ያለበት መሆኑን በመስማማት ነበር የተለያዩት፡፡
ይህንንም ተከትሎ የስታቫንገሩን የወያኔ ፕሮግራም ለማክሸፍ ከፍተኛው ሚና የተጫዎተውን ግብረ-ሓይል በማጠናከር ሳምንቱን ሁሉ ውጤታማ ሥራ ለማድረግ የሙስሊም ወንድሞቻችንን፤ ኦሮሞና ሶማሌ ኢትዮጵያዊያንን በማስተባበር ሌት ከቀን ሲሰራ ሰነንብቷል፡፡ የጀግኖች ኢትዮጵያዊያንን ከፍተኛ ዝግጅትና ቅስቀሳ ሲከታተሉ የነበሩ የወያኔ ቅጥረኞችና አገላጋዮች ስብሰባ ሊደረግ ታቅዶበት የነበረውን አዳራሽ የስብሰባው ሰዓት ሊደርስ አንድ ሰዓት ተኩል ሲቀረው የመሰብሰቢያው አዳራሽ በፀጥታው፣ በጥራቱና በደህንነቱ በታወቀው ራድሰን ብሉ ሆቴል እንደሚካሄድ አስታውቀው፣ ስብሰባውን ለመሳተፍ ግን ህጋዊ መታወቂያ እንደሚያስፈልግ ተገልፆ የሞባይል አጭር መልዕክት ተላለፈ፡፡ ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ስብሰባው ይካሄድበታል ተብሎ ከታሰበበት አዳራሽ አካባቢ ከአስር ሰዓት ጀምሮ ወደዚያ የሚያልፈውን የወያኔ ቅጥረኛ ለመቃኘት ወረውት የነበረ ቢሆንም ዘግይቶ የመጣውን አጭር የሞባይል መልዕክት ማለትም የስብሰባ ቦታ መቀየር በመረዳት፣ ወደዚያው ተመመ፡፡
ብዙዎቹ ኢትዮጵያዊያን ከመድረሳቸው በፊት በገቡት የወያኔ ተወካዮች በመበሳጨቱ ወደ ሆቴሉ ለመግባት በነበረው ግብግብ፣ ምንም ዓይነት ሰው እንዳይገባ ተከለከለ፡፡ ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያዊያንን ቁጣ ለማስቆም ከ15 መኪና በላይ የፖለስ ሃይል የተጨመረ ቢሆንም የጀግኖች ኢትዮጵያዊአንን ቁጣና እልህ መቋቋም አልቻሉም ነበር፡፡ አካባቢው የግልና ተቃውሞውም ህገወጥ እንደሆነ በማስረዳት ከአካባቢው ገለል ለማድረግ ቢሞክሩም አልተቻለም፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ በሆቴሉ የታደሙት የወያኔ ቅጥረኞት ወጥተው ካልሄዱ አካባቢውን ለቀን አንሄድም፤ ይውጡ እንለቃለን፤ ይውጡ እንለቃለን፤ ይውጡ እንለቃለን፤ ይውጡ እንለቃለንበማለት አብዘተው ጮሁ፡፡ ይህንንም ተከትሎ ሁለት ሴቶች እህቶቻችንና ዘጠኝ ወንድሞቻችን ለሰዓታት ታስረው የተፈቱ ሲሆን፤ ፖሊስም የተቃውሞውን ሓይለኝነት በማየት የወያኔ ተወካዮችንና የስብሰባው አስተባባሪዎች በጓሮ በር ማለትም በመኪና ማቆሚያ በኩል ከህዝብ ሰውረው ከሆቴሉ ሸኝተዋቸዋል፡፡
ከዚያም ኢትዮጵያዊያን አያ ሆሆ ማታ ነው ድሌ፤ አያ ሆሆ ማታ ነው ድሌ፤ አያ ሆሆ ማታ ነው ድሌ እያሉ በመዝለል ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡ የሚከተሉትን የፎቶ ትዕይንት ይመልከቱ፡፡
No comments:
Post a Comment