FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, September 13, 2013

አንድነት ፓርቲ በመስከረም 05 ሊያካሂድ የነበረው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ፣ በመንግስት ዕውቅና አግኝቶ ለመስከረም 19 ተላለፈ!


አንድነት ፓርቲ በመስከረም 05 ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ ይታወቃል፡፡ ይሁን አንጂ መንግስት ሁለት ምክንያቶች በማቅረብ ለሐምሌ 19 እንዲተላለፍ ጠይቋል፡፡ በመስቀል አደባባይ አካባቢ በባቡር ግንባታ ምክንያት የታጠሩ ቆርቆሮዎችን ለማንሳትና አዲሱን ዓመት አስመልክቶ በአካባቢው ባዛር እየተደረገ በመሆኑ መንግስት እንዲራዘም ጠይቋል፡፡ ለመንግስት በአዋጅ የተሰጠው ስልጣን በቂ ምክንያት ሲቀርብ እንዲያራዝም ህጉ የሚፈቅድ በመሆኑ ፓርቲያችን ህግን ተከትሎ ተቀብሎታል፡፡Andenat Party UDJ
ስለሆነም ይህ ከመንግስት እውቅና የተሰጠውን ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ መስከረም 19 በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል፡፡ ሰልፉ ከ23 የአንድነት የአዲስ አበባ መዋቅር አደረጃጀቶች ተነስቶ ወደ መስቀል አደባባይ ይተማል፡፡ በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ የአዲስ አበባ ነዋሪ በነቂስ ወጥቶ ብሶቱን እዲገልፅ አንድነት ፓርቲ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ድል የሕዝብ ነው!
Andenat Party UDJ

No comments:

Post a Comment