FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, September 20, 2013

ከፍተኛ መሬት መንቀጥቀጥ በኤርትራ ተከሰተ

በሱዳን እንደተሰማም ተገለጸ




ረቡዕ መስከረም 8፤2006ዓም ልክ በ6፡08 ሰዓት ላይ በኤርትራ የመሬት መንቀጥቀጥ መድረሱን CMI የተሰኘው የጣሊያን ዜና ወኪል አስታውቋል፡፡
በተለያዩ የዓለም ተቋማት የተገኘው መረጃ እንደሚያብራራው የመሬት መንቀጥቀጡ የተነሳው ከምጽዋ ጥቂት ኪሎሜትሮች ወጣ በማለት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ መጠኑ 5.0 ነው የተባለለት የመሬት መንቀጥቀጥ 18ሺህ ሕዝብ በሚኖርባት ምጽዋም ሆነ ባካባቢው ያደረሰውን ጉዳት ለማወቅ በቂ መረጃ እንደሌለ የዜና ወኪሉ ጠቁሟል፡፡
massawaየመሬት መንቀጥቀጡ በሱዳን መሰማቱንም የሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት አካባቢ መድረሱ የጠቆመው ዜና የሱዳን ከርሰ ምድር ጥናት ማዕከል 5.9 መጠን ያለው ስለመሆኑ የሰጠውን ማስረጃ በማከል አቅርቧል፡፡
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር የመሬት መንቀጥቀጥ መድረሱንና ሰዓቱ ከመግለጽ በስተቀር ስለደረሰው ጉዳት የሰጠው መግለጫ የለም፡፡
ከባህር ውስጥ የሚነሳ የመሬት መንቀጥቀጥ የሱናሚ ዓይነት ተጽዕኖ ያለውና የሚያደርሰው ጥፋት ከመንቀጥቀጡ ጋር አብሮ የሚያስነሳው ማዕበልና ጎርፍ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ (ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ)

No comments:

Post a Comment